ዋናዋና ዜናዎች

| ዓለም አቀፍ ዜና






  • " 20 ዓመት ፖሊስ ሆኜ ሰርቻለሁ። እስካሁን በሕይወቴ እንዲህ አይነት አሰቃቂ አደጋ አይቼ አላውቅም " - ኢንስፔክተር ሽመልስ ቦሬሳ ትላንት እሁድ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደጋም ወረዳ " ወርቢ " በምትባል ቦታ በደረሰ እጅግ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡት 13ቱ ሰዎች መካከል መምህርት አስመሬ ጎሶማ እና አራት ልጆቿ ይገኙበታል። መምህርቷ የ18፣ 15፣ 8 እና የ1 ዓመት ልጆቻቸውን ይዘው ከአዲስ አበባ ወደ ጎሃ ጽዮን ቤተሰብ ጥየቃ እየጓዙ የነበረ ሲሆን፣ በአደጋው የእናት እና #የሁሉም_ልጆቻቸው ሕይወት አልፏል። ለዚህ የትራፊክ አደጋ ምክንያቱ ቁልቁለት ቦታ ላይ ከባድ የጭነት መኪና በሕዝብ ማመላለሽ ሚኒባስ ላይ ስለወጣበት መሆኑን በደገም ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አሳውቋል። የፖሊስ ጽ/ቤት ኢንስፔክተር ሽመልስ ቦሬሳ ምን አሉ ? ኢንስፔክተር ሽመልስ ቦሬሳ ፦ " አደጋውን ያደረሰው የጭነት ተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር 500 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሳቢ መኪና ነው። ቁልቁለት ላይ ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ ሲጓዝ ነበር። ከባድ ተሸከርካሪው ቁልቁለት መንገድ ላይ ከቁጥጥር ውጭ ከሆነ በኋላ ሁለት መኪኖችን ገጭቶ በመጨረሻ የሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ መኪና ላይ ሙሉ በሙሉ ስለወጣበት በውጡ የነበሩ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል። የ13ቱ ሰዎች ወዲያውኑ ነው ሕይወታቸው ያለፈው፤ ሌሎች ሦስት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በኩዩ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ነው። አደጋው የደረሰባቸው ሰዎች ሲጓዙበት የነበረው ሚኒባስ ሙሉ በሙሉ ወድሟል ፤ ሌሎች ሦስት ተሸከርካሪዎች ላይም ከባድ ጉዳት አጋጥሟል። 20 ዓመት ፖሊስ ሆኜ ሰርቻለሁ። እስካሁን በሕይወቴ እንዲህ አይነት አሰቃቂ አደጋ አይቼ አላውቅም። የሰዎችን አስክሬን ማውጣት በራሱ እጅግ ሰቅጣጭ ነበር። በሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባሱ ውስጥ ከነበሩት መካከል በሕይወት የወጡት ሁለት ብቻ ናቸው ፤ እነርሱም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአካባቢው መንገድ ጠመዝማዛማና ቁልቁለታማ ከመሆኑም በላይ ወቅቱ የዝናብ በመሆኑ አሸከርካሪዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ ማሽከርከር አለባቸው። "

    July 17, 2023

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • ''አፍሪካ፡ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት” በሚል መሪ ሀሳብ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ አቺቭመንት እና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙት ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር ‘የአፍሪካ የላቀ አመራር’ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

    ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም. የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ስታስጀምር፣ በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢልዮን ችግኞችን ለመትከል ማቀዷ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ ከታቀደው ግብ አልፋ በመላ ሀገሪቱ 25 ቢልዮን ችግኞች በመትከል የአራት ዓመት ዕቅዷን አሳክታለች።

    በዚህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እና ለደን መልሶ ልማት ላደረገችው አስተዋጽዖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ማግኘቷን ከጠ/ሚኒስትቴር ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል ።

    December 13, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፕሬዚዳንት ሙሐመድ ቢን ዛይድ እና ለሀገሪቱ ህዝቦች ብሔራዊ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትና መልካም ምኞታቸውን ገለፁ።

    ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ገፃቸው ባስተላላፉት መልዕክት ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንትና ለህዝቡ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “ለውድ ወንድሜና ጓደኛዬ ለፕሬዚዳንት ሞሐመድ ቢን ዛይድ እንዲሁም የተከበረው የተባበሩት አረብ ኤመሬትስ ህዝብ እንኳን ለ51 ኛው ብሔራዊ ቀን አደረሳችሁ” ብለዋል።

    በዛሬው ዕለት 51ኛ ብሔራዊ ቀን ሆኖ የሚከበረው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ሕዝቦች በዓል እ.አ.አ 1971 ጀምሮ መከበር የጀመረ ሲሆን በአረብ ኤመሬት ውስጥ ለየብቻ ይተዳደሩ የነበሩ ኤሜሬቶች ወይም ግዛቶች በአንድነት መተዳደር የጀመሩበት ዕለት ነው።

    December 2, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው 17ኛው ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

    በጉባኤውም ከተለያዩ የዓለም አገራት የመጡ ተወካዩች እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን “ለዲጅታል አካታችነት መሰረተ ልማት መልካም ተሞክሮዎችና ምክረ ሀሳቦች” በሚል ሃሳብ ላይ ውይይት ተደርጓል። የኢትዮጵያን ተሞክሮ ያቀረቡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ለኢንተርኔት መሰረተ ልማት መስፋፋት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

    በቀጣይም ኢትዮጵያ ለዜጎች የኢንተርኔት ተደራሽነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታውቀው፤ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው መስራት ለሚፈልጉ አካላት ጥሪ አቅርበዋል። የ17ኛው ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ዋናው መክፈቻ በነገው እለት እንደሚካሄድ ተነግሯል።

    የዓለምን የምጣኔ ሀብት እድገትና የሰዎችን የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ካቀላጠፋት ጉዳዮች አንዱ የኢንተርኔት ተደራሽነት ሲሆን ዘርፉን በባለቤትነት በመምራት ለዓለም ህዝብ ጥቅም እንዲሰጥ በማሰብ የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም ከ17 ዓመት በፊት እንዲመሰረት ተደርጓል።

    በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የተጀመረው 17ኛው ጉባኤ እስከ ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን፤ የዓለም አገራት ስለ ኢንተርኔት አስተዳደር የሚመክሩበት፣ ለፓሊሲ አውጪዎች እና ውሳኔ ሰጪዎች የሚቀርቡ ምክረ -ሀሳቦች የሚነሱበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

    November 28, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ ጋር ተወያይተዋል፡፡

    በውይይታቸው ላይም አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በደቡብ አፍሪካ ስለተፈረመው የሰላም ስምምነት ገለጻ አድርገዋል፡፡

    ኢትዮጵያ ፈተና በገጠማት ወቅት አልጀሪያ ለወሰደችው በመርህ ላይ የተመሠረተ አቋም አቶ ደመቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

    የአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ በበኩላቸው የሰላም ስምምነቱ አፍሪካ የራሷን ችግር የመፍታት አቅም እንዳላት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

    የኢትዮጵያዊያን ደህንነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር አልጀሪያ እንደምትፈልግም አስረድተዋል።

    በውይይታቸውም የኢትዮ-አልጄሪያ ወዳጅነት እንዲጠናከር በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

    November 23, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • የአሜሪካ የኮንግረስ አባል ዶን ቤየር ኢትዮጵያ ወደ የአፍሪካ የእድገትና ዕድል ድንጋጌ (አጎዋ) ተጠቃሚነት እንድትመለስ ለአገራቸው መንግስት ጥያቄ አቀረቡ።

    አጎዋ የኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ትብብርን ያጠናከረ ቁልፍ መሳሪያ ነውም ብለዋል። የኮንግረስ አባል ዶን ቤየር (ቨርጂኒያ, ዴሞክራቲክ ፓርቲ) ለአሜሪካ የንግድ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይ ባጸፉት ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት ከሕወሓት ጋር የተፈራረመውን ስምምነት ተፈጻሚ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

    በስምምነቱ አማካኝነት መንግስት ተኩስ በማቆምና ሰብአዊ እርዳታን ባልተገደበ መልኩ ተደራሽ እያደረገ ነው ብለዋል። በዚሁ መሰረት የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያን ወደ የአፍሪካ የእድገትና ዕድል ድንጋጌ (አጎዋ) የመመለስን ጉዳት ሊያጤነው እንደሚገባ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚ በነበረችበት ወቅት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ እድገት እንዲያሳይ፣ በ10 ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረና የሁለቱን አገራት የንግድ አጋርነት ለማሳደግ አስተዋጽኦ ማድረጉን አመልክተዋል።

    ኢትዮጵያ ተጠቃሚነቷን ስታጣ በአጎዋ ጥላ ስር ምርታቸውን ወደ አሜሪካ ይልኩ የነበሩ ኩባንያዎች የማስፋፋፊያ እቅዳቸውን መተዋቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን መቀነሳቸውን ነው የኮንግረስ አባሉ ለአምባሳደር ካትሪን በጻፉት ደብዳቤ የገለጹት። ኢትዮጵያን ከአጎዋ የማስወጣት ውሳኔ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ላይ መቀዛቀዝ እንዲታይ ማድረጉንም አመልክተዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚነት በድጋሚ መመለስ ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውይይት እንዲያደርግ ዶን ቤየር ለአምባሳደር ካትሪን ጥሪ አቅርበዋል።

    በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር የተፈረመው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት ኢትዮጵያን በፍጥነት ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት ይመልሳታል ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የ72 ዓመቱ ዶን ቤየር የቨርጂኒያ ግዛትን ወክለው እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ2015 ጀምሮ በኮንግረስ አባልነት እያገለገሉ ይገኛል።

    በቅርቡ በተካሄደው የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ(ሚድ ተርም ኢሌክሽን) በኮንግረስ አባልነት በድጋሚ ተመርጠዋል። ዶን ቤየር ‘የአሜሪካን ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቴ’ (ኤፓክ) የተሰኘው የፖለቲካ ተግባር ኮሚቴ በአጋማሽ ዘመን ምርጫ ይሁንታ ከሰጣቸው 34 እጩዎች መካከል ይገኙበታል።

    በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅትም ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት ለመመለስ አበክረው እንደሚሰሩ መግለጻቸው ይታወቃል። የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባል ዶን ቤየር የኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ትብብር እንዲጠናከር ገንቢ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም ይነገርላቸዋል።

    በሚኖሩበት ቨርጂኒያ ግዛት ከሚኖሩ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በየጊዜው ውይይት በማድረግ መልካም የሚባል ግንኙነት መገንባት ችለዋል።የዘገበው ኢዜአ ነው።

    November 19, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • ኮትዲቫር በአሚሶም ጥላ ስር የሚገኙትን ወታደሮቿን ቀስ በቀስ ከማሊ እንድምታስወጣ ስታስታውቅ እስከ ነሐሴ ወር ድረስ ግን ወታደሮቿ ሙሉ ለሙሉ ከማሊ እንደሚወጡ አስታውቃለች፡፡
    ሀገሪቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በአቢጃን እና ባማኮ መካከል የተፈጠረውን የዲፕሎማሲ መሻከርን ተከትሎ ነው፡፡

    ባለፈው ሐምሌ ወር በዋና ከተማ ባማኮ ማሊ 49 የኮትዲቫር ወታደሮች ማሰሯን ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት በውዝግብ ውስጥ የገቡ ሲሆን ማሊ ከታሰሩት ወታደሮች መካከል ሦስቱን ስትለቅ ቀሪዎቹን አሁንም እንዳሰረች ነው የተገለጸው፡፡

    በተመሳሳይ እንግሊዝም በማሊ ያላትን ወታደሮች እንደምታስወጣ ያስታወቀች ሲሆን ሀገሪቱ 300 ወታደሮች በማሊ እንዳላት ተመላክቷል፡፡

    እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2012 ጀምሮ ማሊ በፅንፈኞች ተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስባት ሀገር ስትሆን ሀገሪቱን ለማረጋጋት የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲገባ መደረጉን የአፍሪካ ኒውስ ዘገባ አመላክቷል፡፡

    November 16, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ከአለም የምግብና እርሻ ድርጅት -ፋኦ የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስስ ፋራይ ዚሙድዚ ጋር ተወያይተዋል።

    አቶ እርስቱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግስት የግብርናውን ዘርፍ በማሳደግ የአርሶ አደሩን ገቢና የአመጋገብ ስርኣት ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

    መንግስት በግብርናው ዘርፍ ረገድ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በተቀናጀ እንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑንም አስታውቀዋል ።በዚህም ዘርፉ ህዝቡን በአግባቡ ከመመገብ ባለፈ የሀገሪቱ የእድገት መሰረት እንዲሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት ሰርተን ውጤታማ የሆንበት የስንዴ ምርትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ሲሉ ለዳይሬተሯ ገለጻ አድርገዋል።

    በተለይም ደግሞ በቅርብ የተጀመረውና በእያንዳንዱ አርሶ አደር ደረጃ የአመጋገብ ስርኣትና ምጣኔ ለማሻሻል እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ተስፋን የሚያጭር ነው ብለዋል።

    ለዚህ የክልሉ መንግሥት የግብርና ልማት ሂደት እንደ ፋኦ ያሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዘርፉን በማዘመን፣በግብይት ስርኣት፣ በማሽነሪ አቅርቦትና በአቅም ግንባታ ረገድ ድጋፍ እንዲያደርጉ አቶ እርስቱ ጥሪ አቅርበዋል። በተለይም ደግሞ የክልሉን የምግብ እህል ምርት ከፍተኛ አቅም ለማጎልበትና በአርሶ አደር ደረጃ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተቋማቱ ድጋፍ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተናግረዋል ።

    በአለም የምግብ ፕሮግራም- FAO የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስስ ፋራይ ዚሙድዚ በበኩላቸው ድርጅቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ8 የምስራቃዊ አፍሪካ ሀገራት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን እያገዘ መሆኑን አስታውቀዋል ።በዚህም የእርሻውን ዘርፍ የሚደግፉ የድጋፍ ማዕቀፎች በመተግበር ሲደግፍ ቆይቷል ብለዋል። የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እንደዘገበዉ በቀጣይም በክልሉ የግብርናው ዘርፍ በሚፈለገው ደረጃ አድጎ የምግብ ዋስትናን እንዲያረጋግጥ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ካንትሪ ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል ።

    በውይይቱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞንና የርዕሰ መስተዳድሩ ዋና አማካሪ አቶ ስንታየሁ ሀሰን ተገኝተዋል።

    November 9, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • በውይይታቸው ወቅትም በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።

    ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን ለመፈለግ እና አፍሪካን ጽኑ ለማድረግ በአብሮነት መሥራታችንን እንቀጥላለንም ብለዋል።

    November 7, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • አውሮፕላኑ የተከሰከሰበት ፕሪሲሽን የተሰኘው አየር መንገድ እንደገለጸው ከሆነ ከ43 ተሳፋሪዎች መካከል 24ቱ በሕይወት ተርፈዋል።

    የአውሮፕላኑ አብራሪዎች አደጋው እንደደረሰ ለባለስልጣናት የድረሱልን መልክት ያስተላለፉ ቢሆንም በሂደት ግን የእነርሱ ሕይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ የታንዛኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል።

    አውሮፕላኑ ቡኮባ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኘው የሐይቁ ዳርቻ ላይ ነበር የተከሰከሰው። የነፍስ አድን ሠራተኞች በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ለመታደግ ችለዋል።

    ወደ ታንዛኒያዋ ትልቅ ከተማ ዳሬ ሰላም ለመመለስ በረራውን ለመጠበቅ በአየር ማረፊያ ተገኝቶ የነበረው አብዲ ኑር ስለተመለከተው ነገር ለቢቢሲ ተናግሯል።

    ‘’በጣም ነው የደነገጥነው። አንዳንድ ሰዎች በድንጋጤ ሲያለቅሱ እና ሲጮሁ ነበር። . . . መንገደኞችን ለመቀበል የተሰበሰቡ ሰዎችም በጣም ተደናግጠው ነበር። ብዙዎቹ ዘመዶቻቸውን ለመቀበል ሲጠብቁ ነበር’’ ሲልም ተናግሯል።

    የበረራ አስተናጋጅ የአውሮፕላኑን የአደጋ ግዜ መውጫ በር ከከፈቱ በኋላ አሳ አጥማጆቹ ወደ አውሮፕላኑ በመግባት ሰዎችን መታደግ መቻላቸውንም ተነግሯል።

    ዕሁድ ጠዋት ሶሰት ሰዓት ገደማ ያጋጠመው ይህ አደጋ መነሻው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ መሆኑም ይገመታል።

    November 7, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ሃላፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሻርም ኤል ሼክ በኮፒ 27 ስብሰባ ላይ የተሳተፉትን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ተቀብለው አነጋገሩ።

    November 7, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸዉ ግብፅ፣ ሻርም አል-ሼይክ ገብተዋል።

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ግብፅ፣ ሻርም አል-ሼይክ ገብተዋል።

    November 6, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • ኢሻሌ ወርቁ በ61 cm ልጅ የወለደች እናት በመባል የአፍሪካ ድንቃድንቆችን ክብረወሰን በመስበር በአፍሪካ ድንቃድቅ መዝገብ ስሟ ሰፍሯል።

    ሰርተፍኬቱን ለእሻሌ ድርጅቱ እስከወለደችበት ሆስፒታል ድረስ በመምጣት አስረክቧል። እሻለ ከዚህ በፊት በ61 cm አጭር ሴት በመባል የአፍሪካ ድንቃድንቆችን ክብረወሰን ባለቤት መሆኗ ይታወሳል።
    በ61 ሴንቲ ሜትር ርዝመት በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ በኢትዮጵያ አጭሯ ሴት ተብላ የተመዘገበችው ኤሻሌ ወርቁ ሴት ልጅ በሠላም ተገላግላለች። ኢሻሌ ወርቁ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በሚገኘዉ በሚገኘው ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል መውለዷን የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሥራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ዓለም ተናግረዋል።
    ሥራ አስኪያጁ ድርጅቱ ኤሻሌ ወርቁን በ61 ሴንቲ ሜትር ርዝመት የኢትዮጵያ አጭሯ ሴት ብሎ መመዝገቡን አስታውሰዋል፡፡ ኤሻሌ ወርቁ የሰባት ወራት የእርግዝና ጊዜ እንደነበራትና በሕክምና ክትትል በቀዶ ጥገና እንደወለደችም ነው ሥራ አስኪያጁ ጨምረው የጠቆሙት፡፡
    የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሥራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ዓለም ÷ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ዓለም ላይ 61 ሴንቲ ሜትር ቁመት ርዝመት ያላት እናት መውለዷን የሚጠቁም መረጃ እንደሌላቸው ጠቁመዋል። ኢሻሌ ወርቁ በ61 cm ልጅ የወለደች እናት በመባል የአፍሪካ ድንቃድንቆችን ክብረወሰን በመስበር በአፍሪካ ድንቃድቅ መዝገብ ስሟ ሰፍሯል። ሰርተፍኬቱን ለእሻሌ ድርጅቱ እስከለደችበት ሆስፒታል ድረስ በመምጣት አስረክቧል። እሻለ ከዚህ በፊት በ61 cm አጭር ሴት በመባል የአፍሪካ ድንቃድንቆችን ክብረወሰን ባለቤት መሆኗ ይታወሳል።
    የዞኑ መ/ኮ

    October 16, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • በሶሪያ መጠለያዎች ውስጥ ያሉ ስደተኞች በቲክቶክ ላይ ድጋፍ እየለመኑ ከሚያገኙት ገቢ ኩባንያው እስከ 70 በመቶውን እንደሚወስድ የቢቢሲ ምርመራ አረጋገጠ።
    ልጆች ወደ ገንዘብ የሚቀየሩ ዲጂታል ስጦታዎችን ለማግኘት በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ለሰዓታት በቀጥታ ስርጭት ሲማጸኑ ይቆያሉ።
    ስደተኞቹ ከቀጥታ ስርጭቶቹ በሰዓት እስከ 1,000 ዶላር እንደሚያገኙ ቢቢሲ ተመልክቷል። ስደተኞቹ ኪስ የሚገባው ግን በጣም ጥቂት ነው።
    ቲክቶክ "በልመና" ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግሯል። ኩባንያው በልመና ገንዘብ መሰብሰብን እንደማይፈቅድ ገልጾ ከዲጂታል ስጦታዎች የሚቀበሉ ደርሻ ከ70 በመቶ ያነሰ ነው ቢልም ትክክለኛውን መጠን ከመግለጽ ግን ተቆጥቧል።

    October 12, 2022

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • በኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች በተያዘው ዓመት መጨረሻ ሀገሪቱን ለቀው እንደሚወጡ ተገልጿል፡፡

    የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ÷ አሜሪካ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ኢራቅ ላይ የነበራትን ተልዕኮ ታጠናቅቃለች ብለዋል፡፡ የኢራቅን ወታደሮች የማሰልጠን እና የማማከር ስራ መስራት ግን እንደሚቀጥል ነው ያመላከቱት፡፡
    ባይደን መግለጫውን የሰጡት የኢራቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ አል ካዲኢሚን በነጩ ቤተ መንግስት ጠርተው ካወያዩ በኋላ ነው፡፡
    አሁን ላይ ከ2 ሺ 500 በላይ የአሜሪካ ወታደሮች በኢራቅ የሚገኙ ሲሆን÷ ዋና አላማቸውም በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱትን የአይ ኤ ስ የሽብር ቡድን አባላት ለሚዋጉ የሀገሪቷ ወታደሮች ድጋፍ መስጠት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
    ባለፈው ዓመት የኢራኑ ከፍተኛ ጀነራል ቃሲም ሱሌይማኒ÷ በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት፣ በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ፣ መገደላቸውን ተከትሎ አሜሪካ ሀገሪቷን ለቃ እንድትወጣ ግፊት ሲደረግ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

    August 16, 2021

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • በዛምቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲው ዕጩ ሃካይንዴ ሂቺሌማ አሸነፉ፡፡

    የዛምቢያ ምርጫ ኮሚሽን ጉዳዩን አስመክቶ ባወጣው መግለጫ÷ በሀገሪቱ ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚው መሪ ሃካይንዴ ሂቺሌማ ማሸነፋቸውን አረጋግጧል፡፡
    ሂቺሌማ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉን ከ1 ሚሊየን በላይ በሆነ ድምፅ በማግኘት ነው ምርጫውን ያሸነፉት፡፡
    የተቃዋሚ መሪው ማሸነፋቸውን ተከትሎም ደጋፊዎቻቸው በዛምቢያ ዋና ከተማ ሉሳካ ጎዳናዎች ወጥተው ደስታቸውን እየገለጹ ነው፡፡
    የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሉንጉም በበኩላቸው÷ ምርጫው ነፃ ፣ ፍትሃዊ እና ተዓማኒ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ በምርጫ ጣቢያዎች የተገኙ አባሎቻቸው በምርጫ ሃላፊዎች መዋከብ ደርሶባቸዋል፤ በዚህም የምርጫው ድምጽ ለመጭበርበር ተጋልጧል ነው ያሉት፡፡
    ሂቺሌማ በምላሻቸው በቀድሞው ፕሬዚዳንት የቀረቡ ትችቶችን ውድቅ በማድረግ መሰል አስተያየቶች ከተሸናፊ አካል የሚጠበቁ መሆናቸው ጠቁመዋል፡፡
    ሂቺሌማ ከዚህ ቀደም ከ6 ጊዜ በላይ ለዛምቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በዕጩነት መቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

    August 16, 2021

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • በሊቢያ እና ማልታ ዳርቻዎች ከ 700 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ባህር አቋርጠው ሲጓዙ የህይወት አድን ሰራተኞች ታድገዋቸዋል፡፡

    በዚህ ሳምንት ከሊቢያና ማልታ ዳርቻዎች ስደተኞቹ የሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ ነው በሕይወት አድን መርከበኞች የተደረሰባቸው ፡፡
    ሕይወት አድን ሰራተኞቹ አራት መቶ የሚሆኑትን ስደተኞች ሕይወት ሊታደጉ የቻሉት በመካከለኛው የሜዲትራኒያን ባህር አካባቢ ሲሆን፥ የመቶዎቹ ሕይወት ሊተርፍ የቻለው ደግሞ ከማልታ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
    በሌሎች አራት ጀልባዎች የነበሩ ስደተኞችም በሕይወት አድን ሰራተኞች ሊተርፉ ችለዋል፡፡
    አብዛኞቹ ስደተኞች ከሊቢያ ዳርቻዎች ተነስተው 300 ኪሎ ሜትሮች በማቋረጥ መዳረሻቸውን በአውሮፓ ከምትገኘው ጣሊያን ለማድረግ አስበው እንደነበርም ነው ለማወቅ የተቻለው፡፡
    በዚህ ዓመት ብቻ ተመሳሳይ ሙከራዎችን በማድረግ የ900 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

    August 16, 2021

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • የሱዳን የሽግግር ጊዜ አስተዳደር ካርቱም ዓለም አቀፉን የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመቀላቀል የቀረበውን ረቂቅ ማጽደቁ ተሰማ።

    ረቂቁ ሃገሪቱ ዓለም አቀፉን የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመቀላቀል የሚያስችላትን መንገድ የሚከፍት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
    ይህን ተከትሎም የሃገሪቱ ሉዓላዊ ምክር ቤት የመንግስት ካቢኔ ረቂቁን ህግ አድርገው ለማጽደቅ ይወያያሉም ነው የተባለው።
    ፍትህና ተጠያቂነት የህግ የበላይነትን የምናረጋግጥበት የሱዳን የጀርባ አጥንት ናቸው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው።
    የረቂቁ መጽደቅም ሱዳን የቀድሞውን ፕሬዚዳንት አልበሽርን ጨምሮ በዳርፉር ተፈጽሟል በተባለው የጦር ወንጀል የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችን ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፋ ለመስጠት መቃረቧን ያመላክታል ተብሏል።
    ከዳርፉር የጦር ወንጀል ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሲያየው የነበረውን መዝገብ ባለፈው ግንቦት ወር ማጠናቀቁን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

    August 16, 2021

    | ዓለም አቀፍ ዜና





  • ቻይና እና ሩሲያ በቻይና መካከለኛው ሰሜን አካባቢ መጠነ ሰፊ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ ነው፡፡

    “ትብብር – 2021” በተሰኘው በዚህ የጋራ ልምምድ 10 ሺህ የሚደርሱ የምድር እና የአየር ሃይል አባላት ተሳትፈዋል፡፡
    ሩሲያ ለልምምዱ ተዋጊ ጀቶችን፣ ሞተራይዝድ መሳሪያዎችን እና የአየር መቃወሚያ ስርዓቶችን ወደ ቻይና መላኳ ተጠቁሟል፡፡
    ልምምዱ ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት የተጀመረ ሲሆን ÷ የፊታችን ዓርብ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
    የጦር ልምምዱ ሽብርተኝነትን ከመከላከል እና የጋራ ደህንነትን ከማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
    ከዚህ ባለፈም በሀገራቱ መካከል እየዳበረ የመጣውን ሁለንተናዊ ትብብር እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርስ እና የሀገራቱን ቅንጅት የሚያጠናክር ነው ተብሏል፡፡

    August 16, 2021

    | ዓለም አቀፍ ዜና