ዋናዋና ዜናዎች

| ክልላዊ ዜና


 • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ውሳኔ ማስተላለፉን በማስመልከት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ርዕሰ መስተዳድሩ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ውሳኔ ማሳለፉን መሰረት አድርገው ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር ቀልብን ከሚስቡ የቱሪዝም ኃብቶቻችን መካከል አንዱ ነው ብለዋል፡፡ የጌዴኦ ህዝብ ደን የሰው ልጅ ህይወት መሆኑን ቀድሞ የተረዳና እንደልጁ ተንከባክቦ ከትውልድ ትውልድ የሚያሸጋግር አኩሪ ባህል ያለው ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ባህላዊ መልክዓ ምድሩም የዚህ ድንቅ ባህል ውጤት ነው በማለትም አብራርተዋል። የክልሉ መንግስት የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ የዛሬው ውጤት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የፌደራል መንግስት ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በመግጫቸው የክልሉ መንግስት ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት ለቅርሱ ዘላቂ እንክብካቤ በማድረግ፣ የቱሪዝም መስህብ እንዲሆን አበክሮ ይሰራልም በማለት በድጋሚ ለጌዴኦ፣ ለክልሉ ብሎም ለመላው የሃገራችን ህዝቦች እንኳን ደስ አለን ብለዋል።

  September 18, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባዬሁ ታደሰ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ይፋዊ የክላስተሩን ስራ ለማስጀመር ጅንካ ከተማ ገቡ። ከፍተኛ አመራሩ ወደ ጂንካ ከተማ ሲደርስ የደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና የጅንካ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በፕሮግራሙ ላይ የክልሉ ምክትል አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ወላይቴ ቢተውን ጨምሮ ሌሎች የክላስተሩ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የማህበራዊ ክላስተር ይፋዊ ስራ ዛሬ ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ትላንት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ በክልሉ በሁሉም ክላስተር ከተሞች ከዛሬ ጀምሮ ስራ እንደምጀምር መግለጻቸውን መዘገባችን የምታወስ ነው።

  August 31, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ክልሉ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ። ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት ክልሉ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ በይፋ ሥራ መጀመሩን ጠቅሰዋል። በርዕሰ መስተዳድሩ መቀመጫ ከተማ ወላይታ ሶዶ በቀዳሚነት ሥራ መጀመሩን ጠቅሰው በቀጣይ ጊዜያቶች በሁሉም መዋቅሮች ከነሀሴ 25/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ የማስጀመር መርሃ ግብር እንደሚካሄድ ገልጸዋል። ለዚህም አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት መደረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል። አቶ ጥላሁን አክለውም ቀጣይ 6 መሠረታዊ የትኩረት አቅጣጫዎች መለየታቸውን አስታውቀዋል። እነዚህም የህዝብ ሠላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣ ያደሩ ጥያቄዎችን መፍታትና ህዝቡን በልማት ሥራ ማረባረብ፣ የግብርና ልማት ሥራዎችን ማጠናከር፣ የቆዩና ያደሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣ በስድስቱም የክልሉ ማዕከላት ለህዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ማሳለጥ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ማጠናከር ናቸው።

  August 30, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የጋሞ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሐ ግብር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ አሰቸኳይ ጉባኤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ህገ- መንግስት አፅዳቂ ኮሚሽን አባላትን በመሰየም ተጠናቀቀ። የዞኑ ምክር አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች የተሳተፉበት የምክር ቤቱ 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በቀረበው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ህገ- መንግስት ላይ ተወያይቷል። በአዲስ መልክ ከተዋቀሩ ክልሎች አንዱ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ- መንግስት ቀድሞ የነበረውን የፍትሀዊነት ጥያቄ በሚመልስ መልኩ መዘጋጀቱ ለምክር ቤቱ አባላት ተብራርቷል ። አርባምንጭ ከተማ ግዙፍ የኢኮኖሚ ማዕከል በመሆን በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች መሆንዋም ተጠቁሟል። በከተማዋ የተጀመረውን ሁለንተናዊ ዕድገት በማስቀጠል የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል የአካባቢውን ሠላም በማስጠበቅ የሕዝቡን እንድነት በሚያጠናክር ሁኔታ ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ አሰፈላጊ መሆኑም ተገልጿል ። የአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ህገ- መንግስት ፀድቆ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት በየደረጃው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን የማወያየት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል ። አስቸኳይ ጉባኤውም በቀረበው ሰነድ ላይ ተወያይቶ መካተትና መቀነስ እንዲሁም መሻሻል ባለባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ምክረ ሀሳብ በመስጠት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ህገ መንግስት አፅዳቂ ኮሚሽን እንዲቀርብ በሙሉ ድምፅ ወስኗል ። አስቸኳይ ጉባኤው ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ህገ-መንግስት አፅዳቂ ኮሚሽን አባላትን በመሰየም ተጠናቋል ።

  August 11, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ የክልሉ ህገ-መንግሥት አፅዳቂ ጉባኤ ላይ ተሳታፊ ተወካዮችን በመምረጥ ተጠናቀቀ። የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃግብር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ የክልሉ ህገ-መንግሥት አፅዳቂ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን በመምረጥ ተጠናቀቀ። ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ሕገ-መንግስት ላይ መወያየትና ግብዓቶችን በማከል በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። የጎፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው በማጠቃለያቸው መሪው ፓርቲያችን የክልሉ አደረጃጀት አጠቃላይ ሂደት በጥበብ እንድመራና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ወደ መሬት እንዲወርድ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን ተናገረው እስከ አሁን ላለው ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጉ የክልሉን መንግሥት ፣ አመራሮችን ፣ ምሁራንና መላው የዞኑ ህዝቦችን አመስግነዋል። በሂደቱ በየደረጃው ህዝቡ እንዲሳተፍበትና ይሁንታ እንዲታከልበት የተደረገበት አግባብ እንደ ሀገር ታርካዊና የዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን እየጎለበተ የመሆኑ ማሳያ ነው ስሉ ገልፀዋል። በተመሳሳይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግስት ለማጽደቅ በክልሉ ጉባኤ የሚሳተፉና የሚወከሉ 15 የክልል የምክር ቤት አባላትን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። እነዚህም የተከበሩ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው ፣ ኢ/ር አክልሉ አዳኝ ፣ ወ/ሮ ብዙነሽ ዘውዴ ፣ አቶ ጠንክር ጠንካ ፣ አቶ በላይነህ ባህሩ ፣ አቶ ተፈሪ አባቴ ፣ ወ/ሮ ጥሩነሽ ካሳ ፣ አቶ ልዑልሰገድ ገመዳ ፣ አቶ እምሩ ደፈርሻ ፣ ወ/ሮ አለምገነት ላቀው ፣ የተከበሩ ኢንጅነር እድሬ እርኮ ፣ ወ/ሮ ግስታን ግርማ ፣ ወ/ሮ መኪያ እንድሪስ ፣ ወ/ሮ እመቤት በዛብህ እና አቶ ታደለ ቃዳ ተመርጠዋል። በተጨማሪም የተከበሩ አቶ ታምራት ተሰማ እና ክብርት ወ/ሮ ሀብታምነሽ ግራዝማች የጎፋ እና ኦይዳ ብሔረሰብን በመወከል የብሔረሰቦች ምክር ቤት አባል ሆነው እንዲሳተፉ ተመርጠዋል። በአጠቃላይ 17 ተወካዮች በክልሉ ህገ-መንግስት አፅዳቂ ጉባኤ ላይ ጎፋ ዞንን ወክለው እንድሳተፉ ተመርጠዋል።

  August 11, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • አደረጃጀት በራሱ ግብ ባለመሆኑ የነበረንን የሚያሳጣ ሳይሆን ለህብረተሰቡ እሴት የሚጨምር ሊሆን ይገባል - አቶ አደም ፋራህ በደቡብ ክልል ከክልል አደረጃጀት ጋር በተያያዘ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችል የአመራር የውይይት መድረክ በሀዋሳ እየተካሔደ ነው የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት አደረጃጀት በራሱ ግብ ባለመሆኑ የነበረንን የሚያሳጣ ሳይሆን ለህብረተሰቡ እሴት የሚጨምር ሊሆን ይገባል ብለዋል። በፓርቲው ጉባኤ ወቅት በየአካባቢው ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች እየተመለሱ ሊሄዱ ይገባል የሚል አቅጣጫ መቀመጡን ተከትሎ በደቡብ ክልል ህዝቡ የሚያነሳቸውን የአደረጃጀት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ወደ ተግባር መገባቱንም በአብነት ጠቅሰዋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ በደቡብ ክልል እየተነሳ ያለውን የአደረጃጀት ጥያቄዎች በ90 ቀን እቅድ ውስጥ እንዲካተት በማድረግ ተግባሩ የሚመራበት ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት ከአመራሩ እና ከህዝቡ ጋር በጋራ መምከር እንደተቻለም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል። የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች ላይ እስካሁን የተሰሩ ስራዎች እና ቀሪ የአመራሩ ሚና ላይ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ የሚያስችል መድረክ ነው ብለዋል። ህዝቡ እያነሳ ያለውን የአደረጃጀት ጥያቄ እንደ ፓርቲ መርተን እየፈጸም ነው ያለ ታሪካዊ ክንውን ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ አመራሩ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን ተገንዝቦ ለቀሪ ተግባራት መዘጋጀት እንዳለበትም አስረድተዋል። በአመራር ደረጃ የህዝቡን የአደረጃጀት ጥያቄዎች ለመመለስ መላውን ህዝብ ያሳተፈ እና ህገ መንግስታዊ በሆነ ሂደት ውስጥ ማለፍ እንደተቻለም ጠቁመዋል።ከአመራር እስከ ህዝቡ ወጥነት ያለው የጋራ ተግባቦት ስለመፈጠሩም አቶ አደም ጠቁመዋል። ከክልል አደረጃጀት ጋር በተያያዘ ቀሪ ተግባራትን በአጭር ጊዜ በመፈጸም ሁለቱም ክልሎች ፈጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያስችል ስራ ይሰራልም ብለዋል። ሁለቱም ክልሎች የተረጋጉ ሆነው ለህዝቡ ከሰላም ከልማት እና ከመልካም አስተዳደር አኳያ እሴት የሚጨምሩ እና እንደ ሀገር ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ ማስቻል ይገባል ሲሉም አብራርተዋል። ሰላማችንን ለማረጋገጥ፣ልማታችንን ይበልጥ ለማፋጠን እንዲሁም ህዝቡን የሚያረካ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል በማለት ነው የተናገሩት። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በውይይት መድረኩ እንደገለጹት ከክልል አደረጃጀት አኳያ በአመራር ደረጃ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ እየተነሳ ያለው የአደረጃጀት ጥያቄዎች ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መሸጋገሩን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ የአደረጃጀት ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ ለመሩ እና ላስተባበሩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

  August 3, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የአለም የአየር ሁኔታ በየጊዜው ተለዋዋጭ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያም ተጎጂ ሆናለች -አቶ አገኘሁ ተሻገር በደቡብ ክልል በአንድ ጀንበር የ110 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በሁሉም አካባቢዎች እየተካሔደ ነው የፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንደገለጹት የአለም የአየር ሁኔታ በየጊዜው ተለዋዋጭ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያንም ተጎጂ እያደረጋት ነው ብለዋል። በሀገሪቱ በመጀመሪያው ምዕራፍ 25 ቢሊየን ችግኞች በመትከል በአለም አንጸባራቂ ድል መጎናጸፍ ችለናል ያሉት ዋና አፈ ጉባኤው ይህንን ግብ ወደ 50 ቢሊየን ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በዛሬው እለት 500 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ጀንበር በመትከል ታሪክ እንሰራለን ብለዋል። የተጀመረው ዘላቂ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ፋይዳው ከፍተኛ ስለመሆኑም አቶ አገኘሁ አስረድተዋል። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እንደገለጹት በክልሉ በተደጋጋሚ እያጋጠመ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ የድርቅ፣የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ለመከላከል የአካባቢ እንክብካቤ እና ጥበቃ ስራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል። መላው የክልሉ ህዝብ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን ጥሪ ተቀብሎ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ በንቃት እየተሳተፈ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ በተያዘው አመት ከ 1ነጥብ 3 ቢሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል እየተሰራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዛሬው እለት ደግሞ 500 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ታሪኳን ታኖራለች ብለዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የታቀደውን የችግኝ ተከላ ግብ ለማሳካት መላው የክልሉ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል። በሁሉም መስኮች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ እውን እናደርጋለን በማለት አውስተዋል። የደቡብ ክልል በተፈጥሮ አደጋ እየተፈተነ ያለ አካባቢ ስለመሆኑ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ችግሩን ለመቅረፍ የአካባቢ እንክብካቤና ጥበቃ ስራ ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አብራርተዋል። የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሐመድ በበኩላቸው አረንጓዴ አሻራችንን ስናሳርፍ ያለንን ተስማሚ አየር ጠብቆ ለማቆየት፣የዓፈር ለምነትን ለማስጠበቅ ፣በረሀማነትን ለማስቀረት ያግዛል ብለዋል ። የችግኝ ተከላው ከሀገራዊ ፋይዳው ባለፈ በቀጠናዊና በአለም አቀፋዊ በረከቶች ላይ ተጠቃሚ እንድንሆን ያስችለናል ሲሉም ተናግረዋል። የደን ልማት የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳያችን ነው ያሉት ሚኒስትሯ የድርቅን አደጋ ለመቋቋም እድል ይሰጠናል በማለት አውስተዋል። በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት የአለም ስጋት የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አደጋ አስቀድሞ መገንዘብ ከምንም በላይ ትኩረት ያሻል ብለዋል። ለፍጥረታት ሁሉ ምቹና ለምለም ምድር ለመፍጠር የአረንጓዴ አሻራ ስራ በስፋት ማከናወን አስፈላጊ መሆኑን አቶ ኡስማን ጠቁመዋል። ይህን ተከትሎም በክልሉ ባለፉት ዓመታት ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል እንደተቻለም ኃላፊው አስረድተዋል። እንደ አቶ ኡስማን ገለጻ በክልሉ በተካሄደ የአረንጓዴ አሻራ ስራ በየጊዜው በጎርፍ እየታጠበ የሚሄደውን ለም አፈር ማቀብ፣የመሬት ምርታማነትን መጨመር፣የደን መራቆትን መከላከል፣የመስኖ እና የውሃ አቅምን ማሳደግ እንዳስቻለም አብራርተዋል። በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ተሳታፊ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደገለጹት በአንድ ጀንበር 500ሚሊየን ችግኞች ለመትከል የተጀመረውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል ሲል የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።

  July 17, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ለ2016 በጀት ዓመት ከ22 ቢሊዮን 637 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ ለ2016 በጀት ዓመት የቀረበለትን ከ22 ቢሊዮን 637 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ። በበጀት ዓመቱ በክልሉ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ተገልጿል። የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አራርሶ ገረመው የበጀት ረቂቁን እና በጀቱ የሚውልባቸውን የልማት መስኮች በዝርዝር ለምክር ቤቱ አቅርበዋል። በጀቱ በክልሉ ለሚካሄዱ የዘላቂ ልማት ግቦችና ለአስተዳደራዊ ተግባራት እንደሚውል ባቀረቡት የበጀት ረቂቅ አመልክተዋል። በጀቱ ለክልል ማዕከል፣ ሀዋሳን ጨምሮ ለዞን፣ ለከተማና ለወረዳ አስተዳደሮች እንደሚውልም ነው የተገለጸው። በቀረበው የበጀት ረቂቅ ላይ የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ አስተያየቶችን አንስተዋል። በእዚህም በበጀቱ ለድህነት ቅነሳ፣ ለመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም የነዋሪውን የልማት ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ተግባራት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል። የክልሉን ሠላምና ጸጥታ አስተማማኝ የማድረግ ስራም ሊተኮርበት እንደሚገባ ያነሱት የምክር ቤቱ አባላት፣ በተለይ በአጎራባች አካባቢዎች ህዝብን በማሳተፍ ሰላምና ጸጥታን ለማጠናከር የሚሰሩ ሥራዎች እንዲጠናከሩ አመልክተዋል። በመንገድ መሰረተ ልማት የተጀመረው ጥረት መቀጠል እንዳለበት ጠቁመው፣ በተለይ ለገጠር ተደራሽ መንገዶች ግንባታና ጥገና የተሰጠው ትኩረት እንዲጠናከርም አሳስበዋል። እነዚህና ሌሌች አስተያየቶች በምክር ቤቱ አባላት ከተሰጡ በኋላ የቀረበውን የበጀት ረቂቅ ምክር ቤቱ ተቀብሎ አጽድቆታል። በተያያዘ ዜና በበጀት ዓመቱ በሲዳማ ክልል የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ የ2016 በጀት ዓመት የክልሉን መንግስት የትኩረት አቅጣጫ ዛሬ ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላትም በቀረበው የሥራ ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ተወያይተው አፅድቀዋል። አቅጣጫውን ያቀረቡት የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ደስታ፣ በጀት ዓመቱ በዋናነት የግብርናን ምርታማነት በማጠናከር የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። ለእዚህም "የእርሻ ሥራን በማዘመን፣ የተለያዩ የመስኖ አውታሮች በመገንባት፣ የውሃ አማራጮችን በማስፋት ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ይከናወናሉ" ብለዋል። ለእንስሳት ሀብት ልማት ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቁመው፣ በዘርፉም የእንስሳት ዝርያ ማሻሻልን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎች በማከናወን ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል። እንዲሁም የዶሮ ልማት ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን የጠቀሱት አቶ ደስታ፣ በበጀት ዓመቱ ከ8 ሚሊዮን በላይ የተሻሻሉ የዶሮ ጫጩቶችን ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት እንደሚሰራ ተናግረዋል። አካባቢው ያለውን አቅም በመጠቀም የዓሣ ሀብትና የንብ ማነብ ልማትን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም አምልክትዋል። መሰረተ ልማትን ከማስፋፋትና ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንጻር ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰው፣ በተለይ መንገድ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የጤናና የትምህርት ተደራሽነትን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። "በክልሉ የሚገኙ ከተሞች በፕላን እንዲመሩ ለማድረግ መታቀዱን አቶ ደስታ ጠቁመው፣ "በበጀት ዓመቱ 10 ከተሞች ስታንዳርዱ በሚፈቅደው መሰረት እንዲመሩ ለማስቻል ይሰራል" ሲሉም አክለዋል። "ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንጻር ያሉንን አቅሞች በመጠቀምና የገጠሙ ክፍተቶችን በማረም ዜጎች ተጠቃሚ የሚሆኑባቸው ሥራዎች ይሰራሉ" ሲሉም ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረቡት የሥራ ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ይተኮርባቸው ያሏቸውን የማጠናከሪያ ሀሳቦች በመስጠት ዕቅዱን አጽድቀዋል። የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባም በነገው እለት የሚቀጥል ሲሆን የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን በመስጠት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

  July 16, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ እያጋጠመ ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የአመራሩ ሚና የላቀ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ በደቡብ ክልል በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ የአመራር የውይይት መድረክ በሀዋሳ እየተካሔደ ነው በደቡብ ክልል በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ባደረገው የውይይት መድረክ ተሳታፊ የሆኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንደገለጹት ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ እያጋጠመ ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የአመራሩ ሚና የላቀ ሊሆን ይገባል ብለዋል። የኑሮ ውድነት፣ስራ አጥነት፣የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና ሌሎችም መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ዝግጁ መሆናቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቁመዋል። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በርካታ ፈተናዎች ማጋጠማቸውን የገለጹት አስተያየት ሰጪዎቹ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት መንግስት ለችግሮች መፍትሄ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል። ሀገራዊ የለውጥ ሂደቱ ተግባራዊ እየተደረገ በነበረበት ወቅት ኢኮኖሚያችን በሚፈለገው መጠን ያለማደጉ እንዲሁም ከፍተኛ የብድር ጫና በነበረበት ወቅት መሆኑ በፍላጎት እና በአቅርቦት መካከል ያለመጣጣም ችግሮች መስተዋላቸውን ተናግረዋል። ሀገሪቱ የገጠማት የውስጥ እና የውጭ ጫናዎች እንዲሁም ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች የለውጡ አብይ ፈተና እንደነበር የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ ፈተናዎችን ወደ እድል በመለወጥ ያሉንን ጸጋዎች በተገቢው መንገድ በመጠቀም ማተኮር እንደሚገባም በውይይት መድረኩ የጋራ አቋም መያዝ እንደተቻለም አብራርተዋል። ለውጡን ተከትሎ በሀገሪቱ ግንባታቸው የተጓተቱ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ በሁሉም አቅጣጫ እየተነሳ ያለውን የህዝብ ጥያቄ ምላሽ መስጠት እና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሲደረግ መቆየቱን አብራርተዋል። መንግስት እንደ ሀገር ያጋጠሙ ችግሮችን ሲፈትሽ ቆይቷል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በተለይ የኢኮኖሚ ሪፎርም በማድረግ የታየው መነቃቃት የተሻለ ለውጥ እንዲመዘገብ ምክንያት መሆኑንም አውስተዋል። በግብርናውም ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ስኬታማ መሆኑን ገልጸዋል።

  March 22, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • በደቡብ ክልል ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ይሻሉ አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው የደቡብ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክርቤት በክልሉ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በቀረበው ሪፖርት ላይ መክሯል የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ እርስቱ ይርዳው በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት በክልሉ ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ ይሻሉ ብለዋል። ከዚህ ቀደም በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ ከ 917 ሺ በላይ ዜጎች በተጨማሪ ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚፈልጉ ነው የጠቆሙት። እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ በክልሉ ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ ወደ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ የቤት እንስሳት ተጎጂ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይታመናል ብለዋል። የክልሉ አደጋ ስጋት ምክርቤት ከተፈጠረው ድርቅ ጋር በተያያዘ ሰብአዊ ጉዳት እንድደርስ እየሰራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም እየተደረገ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል። የፌደራል እና የክልሉ መንግስት ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ በየደረጃው ያለውን ህብረተሰብ በማሳተፍ የሰብአዊ ድጋፍ ስራውን ተደራሽነት ለማሳደግ መስራት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። የክልሉ መንግስት በዚህ ዓመት ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች አንድ መቶ ሚሊየን ብር መድቦ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ተጨማሪ በጀት በማፈላለግ የሰብአዊ ድጋፍ ስራውን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በመንግስት ከሚደረገው ድጋፍ ባለፈ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች በኩል የሚደረገውን ድጋፍ ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባም ጠቁመዋል። ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች እየተካሔደ ያለውን የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ማጠናከር የጤና፣የንጹህ መጠጥ ውሃ፣የእንስሳት መኖ እና ተዛማጅ ተግባራት ላይ ማተኮር እንደሚገባም አስረድተዋል። የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክርቤት አባላት ሰሞኑን በጋሞ፣በጎፋ፣በደቡብ ኦሞ እና በኮንሶ ዞኖች ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የመስክ ምልከታ በማድረግ ለምክርቤቱ ሪፖርት አቅርበዋል። የምክር ቤቱ አባላትም በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል ሲል የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ባሮ ዘግቧል።

  February 17, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የደቡብ ክልል የዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ስራ በይፋ ተጀመረ የክልሉ ግብርና ቢሮ የ2015 ዓ.ም የተፋሰስ ልማት ስራ በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በታችኛዉ በዴኔ ቀበለ በይፋ ተጀምሯል። የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ የ2015 ዓ.ም የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ የፌዴራል፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሀላባ ዞን ተጀምሯል። በዌራ ወረዳ ታችኛዉ በደኔ ቀበሌ ዛሬ ጥር 15 ቀን ክልላዊ የተፋሰስ ልማት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው፣ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ፣በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር፣ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ለማ ገዙሜ፣ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር መሐመድ ኑርዬ እና ሌሎች የክልልና የዞን የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

  January 23, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን አደረሳችሁ ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል ፡- እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! የጥምቀት በዓል ብዙ ትርጉሞችን ይዞ የሚከበር በዓል ነው፡፡ በአንድ በኩል ለክርስቲያኖች ትኅትናን የሚማሩበት፣ በእግዚአብሔር ማመናቸውን የሚያውጁበት፣ ንስሐና ድኅነት የሚያገኙበት ምልክት ሆኖ ያገለግላል፡፡ በሌላ በኩል እንደ ሀገር የጥምቀት ክብረ በዓል መልከ ብዙ የሆንን ኢትዮጵያውያን ኅብር ፈጥረን የምንደምቅበት በመሆኑ ታላቅ ቦታ ሰጥተን እናከብረዋለን፡፡ በዓለ ጥምቀትና ትኅትና ተነጣጥለው የሚታዩ ጉዳዮች አይደሉም፡፡ ምክንያቱም ጥምቀት ፈጣሪ በፍጡር፣ አምላክ በሰው፣ ጌታ በአገልጋዩ የተጠመቀበት እለት ነውና። ከነበረበት ከፍታ ወርዶ ከሰው የተስተካከለበት፣ ከቆመበት የጌትነት ስፍራ ዝቅ ብሎ ትኅትናን ያሳየበት፣ ትእቢትን ሽሮ ለሰው ልጆች ትኅትናን ያስተማረበት አጋጣሚ ነው - ሥርዓተ ጥምቀቱ። በሥርዓተ ጥምቀቱ አጥማቂው ዮሐንስም ያሳየው ትኅትና እንዲሁ በምሳሌነት ይጠቀሳል፡፡ ፈጣሪው የሰጠውን ክብር እንደሚገባው ቆጥሮ በተዓብዮ ሳይታጠር፤ ‘እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?’ ብሎ ማከላከሉ የመከበር ምሥጢሩ ትኅትና እንደሆነ፣ የኃይልና የብርታት ቁልፍ ታዛዥነት ውስጥ እንዳለ፣ የበላይነት መገኛውም ወደታች ወረዶ እያገለገሉ ጽድቅን መፈጸም እንደሆነ ያስተምረናል። ሰዎች ከላይ የሆኑ ሲመስላቸው የታቹን የማያዩና የገዘፉ ሲመስላቸው በቅንነት ጎንበስ የማይሉ ከሆነ እነሱ የጥምቀቱ ትርጉም አልገባቸው። ትኅትናን ንቀው ትዕቢትን የመረጡ፣ ዝቅ ማለት ከብዷቸው ራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደረጉ፣ ቅንነትን ጠልተው ግፍ መሥራት የወደዱ መጨረሻቸው ዕድገት ሳይሆን ቁልቁለት፣ ክብር ሳይሆን ውርደት መሆኑን በብዙ አጋጣሚዎች ዓለም አሳይታናለች። በተቃራኒው የተሰጣቸውን ኃይል ለመልካም ዓላማ የተጠቀሙ ዘወትር ሥማቸው በጥሩ ሲነሣ ይኖራሉ። እንደ ሙሴ ያሉት የተሰጣቸውን በትር ባሕር ከፍለው ሕዝብን ወደ ተስፋ ሲያሻግሩ፤ እንደ ጎልያድ ያሉት ከሰው ሁሉ በላይ መግዘፋቸውን ለበደል ተጠቅመውታል፤ በዚህም ምክንያት ሙሴዎች ሲወደሱ ጎልያዶች በቀላሉ በጠጠር ወድቀዋል። ዓይናችንን ገልጠን ብንመለከት በዙሪያችን ከፍታቸውን ለክፋት፣ ኃይላቸውን ለጭቆና በመጠቀማቸው አሳዛኝ ውድቀት የገጠማቸው ጎልያዶችን በአቅራቢያችን እናገኛለን። ተመሳሳዩ ዕጣ እንዳይገጥመን ሁላችንም ትኅትናና መልካምነትን ገንዘባችን ልናደርግ ይገባል። ሌላኛው የጥምቀት ምሳሌ የመዳንና የንስሐ ምልክት መሆኑ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ፈለገ ዮርዳኖስ ከመውረዱ በፊት በኃጢአት የተሸፈነውን አዳም የኃጢአት ልብሱን ከላዩ ላይ ሊጥልለት የሞከረ አልነበረም። ጌታ ኢየሱስ በማዕከለ ዮርዳኖስ የመቆሙ ምክንያት የአዳምን ውርደት ለመቀበል፣ ኃጢአቱን ወስዶ ከመከራው ለማዳን፣ የሚነትበውን ልብስ ጥሎ በማይነትብ ዘላለማዊ ልብስ ለመተካት ነበር። በየዓመቱ ጥምቀቱን የምናከብረውም ከፊት-ቀድሞ ከመከራ የታደገን ክርስቶስን እያሰብን ነው። ዛሬ የምናያቸውና የምንረማመድባቸው መንገዶች በአንድ ወቅት ጢሻ የነበሩና በፊት ቀደሞች መሥመር የወጣላቸው ናቸው። ዛሬ የሠለጠኑ ሀገሮች የሥልጣኔ ከፍታ ላይ የደረሱት በአንድ ወቅት ፊት አውራሪዎቻቸው በመከራ ውስጥ አልፈው፣ ችግርና ፈተናውን ተሻግረው መሠረት ስላኖሩላቸው እንጂ አዲስ ተዓምር ተፈጥሮላቸው አይደለም። ድኅነት፣ መታደስና ብልጽግና የሚመጣው ፊት ቀዳሚዎች ችግርና መከራውን ተጋፍጠው መንገድ ማስመር ሲችሉ ብቻ ነው። እኛ የዛሬው ትውልዶች ለሀገራችን ፊት ቀዳሚዎቿ እንደሆንን ማመን ይገባናል። እኛ መከራዋን ሳንቀበል ለኢትዮጵያችን ምቾት፣ ዝቅታውን ሳናይ ለሀገራችን ከፍታ፣ ጭለማውን ሳንጎበኝ ለልጅ ልጆቻችን ብርሃን እንደማይመጣ ማወቅ አለብን። ሀገራችን በድህነትና እርዛት የጠየመ ፊቷን፣ በኋላቀርነትና በጉስቁልና ያደፈ ልብሷን እኛ ወስደን በአዲስና በሚያበራ የመተካት ኃላፊነት እያንዳንዳችን ትከሻ ላይ ወድቋል። ኃላፊነታችንን በአግባቡ ከተወጣን የማናፍርባትን ሀገር፣ የሰለጠነች ኢትዮጵያን፣ የምንኮራበት ታሪክን ለልጅ ልጆቻችን ማስተላለፍ እንችላለን። ቅድመ አያቶቻችን ዋጋ ከፍለው በማለፋቸው ዛሬ የምንኮራባቸውን ሀገራዊ እሴቶች እንዳገኘን ሁሉ፤ እኛም ለመጪው ትውልድ ተመሳሳዩን ማድረግ ይጠበቅብናል። ውድ የሀገሬ ሕዝቦች፣ በዓለ ጥምቀቱ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ከሃይማኖታዊ ክብረ በዓልነቱ በዘለለ ባህላዊ እሴቶቻችን የሚስተናገዱበት በዓል ጭምር ነው። ከጎንደር እስከ ሐረር፣ ከመቀሌ እስከ ባሌ፣ ከመተማ እስከ ጅማ በየስፍራው ኢትዮጵያውያን ወደ አደባባይ ይወጣሉ። አያሌዎች ዘመድ ለመጠየቅ ከቦታ ቦታ ይተምማሉ። ማኅበራዊ ኑሯችን የሚደምቅበት፣ በልዩ ልዩ አልባሳት የምናጌጥበት፣ ልዩ ልዩ ኅብረ ዜማዎችን የምንሰማበት ዕለት ነው። ጥምቀት የአደባባይ የባህል ሙዝየማችን ነው። ኢትዮጵያ ምን ዓይነት ብሔሮች፣ ቋንቋዎች፣ አለባበሶች፣ የፀጉር አሠራሮች፣ ዜማዎች ወዘተ አሏት ብሎ ለሚጠይቅ፤ የጥምቀትን በዓል ተመልከት! ብሎ መመለስ ይቻላል። በዚህ ምክንያት ከዓለም በተለየ ጥምቀትን የእኛ ቅርስ ማድረግ ችለናል። ይሄንን ልምድ በሌሎች ዘርፎችም ልንደግመው ይገባል። ዴሞክራሲን በእኛው ቁመትና ወርድ ሰፍተን ካበጃጀነው፣ ቴክኖሎጂዎችን ኢትዮጵያዊ ለዛ ሰጥተን ከሠራነው፣ በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች እኛን የሚመስሉ እሴትና ወረቶችን ካዳበርን በርግጥም ዓለም ፊቱን ወደእኛ ማድረጉ አይቀርም። ዛሬ ባሕረ ዮርዳኖስ ከሚገኝበት ሀገረ እስራኤል ጨምሮ ከመላው ዓለም ጥምቀትን ለመታደም በየዓመቱ ቱሪስቶች ወደ እኛ ይመጣሉ። የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኝዎችን የሚስብ ታላቅ ቀን በመሆኑ ጥምቀት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳም እናገኝበታለን። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አንድ ማወቅ ያለብን እውነት የኢትዮጵያ በዓላት የኢትዮጵያውያን ሁሉ በዓላት መሆናቸው ነው። በእምነቱ ብናምንም ባናምንም፣ በዓሉ ግን በዜግነት የሁላችንም ነው። የጥምቀትም፣ የዒድ አል ፈጥርም፣ የፋሲካም፣ የዒድ አልአድሐም፣ የገናም፣ የመውሊድም በዓል የሁላችንም ናቸው። የሀገራችን ሀብት የወገኖቻችን ደስታ ናቸውና እንኮራባቸዋለን። ሁላችንም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳና እና ማኅበራዊ ጥቅም እናገኝባቸዋለን። በተለይ እንደ ጥምቀትና አረፋ ያሉ የአደባባይ በዓሎቻችንን በአማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበሩ ሁላችንም እኩል ልንደክም ይገባል። መቼም ቢሆን፣ ጥምቀት ተስተጓጉሎ አረፋ፤ አረፋ ተስተጓጉሎ ጥምቀት አይሠምርምና። ለሁላችንም ደስታ እያንዳንዳችን የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ይገባናል። በዓሉ በሰላም፣ በድምቀትና በክብር እንዲከናወን የምትተጉ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል። በድጋሚ፣መልካም የከተራና የጥምቀት በዓል እንዲሆን እመኛለሁ። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ጥር 10፣ 2015 ዓ.ም

  January 18, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጂ ከ300 ሺህ በላይ የፍራፍሬ ችግኞችን እያዘጋጀ ነው

  በደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጂ ለገቢ ማመንጫ፣ ለምግብ ዋስትና ማረጋገጫ፣ ለአካባቢ ጥበቃና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በማዘጋጀት በክልሉ የተጀመረው የ30 -40-30 ፕሮግራም እንዲሳካ እየሰራ ነው።

  ኮሌጁ አምና 3ሺህ የአቦካዶ፣ የማንጎ፣ የፓፓያና የሙዝ ችግኞችን ተክሎ እየተንከባከበ እንደሚገኝ የኮሌጁ ዲን ረዳት ፕሮፌሰር መርክነህ መሰኔ ገልጸው ለህብረተሰቡም ከ150 ሺህ በላይ የፍራፍሬ ችግኞችን ማሰራጨቱን አሳውቀዋል።

  በተያዘው አመትም ክልላዊ ፕሮግራሙን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል 300 ሺህ የአቦካዶ፣ የማንጎ፣ የፓፓያ፣ የሙዝና የቡና ችግኞች እያዘጋጀ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

  ረዳት ፕሮፌሰር መርክነህ ኮሌጁን በአስር አመት ውስጥ የፍራፍሬ ጫካ ለማድረግ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የኮሌጁ ማህበረሰብ እየተረባረበ እንደሚገኝም አስረድተዋል።

  ከኮሌጁ ውጭ የሚገኙ የተጎዱ ቦታዎችንና የተከለሉ ስፍራዎችን የፍራፍሬ ምንጭ ለማድረግ የከተማ ነዋሪውንና የኮሌጁ ማህበረሰብን ያሳተፈ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

  ኮሌጁ የሚታወቅበትን የሽቅብ ግብርና አሁንም አስፋፍቶ መቀጠሉንም ዲኑ አሳውቀው ከዞኑ ሊግ ጽህፈት ቤት ጋር በመቀናጀትም የዞኑ ሴቶች ልምድ እንዲያገኙ የማድረግ፣ችግኝ፣ የፍራፍሬና የአትክልት ዘሮችንም እንዲያገኙ መደረጉንም አመልክተዋል።

  በኮሌጁ ቅጥር ግቢ የተተከሉት ፍራፍሬዎች ምርት መስጠት መጀመራቸውንና ምርቱም ወደህብረተሰቡና ወደኮሌጁ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ እንደሚገኝም ረዳት ፕሮፌሰር መርክነህ መሰኔ አስረድተዋል።

  ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሌጁ በሀገር አቀፍ ኢንተርፕራይዞች ኢግዚቢሽን እና ባዛር እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን ባቀረባቸው ቴክኖሎጂዎች ከፍተኛ አድናቆትን እያገኘ መሆኑን በኢግዚብሽን እና ባዛሩ በአካል በተገኘንበት ወቅት ታዝበናል።ምንጭ:- የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ

  January 16, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የባስኬት ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ "ሾልኣ-ካሻ" በዓል እየተከበረ ነው

  የባስኬት ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ "ሾልኣ-ካሻ" በዓል በአደባባይ እየተከበረ ይገኛል።

  በዓሉ በየዓመቱ በጥር ወር መጀመሪያ ቀናት የሚከበር ሲሆን ከአሮጌ ወደ አዲስ ዓመት የመሸጋገሪያ በዓል ነው፤ በሌላ በኩል በባስኬት ማኅበረሰብ ዘንድ የምሰጋና በዓል ተደርጎ ይወሰዳል።

  ይህም አርሶ አደሩ ሰብል ከሰበሰበ በኋላ ለፈጣሪው ምሰጋና የሚያቀርብበት እና ቀጣዩ ዓመት የሰላም፣ የጤና እና ጥሩ ምርት የሚገኝበት ዘመን እንዲሆንም ጭምር ፈጣሪውን የሚለማመንበት በዓል ነው።

  ዛሬ በተከበረው በዓል ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስቴር አቶ ተሰፋዬ በልጂጌ፣ የደቡብ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም ተሰፋዬን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል ሲል ልዩ ወረዳው መ/ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ዘግቧል።

  January 10, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የበኣል ገበያ ዋጋን ለማረጋጋት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ

  በክልሉ ከ3 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት በስርጭት ላይ መሆኑም ታውቋል።

  ደቡብ ክልል መጪዎቹን የገናና የጥምቀት በኣላት ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የገበያ ዋጋ ንረት ለማስተካከል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል ።

  የቢሮው ሃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ እንዳሉት ዋጋን ለማረጋጋት ከመንግስት የሚቀርቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን አቅርቦት በማጠናከርና የደላላን ጣልቃ ገብነት በመቆጣጠር የሸቀጦች የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር እየተሰራ ይገኛል።

  በተለይም በክልሉ ከዚህ በፊት የነበረውን ክምችት ሳይጨምር ከ3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይትና ከ86ሺ ኩንታል በላይ ስኳር ቀርቦ ለተጠቃሚው እየተሰራጨ መሆኑን አስታውቀዋል።

  የእንስሳት ህገ ወጥ ግብይትን ለመከላከል ጠንካራ ስራ መሰራቱንም አቶ ማሄ ጠቁመዋል ።

  በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የገበያ ሁኔታው የመረጋጋት ሁኔታ እየታየበት መሆኑን ያስረዱት የቢሮ ሃላፊው በዚህ ረገድ የሰንበት ገበያዎች ሚና ትልቅ ነው ብለዋል።

  ህብረተሰቡ በቀጣዮቹ በኣላት ራሱን ጊዜ ካለፈባቸውና ጥራታቸውን ካልጠበቁ ሸቀጦች እንዲጠብቅና ቆዳና ሌጦን በአግባቡ ይዞ ለገበያ እንዲያቀርብ ማሳሰባቸውን የዘገበው የክልሉ መ/ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።

  January 10, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከ37 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ተመርቀዉ ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ፡፡

  ተመርቀዉ አገመልግሎት መስጠት የጀመሩት የመሠረተ ልማት ስራዎች፣ ባለ 3 ወለል የከተማዉ አስተዳደር ህንፃ፣ 3 ነጥብ 5 ኪ.ሜ የመንገድ ዳር መብራትና የኮብልስቶን ( ጌጠኛ ድንጋይ) ንጣፍ መንገድ ናቸዉ፡፡

  በዚህ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የደቡብ ክልል ኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይልማ ሱንታ እና የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅን ጨምሮ ሌሎችም አካላት ተገኝተዋል ፡፡

  January 2, 2023

  | ክልላዊ ዜና

 • የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የገቢ አሰባሰብ ስራው ላይ በተጠያቂነት ሊሰራ እንደሚገባ የደቡብ ክልል ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አሳሰበ

  የደቡብ ክልል ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የ 2015 ዓ.ም የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀሙን ገምግሟል::

  የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሚሊኪያስ እስራኤል በዚሁ ወቅት እንዳሉት 88 ነጥብ 3 በመቶው የተጠናቀቀው የህዳሴ ግድብ ቀሪው ስራ በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ህበረሰተቡ በእውቀት፣ በጉልበት በገንዘብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል::

  እንደ ኃላፊው ገለፃ የህዳሴ ግድቡ መሰረት ከተጣለበት አንስቶ ክልሉ ከ1 ቢሊየን 28 ሚሊየን ብር በላይ አሰባስቦ ገቢ አድርጓል::

  የደቡብ ኦሞ ዞን የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሀይሌ ሽብሩ እንዳሉት ዞኑ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ76 ሚሊየን ብር በላይ ቦንድ መሸጡን ገልጸው የህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር የውሀ ሙሌትን ተከትሎ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ ኩነቶችን በማዘጋጅት በግማሽ ዓመቱ ከ78 ሺ ብር በላይ ገቢ አሰባስቧል::

  ሶስተኛ ዙር ቦንድ የመመልስ ስራ መሰራቱን የገለፁት አቶ ሀይሌ ድጋሚ ቦንድ እንዲገዙ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል::

  የጋሞ ዞን ህዳሴ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ባለሙያ አቶ ዋንጂ ዋናቃ በበኩላቸው የጋሞ ዞን እስካሁን ከ271 ሚሊየን ብር በላይ አሰባስቦ ገቢ ማድረጉን ተናግረዋል::

  ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው ክፍያ ተፈጽሞ ቦንድ አለመስጠት፣ ለአርሶ አደሮች ደረሰኝ አለመስጠት፣ የኦዲት ግኝት ልዩነት እንዲሁም ኦሞ ባንክ አካባቢ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ተግዳሮት መሆናቸውን ተናግረዋል::

  ለመከላከያ ይደረግ ከነበረው ድጋፍ ጋር ተያይዞ በታሰበው ልክ ገቢ መሰብሰብ አለመቻሉንም አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቁመዋል::

  በደቡብ ክልል የርዕሰ መስተዳድርሩ የመሰረተ ልማት አማካሪ አቶ ታረቀኝ ሀ/ማርያም በማጠቃለያው እንደገለፁት ደረሰኝ አለመስጠት እና ሌሎች ክፍተቶችን ለማስተካከል ከክልል ጀምሮ ባለው መዋቅር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አንስተው በቀጣይም ችግሮችን መፍታት የሚያስችል መረጃ መለዋወጥ እንደሚያስፈልግ አበክረዋል::

  እንደ ሀገር የተፈጠረው ግጭት እና ለመከላከያ የሚደረገው ድጋፍ ለገቢ ማሰባሰቡ ተግዳሮት እንደነበር የገልጹት አቶ ሚሊኪያስ በቀጣይ የተለያዩ ገቢ ማሰባሰቢያ ሁነቶችን በማዘጋጀት እንደሚሰራ ገልፀዋል::

  ከደረሰኝና ኦዲት ግኝት ጋር በተያያዘ የሚታዩ ክፍተቶች ላይ ህጋዎ እርምጃ ለመውሰድ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለማጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

  December 31, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የበጋ መስኖ ስራን ውጤታማ ለማድረግ በየደረጃው የሚገኙ አካላት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል አለ የደቡብ ክልል የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ።

  ኤጀንሲው ከዞንና ከልዩ ወረዳ ለተውጣጡ የኮንስትራክሽን አመራሮችና ባለሙያዎች የኮንስትራክሽን ግዢና ኮንትራት አስተዳደር እንዲሁም የኮንስትራክሽን ሱፐርቪዥን ላይ ያተኮረ ስልጠና በወላይታ ሰጥቷል።

  በመድረኩ የተገኙት የኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ካሳዬ ተክሌ እንዳሉት ሀገራችን ትኩረት ከሰጠቻቸው ስራዎች አንዱ የመስኖ ስራ በመሆኑ ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል።

  በተለይ የመስኖ ግንባታና የኮንትራት አስተዳደር እንዲሁም የመስኖ ተቋማት አስተዳደር በሰፊው ካልተሰራበት የበጋን መስኖ በሚገባ ማሳካት አንችልም ብለዋል።

  በመሆኑም ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የ2015 የበጋ መስኖን ውጤታማ ለማድረግ ሰፊ ጥረቶች እያደረጉ መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስኪያጁ በተለይ ግንባታዎቹ በሚገባ ተጠግነውና ደለሎች ወጥተው የውሀ አቅርቦታችንን የማስተካከል ስራ መስራት አለብን ።

  በተለይ በዘርፉ ውጤታማነት ላይ ማነቆ ከሆኑት መካከል አንዱ የአቅም ውስንነት መኖሩ ነው ያሉት አቶ ካሳዬ ይህን ማነቆ ለመፍታት የአቅም ግንባታ ስራዎቻችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።

  በመሆኑም በዘርፉ ላይ የሚታዩ ችግሮች በተለይ በግንባታ ላይ የሚታይ የጥራት ችግር፣ የኮንትራት አስተዳደራችን ደካማ መሆን፣ የጥራት ጉደለቶች መታየትና የሱፐርቪዥን አቅማችን ደካማ መሆን ትኩረት ሰጥተን የምናያቸውና የምንሰራባቸው ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።

  በተለይ በኮንትራት አስተዳደራችን ላይ እንደፈለግን ግዜ የምናራዝምበት ፣ፕሮጀክቶች በፍጥነት የማይጠናቀቁበት፣ በኮንትራት ህግ አስተዳደር መሰረት የማይመሩበት፣ ጥራት የማይጠበቅበት ፣የክፍያ ሰነድ አዘገጃጀት ደካማ መሆን ከአቅም ውስንነት የሚመነጩ በመሆናቸው እነዚህን መቅረፍ በሚያስችል ላይ ያተኮረ ስልጠና ነው ብለዋል።

  ስልጠናውም በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል አቅምን የሚገነባ ነው ያሉት አቶ ካሳዬ ሰልጣኞችም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው በመከታተል የሚያገኙትን እውቀት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

  የስልጠናው ትኩረትም የፕሮጀክት ማናጅመንት ፣የኮንስትራክሽን ግዢና ኮንትራት አስተዳደር እና የኮንስትራክሽን ሱፐርቪዥን ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት እየተደረገበት መሆኑን የዘገበው ደቡብ ክልል መን/ኮ/ ቢሮ ነው።

  December 29, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የሥራ ዘመን ቆይታቸውን አጠናቀው የተመለሱ አምባሳደሮች ምስጋና እና እውቅና ተዘጋጀላቸው

  ኢትዮጵያን በመወከል በተለያዩ አገራት በአምባሳደርነት አገልግለው የሥራ ዘመን ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው ለተመለሱ አምባሳደሮች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቶላቸዋል።

  አምባሳደሮቹም :-

  አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ፣ አምባሳደር ዓለማየሁ ተገኑ፣ አምባሳደር አቡዱልፈታ አብዱላሂ፣ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ፣ አምባሳደር ዘነበ ከበደ፣ አምባሳደር ረታ ዓለሙ፣ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ፣ አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን፣ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፣ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ፣ አምባሳደር ሀሰን ታጁ እና አምባሳደር መለስ ዓለም መሆናቸውን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

  አምባሳደሮቹ የተዘጋጀላቸውን የምስጋና የምስክር ወረቀት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እጅ ተቀብለዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

  December 28, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታና ነባሩን በአዲስ የማደራጀት ማስፈፀሚያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት የክልሉ አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ በተገኘበት የአፈፃፀም ሪፖርቱን በዲላ ከተማ እያስገመገመ ነው።

  የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እርስቱ ይርዳው፣ የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የማስፈፀሚያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ኩታዬ ኩስያ፣ የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ የዞንና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎችና የመንግስት ዋና ተጠሪዎች እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ የፕሮጀክቱ ፅ/ቤት አፈፃፀም ሪፖርት እየተገመገመ ይገኛል።

  የፕሮጀክት ፅ/ቤቱ የአንድ ወር የዕቅድ አፈፃፀሙን ነው በአብይ አስተባባሪ ኮሚቴው እያስገመገመ የሚገኘው።

  December 26, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የክልሉ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሃላፊዎች በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተመረተ ያለ የድንጋይ ከሰል ምርትን ጎብኝተዋል።

  በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በስፋት የሚገኘውን የድንጋይ ከሰል ማዕድን ጥቅም ላይ ለማዋል የተቀናጁ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው።

  በዚሁ መሰረትም በዚህ አመት በተለይ በጋሞና ወላይታ ዞኖች አራት ወረዳዎች ውስጥ የሚገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው የድንጋይ ከሰል በማምረት ጥቅም ላይ ለማዋል ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተጠቁሟል።

  የክልሉ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሃላፊዎች በዛሬው እለት በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ለመጀመሪያ ጊዜ በባለሀብት እየተመረተ ያለ የድንጋይ ከሰል ምርትን ጎብኝተዋል።

  የቢሮው ሃላፊ ኢንጂኔር አክልሊ አዳኝ እንዳሉት በስፋትና በጥራት የሚገኘውን የማዕድን ምርት ወደ ገበያ በማውጣት የዘርፉን የግብኣት ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ ይገኛል።

  በክልሉ የሚገኘው የድንጋይ ከሰል ጥራት ከውጭ ከሚገባው የላቀ እንደሆነም ተናግረዋል ።የማዕድኑ ዘርፍ ሀገሪቱ ለጀመረችው የለውጥ ሂደት የራሱን ድርሻ እንዲያበረክት ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉም ሃላፊው ተናግረዋል ።

  የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አጸደ አይዛ በበኩላቸው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የግንባታ ማዕድናትን ሳይጨምር ከ25 በላይ ማዕድናት መኖራቸው በጥናት መረጋገጡን ጠቁመዋል።

  በተለይ በዚህ አመት ጥራት ያለው የድንጋይ ከሰል በማምረት የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ግብኣት እጥረት ችግርን ለማቃለል እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል ።

  በማምረት ሂደትም የግል ባለሀብቱ ተሳትፎ እያደገ ይገኛል ብለዋል ።

  በዛሬው እለት የክልሉ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት ባለሀብቶች እየተመረተ ያለ የድንጋይ ከሰል ምርትን ጎብኝተዋል።ምንጭ፦ደ/ክ/መ/ኮ/ ቢሮ

  December 23, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በደቡብ ክልል ያሉ ፍርድ ቤቶች በህዝብ ዘንድ አመኔታ እንዲኖራቸው ከሙስናና ብልሹ አሰራር ነጻ ሊሆኑ እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አሳሰቡ።

  የደቡብ ክልል ፍርድ ቤቶች ሙስናን በተግባር የመታገያና የጥቆማ ስርዓቶች ንቅናቄ መድረክ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄዱ ነው።

  መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ፋጤ ሰርሞሎ እንዳሉት ፍርድ ቤቶች ከሙስና ፀድተው ገለልተኝነታቸው ሊረጋገጥና በህዝብ ዘንድ አመኔታ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።

  በሀገር ሰላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የፍትህ ተቋማት ሚና ከፍተኛ ቢሆንም ዘርፉ የሙስና ተግባር እየተስተዋለበት መምጣቱን ተናግረዋል።

  ችግሩ ጥቅመኞች ህግንና ህገመንግስታዊ ሥርዓትን ተከትለው ህዝብን ባለማገልገላቸው የመጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

  ፍርድ ቤቶች በህዝብ ዘንድ አመኔታ ያላቸው ተቋም እንዲሆኑ ከሙስና የፀዱና ገለልተኝነታቸው የተረጋገጠ ሊሆን እንደሚገባም አፈ-ጉባኤዋ አሳስበዋል።

  እንደእሳቸው ገለጻ ባልተገባ የጥቅም ግንኙነትና ወገንተኝነት የሚሰሩ ግለሰቦችን በማጋለጥና በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማስቻል ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል።

  “በተለይ ፍርድ ቤት በሙስና የተጠረጠሩ አካላት ጭምር ፍርድ የሚሰጥበት በመሆኑ ዳኞችም የሙስና ሰለባ ከሆኑ ችግሩን የከፋ ያደርገዋል” ብለዋል።

  ይሄንን በአግባቡ በመገንዘብ በፍርድ ቤቶች ከህግ አግባብ ውጪ የሚሰሩ አካላትን በተቀመጠው የአሰራር ስርዓት ተጠያቂ ለማድረግ ጠንካራ ትግል ማድረግ እንደሚገባ ወይዘሮ ፋጤ አሳስበዋል።

  የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሰኖ አቡሬ በበኩላቸው “በፍርድ ቤቶች የሚስተዋሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመግታት ሙሰኞች ተለይተው የሚጠየቁበትን ሥርዓትን ማጠናከር ያስፈልጋል” ብለዋል።

  ሙስናና ሌብነትን በተለመደው አሰራር ብቻ መታገል የሚፈለገውን ውጤት እንደማያመጣ ጠቁመው፣ ለትግሉ የህዝብ ንቅናቄ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ገልፀዋል። “ህብረተሰቡ፣ ዳኞች እና ሌሎች ፈፃሚዎች ሙሰኞችን ለመጠቆም የሚችሉባቸው መደበኛና የሞባይል ስልኮች፣ ነፃ የስልክ መስመር፣ የፌስቡክ አካውንት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረገጽ እና የቴሌግራም መቀበያ ቁጥሮች ተደራሽ ለማድረግ ይሰራል” ብለዋል።

  ህዝብን ያሳተፈ ንቅናቄ ፈጥሮ በጋራ በመስራት ሌብነትን ለማስቀረትና ፍርድ ቤቶችን ከሙስናና ብልሹ አሰራር ለመታደግ ተቋሙ በኃላፊነት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

  በንቅናቄ መድረኩ ላይ በደቡብ ክልል አስር ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

  December 21, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ''የንባብ ህመምን በንባብ ክሊኒክ ማከም''በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ክልላዊ የንባብ ዘመቻ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

  ለዘመቻው መድረክ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስላለፉት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ እንዳሉት በትምህርት ዘርፍ ውጤታማ ዜጋን የማፍራት ስራ ከታችኛው ክፍል ደረጃ ጀምሮ ሊሰራ ይገባል።

  በወላይታ ዞን በተካሄደው ጥናት 57 በመቶ የሚያህሉ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ መረጋገጡን የጠቆሙት አቶ አክሊሉ ይህም በዘርፉ የታየውን ድክመት አጉልቶ የሚያሳይ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

  ውጤታማ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራት ትምህርት መሠረት ነው ፤ንባብ ደግሞ ለእውቀት ሁሉ በር ከፋች ቁልፍ ስለሆነ መምህራንና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎችን በንባብ ክህሎት ብቁ ለማድረግ ዋጋ ከፍለው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

  በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል የማህበራዊ ክለስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ከትምህርት የተነሳ ዓለም ወደ አንድ መንደር የቀረበች መሆኑን ግንዛቤ በመያዝ የለውጡ መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

  በእውቀት፣ በክህሎትና በስነ ምግባር የበቁ ዜጎችን ለማፍራት አዲሱ የትምህርት ስርዓት ተቀርጾ በተያዘው በጀት ዓመት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

  ለሁሉም ክህሎቶች መነሻው ንባብ በመሆኑ ይህ የዘመቻ መድረክ የተጀመረ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው ለስኬታማነቱ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል።

  በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው የደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክለስተር አስተባባሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ አሳስበዋል።

  በንባብ ክህሎት ላይ የበሚታዩ ችግሮችና በመፍትሄ ሀሳብ ዙሪያ የተዘጋጁ ጥናታዊ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

  በዘመቻ መድረኩ ላይ የሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የትምህርት ዘርፍ አመራሮች፣ የክልሉ መምህራን ማህበር ተወካይ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

  December 20, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከሦስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴን በመኸር ወቅት መሰብሰብ እንደተቻለ ተገለጸ። በክልሉ በምርት ዘመኑ በመኸር ወቅት ከ177 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው መሬት በስንዴ ሰብል ተሸፍኗል። እስካሁን በተደረገው የምርት አሰባሰብ ሂደትም ከሦስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት መሰብሰቡን በደቡብ ክልል በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር ለኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት ገልፀዋል። እንደ አቶ ዑስማን ገለጻ፤ በአብዛኛው በክልሉ ቆላማ አካባቢዎች ሰብልን ከማሳ ወደ ጎተራ የማስገባት ሥራ ለብክነት በማያጋልጥ ሁኔታ እየተካሄደ ሲሆን፤ ከ70 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ40 በመቶ በላይ የስንዴ ሰብል መሰብሰብ ተችሏል። የዘንድሮው የመኸር አዝመራ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈና በሜካናይዜሽን ስልት መከናወኑን የጠቀሱት አቶ ዑስማን በተለይም ምርትን በኮምባይነር የመሰብሰብ ሥራው የምርት ብክነትን በሚቀንስ መልኩ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። እስከ አሁን በመኸር ወቅት በሰብል ከተሸፈነው 177 ሺህ ሄክታር መሬት የስንዴ ምርት ውስጥ ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉን አመላክተዋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ እንደ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሃላባ፣ ከምባታ፣ ሃዲያ፣ ወላይታ ባሉ የስምጥ ሸለቋማ አካባቢዎች እንዲሁም በከፊል የስንዴ ምርት በስፋት በደረሰባቸው ዞኖች የመኸር የስንዴ ምርት መሰብሰብ እንደተቻለ አቶ ዑስማን ገልጸዋል። ሰብሎች ገና እየደረሱ በመሆናቸው የመሰብሰብ ሥራው በቀጣይም በስፋት ይሠራል ብለዋል። የምርት አሰባሰቡ ሂደቱ የምርት መሰብሰብ ብክነትን በመቀነስ፣የገበያ ተወዳዳሪነትን በመጨመር፣ የምርትና ምርታማነት ጥራትን በማሳደግ እንደሆነም አቶ ዑስማን ተናግረዋል። በምርት አሰባሰብ ሥራው ከክልል እስከ ወረዳ ያሉት መዋቅሮች የተሳተፉ ሲሆን ለዚሁ አገልግሎት የተደራጀውን የባለሙያዎች ቡድን በክላስተር በመከፋፈል የክትትል ሥራ መሠራቱንም አስረድተዋል። በምርት ዘመኑ በዘርፉ ምርታማነትን የማሳደግ ሥራ መሠራቱን የጠቀሱት ኃላፊው፤ “በክልሉ በሚሰበሰበው የስንዴ ምርት ከራሳችን ፍጆታ አልፈን ወደ ውጪ ለመላክ እንደ ሀገር የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ክልሉ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት እየሠራ ይገኛል” ሲሉ ገልጸዋል ሲል አዲስ ዘመን ጋዜጣን ዋቢ በማድረግ ኢፕድ ዘግቧል ።

  December 17, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • "በነቃ ተሳትፎ የትምህርት ጥራትን እናረጋግጠለን" በሚል መሪ ቃል 23ኛ ዙር የትምህርት ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው። በጉባኤው ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ክልል ማህበራዊ ክለስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ በትምህርት በዓለም ብቁና ተወዳደሪ ፣ በምክንያትነት የሚያምን፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ያደገ ዜጋ ለመፍጠር ኃላፊነቱ የዚህ ባላድርሻ አካላት መሆኑን ገልጸዋል። ትምህርት የሁሉ አቀፍ በመሆኑ የማህረሰብ ችግር ፈቺ ዜጋ ማፍራት የሁሉም ባድርሻ አካላት ግዴታ እንደሆነ አስገንዝበዋል። የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አብርሃም መጫ በበኩላቸው በትምህርት ጥራት የተገነባ ዜጋ በማፍራት ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚሰማቸው ማህበረሰብ መፍጠር ይገባል ብለዋል። እያንደንዱ ትምህርት ቤት የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ የተማሪዎች ኩረጃ ማስቀረት አለበተ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ኮርጆን ማስቀረት ካልተቻለ የኢኮኖሚ ብክነትና የአዕምሮ መጭበርበር ችግር ይሆናል ነው ያሉት። በሁለንታናዊ ስብዕና የበቃ ዜጋ በማፍራት ለሀገር ብልጽግና ማብቃት እንደሚገባ የገለፁት የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ክበሞ ዴታሞ ናቸው። በመሆኑም ባላድርሻ አካላት በቅንጅታዊ የትምህርት አሠራር፣ ፍትሐዊነትንና አግባቢነት ያለውን ትምህርት በመስጠት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል። በጉባኤው የሀዲያ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጌታቸው ሊልሾን ጨምሮ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች እና የትምህርት ባላድርሻ አካላት ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው።

  December 14, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ እንዳስረዱት፤ የድሽታ ግና በዓል እሴቶች ብልፅግናን የሚያረጋግጡና የመልማት ዕድሎችን የሚፈጥር የሕዝቡ ቱባ ባህል በመሆኑ በአለም አደባባይ እንዲታወቅ መሥራት ያስፈልጋል፡፡

  የደቡብ ኦሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደሰ ካይ እንደገለፁት፤ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማጠናከር የበዓሉ ፋይዳ ለትውልድ እንዲተላለፍ ይሠራል፡፡

  ጥንት አባቶቻችን ጠብቀው ያቆዩትን በዓል አዲሱ ትውልድ ተረክቦ እሴቱ እንዳይጠፋ መጠበቅና ለዓለም ሕዝብ ይበልጥ ማስተዋወቅ እንዳለበት የደቡብ አሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዳልቅ አልቅሚ ገልፀዋል፡፡

  የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ጠልክስ እና ሌሎች የበዓሉ ታዳሚዎች እርቀ ሠላም ለድሽታ ግና በዓል መሠረት መሆኑን አንስተው ከዕለቱ ጋር በተያያዘም መልዕክት አሰተላልፈዋል፡፡

  የበዓሉን እሴቶች ለትውልድ ለማስተላለፍ አስተዋጽኦ ያለው ድሽታ ግና የሕዝብ ቤተ መጽሐፍት የመሠረተ ድንጋይ በዕለቱ የክብር እንግዶች ተቀምጧል፡፡

  December 8, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • ከአንድ ዓመት በላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባት ሽረ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

  ሁመራ እና አካባቢውም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
  በአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር መላኩ ታዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ሙሉ በሙሉ ወድሞ የነበረው የሽረ ኤሌክትሪክ መሰረት ልማት ተጠግኖ ምሽቱን ሽረ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም አግኝታለች፡፡

  አገልግሎቱ ዳግም እንዲጀምር አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁመራ እና አካባቢው አገልግሎቱን ዳግም እንዲያገኙ የጥገናና እና ፍተሸ ሥራው መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከተቻለ ምሽቱን ካልሆነም ነገ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ባለሙያዎች ርብርብ እያደረጉ መሆንም ገልጸዋል፡፡ በትግራይ ክልል ያሉ ከተሞችም አገልግሎት እንዲያገኙ የቴክኒክ ኮሚቴ መቋቋሙንና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

  December 8, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የሣውላ ከተማ አስተዳደር ንግዱ ማህበረሰብ ከ 1.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ 600 ኩንታል በመጫን እርዳታውን ወደ ወረዳዎች ለማድረስ ጉዞ ጀምሯል።

  የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበዉ በ 10 የጭነት መኪኖች የተጫነው 600 ኩንታል ውስጥ 500 ኩንታሉ ለዛላ ወረዳ ሲሆን 100 ኩንታሉ ለዑባ ደብረፀሃይ ወረዳ መሆኑን የሣውላ ከተማ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ መሠረት ለማ ገልፀዋል ሲል የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል።

  December 7, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • "ሙስናን መታገል በተግባር" በሚል መሪ ቃለ የፀረ_ሙስና ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ፣ በአገር ደረጃ ለ18ኛ እና በክልሉ ለ17 ጊዜ ነው እየተከበረ የሚገኘው።

  በማጠቃለያ ስነስርዓቱ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የደቡብ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማኔጅመንቱ እና ሰራተኞች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

  በስነስርዓቱ የደቡብ ክልል የስነ-ምግባር መዝሙር ይመረቃል፤ "ሙስናን መታገል በተግባር" በሚል ርዕሰ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ይደረጋል፤ በተጨማሪም የዕውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ተከናውኖ ቀጣይ የስራ መመሪያ በመስጠት መርሃ-ግብሩ ይጠቃለላል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበው የደቡብ ክልል መን/ኮሙ ቢሮ ነው።

  December 6, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • ምርታማነትን የሚያሳድጉ የሰብል ዝሪያዎችን በጥናትና ምርምር በማግኘት የማላመድ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።

  ኢዜአ እንደዘገበዉ ማዕከሉ በደቡብ ኦሞ ዞን በበና ፀማይ ወረዳ በአርሶ አደር ማሳዎች በኩታ ገጠም እየለማ ያለው የማሽላ ሰብል ተጎብኝቷል።

  የማሽላ ምርትን በእጥፍ ማሳደግ የሚችልና ”መልካም” በሚል የተሰየመ ምርጥ የማሽላ ዘር መሆኑም ተገልጿል። በምርምር ማዕከሉ የሰብል ምርምር የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አወቀ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለፁት ”መልካም” የተሰኘው የማሽላ ዝሪያ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚለማው የማሽላ ዝሪያ በተሻለ የአካባቢውን አየር መላመድና በሽታን መቋቋም የሚችል ነው።

  ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚለማው የማሽላ ዝሪያ በሄክታር ከ 10 እስከ 27 ኩንታል ምርት እንደሚገኝ ጠቁመው “መልካም” የተሰኘው የማሽላ ዝሪያ በሄክታር ከ45 እስከ 54 ኩንታል ምርት መስጠት እንደሚችል ገልጸዋል።

  የማሽላ ዝሪያውን በሌሎች አካባቢዎችም ለማስፋፋት እንዲያግዝ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ውጤት ላይ የልምድ ልውውጥና የመስክ ምልከታ በበና ፀማይ ወረዳ ወይጦ ክላስተር ተካሂዷል።

  በመስክ ምልከታው የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ያሲን ጉኣ፣ የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ማቲዮስ አንየው፣ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ንጋቱ ዳንሳን ጨምሮ የሰብል ተመራማሪዎችና አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል።

  December 5, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ይህንን ያሉት በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ 17ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ከወንድም ሲዳማ ህዝብ ጋር ለማክበር ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

  የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ይህ ቀን የኢትዮጵያ ብሔሮች ባህላቸውንና እሴቶቻቸውን በአደባባይ እንዲያከብሩ መሠረት የጣለ እንደሆነ አውስተው፥ የተፈቀዱ መብቶች እንዳልተፈቀዱ ተከድነው የቆዩበት ሥርዓት በለውጡ መንግስት መቀየሩን ተናግረዋል።

  የሲዳማና የወላይታ ህዝብ የተጠናከረና የቆየ ትስስር ያላቸው ህዝቦች ናቸው ያሉት አቶ አክሊሉ ይህንንም የሲዳማ ህዝብ በወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫና በሌሎች በዓላት ላይ በመገኘት አሳይቷል ብለዋል።

  ማህበራዊ ትስስሩ የቆየ እንደሆነ ገልጸው፥ የሲዳማና የወላይታ ህዝብ ሲተሳሰር ኢትዮጵያ ትጠነክራለች ብለዋል። እንግዶችንም በጋራ እንቀበላለን ያሉት አስተዳዳሪው፥ ትስስሩንም ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል።

  ምንጭ፣ Sidama National Regional State Press Secretariat

  December 3, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • አዲስ በሚደራጀው 'የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል' አደረጃጀት ዙሪያ የሀላባ ዞን አመራሮች ውይይት አድርገዋል።

  መድረኩ በሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር መሐመድ ኑርዬና የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ም/ል ተጠሪ አቶ ረመቶ መሀመድ በጋራ በመሆን መርተዋል።

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉራጌ፣ሀዲያ፣ ስልጤ፣ ከምባታ ጠምባሮ እና ሀላባ ዞኖች እንዲሁም የየም ልዩ ወረዳ 'በአንድ ክልል ተደራጅተው' እንዲቀጥሉ በወሰነው ውሳኔ መሠረት እነዚህን ስድስት መዋቅሮች ይዞ አዲስ በሚደራጀው "ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል" አደረጃጀት ዙሪያ በቀረበው ሰነድ ላይ የሀላባ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

  የውይይት መድረኩን የመሩት የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳር ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ ከክልል አደረጃጀት ጋር ተያይዞ ከሕዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በአፋጣኝ መመለስ እንደሚገባ የብልፅግና ፓርቲ ከጉባኤው ማግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ ነበር ብለዋል።

  ከሕዝብ በተደጋጋሚ የሚነሳውን ጥያቄ ለመመለስ የደቡብ ክልል በሁለት ክልሎች እንዲደራጅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የፕሮጀክት ጽ/ቤት ተቋቁሞ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን 'ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል' በሚል የሚደራጀው ክልል በሕዝበ ውሳኔ ቀሪው ደግሞ 'ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል' በሚል ስያሜ ያለ ሕዝበ ውሳኔ እንደሚደራጁም ነው ዋና አስተዳዳሪው ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ የገለፁት።

  በአዲሱ 'ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል' ከምባታ ጠምባሮ፣ ሀዲያ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ እና ሀላባ ዞኖች እንዲሁም የም ልዩ ወረዳ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስቀመጠው ውሳኔ መሠረት ያለ ሕዝበ ውሳኔ የሚደራጁ ሲሆን የአደረጃጀቱ ሒደት በተያዘው ዕቅድ መሠረት እንዲከናወን መላው የዞኑ አመራር እና ሕዝቡ ሊደግፉት እንደሚገባም አሳስበዋል።

  የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ምትክል የመንግሥት ተጠሪ አቶ ረመቶ መሀመድ በበኩላቸው በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት ነባሩን ክልል በአዲስ መልክ የማደራጀት ሥራ እየተሠራ ሲሆን 11 መዋቅሮችን የሚያቅፈው 'የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል' በሕዝበ ውሳኔ ሲወጣ ስድስት መዋቅሮችን የሚይዘው 'ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል' በተመሳሳይ ሁኔታ ያለ ሕዝበ ውሳኔ ይደራጃል ብለዋል።

  መልሶ የማደራጀቱን ተግባር በስኬት ለማጠናቀቅ የአመራሩ ግንባር ቀደም መሪነት እና የኅብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አቶ ረመቶ መሀመድ አስገንዝበዋል።

  ውይይት በዞኑ ሁሉም መዋቅሮች የሚካሔድ መሆኑም ታውቋል። በመድረኩ ላይ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአራቱም አስተዳደርና አስተበባሪዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተገኝተዋል። የሃላባ ዞን /መ/ኮ/መምሪያ

  December 3, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

  ውይይቱን የተከታተሉት የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን እንደገለጹት በአምባሳደር ትሬሲ የተመራ ልኡክ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የአሜሪካ መንግስት በተለያዩ የተራድኦ ድርጅቶች አማካኝነት በክልሉ እያደረገ ያለውን ሰብዓዊ ድጋፍ አስመልክቶ ከአምባሳደሯ ጋር በሰፊው መክረዋል።

  በእናቶችና ህጻናት ጤና፣በአርሶ እና በአርብቶ አደሩ አካባቢዎች ምርታማነትን ለማሳደግ እየተደረገ ስላለው ጥረት፣ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቋቋም እየተደረገ ስላለው እንቅስቃሴ በጋራ መክረዋል። የአሜሪካ መንግስት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እያደረገ ያለውን ጥረት ርዕሰ መስተዳድሩ አድንቀው በተለያየ ዘርፍ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጠይቀዋል። በሀገራችን ላይ የተጣለው የአገዋ እገዳ በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያስከትለውን ጫና ለማስቀረት የአሜሪካ መንግስት ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን እና በቀጣይም እገዳው ስለሚነሳበት ጉዳይ አምባሳደሯ ጠቁመዋል።

  በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀትን አስመልክቶ የፌደሬሽን ምክር ቤት የህዝቦችን ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እያደረገ ያለውን ጥረት አምባሳደሯ አድንቀዋል። የክልሉ መንግስትም ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን እያበረከተ ስላለው አስተዋጽኦ አምባሳደሯ ምስጋና አቅርበዋል። ምንጭ፦ የደቡብ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ

  December 2, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • አዲስ በሚደራጀው 'የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል' አደረጃጀት ዙሪያ የከምባታ ጠምባሮ ዞን አመራሮች በዞኑ ምክር ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተወያዩ ነው።

  የውይይት መድረኩን የመሩት የከምባታ ጠምባሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መለሰ አጭሶ ከክልል አደረጃጀት ጋር ተያይዞ ከሕዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በአፋጣኝ መመለስ እንደሚገባ የብልፅግና ፓርቲ ከጉባኤው ማግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ ነበር ብለዋል።

  ከሕዝብ በተደጋጋሚ የሚነሳውን ጥያቄ ለመመለስ የደቡብ ክልል በሁለት ክልሎች እንዲደራጅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የፕሮጀክት ጽ/ቤት ተቋቁሞ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን 'ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል' በሚል የሚደራጀው ክልል በሕዝበ ውሳኔ ቀሪው ደግሞ 'ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል' በሚል ስያሜ ያለ ሕዝበ ውሳኔ እንደሚደራጁም ነው ዋና አስተዳዳሪው አቶ መለሰ አጭሶ የገለፁት።

  በአዲሱ 'ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል' ከምባታ ጠምባሮ፣ ሀዲያ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ እና ሀላባ ዞኖች እንዲሁም የም ልዩ ወረዳ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስቀመጠው ውሳኔ መሠረት ያለ ሕዝበ ውሳኔ የሚደራጁ ሲሆን የአደረጃጀቱ ሒደት በተያዘው ዕቅድ መሠረት እንዲከናወን መላው የዞኑ አመራር እና ሕዝቡ ሊደግፉት እንደሚገባም አሳስበዋል።

  የከምባታ ጠምባሮ ዞን ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ሀብቴ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት ነባሩን ክልል በአዲስ መልክ የማደራጀት ሥራ እየተሠራ ሲሆን 11 መዋቅሮችን የሚያቅፈው 'የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል' በሕዝበ ውሳኔ ሲወጣ ስድስት መዋቅሮችን የሚይዘው 'ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል' በተመሳሳይ ሁኔታ ያለ ሕዝበ ውሳኔ ይደራጃል ብለዋል።

  መልሶ የማደራጀቱን ተግባር በስኬት ለማጠናቀቅ የአመራሩ ግንባር ቀደም መሪነት እና የኅብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አቶ ሀብቴ ገ/ሚካኤል አስገንዝበዋል። መሰል ውይይት በዞኑ ሁሉም መዋቅሮች የሚካሔድ መሆኑም ታውቋል። የከምባታ ዞ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

  December 2, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በጎፋ ዞን ኦይዳ ወረዳ በታሪካዊው ጃውሻ ተራራ የዘንድሮ 17ኛው ዙር የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል "ሕብረብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሠላም" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

  የኦይዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተገኝ አበበ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት የኦይዳ ብሔረሰብ የራሱን ባህል፣ ታሪክና ቋንቋውን እንዲያስተዋውቅ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል የጎላ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

  የመሬት እምብርት ተብሎ የሚጠራው የ"ጃውሻ ተራራ"/ "ሳአ ጉልአ" ተራራ በጎፋ ዞን ኦይዳ ወረዳ ዑባ ዳማ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ ተፈጥሯዊ የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚታወቅ ታሪካዊ ሥፍራ ነው ሲሉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል።

  ጃወሻ ተራራን ጨምሮ በወረዳው የሚገኙ ተፈጥሯዊና ባህላዊ መስህቦች እንዲለሙ በማድረግ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ የወረዳው መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። የጎፋ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ድንበሩ ድርቤ በዞኑ የሚገኙ ተፈጥሯዊ መስቦችን በማልማትና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሰሩ ካሉ በኦይዳ ወረዳ የሚገኘው የጃውሻ ተራራ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

  የዘንድሮ ዞናዊ የማጠቃለያ የ17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ታሪካዊ በሆነው በጃውሻ እንዲከበር የተደረገበት ዋና ዓላማ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በአካባቢው የሚገኙ ተፈጥሯዊና ባህላዊ መስህቦችን ለማስተዋወቅ መሆኑን የመምሪያው ኃላፊ አስረድተዋል። የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ጠንክር ጠንካ የበዓሉ ዋና ዓላማ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የእርስ በእርስ ትስስር በማጠናከር በብዝሃነት ላይ የተመሠረተ ሕብረብሔራዊና ሀገራዊ አንድነት ሥር እንዲሰድ ለማድረግ የገቡትን ቃል ኪዳን በማደስ ለሠላም፣ ለልማትና ለዲሞክራሲ ግንባታ እንዲነሳሱ ማድረግ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

  የዘንድሮ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በየደረጃው በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ብለዋል። የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል የሕዝቦችን አብሮነትና ወንድማማችነት ይበልጥ እንዲጠናከርና ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ እንዲታወቅ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን አስገንዝበዋል። በዞናችን የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች እንዲለሙ፣ እንዳታወቁና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲያበረክቱ የዞኑ መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

  ዋና አስተዳዳሪው በመልዕክታቸው የመንገድና በየአካባቢው የሚነሱ ሌሎች የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ የሕዝባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

  በክብረ በዓሉ ላይ የጎፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎችና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የዞኑ ካቢኔ አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች፣ የባህል አምባሳደሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊሆነዋል። የጎፋ ዞ/መ/ኮ/መምሪያ።

  December 1, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • ከኦሮሚያ ክልል በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለአባይ ግድብ ግንባታ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

  የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በክልሉ የተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ የክልሉ መንግስት የግድቡ ዋንጫን ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ከድሬዳዋ ተረክቦ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ሲዘዋወርና የገቢ ማሰባሰብ ሁነቶች ሲካሄዱ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።

  ዋንጫው በክልሉ ባደረገው የአንድ ዓመት ቆይታ የክልሉ ህዝብ ለግድቡ ግንባታ በስጦታ፣ በቦንድ ግዢ እና በአጭር መልእክት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

  ዋንጫው በክልሉ ያለውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ሲዳማ ክልል ለመሸኘት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል። በተመሳሳይ ሀላፊው በክልሉ ባለፉት አራት ወራት በመደበኛና በማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ 22 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ጠቅሰው ይህን የእቅዱ 87.3 በመቶ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ግብርናን በተመለከተ እስካሁን 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር ላይ የደረሰ ሰብል መሰብሰቡን እንዲሁም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማትም 278 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል ብለዋል።

  በአጠቃላይ 209 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ መናገራቸውን ከክልሉ ፕሬዝዳንት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።ምንጭ፦ኢ.ፕ.ድ

  November 28, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች አለም አቀፍ የጸረ_ሙስና ቀንና የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በጋራ አክብረዋል።

  ለ17 ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን "ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም" እንዲሁም ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የጸረ _ሙስና ቀን "ሙስናን መታገል በተግባር" በሚል መሪ ቃል ነው።

  በዚሁ ቀን የተገኙት በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ እንደገለጹት የትምህርት ተቋም ዘመን ተሻጋሪ ትውልድና በራሱ መናገር የሚችል፣ የሰው የማይፈልግ ትውልድ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሀላፊነት የተጣለበት ተቋም ነው።

  በመሆኑም በትምህርት ተቋሙ ላይ የስነ_ምግባር ስብራት አለ ያሉት ሀላፊው በዚህ አመት በአስራ ሁለተኛ ብሔራዊ ፈተና ላይ ያጋጠመን ኩረጃ አንዱ የስብራት መገለጫ ነው ብለዋል። ይህ የስነ_ምግባር ስብራት በተማሪዎች ብቻ ያጋጠመን አይደለም ያሉት ዶ/ር ዲላሞ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ገብተው የሚያስተምሩ መምህራንም ገጥመውናል።

  በትምህርት ተቋም ላይ ህጻናትን የማብቃት ፣ የኩረጃና የሌብነት ጉዳይ አሳሳቢ በመሆኑ እነዚህ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠይቃል ብለዋል።

  የብሔረሰቦች ቀንን አስመልክቶ በመልዕክታቸው እንደገለጹት ይህ ቀን የኢትዮጵያ ህዝቦች በተገቢው መንገድ የስልጣን ባለቤት መሆናቸው ያረጋገጡበት በህገ_መንግስታዊ ስርዓት መተዳደር የቻሉበት እንዲሁም የህዝቦች ድምጽ በሀገሪቱ ህግ አውጪ አካላት ላይ እንዲደመጥ እድል የሰጠበት በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

  በተለይም ለደቡብ ክልል ብሔር ብሔረሰቦች ፋይዳው የጎላ ነው ያሉት ሀላፊው ለዚህም ትልቁ ማረጋገጫ በፌደሬሽን ምክር ቤት ላይ ትልቁን መቀመጫና ብዛት የያዙት የደቡብ ክልል ህዝቦች በመሆናቸው ነው ሲሉ አብራርተዋል።

  ሀላፊው አክለውም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በትግል ይሳተፋሉ እንዲሁም የሀገርን ሉአላዊነት በማስከበር ረገድ ትልቅ ሚና ይወጣሉ ብለዋል። በተለይም ይህ ቀን ሲከበር ዘመን ተሻጋሪ ትውልድ በመቅረጽ ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው ያሉት ሀላፊው ህጻናትም ይህን አውቀው እንዲያድጉ በማድረግ ረገድ በስነ_ምግባር ትምህርት ውስጥ በማካተት ሊማሩ ይገባል ብለዋል።

  የህብረ ብሔራዊ ፌደራል ስርዓት ምንነት ባህርያት እና የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በአቶ ሀብታሙ ቶማስ እና አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን አስመልክቶ በአቶ ወርቅአገኘሁ አሻግሬ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ምንጭ፦ ደቡብ ክልል መ/ኮሙኒኬሽን ቢሮ

  November 28, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በልዩ ወረዳው ለነባር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ደህንነትና ብቃት ማረጋገጫ ዙሪያ የታድሶ ስልጠና ተሰጠ።

  የአሽከርካሪንና ተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶረት ለነባር አሽከርካሪዎች፣ መሠረታዊ የተሽከርካሪ ውስጣዊና ውጫዊ ክፍል አያያዝና አጠቃቀም አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

  የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬቶረት ቡድን መሪ አቶ አዱኛ ኤለማ በስልጠናው ወቅት እንደገለፁት ማንኛውም ተሽከርካሪ ውስጣዊና ውጫዊ ክፍል ደህንነቱ በደንብ ሳይፈትሽ መንቀሳቀስ ያልታሰበ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመዋል። በዋናነት የተሽከርካሪ መቆጣጠርያ ክፍሎች በተገናኘ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

  የመንገድ ደህንነት ቡድን መሪ አቶ ጀግና ሽታዬ በበኩላቸው አሽከርካሪዎች ገንዘብ ሣይሆን ቅድሚያ ለተገልጋዮች ትኩረት መስጠት አለባቸው ብለዋል።
  የአማሮ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ፅ/ቤት ዘግቧል።

  November 26, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በጎፋ ዞን አቃቤ ህግ መምሪያ ልዩ ልዩ የወንጀል ጉዳዮች ሥራ ሂደት ዋና አስተባባሪ አቶ ምስራቅ በላቸው እንደገለጹት ለህጻናቱ ህይወት ህልፈት በፖሊስ የወንጀል ምርመራ በመረጋገጡ ነው የፍርድ ውሳኔ የተላለፈው፡፡

  በዞኑ ኡባ ደብረ ፀሀይ ወረዳ ጋዶላ ጎዱማ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አሳሼ አታረ የስድስትና የስምንት ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሁለት የወንድሙ ልጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ረቡዕ ዕለት በግምት ከቀኑ 11 ሰዓት አከባቢ ሲሆን በእርሻ ማሳዬ የሚገኘውን አትክልት በበግ አስበልተዋል በሚል ሰበብ መሆኑን አንስተዋል።

  ተከሳሹ ሁለቱን ህጻናት አባብሎ ወደ ቤቱ አስገብቶ በስለት ወግቶና ቆራርጦ በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ በኋላ በማዳበሪያ ጠቅልሎ ሽንት ቤት ውስጥ መጣሉንም አስረድተዋል። የዞኑ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ አለሙ መለሰ እንደገለጹት ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆኖ የጎፋ ዞን አቃቤ ህግም የወንጀል ህግ አንቀፅ 539(1)ሀ/ድንጋጌን በመጥቀስ ክስ መስርቶበት በማስረጃ በመረጋገጡ ግለሰቡ በእስራት እንዲቀጣ መደረጉን ገልጸዋል።

  በዚሁ መሰረት የጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 15/2015 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት በተከሳሽ አቶ አሳሼ አታረ ላይ የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ መተላለፉን ዳኛው ተናግረዋል።

  ወንጀለኞች የሚቀጡት ለራሳቸው እንዲታረሙና ሌሎች እንዲማሩበት መሆኑን የገለፁት የአቃቤ ህግ ባለሙያ አቶ መንግስቱ ግሩም ህብረተሰቡ ከወንጀል ነክ ድርጊቶች እንዲቆጠቡና ልማት ላይ እንዲረባረቡ አሳስበዋል ሲል ደቡብ ቴሌቪዥን ነው የዘገበው።

  November 25, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በከተማዋ ያለው የነዳጅ አቅርቦት በቂና ፊትሃዊ ባለመሆኑ ምክንያት ምቹ አገልግሎት ለመስጠት መቸገራቸውን በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የታክሲና ባጃጅ ሾፌሮች ተናግረዋል።

  በከተማዋ በቂ የነዳጅ ማደያዎች መኖራቸውን የሚናገሩት አሽከርካሪዎቹ ይሁን እንጂ ነዳጅ በበቂ ሁኔታ እና በፍትሐዊነት ማግኘት እንደማይችሉ ገልፀዋል ።

  በቅጅ(ጀብሎ) በሚገዙት ነዳጅ በታሪፍ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚቸገሩም የጠቆሙት አስተያየት ሰጪዎቹ በዚህም ጉዳይ ከተሳፋሪ ጋር በተደጋጋሚ አለመግባባት ይፈጠራል ብለዋል ። አቶ ቴዎድሮስ ኩታ እና ወጣት ሰሚራ ጌታ የከተማዋ ነዋሪዎች ሲሆኑ በተለይ ባጃጆች ከታሪፍ በላይ እያስከፈሉ በመሆናቸው የትራፊክ ፖሊስ ትኩረት ሰጥቶ እንዲቆጣጠር ጠይቀዋል።

  የጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አበራ የነዳጅ አቅርቦት ሀገራዊ ችግር መሆኑን ገልፀው ህገ-ወጦችን በመቆጣጠር እና የስርጭት ፍትሐዊነት ለማስፈን ከባጃጅ ማህበራትና ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነው ብለዋል።

  ምንጭ፣የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን

  November 25, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • ከፌዴራልና ከክልል የተወጣጣው ቡድን በጎፋ ዞን የተወሰኑ ወረዳዎች በአየር መዛባት ለተከታታይ ዓመታት የተከሰተውን የምግብ እጥረት መነሻ በማድረግ በዛላ ፣ ዑባ-ደብረፀሃይ ፣ ደምባ ጎፋ እና መሎ ኮዛ ወረዳዎች ላይ ያደረገውን የመስክ ምልከታ ለዞኑ የአደጋ ስጋት ምክር ቤት ግብረ-መልስ ሰጥቷል።

  የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብረሃም ዞራ መድረኩን የመሩ ሲሆን ከፌዴራል እና ከክልል የመጡ ባለድርሻ አካላት በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች ላይ የተከሰተውን የምግብ እጥረት የመስክ ምልከታ ግብረ-መልስ አቅርበዋል።

  ቡድኑ በዋናነት በጤና ፣ በንጹህ መጠጥ ዉሃ ፣በትምህርት ፣ በሴቶችና ህፃናት እና በግብርና ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የመስክ ምልከታ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

  ከዚህ በፊት የተጠናውን የዳሰሳ ጥናት መነሻ በማድረግ የመስክ ምልከታ ያደረገው ቡድን በዞኑ የተወሰኑ አከባቢዎች ከፍተኛ የምግብ እጥረት መከሰቱን በማረጋገጥ ከተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ የተራዲኦ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ለህብረተሰቡ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታዎችን ለማድረስ እንደሚሠሩ ገልፀዋል።

  የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ በመድረኩ እንደተናገሩት ዞኑ ከተደራጀ አጭር ጊዜ መሆኑን በመግለፅ ከፍተኛ የሆነ የበጀት እጥረት ቢኖርበትም ለአጭር ጊዜ የሚሆን 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው አጠቃላይ አመራሩ ከደመዎዙ ከ 20% ጀምሮ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

  ምክትል አስተዳዳሪው አክለውም በዘላቂነት ችግሩን ለመቅረፍ መንግሥት ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ የተራዲኦ ተቋማት የከርሰ ምድር ውሃዎችን ለማልማት የሚያስችሉ ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል ።ዘገባው የጎፋ ዞን መ/ኮ/ጉ መምሪያ ነው።

  November 23, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በመድረኩ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው፣የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

  በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ክልላዊ የሌማት ቱሩፋትን ፋይዳ ባስተዋወቁበት ወቅት እንዳሉት በክልሉ ያለውን ጸጋ በመጠቀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።

  የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እንደዘገበዉ የሌማት ቱሩፋትን እውን ለማድረግ የወተት፣ የዶሮ፣ ስጋና ማር በተጨማሪ የአትክልት፣ የስራስር ፣እና የእንሰት ሰብሎች ሲታከልበት ሌማታችን የተሟላ ይሆናል ብለዋል።

  በክልሉ የእንስሳትን ዝርያ በማሻሻል የወተት ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል።

  በክልሉ ከወተት ምርታማነት አንጻር በአማካይ ከ14 እስከ 38 ሊትር ወተት ማሳደግ እንደተቻለም አቶ ኡስማን አብራርተዋል።

  ክልሉ ካለው ጸጋ አንጻር ከዶሮ፣ከስጋ፣ከወተት፣ ከማር እና ከዓሳ የሚገኘውን ሀብት ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ኃላፊው አብራርተዋል።

  November 22, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • አዲሱን " የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል" ለማቋቋም እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት አፈጻጸምና የቀጣይ የትኩረት አጀንዳ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጎፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ከተማ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።

  መድረኩን የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው እና የዞኑ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ማሩፋ መኩሪያ በጋራ የመሩት ሲሆን በመድረኩ የዞኑ አጠቃላይ አመራሮች ፣ የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር አስተባባሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

  የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ጌትነት በጋሻው በመድረኩ እንደገለፁት ስራው በወንድማማችነት መንፈስ እንደሚሠራ እና ህዝቤ ውሳኔው ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍታሃዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረግ እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል፡፡

  የፀጥታና ደህንነት ሁኔታ በጥንቃቄና በአግባቡ በመምራት ያለምንም ስጋት ሂደቱ ሠላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቅ እንዳለበትም አስተዳዳሪው አጽኖኦፆት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

  ዋና አስተዳዳሪው አክለዉም በምርጫ ቦርድ የተመረጡ የምርጫ አስፈጻሚዎች ደህንነታቸውንና ነጻነታቸው የተጠበቀላቸው ሊሆን ይገባልም ብለዋል፡፡

  የጎፋ ዞን የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ማሩፋ መኩሪያ በበኩላቸው የአዲሱን ክልል ለመመስረት በየደረጃው የተሰሩና በቀጣይ ስለሚካሄደው የህዝበ ውሳኔ አጠቃላይ ዝግጅቶች፣ ከህዝቡና ከአመራሩ በቀጣይ ምን ይጠበቃል በሚሉ ጉዳዮችና እነዚህን ለማስፈጸም በተደረጉ ጥረቶች ላይ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል።

  የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በመፍጠር የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ወደ ስኬት ለመቀየር በየደረጃው የሚገኘው አደረጃጀት ተግቶ ሊረባረብ እንደሚገባም አቶ ማሩፋ መኩሪያ አሳስበዋል። ከመራጮች ምዝገባ እስከ ድምፅ አሰጣጥ ድረስ ያለው እያንዳንዱ ተግባር በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ በየደረጃው በተቋቋሙ ኮሚቴዎች እንደሚመራ በመድረኩ ተገልጿል።

  የጎፋ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጅፋሬ አጠቃላይ ዞናዊ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ትኩረት በሚያሻቸው መዋቅሮች ላይ በልዩ ትኩረት ተግባራት መፈፀም እንዳለባቸው የጠቆሙ መሆናቸውን የጎፋ ዞን /መ/ኮ/መምሪያ ዘግቧል።

  November 21, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የደቡብ ክልል ስልጠና ኢንስቲቲዩት ከክልሉ ኮሌጆች የተውጣጡ 30 አሰልጣኝ መምህራንን የስራ ፈጠራ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ ለአንድ ሳምንት የሚቆየው ይህ ስልጠና አሰልጣኝ መምህራኑ ከክህሎትና ከቴክኖሎጂ ባሻገር ስራን በራሳቸው ፈጥረው መስራት የሚያስችላው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

  የእለቱ የክብር እንግዳ ከቡር ዶ/ር ሃሰን ሁሴን የኢትዮጲያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ በመልእክታቸውም ስልጠናው ሌሎችን ከማሳወቅ ባለፈ የአሰልጣኝ መምህራኑንም ህይወት የሚቀይር በመሆኑ ትኩረት ሰጥተው ሊሰለጥኑ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

  የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ፈርሻ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት ኢንስቲቲዩቱ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራንና ኮሌጆችን አቅም የሚገነባ እንዲሁም ስራ ፈጣሪ ዜጎችንም ማፍራት የሚያስችል ተቋማዊ አውድ በየኮሌጁ የሚፈጥር ተቋም ነው ብለዋል፡፡

  አቶ ሰለሞን አክለውም ተቋሙ በአራት ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ሲሆን በቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት፤ የጥራት ስራ አመራርና ኢንተርፕራይዝ ፤ የስልጠና መሳሪያዎች ደህንነት ክትትልና ቴክኒክ ምክር እና የአቅም ግምባታ ስልጠና ናቸው፡፡ ኮሌጆቹ 70 ፐርሰንት የተግባር 30ፐርሰንት የንድፈ ሃሳብ ስልጠና የሚሰጡ በመሆኑ ሰልጥነው የሚወጡት ሰልጣኞች ገበያው ላይ ስራ ፈጥረው ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ ከማበርከት አንፃር ውስንነት በመኖሩ ስራ ከመፍጠር ይልቅ ስራ የሚፈልጉበት ሲከፋም ስራ አጥ የሚሆኑበት ሁኔታ ታይቷል፡፡

  በመሆኑም መፍትሄ የሚያመጣ ትውልድ ለመፍጠር ከክህሎት ስልጠናና ከቴክኖሎጂ ንድፈ ሃሳብ ማወቅ በተጨማሪ ከቴክኒክና ሙያ የሚወጡ ዜጎች ከአካባቢያቸው በሚገኙ ነገሮችና የስራ ገበያውን በማሰስ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑና ለሃገር አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል ስልጠናው ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

  ሃገራችን በማደግ ላይ ያለች ሃገር ብትሆንም በተፈጥሮ ጸጋዋ የተትረፈረፈች በመሆኗ ከውጭ የሚመጣን ምርት ከመጠበቅ ሃገራችን ውስጥ ያሉ የተፈጥሮ ጸጋዎችን መጠቀምና ማምረት የሚችሉ ስራ ፈጣሪ ትውልድ ማፍራት ይገባልም ተብሏል፡፡

  አቶ ሰለሞን ሰልጣኝ መምህራኑ በስራቸው ያሉ ሌሎች ብዙ ሰልጣኞችን ማፍራት በሚያስችል ዝግጅትና ለህይወታቸው ለውጥ ወሳኝ ስልጠና መሆኑን ተገንዝበው ትኩረት ሰጥተው ሊሰለጥኑ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የዘገበው የደቡብ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው፡፡

  November 21, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የቀኑ መከበር የተለያዩ ባህሎችና የአኗኗር ዘይቤ በስፋት እንዲተዋወቁ ያደርጋል ያሉት አቶ ለማ በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሀዋሳ ከተማ ከመከበሩ ቀድሞ በክልል ደረጃ በተለያዩ ኩነቶች እየታሰበ ይቆያል ብለዋል፡፡

  ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ግንባታ ጋር ተያይዞ ግንዛቤ የሚፈጥሩ መድረኮች በየደረጃዉ እንደሚፈጠሩም ተናግረዋል፡፡ የስርዓቱ ፋይዳ እና ተከትሎ የመጡ ለዉጦች ለወደፊት ሊታረሙ ከሚገቡ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የመድረኮች ትኩረት ይሆናሉ፡፡ የበጎ አድራጎትና ሌሎች የልማት ሥራዎችም እስከ ቀኑ መዳረሻ ድረስ በትኩረት እንደሚሠሩ ዋና አፈ-ጉባኤዉ ጠቁመዋል፡፡

  17ኛዉ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ህዳር 29/2015 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሀዋሳ ከተማ ሲከበር የደቡብ ክልላዊ ማጠቃለያ ህዳር 25/2015 ዓ.ም በሀላባ ከተማ በሲምፖዝዬም ምክክር ይከበራል፡፡

  በተመስገን ተስፋዬ

  November 21, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በስፍራው የተገኙ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በአገር አቀፍ ደረጃ አሁን ለተደረሰው የሠላም ስምምነት የዞኑ ማህበረሰብ የራሱ አበርክቶ እንደነበረው ተናግረዋል።

  የተደረሰው የሠላም ስምምነት ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ህዝቡ ቀድሞ ሲያደርግ የነበረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲያስቀጥልም ጠይቀዋል።

  የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በመክፈቻ ንግግራቸው የክልሉ ምክር ቤት ከ6ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ በኋላ ለየት ባለ ሁኔታና በጠነከረ መልኩ ተልዕኮውን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። አሁን የሚካሄደው የጋራ ምክክር ምክር ቤቶች በህገ መንግሥት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በመደጋገፍ በጋራ እንዲወጡ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል። የምክክር መድረኩ በአፈፃፀም የታዩ ጠንካራ ጎኖችና ተግዳሮቶች ተለይተው ለቀጣይ ሥራ አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑንም በንግግራቸው ጠቅሰዋል።

  በጋራ ምክክር መድረክ የተመረጡ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ሪፖርት እና የድጋፋዊ ክትትል ግብረ መልስ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል። በመርሃ ግብሩ የክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት፣ የህፃናት ፓርላማ አባላት፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች እየተሳተፉ ያሉ ሲሆን ምክክሩ ለ1 ቀን የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።

  በተመስገን ተስፋዬ

  November 17, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የደቡብ ክልል ብሔር ብሔረሰቦቸና ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ በግል ባለሀብቶች እየተከናወኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል፤ኢንቨስተሮችንም አበረታተዋል።

  በጉብኝቱ የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳደርና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አንዲሁም የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

  የአመራር ቡድኑ በከተማው ያለው ፈጣን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ያለበትን ሁኔታ የተመለከተ ሲሆን ለኢንቨስትመንቱ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮች በቀጣይ መፈታት ባለባቸው አቅጣጫዎች ላይ ምክክር አድርጓል።

  የክልሉ መንግስት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እያበቡ እንዲመጡ አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል ያሉት አመራሮቹ ህዝቡ፣መንግስትና የግል ባለሀብቱ ተቀናጅተው በመስራት በዘርፉ አመርቂ ውጤት እንዲመዘገብ መረባረብ እንደሚገባም በጉብኝቱ ወቅት ተነስቷል።

  የኢንቨስትመንቱን እንቅስቃሴ በማፋጠን ምርትና አገልግሎትን የማሳደግና የማሻሻል እንዲሁም ለዜጎች የስራ አድል እንዲፈጠር መረባረብ እንደሚገባም በጉብኝቱ የተገኙ አመራሮች መልእክት አስተላልፈዋል።

  November 16, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ወጪ የተገነባውን የሞርሲጦ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮልጅ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አሰተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መርቀው ከፍተዋል።

  ፕሮጀክቱ በወርቅነህ ወድነህ ስራ ተቋራጭ የተገነባ ሲሆን 15 ብሎኮች፣ የተለያዩ ወርክ ሾፖች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር ህንፃ በውስጡ ይገኛል።

  የኮሌጁ ግንባታ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ 97 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወጪ የተረገበት መሆኑም ተገልጿል።
  በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤልን ጨምሮ የክልል ፣ የዞን፣ የወረዳ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ አመራሮች እንዲሁም የሞርሲጦ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። ዘገባው የደቡብ ክልል መ/ኮ/ቢሮ ነው።

  November 10, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • ኤጄንሲው የ2015 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

  መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኤጀንሲው ም/ዳይሬክተር ወ/ሮ አበበች እራሾ በወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዙሪያ በተሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራና ድጋፋዊ ክትትል በህብረተሰቡ ዘንድ ለውጥ መመዝገቡን ተናግረዋል።

  በክልሉ ባሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በአንደኛ ሩብ አመት በአምስቱም የኩነት ዓይነቶች 60 ሺህ 148 ኩነቶችን ለመመዝገብ ታቅዶ 162 ሺህ 150 ኩነቶች መመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል ።

  በምዝገባ ሂደት ወቅታዊ የምዝገባ አፈጻጸምና ማሳወቂያ ወረቀት የተደገፈ የልደትና ሞት ምዝገባ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን፣ የምዝገባውን ሥራ ከማኑዋል ወደ ሶፍትዌር በመቀየር ዲጂታል ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም በሁሉም አካባቢዎች ወጥ ያለመሆንና የቴክኖሎጂ ግብአት ጉድለቶች እንዲሁም የባለድርሻ ቅንጅታዊ አሰራር መቀዛቀዝ በሩብ ዓመቱ የታዩ ክፍተቶች እንደሆኑ ወ/ሮ አበበች አንስተዋል።

  በመድረኩ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የሥራ ሪፖርት አቅርበው ውይይት ይደረጋል።
  በዕድገት እስራኤል

  November 10, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የጎፋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ "የንግድና ገበያ ሥርዓትን በማዘመንና ፍትሐዊ በማድረግ የሸማቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል የ2014 አፈፃፀም፣ የ2015 ዕቅድ እንዲሁም የ2015 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ክንውን ሪፖርት እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ዞናዊ ሴክቶሪያል ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።

  የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ ትዝታ አብርሃም የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት በሀገራችን የመጣውን ሠላም አስጠብቀን እንደ ሀገር ብሎም እንደ ዞናችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናሬ የመጣውን የኑሮ ውድነት የምናረጋግጥበትን ሁኔታ በመፍጠር ሕዝባችን በምግብ ራሱን እንዲችል የጀመርነውን የልማት ፕሮግራም አጠናክረን ማስቀጠል ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል።

  በተጠናቀቀውና በ2015 በጀት ዓመት በርካታ ተግባራት በተቋም ደረጃ መከናወኑን የገለጹት ወ/ሮ ትዝታ አብርሃም፣ በተለይም የንግድ ምዝገባ ፈቃድና መረጃ አገልግሎት ለማዘመን ታቅዶ በሰባት መዋቅሮች ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በ2014 በጀት ዓመት የኢንስፔክሽን ሥራዎችን በማጠናከር በሕገወጥ መንገድ ስንቀሳቀስ ከተያዙ ምርቶች እንዲሁም ከንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት ቅጣት በድምሩ ከ206 ሺህ ብር በላይ ለመንግሥት ገቢ መደረጉን ገልጸዋል።

  በሰብልና ግብይት ኤክስፖርት ዘርፍ ለማዕከላዊ ገበያ የተላከ ማሾ 522.7 ቶን፣ ሰሊጥ 1214 ቶን እና ቀይ ቦሎቄ 261 ቶን በማቅረብ 2 ሚሊዮን 744 ሺህ 361.36 ብር ገቢ ማግኘት መቻሉንም የመምሪያው ኃላፊ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ በቁም እንስሳትና ግብይት ዘርፍ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የቀረበ ዳልጋ በግና ፍየል በቁጥር ከ 117,000 ሺህ በላይ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ትዝታ፣ ከዚህም 8 ሚሊዮን 611 ሺህ 075 ገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

  የጎፋ ዞን የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ጳውሎስ ፋይሌ በበኩላቸው የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ተልዕኮው ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት በመዘርጋት ጤናማ የሆነ የንግድ ውድድር እንዲኖርና ዜጎችን ከአላስፈላጊ በመከላከል ኢኮኖሚው እንዲቋቋም የንግዱ ማህበረሰብ የሚጫወተውን ሚና ለማሳደግ ከፍተኛ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም መሆኑን ተናግረዋል።

  ይህ ተቋም ተቋም ከፌዴራል እስከ እያንዳንዱ ወረዳና ከተማ አስተዳደር የተደራጀ የመንግሥት መዋቅር ሲሆን፣ በየደረጃው ያለው የሕብረተሰብ ክፍል ከንግዱ ክፍሌ ኢኮኖሚ ማግኘት ያለበትን አገልግሎት በተሳለጠ ሁኔታ እንዲያገኝ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። የዞኑ መ/ኮ/እንደዘገበዉ ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት እንድኖር ሁሉም በንግዱ የተሰማሩ አካላት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ እንዲኖራቸው ማድረግ ሚና አለው ያሉት አቶ ጳውሎስ፣ ይህን ለማረጋገጥ በየዓመቱ በንቅናቄ የሚሰሩ ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

  በጉባኤው የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዓለምገነት ላቀውን ጨምሮ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎችና ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊዎች፣ የንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የሥራ ሂደት አስተባባሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈውበታል።

  November 9, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል መንግስት የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሔደ ነው ።

  የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት የትግራይን ህዝብ ጨምሮ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ለማቋቋም የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

  በሰላም ስምምነቱ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆናለች ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በትኩረት ይሰራል በማለት አብራርተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው እንደጠቆሙት በጦርነቱ ምክንያት የደረሰውን ኪሳራ ለማካካስ በትኩረት መሰራት ይገባል ብለዋል። የክልሉ ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።
  ለዚህ ድል እንድንበቃ የህይወት መስዋዕትነት ለከፈሉ ለጸጥታ ሀይሎቻችን እውቅና መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

  በደማችን ያገኘነውን ድል በላባችን ማጽናት አለብን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ በሁሉም ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል። ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የ10 ዓመት መሪ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መገባቱን ርዕሰ መስተዳድሩ አውስተዋል።

  ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በመፈተሽ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል። መላው የክልሉ አመራሮች እና ሰራተኞች በውጤት ላይ የተመሰረተ አፈጻጸም እንዲያስመዘግቡ የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ እንዳለባቸውም አብራርተዋል ሲል የዘገበው የክልሉ መ/ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።

  November 7, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በመድረኩ የወባ በሽታ ጫና ባለፉት ጊዜያት መጨመሩ የተገለጸ ሲሆን ከአየር ለውጥ ጋር ተያይዞ ያለው ሁኔታ፣ የኢኮኖሚ ጫናው፣ የመከላከል ሥራዎች መቀዛቀዝ፣ የህብረተሰብ ተሳትፎ መቀነስ እና ቀድሞ የነበሩ ሥራዎች በአብዛኛው ኮቪድ ላይ ማተኮራቸው ጫናው እንዲጨምር ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ ተናግረዋል።

  የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መና መኩርያ በበኩላቸው በክልሉ የወባ ጫና ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 28 ከመቶ ጨምሮ መገኘቱን ገልጸዋል።

  በቀጣይ ጊዜ ባለፉት ሦስት ወራት ከፍ ብሎ የተመዘገበው የወባ ወረርሽኝ እንዲቀንስ ለማድረግ በንቅናቄ መድረክ ከተገኙ አካላት ትልቅ ኃላፊነት ይጠበቃል ብለዋል።

  በንቅናቄ መድረኩ የተሳተፉ አካላት በሰጡት አስተያየት በቀጣይ ወደአካባቢያቸው ሲመለሱ መሰል ንቅናቄ እንደሚፈጥሩና ህብረተሰቡን በማሳተፍ የወባ ጫና ለመቀነስ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

  በመድረኩ ማጠቃለያ የወባ ጫና እየጨመረ በመሆኑ ማህበረሰቡ የወባ በሽታ ምልክት ሲያጋጥም ወድያውኑ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራና ህክምና ማድረግ እንዳለበት ተጠይቋል።

  በተመስገን ተስፋዬ

  November 5, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የጎፋ ዩኒቨርሳል ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ መስኮች በዲግሪና በዲፕሎማ መርሃግብር ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 695 ተማሪዎችን አስመርቋል።

  በተለያዩ ምክንያቶች መማር እየፈለጉ የትምህርት ዕድል ያላገኙ 18 ተማሪዎች በኮሌጁ በተደረገላቸው ድጋፍ የነፃ የትምህርት ዕድል በመስጠት አስተምሮአቸው ያስመረቀ መሆኑ በምረቃው ፕሮግራም ላይ ተገልጿል።

  የጎፋ ዩኒቨርሳል ኮሌጅ ዲን አቶ ዘላለም ዘካሪያስ የእንኳን ደስ ያላችሁ፣ አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

  አቶ ዘላለም በመልዕክታቸው ኮሌጁ በዲግሪ መርሐግብር ለ4 ዓመት በነርሲንግ 65 ተማሪዎችን እንዲሁም በዲፕሎማ መርሐግብር በ5 የትምህርት መስኮች ማለትም በእንስሳት ጤና፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በአካውንቲንግ፣ የሰው ሀብት አስተዳደር እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ 630 በአጠቃላይ 695 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ማስመረቁን ተናግረዋል።

  በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታና የጎፋ ዩኒቨርሳል ኮሌጅ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ ለተመራቂዎችና ወላጆቻቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

  ፕሮፌሰር ኢያሱ በመልዕክታቸው የዘንድሮው የተማሪዎች ምረቃ ልዩ የሚያደርጉ ሁለት አበይት ጉዳዮች መኖራቸውን ገልጸው፣ የመጀመሪያው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎፋ ዞን በጎበኙበትና ለሕዝባችን ያላቸውን አክብሮትና አድናቆት በገለጹበት ማግስት መካሄዱ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

  ሁለተኛው ባለፉት ሁለት ዓመታት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሲካሄድ የቆየውን አስከፊ ጦርነት ሠላማዊ እልባት እንዲያገኝ ሲደረግ የነበረው የሠላም ድርድር የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት በሚያስጠብቅ ሁኔታ በሠላም በተጠናቀቀበት ማግስት መሆኑን ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

  ኮሌጁ አስካሁን በተለያዩ የሙያ መስኮች በዲግሪና በዲፕሎማ ያሰለጠናቸው የተመራቂ ተማሪዎች ቁጥር 6 ሺህ 550 መድረሱንም ጠቁመዋል። ከእነዚህ አንዳንዶቹ ዶክተሬት ዲግሪያቸውን እየተከታተሉ ሲሆን ብዙዎቹ ወደ ማስትሬት ዲግሪ ደረጃ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።

  ፕሮፌሰሩ አክለውም ተመራቂ ተማሪዎች በተማሩበት የሙያ መስክ የበለጠ ልቀትን በማሳየት መንግሥትንና ሕዝብን በፍጹም ታማኝነትና ቅንነት በማገልገል የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ እንዲሁም ለራሳቸው ተቸግረው ያስተማሩ ቤተሰቦቻቸውን በልዩ ሁኔታ እንዲያከብሩ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

  በመጨረሻም የዛሬ ተመራቂዎችን ጨምሮ ኮሌጁ ለሚሰጠው የሥልጠና ፕሮግራም ድጋፍ ላደረጉ ድርጅቶችና ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል። የጎፋ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ዞራ ለተመራቂ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ፈተናን ተቋቁሞ ለፍሬ መብቃት የዓላማ ግልጸኝነትና ትጋት የሚጠይቅ ሲሆን እናንተ ደግሞ ለግልጽ ዓላማ ተግታችሁ በመስራት ለዛሬው ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

  ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ተግዳሮቶችን በጽናት በማለፍ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ በምትገኝበት ወቅት ላይ እንገኛለን ያሉት አቶ አብርሃም፣ መሬትና ውሃ ይዘን እርዳታ የምንጠብቅበት ምዕራፍ ለማስቆም ሁላችንም መረባረብ አለብን ብለዋል።
  የዞኑ መ/ኮ/ እንደዘገበዉ ወቅቱ ሥራን ከመጠበቅ ይልቅ ሥራ ዕድል መፍጠርን የምሻ በመሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች ያገኙትን እውቀት በመጠቀም አዳዲስ የሥራ አማራጮችን በመፍጠር ለአካባቢያችን ኢኮኖሚያዊ እድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
  በመጨረሻም በኮሌጅ ቆይታቸው በተማሩበት የሙያ መስክ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና ሰርቲፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

  November 5, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የ320 ሚሊየን ብር ድጋፍን ለደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ለአቶ እርስቱ ይርዳው አስረክበዋል።

  የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ችግሮች የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እንዲሁም በሰሜኑ በጦርነት ምክንያት የሽብር ቡድኑ ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶችን በእልህ እና በቁጭት እየተገነቡ ነው ብለዋል።

  እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ 3 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ18 ተቋማት ግንባታ ማካሔድ በመቻሉ በጨለማ ውስጥ ብርሃን እንዳለ ማሳያ ነው።

  የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል። በሰሜኑ ጦርነት የሽብር ቡድኑ ያደረሰውን በሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት መልሶ በማቋቋም ረገድ የክልሉ መንግስት አጋርነቱን ሲያሳይ መቆየቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

  ባለፈው ዓመት በክልሉ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ችግሮች ተፈናቅለው የነበሩ 123ሺ ዜጎች ወደ አካባቢያቸው መመለሳቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ አሁን ተፈናቅለው የሚገኙ ከ90 ሺ በላይ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

  ምንጭ፦ የደቡብ ክልል መ/ኮሙዩኒኬሽን

  October 21, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የንቅናቄ መድረኩን ያስጀመሩት የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ በክልሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጆች ተደራሽነታቸውን ከማሳደግ አንፃር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

  በተለይም የኮሌጆችን ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ማስጨረስ እና ግብአት ከማሟላት እንፃርም ሰፊ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል። ይህምሆኖ ግን የባለድርሻ አካላት ቅንጅት አናሳ በመሆኑ ዘርፉን ወደሚፈለገው ግብ ማድረስ አለመቻሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

  የቴ/ሙ ት/ስልጠና ዘርፍ ብቁ ዜጋና በገበያ ተፈላጊ ባለሙያ ከማፍራት አኳያ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል ። በንቅናቄ መድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በመደገፍና በመቆጣጠር የድርሻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር እንዳልካቸው በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ ት/ት ስልጠና ተቋማት የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ሰፊ ስራ አየሰሩ ቢሆንም ከቅንጅት ማነስ የተነሳ የታለመውን ውጤት ማምጣትና በክህሎት የበቃና ዘላቂ ስራ ፈጣሪዎችን ከመፍጠር አንፃር ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ ጠቁመዋል።

  የዘርፉን ስኬት ለማሳደግም የህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ይህ የንቅናቄ መድረክ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። በንቅናቄ መድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በበኩላቸው ለቴክኒክና ሙያ ተቋማት ላይ የህብረተሰቡ ግንዛቤ አናሳ መሆኑ ለዘርፉ ስኬት ማነቆ መሆኑን ገልጸዋል።

  እንደክልል የስራ አጥነት ችግር እንዲቀንስ ሙያለውን ወጣት መፍጠር የግድ ስለሆነ የህብረሰተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል።

  በንቅናቄ መድረኩ የደቡብ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት የቴክኒክና ሙያ መዋቅር መሪዎች የዞንና የልዩ ወረዳ እስተዳዳሪዎችና የመንግስት ተጠሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈዋል።

  በሰብለወርቅ ኤልያስ

  October 16, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በክልሉ "አዲስ እሳቤ ለግብርናችን ሽግግር "በሚል መሪ ቃል የግብርና ሴክተር የ2015 ሴክቶራል ጉባኤ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው ::

  በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለጹት ክልሉ ሁሉንም አይነት ስነ ምህዳር ያካተተ በመሆኑ ለግብርና ስራ ባለው አመቺነት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ አርሶ እና አርብቶ አደሮች፣በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ኢንቬስተሮች ተጠቃሚ ሆነዋል።

  በክልሉ በእርሻ ሰብሎች፣በሆርቲካልቸር ፣በእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት፣በቡናና ቅመማ ቅመም ምርት፣በተካሄደ ሁሉን አቀፍ ጥረት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማጎልበት መቻሉንም ጠቁመዋል። በክልሉ 5ሺ109 ሄ/ር መሬት በማረስ 152 ሺ ኩንታል ስንዴ በበጋ መስኖ ማምረት መቻሉንም ገልጸዋል። በተያዘው ዓመት ከ22ሺ ሄ/ር በላይ መሬት በማረስ ከ748 ሺ ኩንታል በላይ ስንዴ በበጋ መስኖ ለማምረት መታቀዱንም አቶ ኡስማን አብራርተዋል። በበጋ ስንዴ ልማት የአርሶ አደሩን የስራ ባህል መለወጥ እንደተቻለም አብራርተዋል። ለተፈጥሮ ሀብት ልማት ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ የዓፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራን ማጠናከር ተችሏል ሲሉም አውስተዋል። በ304030 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት በተመረጡ 26 የፍራፍሬ መንደር እና ይዞታ ባላቸው ተቋማት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የአግሮ ፎረስተሪ የደን ተከላ ማካሔድ ተችሏል።

  በክልሉ በአንድ ጀንበር 100 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል በተደረገ ጥረት 98 በመቶ ማሳካት እንደተቻለም አቶ ኡስማን አብራርተዋል። የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው እዳሉት ዞኑ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት የተቸረው በመሆኑ ለግብርና ስራ ምቹ ነው ብለዋል።ከ242 ሺ ሄ/ር በላይ መሬት በሰብል የተሸፈነ መሆኑን ጠቁመዋል።ቡና ኮረሪማ ሰሊጥ የቁም እንስሳት እና ሌሎች የግብርና ግብዓቶችን በስፋት ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረበ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው አስረድተዋል።
  የክልሉ መ/ኮ/ቢሮ

  October 14, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • ለሠራተኞች ሰለማዊ የሥራ አካባቢ ለመፍጠርና ለማህበራዊ ችግር ቢሮው 2014 በጀት ዓመት ሥራ አፈፃፀምና 2015 ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ጉባኤ በዲላ ከተማ እያካሄደ ይገኛል ።

  የሴክተር ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ አቶሬ በክልሉ የማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖች ለመደገፍና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ መረሠታዊ የሆነ የአካቶ ዕቅድ በማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑን ተናገረዋል።

  በዚህም አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋዊያንን፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ ወላጅ አጥ ህፃናትና ሌሎች ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን ሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የቤት ግንባታና ቁሳቁስ ድጋፍ፣ የክህሎት ሥልጠና እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ ጥረት ተደርጓል ብለዋል።

  የአሰሪና ሠራተኛ ግንኙነት ሰለማዊ እንዲሆን፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት ለመቆጣጠር፣ ከስደት ተመላሾችን የመደገፍ ሥራ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ዶክተር ዲላሞ አሳስበዋል።

  የደቡብ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኦንጋዮ ኦዳ በበኩላቸው በ2014 በጀት ዓመት ሰላማዊ የሥራ አካባቢ ለሠራተኞች እንዲፈጠር፣ የውጭ ሀገር ጉዞ ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እንዲደረግ፣ በሥራ ቦታ በሚደረግ ቁጥጥር ለሥራ ዕድሜ ያልደረሳቸው ህፃናትን ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ በትኩረት መሠራቱን ገልፀዋል።

  በክረምት ፈቃድ አገልግሎት ሥራም ለአካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን የቤት ግንባታና ቁሳቁስ ድጋፍ ፣ የድሃ ድሃ እና ወላጅ አጥ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ዶክተር ኦንጋዮ ተናግረዋል ። ለሥራ አጥ ወጣቶች ሥራ ለመፍጠርና የሠራተኞች ደህንነት እንዲጠበቅ የግልና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ኃላፊው አንስተዋል።

  ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት እየጨመረ በመምጣቱ የጎዳና ተዳዳሪዎችና ለምኖ አዳሪዎች ቁጥጥር እየበዛ ስለሚገኝ ችግሩን ለመቅረፍ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ሥራ ይጠይቃል ብለዋል። በጉባኤው የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን፣ የደቡብ ክልል አካል ጉዳተኞች ማህበር ፌደሬሽን፣ የደቡብ ክልል አረጋዊያን ማህበር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

  በዕድገት እስራኤል

  October 14, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • የዞኑ ግብርና መምሪያ የ2014/15 ምርት ዘመን የእርሻ ስራዎች ዓመታዊ የመስክ በዓልና የልምድ ልውውጥ በምስራቅ አዘርነት በርበሬና ሚቶ ወረዳዎች አካሂዷል።

  የስልጤ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ አመራሮች ፣ ሞዴል አርሶአደሮች እና ባለድርሻ አካላት በሁለቱ ወረዳዎች በመኽር እርሻው በክላስተር የለሙ የስንዴ ማሳዎች፣ በፍራፍሬ፣ በመኖ ልማት፣ እና እየተከናወኑ ያሉ ሌሎች የግብርና ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
  በስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አሊ ከድር የተመራው ልዑክ በምስራቅ አዘርነት በርበሬ የማሀል አዳዘር ቀበሌ የስንዴ ክላስተር፣ በሾሞ አቤቾ ቀበሌ ባለፉት ዓመታት በተፋሰስ ልማት በጠረጴዛማ እርከን በለሙ ቦታዎች ላይ ወጣቶች ተደራጅተው እያለሙ ያሉትን የአጃና ገብስ ሰብሎች ማሳ ጎብኝተዋል። ልዑኩ በተመሳሳይ በዞኑ ሚቶ ወረዳ በኤደነባ አገዎ ቀበሌ በመኽር እርሻ በሰፊው እየለማ ያለ የስንዴ ክላስተር ማሳ ተዘዋውረው ተመልክተዋል::

  በመስክ ጉብኝቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር አርሶ አደሩ የተሻለ የግብርና ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ምርጥ ተሞክሮና አዳዲስ አሰራሮችን በመቀመር የተሻለ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ እንዲቻል እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል። የሀገሪቱ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚረጋገጠው በሁሉም ልማታዊ ተግባራት እንቅስቃሴ በማድረግ በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ፣በአታክልትና ፍራፍሬ ልማት፣በእንሰሳት ሀብት፣በንብ ማነብ፣በቅመማ ቅመም እንዲሁም በሌሎች የግብርና ዘርፎች በትጋት ሊሰራ ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በመስክ ጉብኝታችን ወቅት በሞዴልና በሌሎች አርሶ አደሮች መካከል ያለውን የምርታማነት ልዩነት ለማጥበብና ዘርፉን ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት ይበልጥ ምቹ ለማድረግ የኩታገጠም አስተራረስ ወሳኝነት እንዳለው አንስተዋል።

  በዞኑ በሞዴል አርሶ አደሮች የተጀመረው ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ ባለድርሻ አካላት ሰፊ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

  የዞኑ ምክትል አስተዳደሪና የግብርና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሙርሰል አማን እንዳሉት ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በቱክረት እየተሰራ ነው። በዚህም መነሻ በዞኑ በ2014/15 ምርት ዘመን በመህር እርሻ በመደበኛ 67 ሺህ ሄ/ር በላይ በዋና ዋና ሰብሎች የለማ ሲሆን 34% በክላስተር የለማ መሬት የለማ እንደሆነ ተናግረዋል። አፈፃፀሙ ከአምናው ተመሳሰይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮው አብላጫ እንዳለው አመላክተዋል። የጉብኝቱ ዓላማ አርሶ አደሩ የተሻለ የግብርና ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ምርጥ ተሞክሮና አዳዲስ አሰራሮችን በመቀመር የተሻለ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ እንዲቻል ለማድረግ መሆኑ ነው መሆኑንም አመላክተዋል። የመስክ በዓሉ በዘርፉ በሞዴል አርሶ አደሮች የተገኙ መነሻ ልምዶችን እንደ እርሾ በመጠቀም ወደ ሁሉም አካባቢ ለማስፋት ያለመ ነው ብለዋል።
  በመስክ ጉብኝቱ ላይ ያነጋገርናቸው የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ መይዲያ ቡሴርና የሚቶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰበሃዲን ሎባ እንዳሉት አነስተኛ የሆነ ማሳ ያላቸውን አ/አደሮች የኩታገጠም ውህደትን በማበረታታት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል። በክላስተር ማልማት ውጤት ታይቶበታል ያሉት ዋና አስተዳዳሪዎቹ በቀጣይ በስፋት ለመስራት በዕቅድ መያዙንም አረጋግጠዋል፡፡ ዘገባው የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው

  October 14, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በ2014 አ.ም በክልሉ ከ14 ቢልየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 305 ባለሀብቶች ወደ ስራ መግባት የሚያስችላቸውን የኢንቨስተመንት ፈቃድ እንደተሰጣቸው ተገለጸ።

  ይህ የተገለጸው የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ዛሬ መስከረም 27/2015 አ.ም በዲላ ከተማ አያካሄደ ባለው የበጀት አመቱን ዕቅድ አፈጻጸም ጉባዔ መድረክ ላይ ነው። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮው ሀላፊ አቶ ሐልጌዬ ጂሎ በበጀት አመቱ ብዙ ፈተናዎችን ተቋቁመን በግሉ ኢንቨስትመንት ዘርፍ አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡበት አመት እንደነበረ ገለጸዋል። እንደ ሀላፊው ገለጻ በቢሮ ደረጃ ዘርፉን ስኬታማ የሚያደርጉ ሰፋፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል ።

  በተለይ ለቀጣይ አስር አመታት የሚቆይ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ የኢትዮጵያ ታምርት የንቅናቄ መድረክና ከባለድርሻ አካለት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር የሚያጠናክሩ ስራዎች ተከናውነዋል ። ከዚህ ጎን ለጎን ባለሀብቶች ወደ ክልሉ ገብተው መዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በበጀት አመቱ ከ14 ቢልየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 305 ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስቸመንት ዘርፎች ለመሰማራት የኢንቨስተመንት ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑ ገልጸዋል።

  በዚህ መድረክ የክልል ቢሮ ሀላፊዎች:የሴክተሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት :የዞን አና ልዩ ወረዳ የመዋቅሩ አመራሮች አና ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ ።

  October 7, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • ሀሰተኛ የጤና ትምህርት ማስረጃዎችና የሙያ ብቃት ማረጋገጫዎች መበራከት አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ

  ሀሰተኛ የጤና ትምህርት ማስረጃዎችና የሙያ ብቃት ማረጋገጫዎች የያዙ ህገ ወጥ ግለሰቦች ህጋዊ የቅጣት ዕርምጃዎች መወሰዳቸውን የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብአት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ ።

  የጤና ባለሙያዎች ምዝገባና የሙያ ስራ ፍቃድ ለመውሰድ ወደ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤታችን ከመጡት መካከል 13 ሴቶችና 7 ወንዶች በጠቅላላ 20 ግለሰቦች አጠራጣሪ የሲኦሲ(COC) ሰርተፍኬት (የሙያ ብቃት ማረጋገጫ) ይዘው በመቅረባቸው ለደቡብ ክልል መንግሥት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ እንዲጣራ ማቅረቡን የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብአት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ ገልፀዋል፡፡

  የደቡብ ክልል መንግሥት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ባደረገው ማጣራት ከቀረቡት የ20 ግለሰቦች የሲኦሲ(COC) ሰርተፍኬት ውስጥ በመንግስት ተቀጥረው ከሚገኙት ሰራተኞች መካከል በ3 ወንዶችና በ3 ሴቶች ላይ ከስራ እንዲታገዱ ተደርጓል፡፡

  አንድኛው ግለሰብ ሀሰተኛ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ይዞ መድሐኒት መደብር ከፍቶ ይሰራ እንደነበር ተረጋግጦ በተወሰደው ዕርምጃ ተቋሙ እንዲዘጋ የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ በመንግስትና በግል ይሰሩ የነበሩ 7 ሌሎች ግለሰቦች ጉዳያቸው በህግ እየተጣራ መሆኑን አቶ ሽመልስ ገልጸል።

  ኃላፊው አክለው እንደገለጹትም ሀሰተኛ የጤና ባለሙያዎች ምዝገባና የሙያ ስራ ፍቃድ ይዘው በግልና በመንግስት ተቋም ተቀጥረው ሲሰሩ በነበሩት በቁጥጥር ወቅት አራት ህገ ወጦች ማግኘት የተቻለ በመሆኑ ከእነዚህ መካከል አንድ የግል ክልኒክ ፍቃድ አውጥቶ ሲስራ በነበረና በመንግስት ተቋም ተቀጥራ ስትሰራ በነበረች አንድ ግለሰብ በሀሰተኛ ሰነድ የሚሰሩ መሆኑ በመረጋገጡ በሁለቱም ላይ የ5 ዓመት ጽኑ እስራት እና 500 መቶ ብር መቀጫ የተጠለባቸው የተቀሩት ሁለቱ ግለሰቦች ደግሞ ከስራ ተግደው ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በህግ እየጣራ መሆኑን አብራርቷል።

  ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በሳውላ ከተማ በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ ሚዲያዎች እንደተለለፈው ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት እና የህክምና ፈቃድ ሲሰጥ የነበረው ወንጀል አድራጊ ግለሰብ አቶ ይሁን በላቸው የተባለው ነዋርነቱ ኦሮምያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ቢሆንም ቤንሻንጉል ክልል በህገ ወጥ ስራው ተይዞ በህግ ቁጥጥር ስር ካለበት አምልጦ ወደ አማራ ክልልና ሌሎች ክልሎች እየተዘዋወረ ለመስራት ቢሞክርም ወደ ደቡብ ክልል ለህገወጥ ተግባሩ በመጣበት ወቅት በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

  በጤናዉ ሴክተር የሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግበራትን በተቀናጀ ሁኔታ ለመስራት በታቀደ መሰረት ከቤንሻንጉል ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ይሁን በላቸው የተባሉ ግለሰብ ህገ ወጥ ስራ ላይ ተይዞ ከእስር ቤት እንዳመለጡ መረጃ በማገኛታችን ይህ ግለሰብ ወደ ደቡብ ክልል ይመጣል በሚል በህገ ወጥ ስራዎችን ለመከላከል ትኩረት አድርገን እየሰራን ባለንበት ወቅት ግለሰቡ ወደ ክልሉ ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በመግባት ለረጅም ጊዜያት ያለ ምንም ስራ አልጋ ይዞ መቆየቱ ህብረተሰቡን ወደ ጥርጣሬ በማስገባቱ መረጃውን መግኘት ተችሏል፡፡

  አቶ ሽመልስ እንደተናገሩት ግለሰቡ ለረዥም ጊዜ ቢቆይም ከህግ ተሰውሮ የሚቀር ወንጀል ባለመኖሩ ህብረተሰቡ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ባደረገው ጥቆማ መሰረት አቶ ይሁን ባላቸውን የጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ጤና ጽ/ቤት እና ፖሊስ ጽ/ቤት እንዲሁም የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብአት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመቀናጀት ግለሰቡ ተይዞ በጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ11 አመት ጽኑ እስራት እና 6000 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ማስተላለፍ ለወንጀል አድራጊዎች መልካም ትምህርት እንደሆነ አቶ ሽመልስ ገልጸዋል፡፡

  በመጨረሻም የደ/ብ/ብ/ህ/ ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብአት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ ህገ-ወጥ ድርጊትን ፈጽመው ከህግ ተሰውረው የሚቀሩ መስሏቸው ለጊዜው ተደብቀው የሚገኙ ግለሰቦችን ለመያዝ እንዲቻል ሁሉም ክልሎች ወንጀልን በጋራ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ ከነ ፎቶግራፎቻቸው ጭምር ማጋራትና እንዲሁም በዞኖች እና በልዩ ወረዳዎች ደግሞ የተለያዩ የሚያጠራጥሩ ጉዳዮችና ግለሰቦች ሲያጋጥሙ በየአካባቢቸው ከሚገኙ የህግ እና ሚመለከታቸው አካላት ጋር በአካል እና በስልክ በመጠቆም ወንጀልን በጋራ መከላከል እንደሚገባ ጥሪ አቅርቦል፡፡

  ምንጭ:- የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ

  October 6, 2022

  | ክልላዊ ዜና

 • በኢትዮጵያ ከተሜነት ፈጣን እድገት እያሳየ በመሆኑ እንደ ሀገር 5.4 ፐርሰንት የደረሰ ሲሆን በደቡብ ክልልም 7 ፐርሰንት ደርሷል ያሉት ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ የኢፌድሪ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ናቸው።

  ከገጠር ወደ ከተማ በሚደረግ ፍልሰት ምክንያት በደቡብ ክልል እየገዘፈ የመጣው ፈጣን ከተሜነት ሊገታ የሚችል ባለመሆኑ ከተሞችን ለኑሮ ምቹ፣ ሰላማዊና ጽዱ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
  ክብርት ኢንጂነር አይሻ እንደተናገሩት ከተሞችን ፅዱ፣ ጤናማና ሳቢ ለማድረግ ጠንካራ የማህበረሰብ ተሳትፎ መገንባትና የአሰራር ደንቦችንና የህግ ማእቀፎችን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
  "ሀላፊነቱን ተረድቶ በአግባቡ የሚሰራ አመራር ያለበት ከተማ ህይወት አለው" የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ።
  አቶ እርስቱ እንደተናገሩት ከተሞችን አረንጓዴ ፣ ጽዱና ለነዋሪው ምቹ ለማድረግ የአመራሩ ትጋትና ተነሳሽነት ወሳኝ በመሆኑ አመራሩ ትኩረት አድርጎ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
  በከተሞች ነዋሪው ተረጋግቶ የሚኖርበት አመራረሩም ተረጋግቶ የሚመራበትና የሚሰራበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት የህግ ማእቅፍና መመሪያ ወደታች ወርዶ ተግባራዊ መሆን አለበት ብለዋል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ።

  August 29, 2021

  | ክልላዊ ዜና

 • በጅንካ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ ተሳታፊ የሆኑት የኢፌደሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለምጸሃይ ጳውሎስ የጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታልን የአገልግሎት አሰጣጥ ጎብኝተዋል።

  ሚኒስትሯ ከጤና ሚኒስቴር፣ከሁሉም ክልሎችና ከ2 ከተማ አስተዳደሮች የተመረጡ የጤና ተቋማት ተውጣጥተው በመድረኩ ላይ ተሳታፊ ከሆኑ የጤና ባለሙያዎችና አመራሮች ጋር በመሆን ነው የሆስፒታሉን ጉብኝት ያካሄዱት።
  የጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል በሀገር አቀፍ ደረጃ በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ የተሻለ አፈጻጸም በማሳየት ተሸላሚ መሆኑ በመድረኩ ላይ ተነግሯል ።
  በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስተናጋጅነት በደቡብ ኦሞ ዞን ጅንካ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ሀገር አቀፍ የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ የልምድ ልውውጥ መድረክ በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ውሎው የየካቲት 12፣የአለርትና የጅንካ ሆስፒታሎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ልምድና ተሞክሮ ተመልክቷል።
  የጤና ሚኒስቴርና የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ተሞሮክሮዎችና በዘርፉ ላይ የተደረጉ ጥናቶችም ለመድረኩ ቀርበዋል።

  August 29, 2021

  | ክልላዊ ዜና

 • የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ እየተዋደቀ ላለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀን በመሆን ሙያዊ ሀላፊነታቸውን ለመወጣት የደቡብ ክልል የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች የሽኝት ስነ-ስርዓት በሀዋሳ ተካሄዷል

  የሽኝት ስነ-ስርዓቱ የተካሄደው ኪነ-ጥበብ ለኢትዮጵያ ክብር እና ልዕልና በሚል መሪ-ቃል ነው።
  የሽኝት ስነ-ስርዓቱ በጦር ግንባር አሸባሪው ህወሓትን በመደምሰስ ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የየክልልሎች ልዩሀይል እና ለሚኒሻ አባላት የኪነ-ጥበብ ስራዎችን በግንባር በመገኘት ለማቅረብና ለማበረታታት ያለመ ነው።

  ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች በጦር ግንባር በመገኘት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለየክልል ልዩሀይል እና ለሚኒሻ አባላት የኪነ-ጥበብ ስራዎችን በማቅረብ ለማበረታታት ላሳዩት ተነሳሽነት አመስግነዋል።
  አቶ እርስቱ ሀገራችንን ኢትዮጵያ የገጠማት ፋተና ህዝቦቿ ይበልጥ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ አድርጓቸዋል በማለት ገልጸዋል።
  በዕለቱ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ግንባር ለሚዘምተው የኪነ-ጥበብ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ አስረክበዋል።
  በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች ተገኝተዋል።

  August 29, 2021

  | ክልላዊ ዜና

 • በደቡብ ክልል በአማሮና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን በሱሮ ቡርጉዳና ገላና አጎራባች ወረዳዎች አካባቢ የተፈጠሩ ግጭቶችን የሚፈታ የውይይት መድረክ በሀዋሳ ተካሂዷል፡፡

  የህዝቦችን የቆየ አብሮ የመኖር እሴትን በማጎልበት የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን ማስቀጠል እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
  በሀዋሳ በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ የተሳተፉ የሁለቱም ክልሎች ተወካዮች በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት የአካባቢያችንን ሰላም ለማስጠበቅ እና የምንፈልገውን ሰላም ለማምጣት ከምንግዜውም በላይ ልንሰራ ይገባል፡፡
  ያለፉት ጥቂት አመታት ወገኖቻችንን ያጣንበት ብዙ የከሰርንበት በመሆኑ ከዚህም ያተረፍነው ምንም ነገር ባለመኖሩ ለጉዳዩ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡
  በዚህ አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ለዘመናት አብረው የኖሩ የተጋቡ የተዋለዱ ናቸው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ይህን መልካም እሴት በማጎልበት የቀደመውን የእርስ በርስ ግንኙነታችንን ማጠናከር ይገባል፡፡
  በየአካባቢው ያሉ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመነጋገር ለጉዳዩ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ብለዋል፡፡
  በጦርነት አሸናፊም ተሸናፊም የለም ያሉት ተሳታፊዎቹ የሰላም ጉዳይ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ ስለ ሰላም ሲባል የሚከፈለውን ሁሉ ከፍሎ ሰላምን ማረጋገጥ ይገባል፡፡

  የሁለቱንም ህዝቦች በጋራ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት በመስራት የቀድሞውን የአንድነት እሴት መመለስ ይቻላል ያሉት ተሳታፊዎቹ በዚህም የሁለቱም ክልሎች አመራሮችና ህዝቦች በመተባበር የቀደመውን አንድነት ለመመለስ አንዱ የሌላውን ጥቅም በማክበር በጋራ ችግሮችን በመፍታት ላይ ሊሰሩ ይገባል፡፡
  ሰላማችንን ማረጋገጥ የምንፈልግ ከሆነ በሁለቱም አካባቢዎች ያሉትን ወንጀለኞች አሳልፈን በመስጠትና ተባባሪ ባለመሆን የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በማድረግ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

  መንግስትም የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የበኩሉን መወጣት አለበት ያሉት ተሳታፊዎቹ ማህበረሰቡም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል፡፡

  August 29, 2021

  | ክልላዊ ዜና