ዋናዋና ዜናዎች

| ሀገራዊ ዜና


 • የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል ወላይታ ሶዶ፤ መስከረም 28/2016፦ 6ኛው የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ይካሄዳል። በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ የ2016 ዓ.ም ዋና ዋና የመንግስት አቅጣጫዎችን የሚያመላክት ንግግር የሚያደርጉ ይሆናል። በንግግራቸው በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ዲፕሎማሲና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የመንግስትን እቅድ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሁለቱም ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ መክፈቻ መርሃ ግብር የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ።

  October 9, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና በትላንትናው ዕለት መጠናቀቁ ተገለጸ። በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና መጠናቀቁን ፓርቲው አስታወቀ። ከመስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል። በማጠቃለያ መድረኩም የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዐቢይ አህመድ የስልጠናውን ማጠቃለያ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለከት የስራ ስምሪት ሰጥተዋል። ስልጠናው ወሳኝ በሆኑ ሃገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የፈጠረ ሲሆን ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ሁለት ሺህ የፓርቲው አመራሮች ተሳትፈዋል። የአቅም ግንባታ ስልጠናው በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች በቀጣይነት የሚሰጥ መሆኑን ከብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።#ኢዜአ

  September 27, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖር ጥሪ አቀረቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ፍትሐዊና አካታች መሆን እንደሚገባው አስታወቁ። 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒውዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። የጀርመን መራሔ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ከጉባኤው ጎን ለጎን የተመድ እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ማሻሻያ አስመልክቶ ያዘጋጁት መደበኛ ያልሆነ የምክክር ስብስባ ተካሄዷል። በስብስባው ላይ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ የአፍሪካ አባል አገራትና ሌሎች አገራት ተሳትፈዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ የቆየ ጥያቄ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በማሻሻያው ላይ ከአፍሪካ ጋር የጋራ አቋም እንዳላት ጠቅሰው ምክር ቤቱ ፍትሐዊና አሳታፊ እንዲሆን የዓለም ሁሉ ፍላጎት ነው ብለዋል። ነገሮችን ባሉበት የማስቀጠል አቋም ውስጥ ያለው ምላሽ ያለመስጠት ፍላጎት የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የልማት ፋይናንስ ፍላጎት እንዳያሟሉ ማድረጉን አመልክተዋል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት አስቸኳይ ማሻሻያ በማድረግ አስፈላጊውን የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው አቶ ደመቀ ጥሪ ያቀረቡት። የጀርመን መራሔ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ በቅርቡ በኢትዮጵያ ባደረጉት የስራ ጉብኝት ያሳዩትን አጋርነትና ወዳጅነት አድንቀዋል። በስብስባው ላይ የተገኙት የኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ሞሪሺየስና ኮሞሮስ ፕሬዝዳንቶች የፀጥታ ምክር ቤት ተቋማዊ ማሸሻያ እንደሚያስፈልገው በመግለጽ የየአገራቸውን አቋም አንጸባርቀዋል። አቶ ደመቀ በስብስባው ጎን ለጎን ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት እና ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሚርጃና ኤገር ጋር ፍሬያማ ውይይቶችን ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

  September 22, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ኢሬቻ የእርቅና የሰላም በዓል በመሆኑ ዘንድሮም አንድነትንና ሕብረትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራ- አባ ገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች ወላይታ ሶዶ ፤ መስከረም 7/2016 (ወቴቪ)፦ ኢሬቻ የእርቅና የሰላም በዓል በመሆኑ ዘንድሮም አንድነትንና ሕብረትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራ ሲሉ አባ ገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች ገለጹ። የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ የኦሮሞ አባገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል መስከረም 26 እና 27/2016 ዓ.ም በሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዲ እንደሚከበር አስታውቀዋል። የቱለማ አባገዳና የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ፀሓፊ አባገዳ ጎበና ሆላ እንደገለፁት የዘንድሮውን ኢሬቻ በዓል የገዳ ስርዓት እሴትን በጠበቀ መልኩ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል። ''ኢሬቻ እርቅና ሰላም በመሆኑ የዘንድሮው ኢሬቻ በደስታ፣ በአንድነትና በፍቅር ይከበራል'' ብለዋል። የሲኮ መንዶ አባገዳና የህብረቱ አባል አባ ገዳ አሊይ መሐመድ ሱሩር፣ ሁሉም የበዓሉ ታዳሚዎች የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት ተምሳሌት በመሆን በዓሉን ማክበር እንዳለባቸው ተናግረዋል። የኦሮሞ ቄሮዎች፣ ቀሬዎችና ፎሌዎች ኢሬቻ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የበኩላቸውን እንዲወወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ኢሬቻ የይቅርታና አብሮነት በዓል በመሆኑ ሰላመዊነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር በትብብር መስራት ይገባል ያሉት ደግሞ ሃዳ ሲንቄዎች ናቸው። ሃዳ ሲንቄ አፀዱ ቶላ ''ኢሬቻ ሰላም መሆኑንና የሰላም እናት መሆናችንን በአንድነት የምናሳይበት በዓል ነው'' ብለዋል። ''ኢሬቻ የይቅርታ፣ የተጣለ የሚታረቅበት፣ የተለያዩ የሚገናኙበትና ፈጣሪ የሚመሰገንበት በዓል ነው'' ሲሉም ገልጸዋል። በዚህም በዓሉ ያለምንም ችግር እንዲከበር፣ በሀገራችን ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር እንዲፀና ሃዳ ሲንቄዎች በትብብር ይሰራሉ ብለዋል። ሃዳ ሲንቄ ጫሊ ቱምሳ በበኩላቸው ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ማንነት መገለጫ በመሆኑ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ መከበር እንዳለበት ገልጸዋል። በዚህም ወጣቶችና ሴቶች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የዘንድሮው ኢሬቻ ያማረና የተሳካ እንዲሆን ማስቻል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

  September 18, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ባሕላዊ መልክዓ- ምድር በዩኔስኮ ተመዘገበ በጌዴኦ ዞን የሚገኘው የጌዴኦ ባሕላዊ መልክዓ- ምድር በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስ እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተመዘገበ፡፡ የጌዴኦ ባሕላዊ መልክዓ- ምድር በዩኔስኮ የተመዘገበው በሪያድ እየተካሄደ በሚገኘው 45ኛው የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ጉባዔ ላይ ነው፡፡ በጉባዔው ላይም ስለ ጌዴኦ ባሕላዊ መልክዓ-ምድር ዝርዝር ማብራሪያ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት እና አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ ነው ምዝገባው የጸደቀው፡፡ በጌዴኦ ዞን የሚገኙትን የጌዴኦ ማሕበረሰብ የመሬት አያያዝ፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ ትክል ድንጋዮች፣ የዋሻ ላይ ጽሑፍና በባሕላዊ መንገድ ብቻ የሚተዳደሩ ደኖችን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ የቅርሶቹ መመዝገብ በቱሪዝሙ ዘርፍ የራሱን አዎንታዊ ሚና እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡

  September 18, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ለጷጉሜን ቀናት የተሰጡ ስያሜዎች ይፋ ተደረጉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት የጷጉሜን ቀናት የሚከበርበትንና ለእያንዳንዱ ቀናት የተሰጡ ስያሜዎችን ይፋ አድርጓል። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ፣ በ2015 በአለም አቀፍ፣በቀጣናዊ እና በአለም አቀፋዊ የድፕሎማሲያዊ መድረክ ኢትዮጵያ ተደማጭነትን ያገኘችበት የድል አመት ነው ብለዋል። ሚኒስትር ዲኤታው የጷጉሜን ቀናት የሚከበርበትንና ለእያንዳንዱ ቀናት የተሰጡ ስያሜዎችንም ገልጸዋል። በዚሁ መሠረት፤ ???? ጷጉሜ 1 የአገልግሎት ቀን ???? ጷጉሜ 2 የመስዋዕትነት ቀን ???? ጷጉሜ 3 የበጎነት ቀን ???? ጷጉሜ 4 የአምራችነት ቀን ???? ጷጉሜ 5 የትውልድ ቀን ???? ጷጉሜ 6 የአብሮነት ቀን ተብለው ተሰይመዋል፡፡ የአብሮነት ቀን በተለየ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበርም ሚኒስትር ዲኤታው አሰታውቀዋል።

  August 31, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • 24ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ 24ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች ፦ 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ከጣሊያን መንግስት ጋር በተፈረሙ ሶስት የብድር ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ ብድሩም የመንግስትን ልማት ተኮር እቅዶች ለመደገፍ የሚውል የ56 ሚሊዮን ዩሮ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 10 ሚሊዮን ዩሮው የቡና እሴት ሰንሰለት ለማሻሻል ለተቀረጸው ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ይውላል፡፡ 22 ሚሊዮን ዩሮው በገጠራማ አካባቢዎች የስራ እድል ፈጠራን በማሳደግ እና የአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡ ቀሪው 24 ሚሊዮን ዩሮ በአዋሽ እና በዋቢ ሸበሌ ተፋሰሶች ዘላቂ የውሃ ሃብት ልማት እና አስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት ይውላል፡፡ ምክር ቤቱም ሁሉም ብድሮች ከወለድ ነፃ መሆናቸው፣ የ16 ዓመታት የችሮታ ጊዜ ያላቸው እና በ30 ዓመታት ተከፍለው የሚጠናቀቁ መሆኑ ከአገሪቱ የብድር ፖሊሲ ጋር እንደሚጣጣሙ በማረጋገጥ ስምምነቶቹን በሙሉ ድምጽ አጽድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡ 2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው ከአለም አቀፉ የልማት ማህበር ጋር በተፈረሙ ሁለት የብድር ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ የሁለቱ ስምምነቶች መጽደቅ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውና በገጠር የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተደራሽነትን ለማሻሻል የሚውል የ250 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደዚሁም የሰው ሀብት ልማት ሴክተር አገልግሎቶች እንዲጠናከሩ ለመደገፍ የ50 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሚያስገኝ ይሆናል፡፡ ምክር ቤቱም ሁለቱም የብድር ስምምነቶች ከወለድ ነፃ ሆነው ማህበሩ ብድሩን በማስተዳደር ረገድ ለሚሰጠው አገልግሎት 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልባቸው፣ የ6 ዓመታት የችሮታ ጊዜ ያላቸው እና በ38 ዓመታት ተከፍለው የሚጠናቀቁ በመሆናቸው ከአገሪቱ የብድር ፖሊሲ ጋር የተገናዘቡ መሆናቸውን በማረጋገጥ ስምምነቶቹን በሙሉ ድምጽ አጽድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡ 3. በተጨማሪም የውጪ ግንኙነት ከማሳለጥ አንጻር የቀረቡ አጀንዳዎችም ውይይት ተደርጎባቸዋል። ከሩሲያ ፌደሬሽን መንግስት ጋር በወታደራዊ-ቴክኒካል ትብብር ወቅት ለሚገኙ አዕምሯዊ የፈጠራ ሥራ ውጤቶች የጋራ ጥበቃ ለማድረግ የተፈረመው ስምምነት ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት ጉዳይ ነው፡፡ የስምምነቱ አላማ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማጠናከር ያለውን ፍላጎት በድጋሚ ማረጋገጥ፣ በሁለትዮሽ ወታደራዊ-ቴክኒካል ትብብር ሂደት በአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ መስክ የተሻለ የጋራ መግባባት እና ትብብር እንዲኖር ማድረግ፣ እንዲሁም በትብብር ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የአዕምሯዊ ንብረትን መብት ጥሰቶችን በጋራ መከላከል ሲሆን ምክር ቤቱም ስምምነቱ የእኩልነትና የጋራ ተጠቃሚነት መርሆዎችን መሰረት በማድረግ የተፈረመ መሆኑን በማረጋገጥ በሙሉ ድምጽ አጽድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡ 4. ምክር ቤቱ በአፍሪካ መድኃኒቶች ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ስምምነት ላይ የተወያየ ሲሆን የአባል ሀገራትን የመድኃኒት ምርቶችን ጥራት ማስጠበቅ፣ ሀገራችን ከመድኃኒት ምርቶች ቁጥጥር ጋር ተያይዞ እያደረገች ያለውን ጥረት በማገዝ የመድሃኒት ጥራት ተቆጣጣሪ አካላትን አቅምና ብቃት ማሳደግ፣ የሀገራችንን ባህላዊ መድሃኒቶች ከዘመናዊው የህክምና ስርዓት ጋር ማስተሳሰር እንደዚሁም በአባል አገራት መካከል የመድሃኒቶች ዝውውር ቅንጅታዊ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት የኤጀንሲው ዋነኛ ተግባራት መሆናቸው ተመላክቷል፡፡ ምክር ቤቱም በስምምነቱ ላይ በሰፊው ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 5. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት ጉዳይ ከሊባኖስ መንግስት ጋር በስራ ስምሪት ዘርፍ ስምምነት ነው፡፡ ሀገራችን በሊባኖስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዜጋ ያላት በመሆኑ የእነዚህን ዜጎች መብት ለማስጠበቅ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እንደሚረዳ የታመነበት ስምምነት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም የስምምነቱ መፈረም በሊባኖስ በተለያዩ ስራ መስኮች ተሰማርተው ለሚገኙ እና ለወደፊትም በስራ ምክንያት ለሚሄዱ ኢትዮጵያውያን መብቶቻቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል፣ የመብት ጥሰቶች በሚያጋጥሙ ጊዜም በአገሪቱ ህግ አግባብ እንዲዳኙ የሚያስችል እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስትም ለዜጎቹ ተገቢውን የህግ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችለው ስምምነት መሆኑን በማረጋገጥ ግብዓቶችን በማከል እንዲጸድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 6. ቀጥሎም ምክር ቤቱ የተወያየው ከደቡብ ኮሪያ እና ከህንድ መንግስታት ጋር የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት በተፈረሙ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የያዙ የሀገራቱ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶች እና ዜጎች ለሥራ ጉዳይ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የተሳለጠ እንዲሆን በማድረግ በተለይም ቪዛ ለማግኘት የሚያስፈልጉትን ቅድመ ሁኔታዎች በማስቀረት የጎላ ፋይዳ እንዳለው የታመነበት ስምምነት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በስምምነቱ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 7. በመጨረሻ ምክር ቤቱ ከፓኪስታን መንግስት ጋር በተፈረመው የንግድ ስምምነት ላይ የተወያየ ሲሆን የስምምነቱ መጽደቅ አገራቱ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በዲፕሎማሲው መስክ ያላቸው መልካም ግንኙነት ብሎም በዓለም አቀፍ መድረኮች የጋራ አቋሞችን በማራመድ ረገድ ያላቸው ትብብር እንደሚያጎለብት የታመነበት ስምምነት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በስምምነቱ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

  August 31, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ሰራዊቱ ጽንፈኛ እና ዘራፊ ቡድኑ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ከተሞች ከስጋት ነጻ እንዲሆኑ በማድረግ ህዝባዊ ባህሪውን እና መከታነቱን በተግባር አረጋግጧል--የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ሰራዊቱ ጽንፈኛ እና ዘራፊ ቡድኑ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድና ከተሞች ከስጋት ነጻ እንዲሆኑ በማድረግ ህዝባዊ ባህሪውን እና መከታነቱን በተግባር ማረጋገጡን የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ገለጸ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ እና የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግሥቴ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያው ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ሰራዊቱ ባከናወነው የህግ ማስከበር ተግባር የአማራ ክልል ከተሞች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ መደረጉን ገልጸዋል። ሰራዊቱ የህግ የበላይነትን ለማስከበር በሰራው ስራ ውስጥ ህዝቡ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመው፤ አሁን ላይ ከተሞቹ ከስጋት ነጻ መሆን መቻላቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገልጸዋል። በዚህም ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ የአውሮፕላን በረራ ወደ ባህርዳር፣ ጎንደር እና ኮምቦልቻ ከተሞች መጀመሩንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የመንግስት እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ በማድረግ ላይ ይገኛልም ብለዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ የመጀመሪያ ተግባሩን በስኬታማነት አጠናቆም ወደ ሁለተኛው ተግባሩ መሸጋገሩንም ጠቁመዋል። አንዳንድ አካላት ህዝባዊ ባህሪ ያለውን የመከላከያ ሰራዊት ስም ለማጠልሸትና ለማጥፋት ከሚያደርጉት ጥረትም ሊቆጠቡ ይገባልም ብለዋል። ጽንፈኛ ቡድኑ አገርን ለማፍረስ በማሰብ ሁሉን ሁኔታ መጠቀሙን ገልፀው ህዝብን መዝረፍ፣ መንገድ መዝጋት፣ አመራሮችን መግደል እና ሌሎችንም እኩይ ተግባራት ማከናወኑንም ጠቁመዋል። ቡድኑ መንገዶችን በመዝጋትም ማዳበሪያ አርሶ አደሩ ጋር እንዳይደርስ የማድረግ እኩይ ተግባር ማከናወኑንም ገልጸዋል። መንግስት ለሰላም አማራጭ የሚችለውን ሁሉ አድርጎ እንደነበርም ጠቁመዋል።

  August 11, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • 19ኛው የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። 19ኛው የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የአፍሪካ የአካባቢ ችግሮችን ለመፍታት ዕድሎችን መጠቀም፣ ትብብርን ማጎልበት በሚል መሪ ሀሳብ ከነሐሴ 8 ጀምሮ እሰከ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ድረሰ በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታሁን ጋረደው ጉባኤውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ 19ኛው የአፍሪካ የአካባቢ የሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ጉባኤው በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ነው። በጉባኤው ሁሉም የአፍሪካ አገራት እኩል ድምጽ የሚያገኙበት ነውም ብለዋል።

  August 11, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ለመዲናዋ የመንግሥት ሠራተኞች ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ ተደርጓል በጀት ዓመት ለአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ መደረጉን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን የበጀት ዓመቱን የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክተው ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ከሠራተኞች ጥያቄ ሲነሳ እንደነበር ጠቅሰዋል። የከተማ አስተዳደሩ አመራር ውይይት አድርጎ አቅም በፈቀደ መጠን ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ መደረጉን ገልጸዋል። ይህም ሠራተኞች ያላቸውን የክፍያ ምጣኔ ታሳቢ ያደረገና እስከ አንድ ሺህ 500ብር እንደሆነ ጠቁመው፤ ይህ አሁን ያለውን መሠረታዊ የቤት ኪራይ ክፍያ ጥያቄ የሚፈታ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ችግሩን ማቃለል ያስቻለ ነው ብለዋል። ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ሠራተኛው የሚያነሳቸው ጥያቄዎች እንዳሉ የገለጹት ኃላፊዋ፤ በሁሉም የመንግሥት መስሪያ ቤት ካፍቴሪያዎች ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን በተወሰነ መጠን መንግሥት መደጎም መቻል እንዳለበት ታምኖ በ2015 መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ እንደተገባ አስታውቀዋል። ይህም ሁሉንም ሠራተኛ ታሳቢ የደረገና በአንድ ሠራተኛ የ20 ብር ድጎማ እንደሆነ ገልጸዋል። በሂደቱ መንግሥት ከ20 ብሩ ድጎማ ባሻገር ለካፍቴሪያ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችንና መሰረተ ልማቶችን የማሟላት ሥራ እንደሚፈጽምም ጠቁመዋል። ሥራው ሲጀመር ተቋማት በጀታቸውን ለሌላ ስራዎች ከፋፍለውት ስለነበር እንዲሁም ምቹ አካባቢ ባለመኖሩ ሁሉም ጋር እኩል የመተግበር ክፍተት እንደነበር ጠቅሰዋል። ሆኖም በ2015 ዓ.ም መመሪያው 111 የሚሆኑ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ ተግባራዊ መደረጉን ጠቅሰው፤ በ2016 በጀት ዓመት በማዕከል፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ ባሉ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ ሴት የመንግሥት ሠራተኞች ልጆቻቸውን የሚያውሉበት“ዴይኬር” አገልግሎት ተግባራዊ መደረጉን፤ ሠራተኞች በሸማች ማህበራት በኩል መሠረታዊ ሸቀጦችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል። ከዚህም ባሻገር በበጀት ዓመቱ በሁለት በዓላት አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑት ሠራተኞች የበዓል መዋያ ድጋፍ አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉንም ተናግረዋል። ለዘመናት ሲጠየቁ የነበሩ የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የወተት አበልና አልባሳት በበጀት ዓመቱ ምላሽ መሰጠቱንም አስታውቀዋል። እንደ ቢሮ ኃላፊዋ ገለጻ፤ በከተማ አስተዳደሩ 165 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች ያሉ ሲሆን፤ 40 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ናቸው። በከተማ አስተዳደሩ አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ የሚባሉት ከስድስት ሺህ ብር በታች የሚከፈላቸው ናቸው።

  August 3, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ለመዲናዋ የመንግሥት ሠራተኞች ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ ተደርጓል በጀት ዓመት ለአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ መደረጉን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን የበጀት ዓመቱን የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክተው ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ከሠራተኞች ጥያቄ ሲነሳ እንደነበር ጠቅሰዋል። የከተማ አስተዳደሩ አመራር ውይይት አድርጎ አቅም በፈቀደ መጠን ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ መደረጉን ገልጸዋል። ይህም ሠራተኞች ያላቸውን የክፍያ ምጣኔ ታሳቢ ያደረገና እስከ አንድ ሺህ 500ብር እንደሆነ ጠቁመው፤ ይህ አሁን ያለውን መሠረታዊ የቤት ኪራይ ክፍያ ጥያቄ የሚፈታ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ችግሩን ማቃለል ያስቻለ ነው ብለዋል። ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ሠራተኛው የሚያነሳቸው ጥያቄዎች እንዳሉ የገለጹት ኃላፊዋ፤ በሁሉም የመንግሥት መስሪያ ቤት ካፍቴሪያዎች ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን በተወሰነ መጠን መንግሥት መደጎም መቻል እንዳለበት ታምኖ በ2015 መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ እንደተገባ አስታውቀዋል። ይህም ሁሉንም ሠራተኛ ታሳቢ የደረገና በአንድ ሠራተኛ የ20 ብር ድጎማ እንደሆነ ገልጸዋል። በሂደቱ መንግሥት ከ20 ብሩ ድጎማ ባሻገር ለካፍቴሪያ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችንና መሰረተ ልማቶችን የማሟላት ሥራ እንደሚፈጽምም ጠቁመዋል። ሥራው ሲጀመር ተቋማት በጀታቸውን ለሌላ ስራዎች ከፋፍለውት ስለነበር እንዲሁም ምቹ አካባቢ ባለመኖሩ ሁሉም ጋር እኩል የመተግበር ክፍተት እንደነበር ጠቅሰዋል። ሆኖም በ2015 ዓ.ም መመሪያው 111 የሚሆኑ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ ተግባራዊ መደረጉን ጠቅሰው፤ በ2016 በጀት ዓመት በማዕከል፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ ባሉ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ ሴት የመንግሥት ሠራተኞች ልጆቻቸውን የሚያውሉበት“ዴይኬር” አገልግሎት ተግባራዊ መደረጉን፤ ሠራተኞች በሸማች ማህበራት በኩል መሠረታዊ ሸቀጦችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል። ከዚህም ባሻገር በበጀት ዓመቱ በሁለት በዓላት አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑት ሠራተኞች የበዓል መዋያ ድጋፍ አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉንም ተናግረዋል። ለዘመናት ሲጠየቁ የነበሩ የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የወተት አበልና አልባሳት በበጀት ዓመቱ ምላሽ መሰጠቱንም አስታውቀዋል። እንደ ቢሮ ኃላፊዋ ገለጻ፤ በከተማ አስተዳደሩ 165 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች ያሉ ሲሆን፤ 40 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ናቸው። በከተማ አስተዳደሩ አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ የሚባሉት ከስድስት ሺህ ብር በታች የሚከፈላቸው ናቸው።

  August 3, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • በትግራይ ክልል በአንድ ቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል በትግራይ ክልል በአንድ ቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል። በትግራይ ክልል በአንድ ቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ላይ የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ-መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤሊያስን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው እየተካሄደ ያለው። አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ባደረጉት ንግግር፤ የትግራይ ክልል በተፋሰስ ልማትና ችግኝ ተከላ የታወቀ መሆኑን በመጥቀስ፤ አሁን የተገኘውን ሰላም በማጽናት የበለጠ የልማት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል። ሰላሙን ለማጽናት የፌዴራል መንግስት ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስም፤ ችግሮች ካሉ በውይይት በመፍታት መጓዝ እንደሚገባ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፤ ሰላም ሰፍኖ ወደዚህ አይነት ተግባር መመለስ መቻሉ መልካም መሆኑን በመጥቀስ፤ የተገኘውን ሰላም ለማጽናት ጠንክረው እንደሚሰሩ አብራርተዋል። በመላው አገሪቱ ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ እስከ 5:30 ባለው ሰዓት 247 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት መግለጹ ይታወሳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

  July 17, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • አረንጓዴ አሻራ በአየር ንብርት ለውጥ የሚከሰተውን ቀውስ ለመቀነስ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ አረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰተውን ቀውስ ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በዛሬው እለት እንደ ሀገር በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ንቅናቄ ምክር ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ በየካ ክፍለ ከተማ የራሱን አረንጓዴ አሻራ ባስቀመጠበት ወቅት ነው፡፡ አረንጓዴ አሻራ የማስቀመጥ ስራ የአለም ሀገራትን ብሎም የኢትዮጵያን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ የእያንዳንዳችን አበይት ትግባር ነው ሲሉ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በዛሬው እለት ኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ እየሰራች እንደሆነ ገልጸው አረንጓዴ አሻራ የማስቀመጥ ስራው በአስቸጋሪ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰተውን ሁለንተናዊ ቀውስ ለመቀነስ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ አረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ የሀገሪቱን የከርሰ እና የገጸ ምድር የውሀ ኃብት ለማበልጸግ፣ የኑሮ ውድነትን በመቀነስ በምግብ ዋስትና ራስን ለማስቻል እና በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የማይተካ ሚና እንዳለውም ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡ ባለፉት አመታት የተተከሉት ችግኞች 80 በመቶ የጸደቁ መሆኑን የገለጹ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ፤ ችግኞች ከተተከሉ በኋላ አድገው ፍሬያማ እስከሚሆኑ ድረስ በቂ እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የህዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል።

  July 17, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • "ዛሬ ኢትዮጵያውያን ተአምር የሚሰሩበት እለት ነው!!" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ተአምር የሚሰሩበት እለት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የአፕል ችግኝ በመትከል የችግኝ ተከላ መርሀግብሩን አስጀምረዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ዛሬ እድሜ እና ጾታ ሳይወስናቸው የዝናብ ሁኔታው ሳይገድባቸው ለችግኝ ተከላው በመሰማራታቸው አመስግነዋል፡፡ በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ ታዳጊዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ መሆኑንም አመልክተዋል ዶክተር ዐቢይ፡፡ የተሻለ አገር የመፍጠር ስራችንን ዛሬ እንጀምር ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ የአየር ሁኔታውን ተቋቁመው በእጃችን ያለውን ችግኝ የመትከል ሪከርድ መስበር አለብን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

  July 17, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዳይ ኢትዮጵያን የመጠበቅ፣ የማክበርና የማበልጸግ ጉዳይ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዳይ ኢትዮጵያን የመጠበቅ፣ የማክበርና የማበልጸግ ጉዳይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ነገ ሰኞ የሚከናወነውን በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ-ግብርን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸውም የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዳይ ታሪክ የመቀየር እና ለትውልድ የመትረፍ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ “ዓላማችን ሪከርዳችንን መስበር ነው!” ብለዋል። ከማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ተግባራት ነጻ የሆነ ቀን የመረጥነው ይህ ቀን ሊያልፈው የሚገባ ኢትዮጵያዊ ስለሌለ ነው። ሰኞን ስንመርጥ የሥራ መጀመሪያችንን ተፈጥሮን በመታደግ እንድንጀምር ነው ሲሉም አክለዋል። ፉክክራችን ከራሳችን ጋር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክልሎች፣ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና መንደሮች ከአምናው የበለጠ በመትከል የየራሳቸውን ሪከርድ እንደሚሰብሩ እናምናለን ብለዋል። “እያንዳንዳችንም የየራሳችንን ሪከርድ መስበር አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኔ ነገ በተደጋጋሚ ለመትከል ተዘጋጅቻለሁ። እናንተስ? ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ችግር የራሱን ሪከርድ እንዲሰብር ልንፈቅድለት አይገባም፤ ችግር የራሱን ሪከርድ ከሰበረ ተሸንፈናል ማለት ነው ሲሉም ገልጸዋል። ችግርን የምናሸንፈው መጀመሪያ የራሳችንን ፣ ቀጥሎ የአካባቢያችንን፤ በመጨረሻም የዓለምን ሪከርድ ስንሰብር ነው በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት አስተላልፈዋል። ነገ ሐምሌ 10 ቀን 2015 የራሳችሁን ሪከርድ በብዙ መጠን እስክትሰባብሩ ድረስ ዛፎችን ለመትከል ተዘጋጁ ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

  July 16, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ረቂቅ ደንቦችን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መራ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ረቂቅ ደንቦችን መርምሮ ለተጨማሪ እይታ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ 25ኛ መደበኛ ስብስባውን ማካሄዱን ኢዜአ ዘግቧል። ምክር ቤቱ ለተጨማሪ እይታ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የመራቸው ረቂቅ ደንቦች የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የተዘጋጀውን ደንብ እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን ነው። ምክር ቤቱ በስብሰባው ረቂቅ ደንቦቹ ላይ የተወያዩ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት አስተያየት እና ጥያቄዎችን አንስተዋል። ምክር ቤቱ ረቂቅ ደንቦቹን መርምሮ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የተዘጋጀውን ረቂቅ ደንብን ለሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን ደግሞ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

  June 22, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ከሀላባ_አንጋጫ_አመቾዋቶ_እና_ዳምቦያ_ዱራሜ እየተገነባ ያለው 65.10 ኪሎ ሜትር መንገድ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ ፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሀላባ አንጋጫ-ዋቶ እና ዳምቦያ ዱራሜ እየተገነባ ያለው 65.10 ኪሎ ሜትር መንገድ ከሚገባው በላይ የተጓተተ በመሆኑ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስቧል። ቋሚ ኮሚቴው በስፍራው ተንቀሳቅሶ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ የተመለከተ ሲሆን የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ እና የቡድኑ አስተባባሪ የተከበሩ ስለሺ ኮሬ (ዶ/ር) የሚመለከተው የመንግስት አካል ለፕሮጀክቱ ከመጠን በላይ መጓተት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት አስቸኳይ የመፍትሄ እርምጃ መውሰድ እና ፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል። የቡድኑ አስተባባሪ አያይዘውም የስሚንቶ ችግር ሀገራዊ መሆኑን አስገንዝበው፤ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች በአግባቡ መቅረብ እንዳለባቸው እና አሰሪው፣ ተቋራጩና አማካሪው በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አስረድተዋል። ሥራው እንዲፋጠን የወሰን ማስከበር ስራው ላይ የሰነድ ዝግጅት እና የቆጠራ ስራዎች መዘግየት እንደሌለባቸው፣ ተቋራጩ ማሟላት ያለበትን ግብዓት ሳያሟላ ሌላ ክፍያ መከፈል እንደሌለበት እና ስራው በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ተጨማሪ ኃይል ማሰማራትና የድርጊት መርሃ-ግብር ማዘጋጀት ይገባል ብለዋል። የድርጊት መርሃ-ግብርን ተከትሎ ከመስራት አንፃር ከአሰሪውም፣ ከአማካሪውም እንዲሁም ከተቋራጩም ክፍተት እንዳለ ገምግመናል ያሉት ዶክተር ስለሺ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም በተጓተተ ቁጥር የግብዓት አቅርቦት ዋጋም እየናረ ስለሚሄድ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ድርጅት ፕሮጀክቱን በጊዜ ለመከወን አቅሙን አሟጥጦ መስራት አለበት ብለዋል። የፕሮጀክቱ አማካሪ መሀንዲስ ኢንጅነር ደርባቸው መዝገቡ የፕሮጀክቱ ግንባታ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 2013 ዓ.ም እንደተጀመረ አስገንዝበው፤ መንገዱ የሞጆ-አርባምንጭ እና የአለም ገና-ሶዶ ዋናውን መንገድ የሚያገናኝ መሆኑንም ገልፀዋል። ግንባታው የሚወስደው ጊዜ 3 ዓመት እንደሆነ እና የሚጠናቀቅበት 2016 ዓ.ም ቢሆንም እስካሁን ያለው አፈፃፀም 12 በመቶ ብቻ እንደሆነ የገለጹት አማካሪ መሀንዲሱ፤ ተቋራጩ በእቅዱ መሰረት ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን አለማቅረቡ ለአፈጻጸሙ መሻሻል እንቅፋት እንደሆነባቸው ነው ያስረዱት። ስራ አስኪያጁ አክለውም የስሚንቶ እና የነዳጅ አቅርቦት በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ፣ ተደጋጋሚ የማሽኖች ብልሽት፣ የመለዋወጫ እጥረት እና የውሃ፣ የቴሌኮሙኒኬሽን እንዲሁም የመብራት መስመር አለመነሳት ለፕሮጀክቱ መዘግየት ምክንያት መሆናቸውን ተናግረዋል። የከምባታ ጠምባሮ ዞን የትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ተሰማ መንገዱ አስቸጋሪ ከመሆኑ አኳያ ማህበረሰቡ ወደ ጤና ተቋማት ሄዶ እንዲታከም እና አምቡላንስ እንዲጠቀም ተለዋጭ መንገድ ያስፈልገዋል ብለዋል። የመምሪያው ኃላፊ አያይዘውም የአካባቢው ማህበረሰብ በፕሮጀክቱ መጓተት እየተማረረ ስለሆነ ቋሚ ኮሚቴው ችግሮቹን ተገንዝቦ ለሚመለከተው አካል በማድረስ አፈጻጸሙንም እንዲከታተልላቸው ጠይቀዋል።

  April 1, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ምክር ቤቱ በህወሓት ላይ ወስኖት የነበረውን የአሸባሪነት ፍረጃ አነሳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባው በአሸባሪነት ተፈርጆ የነበረውን ህወሓት ከአሸባሪነት ዝርዝር በአብላጫ ድምጽ ሰርዟል። ኢ ፕ ድ እንደዘገበው የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ የሰላም ስምምነቱ ቀሪ ጉዳዮች ቢኖሩም ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም እንደሚረዳ ተናግረዋል። ምክር ቤቱ ፍረጃውን ያነሳው የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ሲሆን፤ በስምምነቱ አንቀጽ 7/2 C መሰረት የፌዴራል መንግሥት በህወሓት ላይ የተጣለውን የሽብርተኝነት ስያሜ በምክር ቤቱ እንዲነሳ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች ተገልጿል። ምክር ቤቱ ሚያዚያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ህወሓትን አሸባሪ ብሎ መሠየሙ ይታወሳል። የፌዴራል መንግስትና ህወሓት ጥቅምት 2015 ዓ.ም ላይ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ለ10 ቀናት ድርድር ካካሄዱ በኋላ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ጥቅም ባስከበረ መልኩ ስምምነት መፈጸማቸው ይታወቃል።

  March 22, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • አዲስ አበባ፡- የግብርናው ዘርፍ እንዲዘምንና በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ከተፈለገ የግሉ ዘርፍም እንዲሳተፍበት ማበረታቻ ማቅረብ እንደሚገባ ተገለጸ። በአዲሱ የግብርናና መሬት ልማት ፖሊሲ መሰረት መሬትን በዘመናዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም ያስፈልጋል ሲልም ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢፕድ እንደዘገበው “ኃላፊነት የተሞላበት የመሬት አሥተዳደር የአካታችና ዘላቂ ልማት ጎዳና” በሚል መሪ መልዕክት ብሔራዊ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው። በውይይቱ የተገኙት በግብርና ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ኢፋ ሙለታ፤ በአዲሱ የግብርናና መሬት ልማት ፖሊሲ መሰረት የግብርና መሬትን በዘመናዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል። መሬትን እንዴት ማልማትና ምርታማ ማድረግ እንደሚገባ በአማራና በጋምቤላ ክልሎች እየተሠራ ባለው ፕሮጀክት ጥሩ ተሞክሮ አግኝተናል ያሉት የሚኒስትሩ አማካሪ፤ የግብርና ኢንቨስትመንት ብዙ ችግሮች ያሉበት ቢሆንም ኢኮኖሚውን ሊያሸጋግር የሚችል እንደሆነ አብራርተዋል። በአዲሱ የግብርናና መሬት ልማት ፖሊሲ መሠረት የእርሻ ኢንቨስትመንት በዘመናዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ገልፀው፤ መድረኩ ከውጭም ሆነ በሀገር ውስጥም ያሉትን ልምዶች ለመቀመር የሚያግዝ ነው ሲሉ አቶ ኢፋ ሙለታ ተናግረዋል። በመድረኩ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ጥሩማር አባተ በበኩላቸው፤ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ልማትን ለመተግበር በጋራ እንሠራለን። የግብርናው ዘርፍ እንዲዘምንና በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ የግሉ ዘርፍም እንዲሳተፍበት ማበረታቻ ማቅረብ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ተቋሙ የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝና ባለፉት ሶስት ዓመታት ያጋጠሙ ድክመቶች በመገምገም ለቀጣይ ሶስት ዓመታት ዕቅድ አውጥቶ እየሰራ እንደሆነ በመግለፅ መሬትን ውጤታማ ለማድረግ አጠቃቀም ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ነው የገለጹት። ምክክሩ በግብርና ሚኒስቴር እና በጂ አይ ዜድ ኃላፊነት የተሞላበት የመሬት ኢንቨስትመንት አሥተዳደር ፕሮጀክቶች ትብብር የተዘጋጀ ነው። ፕሮጀክቱ በአማራና በጋምቤላ ክልሎች ከ2019 እስከ 2023 እየተተገበረ የሚገኝ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል። የጂ አይ ዜድና የአውሮፓ ኅብረት ተወካዮች ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሬትን በአግባቡ፣ በውጤታማነት በመጠቀምና በማስተዳደር ምርታማነት እንዲያድግ በጋራ መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከመሬት ባሻገር የሚሠራ የሰው ኃይል፣ ዕውቀት እና ተስማሚ የአየር ንብረት ያላት ናት ያሉት ተወካዮቹ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ፣ የተሻሻለውን ፖሊሲ ይበልጥ ለዘመናዊ ግብርና ጠቃሚ እንዲሆን እንጥራለን ነው ያሉት። ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገትና የግብርና ኢንቨስትመንት ውጤታማነት አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

  March 22, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ለኘሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አተገባበር ስኬታማነት እንግሊዝ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ ተገለፀ ወምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የእንግሊዝ የልማት እና አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር አንድሪው ሚሸልን በፅህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል። ኢዜአ እንደዘገበው በውይይቱ ኢትዮጵያና እንግሊዝ በልማት ትብብር ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ወዳጅነት እንዳላቸው ያስታወሱት አቶ ደመቀ ይህ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ይበልጥ ሊሰሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል። የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተፈፃሚ በማድረግ ረገድ እየተተገበሩ ስላሉ እርምጃዎች ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ፤ የስምምነቱ የእስከ አሁን ሂደት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተናግረዋል። በግጭቱ ወንጀል በመፈፀም የሚጠረጠሩ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግም የሽግግር ፍትህ ስርዓት ተዘርግቶ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። እንግሊዝ ለኢትዮጵያ እያደረገች ላለው የሰብዓዊ ድጋፍ አቶ ደመቀ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ይህ ተግባር በአሁኑ ወቅት በጦርነት እና በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን በመደገፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። በእንግሊዝ የፓርላማ አባል የሆኑትና የአገሪቱ የልማትና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር አንድሪው ሚሸል በበኩላቸው በኢትዮጵያ ሰላምን ለማስፈን በመንግስት በኩል የተወሰደውን እርምጃ እና የታየውን ቁርጠኝነት አገራቸው እንደምታደንቅ የገለፁ ሲሆን ለስኬታማነቱም እንግሊዝ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል። ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ከድርቅና ሌሎች ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ያጋጠማትን ፈተና እንግሊዝ እንደምትገነዘብ ገልጸው ለዚህ የሚሆን ድጋፍ ከረድኤት ድርጅቶችና ከሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን እንደሚደረግ ገልፀዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በሁለትዮሽ እና በሌሎች የትብብር መስኮችም ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ውይይት ተደርጓል።

  March 22, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • በኢትዮጵያ ለተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የአገርን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና አካታች የፖሊሲ አቅጣጫ መከተል ይገባል በኢትዮጵያ ለተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የአገርን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና አካታች የፖሊሲ አቅጣጫዎችን መከተል ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ ። አፈ ጉባዔው ይህን ያሉት በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ የግብዓት ማሰባሰብ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። የሽግግር ፍትህ ስርዓት አንድ ማህበረሰብ ላለፈበት ጉዞ የደረሰበት ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነት ለማስፈን ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። በተለይ ዘላቂ ሰላምና ዕርቅን ለማረጋገጥ ሁነኛ አማራጭ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም የነበሩ ክፍፍሎችን፣ የተፈፀሙ በደሎች ለማከም እና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጦችን ለማስቀጠል እንደሚያግዝ ተናግረዋል። በርካታ አገራት የሽግግር ፍትህ ስርዓትን እንደተጠቀሙ ጠቅሰው፤ በኢትዮጵያ ለተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የአገርን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና አካታች የፖሊሲ አቅጣጫ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ በተጨማሪም የተሻሉ ተሞክሮዎችን ከዓለም አቀፍ መርሆች ጋር በመቀመር መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

  March 6, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን የየክልሎቹ ኮምንኬሽን ቢሮ ኃላፊዎች አስታወቁ። በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን የሁለቱም ክልሎች የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊዎች ዛሬ በጋራ በስጡት መግለጫ አስታወቀዋል። የአማራ ክልል የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ትናንት የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በአገራዊ፣ ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። በውይይቱ ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ግዛቸው፤ መልካም የሆኑ የልማት ስራዎችን በጋራ ለማስቀጠል፣ ፈተናዎችና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ውጤታማ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በበኩላቸው፤ በሁለቱ ክልሎች መካከል የመልካም አስተዳደር፣ የልማት፣ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነትቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት በከፍተኛ አመራሮች መካከል መካሄዱን አስታውቀዋል። ሁለቱ ክልሎች በመናበብ የጋራ የሆኑ ፈተናዎችንና ችግሮችን ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷልም ብለዋል። ውይይቱ በአመራሩ ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በቀጣይም በምሁራን፣ በአገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል ይደረጋል ተብሏል።

  March 1, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ኢትዮጵያ የአፍሪካን የንግድ ልውውጥና የምጣኔ ሃብት ውህደት የሚያፋጥኑ ተግባራትን ማከናወኗ የሚደነቅ ነው- የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኢትዮጵያ የአፍሪካን የንግድ ልውውጥና የምጣኔ ሃብት ውህደት የሚያፋጥኑ ተግባራትን ማከናወኗ የሚደነቅ መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ፔድሮ ተናገሩ። በአፍሪካ የንግድና የምጣኔ ሃብት ቁርኝት እንዲሁም የመሰረተ-ልማት ትስስርን በማፋጠን የአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ዕቅድን ማሳካት ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ሆኗል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ፣ ኢጋድና በአጠቃላይ ከዓለም ጋር የንግድና ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር ለማፋጠን እየሰራች መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ተጠባባቂ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ፔድሮ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአህጉሪቷና በዓለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎትና ተደራሽነቱን በማስፋት የነበረውን ጉልህ ሚና አስታውሰው፤ በመሰረተ-ልማትና ሌሎችም መስኮች ኢትዮጵያ ለአህጉራዊ ትስስር እየሰራች መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ የአፍሪካን የንግድ ልውውጥና የምጣኔ ሃብት ውህደት የሚያፋጥኑ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኗን በአድናቆት ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በአሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በስፋት በማምረት ወደ ሥራ ማስገባት ትልቅ ትኩረት ተደርጓል ያሉት ተጠባባቂ ዋና ጸሐፊው አፍሪካ ለዚህ ጥሩ አቅምና በቂ ሃብት አላት ብለዋል። ኢትዮጵያም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለማበረታታት የወሰደቻቸው የፖሊሲ ማሻሻያ ለዘርፉ ልማት ጥሩ መሰረት የሚጥል ስለመሆኑ ጠቅሰዋል። በአውሮፓውያኑ 2025 የአህጉሪቷ የንግድ ትስስር 7 ነጥብ 7 ትሪሊየን ዶላር እንደሚሆን ሲገመት በ2050 ደግሞ 46 ትሪሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በአፍሪካ በመሰረተ-ልማትና ምጣኔ ሃብት አህጉራዊ ውህደትን ማምጣት በአጀንዳ 2063 ከተቀመጡ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

  February 28, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • በሀገራችን አርብቶ አደሮች አካባቢ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም እና ሰውና እንስሳትን ለማዳን ካውንስሉ አስቸኳይ ውሳኔ አሳለፈ የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ልማት ካውንስል የውሃ አቅርቦት፣ የመልሶ ማቋቋም ስራ፣ የሰውና የእንስሳት መድሃኒት አቅርቦት እና እንስሳቱ በህይወት እንዲቆዩ የሚያስችል አልሚ የሆኑ (nutritious) መኖዎችን በአስቸኳይ እንዲቀርቡ ወስኗል። ውሳኔው በእቸኳይ እንዲፈፀም በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ሰብሳቢነት፣ በግብርና ሚኒስቴር ም/ሰብሳቢነት እና በኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን ፀሃፊነት የሚመራው ኮውንስል በስሩ የተዋቀረው የቴክኒክ ኮሜቴ በሁለት ቀናት ውስጥ አስቸኳይ ( Emergency Plan) ዕቅድ አቅዶ ለአብይ ኮሚቴው እንዲያቀርብ መታዘዙ ታውቋል። ወደ ገበያ መቅረብ የሚችሉትን እንስሳት ወደ ገበያ ማዕከላት ማምጣት፣ አልያም በዕርድ፣ በማድረቂያ ማሽን ተጠቅሞ አድርቆ ከትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ጋር የማስተሳሰር ስራ ይሰራል። በኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን አስተባባሪነት አቅም ያላቸውን ኅብረት ስራ ማኅበራትን በማስተባበር ከብቶችን እንዲገዙ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ታውቋል። የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ልማት ካውንስል በአርብቶ አደር እና በከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ያሉ የእንስሳት ሃብት ልማትና ግብይት እና ሌሎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት እንደተቋቋመ ታውቋል። ካውንስሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ የእንስሳት ባለሙያዎች ማኅበር፣ የብሔራዊ ባንክ እና የልማት አጋሮች አባል የሆኑበት ነው።

  February 28, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የመጀመሪያው አህጉር አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል የመጀመሪያው አህጉር አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቀ። የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን አህጉር አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር መድረክ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ ጉባኤው በመጪው ሳምንት የካቲት 21/2015 ዓ.ም በአፍሪካ ሕብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል ብለዋል። ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፤ ሃይማኖታዊ ትብብርን፣ የአማኞችን አብሮነት የማጠናከርን ዓላማ ያነገበ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህም ባለፈ የውይይት ባህልን ማዳበር እና የአፍሪካ ሕብረት የቡድን 20 አባል እንዲሆን በጉባኤው ምክክር በማድረግ አቋም እንደሚንጽባረቅበት ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

  February 21, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • በአፍሪካ የቡና ግብይትን ለማዘመን ስራ ፈጣሪዎችን ማበረታታትና ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ ገለጹ በአፍሪካ የቡና ግብይትን ለማዘመን ስራ ፈጣሪዎችን ማበረታታትና ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት፣ የኢፌዴሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የአፍሪካ ኢ ትሬድ ግሩፕ እና ኢንተር አፍሪካ ቡና ድርጅት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። በአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ልማት፣ ንግድ፣ ቱሪዝምና ማዕድን ኮሚሽነር አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ እንዳሉት የህብረቱ አባል ሀገራት የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናውን ትግበራ በማፋጠን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስራቸውን ማጎልበት አለባቸው። በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር በማጠናከር በቀጣናው ያለውን ንግድ ማሳደግ ይገባል ብለዋል። በመሆኑም የህብረቱ አባል ሀገራት የዘንድሮውን መሪ ሀሳብ ገቢራዊ በማድረግ የቡናን ንግድ ማሳደግና የወጣቶችን ስራ ፈጣሪነት ማበረታታት እንዳለባቸው ገልጸዋል። የኢፌዴሪ ስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አፍሪካ የወጣቶች ስብስብ መሆኗን እንደመልካም እድል ጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል። በየዓመቱ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በስራ በሙያ ክህሎት፣ ስልጠናና ፋይናንስ በመደገፍ ስራ ፈጣሪዎች ማድረግ ይገባል ብለዋል። በኢትዮጵያ የስራ እድል ፈጠራ በመልካም ሂደት ላይ መሆኑን የገለጹት አቶ ንጉሱ፣ ሂደቱን ቀጣናዊ ለማድረግ "የአፍሪካ ወጣቶች ስብሰባን" ዛሬ ይፋ አድርገዋል። የአፍሪካ ኢ ትሬድ ግሩኘ በቡና ልማት ላይ ለተሰማሩ ስራ ፈጣሪዎች በአገር አቀፍም ሆነ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የአፍሪካ ኢ ትሬዴ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙሉዓለም ስዩም በአፍሪካ በስራ ፈጠራ ላይ ለሚሰማሩ ወጣቶች የፋይናንስ፣ የስልጠናና የገበያ ትስስር ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

  February 20, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ኢትዮጵያ ለህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ያከናወነችው ስኬታማ ዝግጅት ዓለም አቀፍ ግዴታዎቿን በብቃት የመወጣት አቅም እንዳላት ማሳያ ነው- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ያከናወነችው ስኬታማ ዝግጅት ዓለም አቀፍ ግዴታዎቿን በብቃት የመወጣት አቅም እንዳላት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ “የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን ትግበራ ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው 36ኛው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ የሚሳተፉ የዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ተቋማት መሪዎች ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል ተከስቶ የነበረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ በመፍታት የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን መፍታት እንደሚቻል አሳይታለች፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ የሰፈነውን ሰላም ተከትሎ ከ36ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ቀደም ብሎ የሚካሄደው የህብረቱ አባል ሀገራት 42ኛው የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል ብለዋል፡፡ ነገ በሚጀምረው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ከአፍሪካ አገራት መሪዎች ባሻገር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የቻይና የሩሲያ እና ዓለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች ተወካዮች በአዲስ አበባ ከትመዋል ብለዋል፡፡ ጉባኤው በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ በመፍታት አስተማማኝ ሰላም ባሰፈነችበት ማግስት እንደሚከናወንም አስታውሰዋል፡፡ የዘንድሮውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ ስኬታማ ዝግጅት ማድረጓን ጠቅሰው፤ ይህም መደበኛውን ጉባኤ ከማስተናገድ ባለፈ ዓለም አቀፍ ግዴታዎቿን በብቃት መወጣት የሚያስችል ልምድና አቅም እንዳላት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ ምቹ የንግድና ኢንቨስትመንት ሀገር መሆኗን ጭምር የምናሳይበት ነው ብለዋል፡፡ በዚህም በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ በፓን አፍሪካኒዝምና በአረንጓዴ አሻራ ላይ የምታደርገውን እንቅስቃሴ የምናሳይበት መርሃ ግብር አዘጋጅተናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

  February 17, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ስጋትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አርዓያ ሆናለች በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥ ስጋትን ለመቀነስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ግንባር ቀደም በመሆን ለሌሎች ሀገራት አርዓያ መሆኗን የዓለም ሚትዎሮሎጂ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ፕሮፌሰር ፔትሪ ታላስ ተናገሩ፡፡ የዓለም ሜትዎሮሎጂ ድርጅትና የኢትዮጵያ ሜትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በጋራ ባዘጋጁት 18ኛው የአፍሪካ አህጉር የሚትዎሮሎጂ ጉባኤ ላይ ፕሮፌሰር ፔትሪ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ለዓለም ስጋት የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቀነስ ያደረገችው ጥረት ከፍተኛ ነው። ባለፉት አራት ዓመታት 25 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከልና የአህጉሪቱን ሥነምሕዳር ለመጠበቅ ባከናወነቻቸው ተግባራት ለተለያዩ ሀገራት አብነት የሚሆኑ ስራዎችን ሰርታለች ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰር ፔትሪ እንዳስታወቁት፤ ኢትዮጵያ የተከለቻቸው የተለያዩ አይነት ዕፅዋቶች የዓለምን የአየር ንብረት ለውጥ ከመቀነስና የአካባቢን ሥነምሕዳር ከማስተካከል ባሻገር ለግብርናው ዘርፍ ውጤታማነት፣ ለሥራ እድል ፈጠራና የተለያዩ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለማገዝ ወሳኝ ጠቀሜታ አላቸው። በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የተለያዩ መንግሥታት ተሳትፎ እያደረጉ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ፔትሪ፤ በተለይ ኢትዮጵያ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ጉዳቱን ለመቀነስ ለምትሠራቸው ሥራዎች ከአፍሪካ በምሳሌነት እንድትጠቀስ አድርጓታል ብለዋል፡፡ አፍሪካ ከአንዳንድ ቦታዎች ዝናብ ባለማግኘቷ በየጊዜው ድርቅ ሲከሰት ይስተዋላል ያሉት ዋና ጸሐፊው፤ ለእነዚህ ጉዳቶች ኢትዮጵያ የተከለቻቸው ዛፎች በቀጣይ ለሚከናወኑ የግብርና ልማቶች፣ ለኃይል አቅርቦትና ተጓዳኝ ሥራዎች ውጤታማነት የበኩላቸውን እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሜትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ በበኩላቸው፤ የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም ላይ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል፤ ይህን ለመከላከል ኢትዮጵያ መላውን ሕዝቦቿን ያሳተፈ ሥራ እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል። ኢትዮጵያ ተፅዕኖውን ለመቀነስ ብሎም ለማስቀረት የአስር ዓመት እቅድ ነድፋ እየሠራች ባለው ሥራ ከአፍሪካ ተጠቃሽ መሆን ችላለች ሲሉ ገልጸዋል። ለችግሩ መፍትሔ ለመፈለግ ኢትዮጵያ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በትብብር እየሠራች ትገኛለች። የሀገሪቷን አግሮ ኢኮሎጂ ለመጠበቅ የሚረዱ እፅዋቶችን በመትከልና በመንከባከብ ሚሊዮኖች ተሳትፎ እያደረጉ ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡ አቶ ፈጠነ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያን ሜትዎሮሎጂ ለማበልጸግና ለተለያዩ መሠረተ ልማቶች ማሟያ የሚሆን 30 ሚሊዮን ዩሮ ከፊላንድ መንግሥት ድጋፍ አግኝታለች። በቀጣይም ከተለያዩ አካላት የሚገኙ ድጋፎችን በመጠቀም የአካባቢ ጥበቃ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል። በ18ኛው የአፍሪካ አህጉር የሜትሮሎጂ ጉባኤ የ54 አፍሪካ ሀገራት የሜትዎሮሎጂ ተቋማት ኃላፊዎችና አጋር አካላት እንዲሁም ምሑራን ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተዘጋጀው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸው እንዲሁም የአፍሪካ የሜትዎሮሎጂ አገልግሎት አሰጣጥ በሚሻሻልበት ሁኔታ ይመክራል፡፡( ኢፕድ)

  February 17, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ሦስት ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደርሷል በ2015/16 የምርት ዘመን ከሚያስፈልገው 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ውስጥ ሦስት ሚሊዮን ኩንታሉ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። ከዚህ ውስጥም አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታሉ አገር ውስጥ መግባቱ ተጠቁሟል። በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሶፊያ ካሳ እንደገለጹት፤ ለዘንድሮ የምርት ዘመን የ12 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ኩንታል ግዢ ተፈጽሟል። ግዢ ከተፈፀመበት የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ ወደ ሦስት ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደርሷል። ጅቡቲ የደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ወደ አገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ሲሆን፣ አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታሉ ወደ አገር ገብቷል። እንደ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገለፃ፣ እያንዳንዳቸው 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ የሚጭኑ አምሥት መርከቦች የአፈር ማዳበሪያውን ጭነው ጅቡቲ ደርሰዋል። በቅርቡም ስድስተኛዋ መርከብ ጅቡቲ ትደርሳለች። ከተገዛው 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ አምስት ሚሊዮን ኩንታል የሚሆነው በሰብል ቡቃያ ወቅት የሚደረግ ዩርያ ማዳበሪያ ሲሆን፣ የቀረው በዘር ወቅት የሚደረግ ዳፕ ማዳበሪያ እንደሆነም ሚኒስትሯ ገልፀዋል። ግዢ የተፈፀመው የክልሎችን ፍላጎትና ፍጆታ መሠረት በማድረግና የአገሪቱንም አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ያሉት ሚኒስትሯ፣ የግብርና ግብዓት ቀድሞ የማስገባት ሥራ እየተሠራ ያለውም ማዳበሪያው በሚያስፈልግበት ወቅት የግብዓት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም ታሳቢ በማድረግ ነው ብለዋል። አገሪቱ ከተለያዩ የውጭ አገራት ማዳበሪያ ለማስገባት በየዓመቱ የምታወጣውን ወጪ ለማስቀረት በአገር ውስጥ ማዳበሪያ ለማምረት በሚደረግ እንቅስቃሴ ኃላፊነቱ የግብርና ሚኒስቴር ብቻ አይደለም ሲሉም ገልፀዋል። የማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ ለማቋቋምም የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት የራሳቸው ድርሻ እንዳላቸውና ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ አገሪቱ ከውጭ ሳትጠብቅ በራሷ የአፈር ማዳበሪያ ምርት ተጠቃሚ እንድትሆን ለማድረግ እቅድ እንዳለው ገልፀዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

  January 28, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመተባበር ወደ ውጭ አገራት ለስራ የሚሰማሩ ሙያተኞች የተሻለ ክህሎት እንዲኖራቸው እየተሰራ ነው ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመተባበር ወደ ውጭ አገራት ለስራ የሚሰማሩ ሙያተኞች የተሻለ ክህሎት እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ከክልልና ከተጠሪ ተቋማት ጋር የ2015 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሂዷል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ የሚሰማሩ ዜጎች በቂ የክህሎት ስልጠና እንደማይሰጣቸው አስታውሰዋል፡፡ ይህም ዜጎች ልፋታቸውን የሚመጠን ጥቅም ካለማግኘታቸውም በላይ ለአስከፊ የመብት ጥሰት እንዲጋለጡ እድል ፈጥሮ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ በአገር አቀፍ ደረጃ በሚገኙ 77 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የክህሎት ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡ ለዚህም የስርዓተ ስልጠና ክለሳ እና የማሰልጠኛ መሳሪያ ዝግጅት እንደተከናወነ ነው የገለጹት። የአረብኛና እንግሊዘኛ ቋንቋ ስርአተ ስልጠና ተዘጋጅቶ በውጭ አገር ለሚሰማሩ ዜጎች እንደሚሰጥም አብራርተዋል፡፡ ከዚህም ቀደም በሙከራ ደረጃ በነርስና ግብርና ዘርፍ ላይ የውጭ አገር የስራ ስምሪት መሰጠቱን ጠቅሰው፤ በዚህም ጥሩ ልምድ ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡ በተለያዩ አገራት ያለውን የስራ ገበያ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ከባህሬን፣ ኦማን፣ ጣሊያን፣ ዮርዳኖስ፣ ጀርመን፣ ኩዌት፣ ባህሬንና ሊባኖስ ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ሰነድ ለመፈራረም ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪ ከጃፓን፣ እስራኤልና ሳውዲ አረቢያ አገራት ጋር የድርድር ሰነድ የማዘጋጀት ሂደት መጀመሩ ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

  January 28, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አደረገ የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አድርጓል ። የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2014 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በአዲስ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱን አስታውሰው ይህ አዲስ አካሄድ ቀጣይ እርምጃዎቻችንን የሚለኩ ነበሩ ብለዋል። ሀቀኛ እና ትክክለኛ የተማሪዎችን የትምህርት ክህሎት በመለካት የፈተና ሂደቱ ከኩረጃ፣ የፈተና ስርቆት የፀዳ ነው ተብሏል። በዚህ ፈተና ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ የሚኮሩበት ነው ተብሏል። በ2014 ዓም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92.2 % 908ሺ ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም ተብሏል። በደንብ ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ ቀርተዋል። በ2014 የትምህርት ዘመን 899ሺህ 520 ተማሪዎች ተፈትነዋል ። በፆታ ማዕከልነት የአማካይ ውጤት በወንዶች 30.2 እንዲሁም ሴቶች 28.09 % አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል። በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቢ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27.79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል። በክልል ደረጃ ይህየ ነው የሚባል የውጤት ልዩነት እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ፣ሀረሪ እና ድሬደዋ የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል። ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤ 666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች ። በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል። እነዚህ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎይ በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል መባሉን ዋልታ ዘግቧል።

  January 28, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ድርጅት የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፉ ለመደገፍ ዝግጁ ነው የዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ድርጅት የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዓለም አቀፍ የትምህርት አጋርነት ድርጅት ዋና ስራ አሰፈጻሚ ላውራ ፍረጀንት ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተደረጉ ለውጦችን እና እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አብራርተዋል። የትምህርት ጥራትንና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ለማድረስ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል። ሚኒስትሩ የዓለም አቀፍ የትምህርት አጋርነት በኢትዮጵያ በትምህርት መስክ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመው አሁንም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡ የዓለም አቀፍ የትምህርት አጋርነት ዋና ስራ አስፈጻሚ ላውራ ፍረጀንት በበኩላቸው በኢትዮጵያ በትምህርት ተደራሽነት የተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤት ተገኝቶባቸዋል ነው ያሉት፡፡ ድርጅታቸውም የኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ለመደገፍ ከአለም አቀፍ ለጋሾች ጋር በመወያየት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

  January 28, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የሀገራችን ሶስት ሆስፒታሎች በአለም አቀፍ ደረጃ የረጃጅም አጥንቶች ከፍተኛ ኦፕራሲዮን ከሚሰራባቸው ምርጥ 10 ሆስፒታሎች ውስጥ ተካተዋል። SIGN IMN የሚባለው የረጃጅም አጥንቶች ከፍተኛ ኦፕራሲዮን ህክምና በአለም አቀፍ ደረጃ በአሁኑ ወቅት ከሚሰራባቸው ከ404 ሆስፒታሎች የመጀመሪያዎቹ አስር ሆስፒታሎች ዉስጥ የጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ አለርት ሆስፒታል እንዲሁም ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል በቀዳሚነት ዝርዝራቸው ለመግባት መቻሉ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡ አሜሪካን ሀገር የሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የሆስፒታሎችን ደረጃ ማሳወቁን ተከትሎ ክብርት ሚኒስትር እንደተናገሩት ይህ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው እንደ ሀገር በቅንጅት እና ለፕሮግራሙ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ እና በነዚህ ሆስፒታሎች ያሉ አመራሮችና የአጥንት ቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ቁርጠኝነት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በመላው ዓለም በ57 ሀገራት ከሚገኙ SIGN IMN የሚባለው የረጃጅም አጥንቶች ከፍተኛ ኦፕራሲዮን ከሚሰራባቸው 404 ሆስፒታሎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦፕራሲዮን ከተሰራባቸው የመጀመርያ አስር ሆስፒታሎች መካከል የጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 7ኛ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል 9ኛ እንዲሁም አለርት ሆስፒታል 10ኛ ደረጃን ለመያዝ የቻሉ መሆኑን ከድርጅቱ የተገኝው መረጃ ያሳያል፡፡ የጤና ሚኒስቴር ከ SIGN FRACTURE CARE INTERNATIONAL ጋር ባለዉ የጋራ ስምምነት እየደገፈ ሲሆን ዶክተር ሊያ ታደሰ ይህንን ስራ ሲሰሩ ለነበሩ በተለይም SIGN FRACTURE CARE INTERNATIONAL እና ውጤቱን ላስመዘገቡት ሆስፒታሎች ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በተለይም የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለበርካታ አመታት በመስራት፣ ሌሎች ሆስፒታሎችንም በማገዝ ላደረገዉ እና ለሁለተኛ ጊዜ በመጀመሪያዎቹ 10 ሆስፒታሎች በመግባቱ እዉቅና ሰጥተዋል። የSIGN IMN Fixation System በመኪና አደጋና በጦርነት ለሚከሰቱ የትልልቅ አጥንት ስብራቶች በኦፕራሲዮን ማከሚያ ዋና ፍቱን መሳርያ ከመሆኑም በላይ የህክምና መሳሪያው ለሆስፒሎቹ በነፃ የተሰጠ በመሆኑ በሀገራችን አገልግሎቱን ታካሚዎች እንዲያገኙት ለማድረግ አስችሏል፡፡

  January 28, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አባላት መቀሌ ገቡ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አገር በቀል እና የውጭ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር ወደ ትግራይ ተጉዟል። የምክር ቤቱ አባላት በመቀሌ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርሱ የትግራይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ተቋም አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አባላት በትግራይ ያለው የሰብዓዊ፣ መልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ጉዳዮችን በተመለከተ በትግራይ ካሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

  January 23, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ሚኒስቴሩ በትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲ ትግበራ ላይ የምሁራን ውይይት እያካሄደ ነው ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጃው የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲ ትግበራ ላይ ከምሁራን ግር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡ 1986 ዓ.ም የተዘጋጀው የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲ በርካታ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ አዲስ የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት እንዳስፈለገም በመድረኩ ተገልጿል፡፡ አዲስ የተዘጋጀው የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲ ፍኖተ ካርታ ላይ ከ 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተወያይቶበታልም ነው የተባለው፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) አሁን ያለው የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸው ፖሊሲው ብቁ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ተማሪ ለማፍራት አያስችልም ብለዋል፡፡ በመሆኑም አዲስ የተዘጋጀው የትምህርት እና ስልጠና ፖሊስ ፍኖተ ካርታ ለሚቀጥሉት 15 ዓመታት የሚተገር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፖሊሲው ወደ ትግበራ ሲገባ ብቁ እና ተወዳዳሪ ተማሪ ለማፍራት ሁሉም የሚመለከተው አካል ርብርብ ለያደርግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

  January 23, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • በኢትዮጵያ ያሉ ቱባ ኃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን ለዓለም በማስተዋወቁ ትልቅ አደራ አለብን-ዳያስፖራዎች በኢትዮጵያ ያሉ ቱባ ኃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን ለዓለም በማስተዋወቁ ረገድ የዳያስፖራው ማህበረሰብ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ኢዜአ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ገለጹ። የከተራና ጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ደማቅ በሆነ ኃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት እየተከበረ ነው። በበዓሉ አከባበር ላይ የተለያዩ የውጭ አገራት ዜጎች ፣ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች ተግኝተዋል። በበዓሉ ላይ ከታደሙት መካከል በፈረንሳይ ፓሪስ ለረጅም ዓመታት የኖሩት የቀድሞ ብሄራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋች ግርማ ሳሬ አንዱ ናቸው። በአዲስ አበባ ጃንሜዳ በልጅነታቸው ከእድሜ አቻዎቻቸው ጋር በማክበር የማይረሳ ጊዜ ማሳለፋቸውን አስታውሰው ከረጅም ዓመታት በኋላ በአዲስ አበባ ተገኝተው ጥምቀትን በማክበራቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ ኃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላትን ከወገኖቻቸው ጋር ቢያሳልፉ ከሚያገኙት ደስታ ባለፈ መረጃ ሰንደው አገራቸውን ለማስተዋወቅ ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን ይናገራሉ። በመሆኑም እርሳቸውን ጨምሮ በየትኛውም አለም የሚኖሩ ዳያስፖራዎች በኢትዮጵያ ያሉ ቱባ ኃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን ለዓለም በማስተዋወቁ ረገድ በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። የበርካታ ሃብቶችና ቅርሶች ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ የዓለም ቱሪስቶችን ቀልብ የምትገዛ በመሆኗ እንድትጎበኝ ሁላችንም ማስተዋወቅ አለብን ብለዋል። በዚህ ጉዳይ በተለይም የዳያስፖራው ማህበረሰብ ትልቅ አደራና ሃላፊነት አለበት ሲሉም ተናግረዋል። በደቡብ አፍሪካ ለ16 ዓመታት ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አቶ ዮሃንስ አመንቴ በበኩላቸው ከረጅም ዓመታት በኋላ በጃንሜዳ ተገኝቼ በዓሉን በማክበሬ ጥልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል። በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ኃይማኖቱን እና ትውፊቱን ለውጭ አገር ዜጎች በዝርዝር ማስረዳት መቻሉ ጎብኚዎችን ለመሳብ ቁልፍ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል። ዳያስፖራው አገሩን ለማስተዋወቅ ኢትዮጵያ ምን ምን ሃብቶች አሏት? የትኞቹ ጎልተው ቢወጡ ጠቃሚ ይሆናል የሚለው ላይ በቂ መረጃ ሊኖረው እንደሚገባም ነው አጽንኦት የሰጡት። በኢትዮጵያ ያሉ የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ በውጭ ያሉ የዳያስፖራ ማህበራት የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

  January 19, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የጥምቀት በዓል ኃይማኖታዊ ስርዓቱንና ትውፊቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ማድረግ የመላው ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው -የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥምቀት በዓል ኃይማኖታዊ ስርዓቱንና ትውፊቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ማድረግ የመላው ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው ሲል የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ። ምክር ቤቱ የጥምቀት በዓልን በማስመልከት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፤ በመልዕክቱም በዓሉ ኃይማኖታዊ ስርዓቱንና ትውፊቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ማድረግ ለእምነቱ ተከታዮቹ ብቻ የሚተው ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው ብሏል። የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በአደባባይ ከምታከብራቸው ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልፆ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የዕርቅና የመተሳሰብ በዓል ሆኖ እንዲያልፍ መልካም ምኞቱን ገልጿል። በዓሉ ከኃይማኖታዊ አስተምህሮና እሴቱ ባለፈ የኢትዮጵያውያንን ማህበራዊ ትስስር የሚያጠናክር፣ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን የሚያሳልጥ እና ለሀገር ገፅታ ግንባታና ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ዕድገት ያለው ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ ነው ሲልም አስታውቋል። በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ በተረጋጋና በሰከነ መንፈስ በመንቀሳቀስ ህብረተሰቡ ሰላሙን እንዲጠብቅም ምክር ቤቱ ጥሪውን አስተላልፏል። ምክር ቤቱ በመልዕከቱ የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ አካላትም ኃላፊነታቸውን በትጋትና ኃላፊነት በተሞላበት ስሜት እንዲወጡም ምክር ቤቱ አሳስቧል።(ኢዜአ)

  January 18, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ኢትዮጵያ መጎብኘት ካለባቸው 5 ምርጥ የዓለማችን የቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል አንዷነች - ናሽናል ጂኦግራፊ

  ናሽናል ጂኦግራፊ መጎብኘት አለባቸው ካላቸው የዓለማችን አምሥት ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል ኢትዮጵያን አካቷል፡

  ፡ ናሽናል ጂኦግራፊ - ብሪታኒያ የፈረንጆቹን 2023 ዐዲስ ዓመት ዕትምን ይዞ ወጥቷል፡፡

  በሰሜን ኢትዮጵያ አፋር ውስጥ ዳሎልን አካሎ የሚገኘው የደናክል አካባቢ በቀዳሚነት የቱሪስቶችን ቀልብ ይገዛል ተብሎ በዲጂታል ዕትሙ ተጠቁሟል፡

  ፡ የደናክል አካባቢ የምድራችን ደረቁ ፣ እጅግ ሞቃታማው እና ረባዳማው አካባቢ እንደመሆኑ ፈተና እና ጀብዱ የሚወዱ ቱሪስቶች ሳይጎበኙት እንዳያልፉም በመረጃው አስታውሷል፡፡

  አካባቢው በውስጡ ጨዋማ ወንዞችን ፣ ቢጫ ቀለም ያላቸው አሲዳማ እና እንፋሎታማ ምንጮችን እንደ ጅረት የሚፈሱ እሳተ-ገሞራዎችን እንደያዘም ጠቅሷል፡፡

  ናሽናል ጂኦግራፊ -ብሪታኒያ በተለይ በጎንደር እና በላሊበላ አካባቢ በኦርቶዶክስ አማኞቸ ዘንድ በደመቀ ሥነ-ሥርዓት የሚከበሩት የጥምቀት እና የገና በዓላት ምርጥ የቱሪስት መስኅቦች መሆናቸውን አንስቷል።

  በ17ኛው ክፍለ-ዘመን እንደተገነባ የሚነገርለት የጎንደር ቤተ መንግስ እንዲሁም የላሊበላ ውቅር አቢያተ-ክርስቲያናትም መጎብኘት አለባቸው ብሏል-በመረጃው።

  በተጨማሪም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚደረጉት ሃይማኖታዊ ጉዞዎች ምግቦች ፣ መጠጦች እና ባሕላዊ ጭፈራዎች ሌላ የቱሪስቶችን ዕይታ የሚስቡ ትዕይንቶች መሆናቸውንም ዘርዝሯል፡፡

  ቱሪስቶች የአስደናቂ መልክዓ-ምድሮች እና የበርካታ ጎሳዎች መገኛ የሆነውን እስከ ኦሞ ሸለቆ የሚዘልቀው ደቡባዊ ክፍል ያለውን አካባቢ እንዲጎበኙም ተጠቁሟል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል ፡፡

  January 10, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ጋር ተወያዩ

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቻይናን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደኅና መጡ ብለዋቸዋል።

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ "የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አሁንም ጸንቶ ቀጥሏል ፤የዛሬው ውይይታችን ይህንን እና በልማት የምንጋራውን ስልታዊ የጋራ ዓላማ፤ እንዲሁም አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን አጉልቶ አሳይቷል" ሲሉ ገልጸዋል።

  አዲሱ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ማለዳ ነው አዲስ አበባ መግባታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

  January 10, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የሀብት ብክነትን ለመከላከል የግዢ ሥርዓት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል

  ለግዢ የሚውለው የሀገሪቱ 70 በመቶ በጀትን ከሙስና ለማዳን ግልፅ አሰራር ሊዘረጋ ይገባል ሲሉ የፓን አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክቡር ገና ገለጹ፡፡

  የፓን አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክቡር ገና ለኢፕድ እንደገለጹት ከአጠቃላይ የሀገሪቱ በጀት 70 በመቶ የሚሆነው ለግዢ የሚውል ትልቅ በጀት ነው። ይህን በጀት ከሙስና መጠበቅ እንዲቻል ግልፅ የሆነ አሰራር ሊዘረጋ ይገባል

  ዋና ስራ አስፈጻሚው ፤ ሙስና የሚስፋፋው ግልጽ ያልሆነ የአሠራር ሥርዓት ሲዘረጋ መሆኑን ጠቁመው፤ ሌብነትን ለመከላከል ግልጽ አሠራር ሊኖር እንደሚገባ ተናግረዋል።

  የሚዘረጋው የአሠራር ግልጽነትም የግዢ ጨረታ በማውጣት ሂደት ላይ የተድበሰበሱ ጥቄዎች እንዳይኖሩ ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች ብዥታ የሚያስከትሉ አሠራሮችን በማፅዳት ጭምር ሊከወን እንደሚገባም ጠቁመዋል።

  በአንድ የግዥ ኤጀንሲ ብቻ ግዥ መፈጸሙ ብቻውን በዘርፉ ለሚስተዋለው ችግር መንስዔ ላይሆን ይችላል ያሉት አቶ ክቡር፤ ችግሩ የአሠራር ቅልጥፍና አለመኖርና በጨረታ ወቅት ጨረታው ሰዓቱን ጠብቆ አለመከፈትና ከተከፈተም በኋላ ቶሎ መዘጋት አለመቻል የመሳሰሉ ችግሮች እንደሚታዩ ተናግረዋል።

  የግዥ ጨረታዎች በዚህ መንገድ ሲከናወኑ ለሙስና ተጋላጭ ስለሚያደርጉና ተቋሙን ስለሚያስጠረጥሩ በቅልጥፍናና በግልፅ ሊሠሩ እንደሚገባ አብራርተዋል። እንደዚህ ዓይነት አሠራሮችን በማስተካከል ሲንጋፖር፣ ሞርሽየስና የመሳሰሉ ሀገራት በግዥ ላይ የሚፈፀም ሙስናን መቀነስ የቻሉ ሀገራት እንደሆኑ አብራርተዋል።

  በዓለም ላይ በተቋም ደረጃ በማቋቋም ሁለት የግዢ ኤጀሲዎችን የሚጠቀሙ ሀገራት እንዳሉና ሀገራቱ ሁለት የግዢ ኤጀሲዎችን መጠቀማቸውም የጨረታ አማራጭ እንዲኖር፣ በመካከላቸው ፉክክርና ቀልጣፋ አሠራር እንዲሰፍን ያስችላል ተብሎ እንደሚገመት ጠቁመዋል።

  በተጨማሪም ከሁለቱ አንዱ ብልሹ አሠራር ቢታይባቸው አንዱ ተቋም ከሌላው ተቋም የአሠራር ልምድ በመውሰድ ጠንካራና ተወዳዳሪ ሆኖ ወደ ተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ ይመጣል ሲሉ አብራርተዋል።

  አያይዘውም በሀገሪቱ ለግዥ የሚውለውን በጀት ለታሰበለት እቅድ እንዲውል ለማድረግ የሚዲያዎች ድርሻ የጎላ እንደሆነ አብራርተዋል። ሚዲያዎች በጨረታ ወቅት ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆን ትክክል ያልሆኑ አሠራሮችን ለህዝብ በማጋለጥና ከህዝብና ከተዋናዮች የሚነሱ ቅሬታዎችን በሚዛዊነት ሽፋን በመስጠት የበኩላቸውን ከተወጡ በጀቱን ከምዝበራ መጠበቅ ይቻላል ብለዋል።

  በተጨማሪም ሚዲያዎች በጨረታ ሰአት ተደባብሰው የሚቀሩ ድምጾችን ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ሚናቸውን በመወጣት በጀትን ከአላስፈላጊ ምዝበራ የመታደግ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል።

  በተጨማሪም ፍርድ ቤቶች ነፃና ገለልተኛ በመሆን ሙስና ሲሠሩ በተገኙ አካላት ላይ አስተማሪና ከሙስና የሚያርቅ ከባድ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፍ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

  January 9, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የገና በዓልን አስመልክቶ ለክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የገና በዓልን አስመልክቶ ለክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈዋል።

  የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

  እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ! በክርስቲያኖች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የዕርቅ መጀመሪያ ተደርጎ ይታሰባል። ከልደቱ በፊት በፈጣሪና በፍጡር፣ በሰማይና በምድር፣ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ታላቅ የጠብ ግድግዳ ተገንብቶ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል። የልደት በዓል “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚለው የፈጣሪ ቃል በተግባር መፈጸም የጀመረበት፤ በአምላክና በሰው ልጆች መካከል ዕርቅ የተወጠነባት ዕለት ናት። ይህ በዓል መለያየት የጠፋበት፣ ኅብረትና አንድነት የጸናበት፤ መለኮትና ሥጋ፣ ህያውና ሟች፣ ዘላለማዊና ጊዜያዊ፣ ፈጣሪና ፍጡር፣ ሰማያዊና ምድራዊ፣ ምሉዕና ውሱን፣ በተዋሕዶ አንድ ሆነው አዲስ የምሥራች የተበሰረበት ነው። ክፉው በዘራው ዘር መለያየት ነግሦ፣ በሰማይና በምድር መካከል የማይሞላ ገደል ተፈጥሮ እንኖር ነበር። በጠብና በመለየት ምክንያት ኀዘንና ሰቆቃው በዝቶ በሰው ልጆች ታሪክ ጊዜው ዘመነ-ፍዳ ይሰኝ ነበር። የክርስቶስ መወለድ የራቀን አቅርቦ፣ የጠፋውን አግኝቶ፣ የፈረሰውን ገንብቶ፣ የፍዳውን ዘመን ወደ ምሕረት በመቀየር በዘላለማዊ ዕርቅ አንድ አደረገን። የልደቱ ብሥራት እረኞችን ከሜዳ፣ ሰብአ ሰገልን ከሩቅ ከምሥራቅ ወደ አንድ አምጥቷል፤ ሰዎችን ከምድር ጠርቷል፤ መላእክትን ከሰማይ አውርዷል። ዕለቱ የሰማይና የምድር ፍጡራንን በደስታ ሞልቶ በቤተልሔም ከተማ በአንድነት እንዲዘምሩ አድርጓል። ተራርቀው የሚኖሩትን አሰባስቦ በአንድነት እንዲዘምሩ ያደረጋቸው ጉዳይ ከትናንት ለየቅል ታሪካቸው ይልቅ የነገ የጋራ ተስፋቸው ብሩህ ሆኖ ስለታያቸው ነው። እረኞችና ሰብአ ሰገል በትናንት ታሪካቸው የሚገናኙት በጥቂት ነው። ሰዎችና መላእክት በትናንት ሕይወታቸው የሚገናኙት በጥቂት ነው። የነገው ታሪካቸው ግን አዲስ፣ በደቦ የሚሠሩት፣ በጋራ የሚኖሩት፣ በአንድ የሚወርሱትና በሙላት የሚኖሩበት ነው። ለዚህ ነው ዛሬ የሁሉንም ታሪክ ከክርስቶስ ልደት ጋር አስተሣሥረን የምንተርከው። ማን ነበርክ? ከሚለው ይልቅ ማን ለመሆን ትፈልጋለህ? የሚለው የአንድነታቸው መሠረት ነው። የነገውን በጋራ ከተጋሩት የትናንቱን በመተሳሰብ መቀበል አይቸግራቸውም። በነገው ላይ ከተግባቡ በትናንቱ ላይ መስማማት አይፈትናቸውም። በረቷ የክርስቶስ በረት፣ እረኞቹ የክርስቶስ እረኞች፣ ጠቢባኑ የክርስቶስ ጠቢባን፣ መላእክትም የክርስቶስ መላእክት፣ ቀኗም የክርስቶስ የልደት ቀን፣ ዘመኑም የክርስቶስ ዘመን ሆነዋል። ያኛው የጥንቱ የብሉይ፣ ይሄኛው ደግሞ አዲሱ የሐዲስ ኪዳንና ታሪክ ሆነ። የጥንቱ በአዲሱ ምክንያት ታወቀ፤ የቀድሞው በአሁኑ ምክንያት ከበረ፤ የትናንቱ በዛሬው ምክንያት ታደሰ። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ መለያየት የመጣው እንዲሁ አይደለም። ሆን ተብሎ ተሠርቶበት ነው። ክፉው ሆን ብሎ የልዩነትን ዘር ዘርቶ፣ የልዩነትን እሾህ አብቅሎ፣ የጠላትነትን ፍሬ እንዲያፈራ አድርጓል። ልዩነቱም ከመለያየት አልፎ ወደ ጠላትነት እንዲሻገር ሠርቷል። ጠላትነቱም አዳምን ከገነት አፈናቅሏል። አቤልን በቃየል አስገድሏል። በምድር እሾህና አሜከላ አብቅሏል። የጥፋት ውኃን እልቂት አስከትሏል። ጦርነትና ግጭትን አትርፏል። በዚህ ሁሉ ጠላት እንጂ ማንም አልተጠቀመም። አንድነትም የመጣው በብዙ ልፋትና መሥዕዋትነት እንጂ እንዲሁ በቀላሉ አይደለም። ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ፣ ከልደት እስከ ስቅለት፣ ከበረት እስከ ዕርገት ዋጋ ተከፍሎበት ነው። ዛሬ የምናከብረው ልደት ያስፈለገውም መለያየት ብቻ ሳይሆን በመካከላቸው ጠላትነት እንዲሰፍን የተሠራባቸውን ወገኖች አንድ ለማድረግ ነው። ይህን የወገኖች አንድነት ፍለጋ በሰማይ ያሉት ወደ ታች ወርደዋል። እነርሱ ይሄንን እንደ ውርደትም እንደ ውለታም አልቆጠሩትም። በምሥራቅ ያሉት ወደ ምዕራብ ሲመጡ እንደ ድካም አላዩትም። ሁሉም ሰጥቷል፤ ሁሉም ጎድሎበታል። ሁሉም አግኝቷል፤ ሁሉም ትቷል። ሁሉም ከፍ ብሏል፤ ሁሉም ዝቅ ብሏል። ሁሉንም በሁሉ ሆኖ የሞላውና ያሟላው የተወለደው ከሰማይ ወርዶ በግርግም የተወለደው ክርስቶስ ነው። ኢትዮጵያውያን የነገዋን ኢትዮጵያ የተሻለች ለማድረግ ከዚህ የልደት ታሪክ ብዙ ትምህርት ብንወስድ ይጠቅመናል። ዛሬ እዚህም እዚያም የምናየው የመለያየትና የመጠፋፋት አባዜ የባህሪያችን አይደለም። የማናችንም ማንነት መገለጫ አይደለም። ይህ የተዘራብን ክፉ ዘር ውጤት ነው። የውስጥ የውጭ ባዳ አንድ ሆነው የዘሩብን ዘር ውጤት ነው። ያለንበት ዘመን ዘሩ የተዘራበት ጊዜ አይደለም። አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ይመስላቸዋል። ይህ ወቅት ዘሩ ጎምርቶ አፍርቶ ያየንበት ወቅት ነው። የታኅሣሥ መከር የሚዘራው በሐምሌ ነው። አንዳንድ ሰዎች ትናንትኮ እንዲህ ያለ ነገር አልነበረም ይላሉ። ዘሩ ከምድር በታች በመብቀል ላይ ስለነበረ አላስተዋልነውም። ሰርዶው አድጎ እግር መጥለፍ ስላልጀመረ አልተቸገርንም። እንክርዳዱ በዝቶ ራስ ማዞር ስላልጀመረ አልታወቀንም። እሾሁ አፍጥጦ ሰውነት መቧጠጥ ስላልጀመረ አልለየነውም። አሜከላው በርክቶ እግር ለማድማት ስላልደረሰ ከቁብ አልቆጠርነውም። እንጂ ክፉው ዘርስ እየበቀለ ነበረ። ወደ አዲሱ ዘመን፣ ወደ አዲሱ ብርሃን እንምጣ። ወደ አዲሱ ማንነት፣ ወደ አዲሱ ምእራፍ እንምጣ። አዲስ የጋራ ታሪክ ስንሠራ፤ የትናንቱ ታሪክ ያግባባናል። አዲስ መንገድ ስንጀምር የትናንቱ መንገድ አያጣላንም። አዲስ ዘመን ስንወጥን ያለፈው ዘመን አያለያየንም። አዲስ ዓላማ አንግበን ከተነሣን፣ የትናንቱ ዓላማ አያጨቃጭቀንም። የአንዳችን ጠላት ሆኖ የሌላችን ወዳጅ ሊሆን የሚችል የለም። አንዳችን ታምመን ሌላችን ጤነኛ መሆን አይታሰብም። አንዳችን ጎድሎብን ሌላችን ሙሉ ልንሆን አንችልም። አንዳችን ተከፍተን ሌላችን ደስተኛነትን ማጣጣም አንችልም። የሰው ልጅ ከገነት መውጣቱ የመላእክትን ደስታ ነጥቋል። የእንስሳትን ምቾት አጉድሏል። የምድርንና የሰማይን ክብር ገፍፏል። ገነትን ያለ ሰው አስቀርቷል። የሰው ልጅ ጠላት የሆነው ዲያብሎስ ለጊዜው በክፋቱ ስኬት በደስታ ፈንጥዟል። የሁላችንም ደስታ ሙሉ መሆን የቻለው ለሁሉም የሚሆነው ክርስቶስ ሲወለድ ነው። የጠላታችን ዓላማ አንዳችንን ጠቅሞ ሌላችንን መጉዳት ሳይሆን ሁላችንንም ማጥፋት ነው። ዲያብሎስ መጀመሪያ አዳምና ሔዋንን አካሰሰ። ቀጥሎ ሰውን ከፈጣሪው ነጣጠለ። ከዚያ ሰውን ከመኖሪያው ከገነት አፈናቀለ። እሾህና አሜከላ እንዲበቅል አድርጎ ሰውንና ምድርን አቆራረጠ። ቃየልን በአቤል ላይ አስነስቶ አስገደለው። ጠላታችን አንዱን ሕዝብ ከሌላው በማጋጨት አይቆምም፤ አንዱንም ሕዝብ እርስ በርሱም ያባላዋል። ክልልን ከክልል፣ ዞንን ከዞን፣ ወረዳን ከወረዳ፣ ጎጥን ከጎጥ፣ ቤተሰብን ከቤተሰብ፣ ባልን ከሚስት፣ ልጆችን ከወላጆች እያባላ ዓለምን ሁሉ የግጭትና የጠብ ዐውድማ ማድረግ ነው ምኞቱ። ስለዚህ ቆም ብለን እናስብ። መንገዱ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የሚበጅ፣ ለሁላችንም በቅቶ የሚተርፍ፣ አዲስ ማንነትን ይዘን እንደገና መወለድ ነው። ታሪክ ማለፉ አይቀርም። ታሪክ መለወጡም አይቀርም። ቁም ነገሩ የታሪክ ተከሳሽና ተወቃሽ ወይንስ ተዘካሪና ተሞጋሽ እንሆናለን? የሚለው ነው። ከሩቅ መጥተው መሲኹን እንደተገናኙት ጠቢባን ሰብአ ሰገል ታሪክ እንሠራለን ወይስ እንደ ሄሮድስ ታሪክን ለማጥፋት በንጽሐን ላይ ሰይፍ እናነሣለን? የሚለው ነው። እንደ ቅዱሳን መላእክቱ ለአዲስ ታሪክ አዲስ የምሥራች እናበሥራለን ወይስ እንደ ዘመኑ የአይሁድ ልሂቃን ባለፈው ታሪክ ላይ ተተክለን የቀረበልንን ዕድል በንቀት እንገፋለን? የሚለው ነው። የእነዚህን ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ማግኘት፣ ኢትዮጵያ በአዲስ ልደት መንገድ እየተጓዘች የጌታችንንና የመድኃኒታችንን ልደት እንድታከብር ባለ በቂ ምክንያት ያደርጋታል። መልካም የልደት በዓል ይሁንልን! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

  January 10, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የትግራይን ክልል ለማረጋጋትና መልሶ ለማቋቋም አስተዋጽኦ ላበረከቱ አመራሮች የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር ተከናወነ በትግራይ ክልል ህዝቡን በማረጋጋትና የመሰረተ ልማት ተቋማትን መልሶ በመገንባት አገልግሎት ለማስጀመር ሲሰሩ ለነበሩ አመራሮች የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ መርሃ ግብሩ “ሰላም የማይታጠፍ የብልጽግና አቋም” በሚል ርእስ ነው የተካሄደው፡፡ በኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ግጭት ተከትሎ መንግስት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የአመራር ስምሪት በመስጠት መረጋጋት እንዲፈጠርና መሰረተ ልማቶች መልሰው እንዲገነቡ ሲያደረግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ለትግራይ ክልል ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም መልሶ ግንባታ የአመራርና ባለሙያ ስምሪት ተደርጎ የሰብዓዊ አቅርቦት፣ ተፈናቃዮችን የመመለስ፣ መሰረተ ልማት የመገንባትና አገልግሎቶችን መልሶ የማስጀመር ስራ ተከናውኗል፡፡ በዚህም በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲያገኙ፤ እንደ መብራት፣ መንገድ፣ ቴሌኮሙኒኬሽና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ጥገና ተደርጎላቸው ዳግም አገልግሎት እንዲጀምሩ ላደረጉ አካላት እውቅና ተሰጥቷል፡፡ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ግጭት በነበረበት ወቅት የትግራይን ህዝብ ችግር ለመፍታት ቁርጠኛ በመሆን ወደ ስፍራው ያቀኑ አመራሮች የኢትዮጵያ ጀግኖች ናቸው፡፡ አመራሮቹ መንግስትና ብልጽግና ፓርቲ የጣለባቸውን ሃላፊነት በመቀበል ለመንግስትና ለትግራይ ህዝብ የመፍትሔ አካል በመሆን አኩሪ ታሪክ ፈጽመዋል ብለዋል፡፡ የአመራር ስምሪት የተሰጠው በተለይ የትግራይ ህዝብ የመንግስትን ድጋፍ በሚሻበት ወቅት እንደነበር የገለጹት ምክትል ፕሬዘዳንቱ፤ ህዝቡ ሰብዓዊ እርዳታ፣ የመሰረተ ልማትና ህዝባዊ አገልግሎት እንዲያገኝ አድርገዋል ብለዋል፡፡ በመሆኑም የትግራይን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ አኩሪ ተግባር መፈጸማቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህን አገርና ህዝብን የሚያኮራ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ብርቅዬ አመራሮች ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረብ ይገባል ብለዋል፡፡ የትግራይን ክልል በማረጋጋትና መልሶ በማቋቋም ሲያስተባበሩ የነበሩት አቶ በዙ ዋቅቤካና አቶ አዝመራ አንዴሞ የተጣለባቸውን ሃላፊነት በመወጣት ህዝቡ በመንግስት ለይ የነበረውን እምነት ከፍ እንዲል ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያዎቹ ቀናት በህዝቡ ዘንድ ፍርሃትና ስጋት ይስተዋል እንደነበር የገለጹት አስተባባሪዎቹ፤ በሂደት በመንግስት ላይ ያለው እምነት እየጎለበት በሰላምና መረጋጋት እንዲሁም በመልሶ ግንባታ ከጎናችን ተሰልፏል ብለዋል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የተረጋጋና ህዝቡም መደበኛ ህይወት የጀመረበት አውድ መፈጠሩን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

  January 5, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • ለመጪው የገና በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በቅንጅት እየተሰራ ነው--የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለመጪው የገና በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ለገና በዓል የምርት አቅርቦትን በተመለከተ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን፣ የስኳር ኮርፖሬሽን እና የንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለፍጆታ የሚውሉ ምርቶች ፍላጎት ስለሚጨምር የአቅርቦት ክፍተት እንዳይፈጠርና ህብረተሰቡ ላልተገባ ዋጋ እንዳይጋለጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል፡፡ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ንግድና ሸማቾች ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ መስከረም ባህሩ አስፈላጊ ቅድመ-ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የግብርና ምርቶች፣ የእንስሳት ውጤቶች እና የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች እቅርቦት እጥረት እንዳይኖርና ማህበረሰቡ ላልተገባ ዋጋ ጭማሪ እንዳይጋለጥ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተብራርቷል፡፡ የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አብዲ ሙመድ በበኩላቸው በአዲስ አበባ 137 ሸማች ማህበራት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶችን በማቅረብ ኤግዚቢሽንና ባዛር ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡ በቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት ምርቶች እየቀረቡ በመሆኑ ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚፈልገውን ምርት እንዲሸምትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት የምርት እጥረት እንደሌለ የገለፁት ምክትል ኮሚሽነሩ ሽንኩርት ከ15-22፣ ቲማቲም ከ15-23፣ ጤፍ 44-49፣ ስንዴ ዱቄት በኪሎ 55፣ በቆሎ ዱቄት 33 እንዲሁም ዶሮ ከ350-500 ብር በህብረት ስራ ኮሚሽን በኩል እየቀረቡ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ እንዲሸምት ምክትል ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 161 ሺህ 200 ኩንታል በላይ የግብርና ምርቶች ወደ ገበያ መቅረባቸውን የገለፁት አቶ አብዲ ከ225 በላይ የህብረት ስራ ማህበራት ልኳንዳ ቤቶች በዓሉን በማስመልከት በተመጣጣኝ ዋጋ ስጋ እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል የስኳር ኮርፖሬሽን ማርኬቲንግ ክፍል ኃላፊ አቶ ታፈሰ አሰፋ በበኩላቸው በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከ100 ሺህ አስከ 150ሺህ ኩንታል ስኳር በዓሉን ምክንያት በማድረግ በመላ ሀገሪቱ እየተሰራጨ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ30ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር እየተሰራጨ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ቀፀላ ሸዋረጋ በበኩላቸው በሁለት የመንግስት የልማት ድርጅቶች በኩል 43 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዥ መፈፀሙንና ከዚህ ውስጥ 5 ሚሊዮን ሊትር እየተጓጓዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ባለ3 ሊትር ዘይት 314፣ ባለ 5 ሊትር 509፣ እንዲሁም ባለ 20 ሊትር በ2001ብር ለገበያ የቀረበ በመሆኑ ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ በዓሉን እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል፡፡

  January 2, 2023

  | ሀገራዊ ዜና

 • የጤና አገልግሎትን ለሁሉም ለማዳረስ የጤና መድህን መርሐግብርን የበለጠ ተደራሽ ማድረግ ይገባል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

  የጤና አገልግሎትን ለሁሉም ለማዳረስ የጤና መድህን መርሐግብርን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

  የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ብሔራዊ ምክር ቤት ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ እና የጤና መድህን ትግበራ 10ኛ ዓመት ክብረ በዓል መርሀ-ግብር እየተካሔደ ነው።

  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መንግስት የዜጎች የኑሮና የጤና ሁኔታን ለማሻሻልና ከድህነት ለማውጣት በርካታ እስትራቴጂዎችን ቀርጾ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

  በዚህም የማህበረሰብ አቀፍ የጤና አገልግሎት መርሀ ግብር አብዛኛውን አርሶ አደር የሕብረተሰብ ክፍል የሚያቅፍ ወሳኝ የሆነ የጤና አገልገሎት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

  የጤና መድህን ስርዓት በሌሎች አገሮች ያለውን ትግበራ በማንሳት በኢትዮጵያም በፍትሀዊነትና ተደራሽነት የበለጸገና አገሩን የሚወድ፣ ተስፋ የሰነቀ ማህበረሰብን ለመገንባት የጤና መድህን አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።

  ባለፋት አስር አመታት የጤና መድህንን ተግባራዊ በማድረግ ማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ የተገኙ ስኬቶች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል።

  በቀጣይ ሁሉን አቀፍ የጤና መድህንን ተደራሽ ለማድረግ የበለጠ መረባረብ እንደሚገባ አቶ ደመቀ አሳስበዋል።

  የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የጤና መድህን ሽፍን ቁልፍ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

  አገልግሎቱ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በ894 ወረዳዎች ተግባራዊ በማድረግ 45 ሚሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል።

  በመርሐግብሩ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን የጤና መድህን የ10 አመታት ጉዞን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሏል።

  December 31, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ስራ አቁመው የነበሩ የስኳር ፋብሪካዎች ምርት ማምረት በመጀመራቸው የስኳር አቅርቦት እጥረት ይቀረፋል

  ስራ አቁመው የነበሩ አራት የስኳር ፋብሪካዎች ምርት ማምረት በመጀመራቸው ከመጪው ጥር ወር ጀምሮ የስኳር አቅርቦት እጥረት እንደሚፈታ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።

  በጸጥታ ችግርና በመለዋወጫ እጥረት ምክንያት የስኳር ፋብሪካዎች ማምረት በማቆማቸው በውጪ ምንዛሪ እጥረት ከውጪ ተገዝቶ ባለመግባቱ ላለፉት ጥቂት ወራት የስኳር እጥረት መከሰቱ ይታወሳል፡፡

  ችግሩን ለመቅረፍ በተደረገው ርብርብም በአሁኑ ሰዓት አራት የስኳር ፋብሪካዎች ምርት ማምረት ጀምረዋል፡፡

  ወንጅ፣ ኦሞ 2 እና 3 እንዲሁም ፊንጫ ስኳር ፋብሪካዎች ምርት ማምረት ጀምረዋል።

  ታህሳስ 29/2015 ለሚከበረው የገና በዓል ክልሎች፣ከተማ አስተዳደሮችና ተቋማት የኮታቸውን 25 በመቶ ስኳር ማግኘት ይችላሉ።

  የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የመሰረታዊ ሸቀጥ አቅርቦትና ስርጭትን ከአምራቾች፣ አቅራቢዎችና ባለድርሻዎች ጋር ገምግሟል።

  በሀገር ውስጥ ከሚመረተው በተጨማሪ ከውጪ የሚገባውም ግዥ የተፈጸመ በመሆኑ ከመጪው ጥር ወር ጀምሮ የስርጭቱን ኮታ 100 በመቶ ማዳረስ እንደሚቻልና አሁን የተስተዋለው የአቅርቦትና ፍላጎት ክፍተት እንደሚቀረፍ ተገልጸዋል።

  የስኳር ኮርፖሬሽን ስኳርን ከሀገር ውስጥ ምርት እና ከውጪ በማስገባት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ያቀርባል፡፡

  December 31, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ''በአገረ-መንግስት ግንባታ የምሁራን ሚና'' በሚል ርዕስ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

  ከታሕሳስ 21-22/2015 ዓ.ም ባሉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ የምክክር መድረክ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

  በመድረኩ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ብናልፍ አንዷለም የመክፈቻ ንግግር በማድረግ መርሃ ግብሩን አስጀምረዋል።

  የምክክር መድረኩ ምሁራን በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና የጋራ ጉዳዮችን በማጉላት ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ምክረ ሀሳብ የሚያነሱበት እና የሚወያዩበት መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

  በሀገር ግንባታ ላይ የምሁራን ተሳትፎ የላቀ ሚና አለው ያሉት አቶ ብናልፍ ከውይይት መድረኩ ሀገርን የሚጠቅሙ በርካታ ሀሳቦች እንደሚነሱ ይጠበቃል ብለዋል።

  ምሁራን በሀገረ-መንግሥት ግንባታ ላይ የጎላ ሚና ሊኖራቸው ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎችም ሀገርን የሚያንጽ ሀሳብ በማንሳት የዳበረ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

  በመድረኩ ለውይይት መነሻ ሀሳብ እንዲሆን የተዘጋጀ ሰነድ በወላይታ ዞን አስተዳዳሪ እና የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባል በሆኑት አቶ አክሊሉ ለማ እየቀረበ ይገኛል።

  December 30, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የሰላም ሒደቱ ለማመንታት እድል በማይሰጥ መልኩ በፍጥነት ወደ ፊት እየሔደ ነው--ዶክተር አብርሃም በላይ

  የሰላም ሒደቱ ለማመንታት እድል በማይሰጥ መልኩ ሶስት እርምጃ ወደፊት እየሔደና አዎንታዊ ምላሽ እያገኘ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ።

  ዶክተር አብርሃም በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የሰላም እርምጃ ልምምድ የወጣ ተግባር መፈጸምን ይጠይቃል።

  “አሁንም ከባድ ውጣ ውረድና በልዩ የመሪነት ብቃት ታልፎ፣ የሰላም ሒደቱ ለማመንታት እድል በማይሰጥ መልኩ በፍጥነት ሶስት እርምጃ ወደፊት እየሄደና አዎንታዊ ምላሽ እየያዘ ይገኛል” ብለዋል።

  “የሰላም አምባሳደር የልኡካን ቡድንም የፈፀመው የሰላም ግንባር ጀግንነት በመላው ህዝባችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ” በማለት ሰላምን ለሃገራችን ተመኝተዋል።

  December 28, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ መቀሌ መደበኛ በረራ ይጀምራል

  ከአዲስ አበባ መቀሌ ከነገ ጀምሮ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ የአየር ትራንስፖርት በነገው ዕለት ይጀምራል ፡፡

  በፌዴራል መንግስቱና በህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የአቬየሽን ሰራተኞች ወደ መቀሌ አቅንተው የመቀሌ አየር መንገድ ለበረራ ምቹ ሁኔታ ላይ መሆኑን አረጋግጠዋልም ነው ያሉት።

  በመሆኑም ነገ በሚጀምረው በረራ በቀን አንድ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ፥ የደንበኞቹ ፍላጎትን መሰረት በማድረግም የበረራው ቁጥሩ ከፍ ሊል የሚችልበትን ሁኔታ እንደሚፈጠርም ነው ዋና ስራ አሰፈጻሚው የገለፁት፡፡

  ተቋርጦ የነበረውን የበረራ እንቅስቃሴ በሁሉም የትግራይ ክልል የበረራ መዳረሻዎች ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ዋና ስራ አስፈጻሚው አንስተዋል፡፡

  ነገ የሚጀምረው በረራም ከሌላው ወገኑ ጋር ግንኙነቱ ተቋርጦ የነበረውን የትግራይ ህዝብ ዳግም እንዲገናኝ ለማድረግ ትልቅ እድል የሚፈጥር እንደሆነም ነው የተናገሩት።

  ከዚህ ባለፈ የሸቀጦችና ሌሎች ተደራሽ የመሆን እጥረት የነበረባቸውን የሰብዓዊ ድጋፎችን በበቂ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

  ይህም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ከፍ ማድረግ የሚያስችል እንቅስቃሴ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው በመግለጫቸው ገልፀዋል።

  December 27, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የፌዴራል መንግስት ልዑካን ቡድን አባላት በመቀሌ ያደረጉት ጉብኝት የግጭት ግንብን በማፍረስ ሰላምን ለመገንባት መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ

  የፌዴራል መንግስት ልዑካን በመቀሌ ያደረጉት ጉብኝት የግጭትን ግንብ በማፍረስ ሰላምን ለመገንባት መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ገለፁ።

   ሚኒስትር ዴኤታዋ ዛሬ የፌደራል መንግስትና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አመራሮች ከመቀሌ ነዋሪ ለተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

  የመንግስት አመራሮችና የተቋማት ተወካዮች ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በትግራይ ክልል የተጀመሩ የመልሶ ግንባታ ሥራዎችን ለማፋጠን መግባባት ላይ መድረሳቸውን ጠቅሰዋል።

  የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የፌዴራል መንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ውሳኔ ወደ መቀሌ መጥተው ከህዝቡ ጋር መወያየታቸው ድፍረት የተሞላበትና ተገቢ ውሳኔ ነው ብለዋል።

  የሰላም ስምምነቱን አተገባበር ናይሮቢ ላይ ገምግመን በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑ ላይ መግባባት ላይ ደርሰን ነበር ሲሉም ገልፀዋል።

  የፌዴራል መንግስት ልዑካን ቡድን ዛሬ በመቀሌ ያደረገው ጉብኝትም የመንግስትን ቁርጠኝነት ያየንበት ትክክለኛ ውሳኔ ነው ሲሉ በመጥቀስ።

  የአመራሮቹ ተግባር ሰላማዊው መፍትሔ ጫፍ እንዲደርስ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

  ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊትና አቶ ጌታቸው የትግራይ ክልል ህዝብ ያገኘው ሰላም ዘላቂ እንዲሆን እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

  ከሶስተኛ ወገን ነፃ በሆነ መንገድ የተጀመሩ ፖለቲካዊ ውይይቶችና ቅርርቦች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል።

  የፖለቲካ ልዩነታችንን በውይይት እየፈታን ግጭትን በዘላቂነት ማስወገድ ይገባል ብለዋል።

  በዚህም ህዝቡ ወደተሟላ የልማት ስራው እንዲመለስ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ በመግለፅ።

  December 27, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ዛሬ ወደ መቀሌ ያቀናው የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከትግራይ ክልል አመራሮችና ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያየ

  ዛሬ ወደ መቀሌ ያቀናው የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከትግራይ ክልል አመራሮችና ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያየ፡፡

  በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የተመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ዛሬ ወደ መቀሌ አቅንቷል፡፡

  ልዑኩ ከትግራይ ክልል አመራሮች እና ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት÷ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት መንግስት በእሱ በኩል የሚጠበቁበትን ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

  የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች የመሰረተ ልማት አገልግሎቶች መጀመራቸው ይታወቃል፡፡

  ይህን የመሰረተ ልማት አገልግሎት በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለማስጀመር ያስችል ዘንድ ዛሬ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ኃላፊዎች በመቀሌ ተገኝተው ከክልሉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

  የኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ መብራት አገልግሎት፣ የመንገዶች ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የሌሎች ተቋማት ኃላፊዎች መሰረተ ልማቶቹን ማስጀመር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያሉበትን ደረጃ ገልፀዋል።

  በቀጣይ ያልተጀመሩ የመሰረተ ልማት አገልግሎቶችን በአጭር ጊዜ ለማስጀመር እንደሚሠራ አብራርተዋል፡፡

  በተለይም ኢትዮ ቴሌኮም፣ ባንክ፣ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና አየር መንገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመቀሌና አካባቢው ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ ላይ እንደሆኑ ገልፀዋል።

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተወሰኑ ሙያተኞችን ሁኔታውን እንዲያመቻቹ መቀሌ እንዲቆዩ አድርጓል።

  ልዑኩ ከክልሉ አመራሮች ባለፈ ከተወከሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የተወያየ ሲሆን፥ ነዋሪዎች የመጣው ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ያልተጀመሩ መሰረተ ልማቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ጠይቀዋል።

  ከፌዴራል መንግስት ልዑክ ወደ መቀሌ መምጣቱም መንግስት ለሰላም ስምምነቱ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

  እስካሁን በነበረው ሂደት የአፍሪካ ጎረቤት ሀገራት ለማስታረቅ ትልቅ ስራ ሰርተዋል፣ከአሁን በሁዋላ ግን እኛው ተገናኝተን መምከር አለብን ለዚህም ከፍተኛ ልዑክ መቀሌ ተገኝቷል ብለዋል።

  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በርካታ ለውጦች መኖራቸውን ጠቅሰው፥ ይህን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን ለማሳየት ልዑኩ መቀሌ መገኘቱን አስረድተዋል።

  ሰላም ለሁሉም ያስፈልጋል የሰላም አስፈላጊነትን ባለፉት ሁለት አመት አይተናል የእናቶች ሞት፣ ለቅሶ ይበቃል፣ የመሰረተ ልማት ውድመቶች ይበቃል ህዝባችን እረፍት እንዲያገኝ ማድረግ ይኖርብናልም ነው ያሉት።

  ከዚህ በኋላ በስምምነቱ መሰረት የተደረሱባቸውን ጉዳዮች እየተነጋገሩ መፍታት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

  የህወሓት ሊቀ መንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል በበኩላቸው፥ “ያለሶስተኛ ወገን እንደዚህ እኛው ችግሮቻችንን ለመፍታት መገናኘታችን ትልቅ እርምጃ ነው” ብለዋል።

  አሁን ላይ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የተጀመረው የሰላም ሂደት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው ሲሉም ይበልጥ የተቸገረውን ህዝብ ለመድረስ ስራዎች በፍጥነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

  December 26, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ አቀና።

  የየልኡካንቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ ነው።

  የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ታምኖበታል። በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትም ተካትተዋል።

  #የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

  December 26, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ሀገሪቷ ከምትፈተንባቸው ችግሮች ውስጥ የጎላ ድርሻ የሚይዘው ህገ ወጥ የመሳሪያ ፣ የእጽ እና ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጠቃሽ ነው-አቶ ደመቀ መኮንን የኢፌዴሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር

  ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና በሰዎች መነገድን መከላከል ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በደቡብ ክልል ሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል

  በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደገለጹት በለውጥ ሂደት ፈተናዎች የሚጠበቁ ቢሆንም ችግርን መቀነስ እና ውጤትን ማበልጸግ ደግሞ የመንግስት እና የህዝብ ሁነኛ ትብብርና የጋራ ዘመቻ ይጠይቃል ብለዋል።

  የትኛውንም ያህል ስኬት ብናስመዘግብም የዜጎች ሰቆቃና ፈተና የዜጎች ደህንነት አለመከበር ካለ ስኬቱ ብቻውን ሙሉ አይሆንም ሲሉም አብራርተዋል። ሀገሪቷ ከምትፈተንባቸው ችግሮች ውስጥ የጎላ ድርሻ የሚይዘው ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር፣ህገወጥ የእጽ እና የሰዎች ዝውውር ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

  ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ደግሞ እጅግ ጭካኔ የተመላበት ዘግናኝ ድርጊት መሆኑን ተናግረዋል።

  ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር በስፋት ከሚካሔድባቸው አካባቢዎች የሀዲያ ዞን፣የከምባታ ጠምባሮ እና አጎራባች አካባቢዎች መሆናቸውንም ም/ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውስተዋል።

  በሰሜን ምስራቅ በወሎ እና በኦሮሚያ በተወሰኑ አካባቢዎችም ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እንደሚካሔድም ጠቁመዋል።

  ችግሩን ለመፍታትም የተቀናጀ ማህበረሰባዊ ንቅናቄ ያስፈልጋል ሲሉም አስረድተዋል።

  የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ከሚካሔድባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ውስጥ የደቡብ ክልል ተጠቃሽ ነው ብለዋል።በዚህም በርካታ ዜጎች ለሞት ለአካል ጉዳትና ለእስር መጋለጣቸውን ጠቁመዋል።

  በክልሉ በህገ ወጥ ደላሎች አማካኝነት ወጣቶችን አሳዛኝ በሆነ መልኩ ከሀገር እንዲወጡ እያደረጉ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራ እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል።

  በክልሉ ችግሩ በስፋት በሚስተዋልባቸው 6 ዞኖች ከ1ሺ በላይ ቀበሌያት እና ትምህርት ቤቶችን በመለየት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ማከናወን ቢቻልም በሚፈለገው ልክ ለውጥ ማምጣት ግን አልተቻለም ብለዋል።

  እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ በመተላለፊያ መንገዶች በተደረገ ክትትል በአንድ አመት ብቻ ከ3ሺ በላይ ወጣቶች በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሲጓዙ ተይዘው ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅቶች ጋር በመተባበር እና በጊዜያዊ መጠለያዎች ላይ በማቆየት እንዲሁም ልዩ ልዩ ድጋፍ በማድረግ ወደየ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ መደረጉንም አስረድተዋል።

  ከዚህ ቁጥር በሚልቅ መልኩ በቁጥጥር ያልተደረሰባቸው ዜጎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።

  የኢፌዲሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሳቢያ በዚህ ዘመን የሰውልጅ ወጥቶ የሚቀርበት፣ክብርና ስብዕናው የሚዋረድበት በባርነት ቀንበር ስር የሚሆንበት አጋጣሚ መፈጠሩን በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶችን ዋቢ አድርገዋል።

  በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ምክንያት የሰው ልጆች ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ በማለፊ አለም አቀፍ ስጋት ሆኖ መቆየቱንም ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

  ሀገራችን ኢትዮጵያም የዚህ ችግር ሰለባ በመሆኗ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በዜጎቿ ላይ ያስከተለው የሞት፣የአካል አደጋና የመብት ጥሰት በቁጭት ሊያሳስበን ይገባል ብለዋል።

  ይህ አስከፊ ድርጊት ጸጋና በረከት በታደለች ሀገር ሊከሰት ትንደማይገባ በመገንዘብ ዜጎች በሀገር ላይ ሰርቶ መለወጥ እንዲችሉ የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

  ዜጎች በውጭ ሀገር መስራት የሚፈልጉ ከሆነ ፍላጎትና ብቃታቸውን ባማከለ ሁኔታ መብታቸው ተጠብቆ በህጋዊ መንገድ መሰማራት የሚችሉበት መንገድ መንግስት መዘርጋቱንም አስረድተዋል። ምንጭ፦ የደቡብ ክልል መ/ኮ/ ቢሮ ነው።

  December 24, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በድንበር አካባቢ ያለውን ሰላም ለማስቀጠል ቀጠናውን በንግድ፣ በመንገድና በቱሪዝም ማስተሳሰር ይገባል-አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ

  በአጎራባች ሀገራት ድንበር አካባቢ ያለውን ሰላም ለማስቀጠል ቀጠናውን በንግድ፣ በመንገድ መሰረተ ልማት እና በቱሪዝም እና በሌሎች ዘላቂ የልማት ስራዎች በማስተሳሰር ህዝቦችን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ሲሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ።

  የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተሳተፉበት የ”ኤኩሞሞር ፌስቲቫል” ኢትዮጵያ በውጭ ዲፕሎማሲዋ ለጀመረችው ቀጠናዊ ትስስር ስኬታማነት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተገልጿል።

  “ኤኩሞሞር-ለቀጠናዊ ትስስር” በሚል መሪ ሀሳብ የኡጋንዳ፣ ኬኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች የተሳተፉበት የባህል፣ የቱሪዝም እና የሰላም ፌስቲቫል በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቶም ወረዳ ካንጋቴን ከተማ ተካሂዷል።

  በክብረ በዓሉ ላይ የታደሙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደገለጹት፣ የኤኩሞሞር ፌስቲቫል ዘላቂ ሰላምና ቀጠናዊ ትስስርን በማጠናከር በኩል ሚናው የላቀ ነው።

  ባለፉት ሁለት ዓመታት በድንበር አካባቢ የታየው ሰላምና የህዝብ ለህዝብ ቅርርብ የኤኩሞሞር ፌስቲቫል ያመጣው ተጨባጭ ለውጥ ማሳያ መሆኑንም አንስተዋል።

  የደቡብ ክልል ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ሰርመሎ በበኩላቸው፣ የ”ኤኩሞሞር ፌስቲቫል” ኢትዮጵያ በውጭ ዲፕሎማሲ ለጀመረችው ቀጠናዊ ትስስር ስኬታማነት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

  ፌስቲቫሉ ካለው አዎንታዊ አበርክቶ አኳያ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም በተሞክሮነት ሊወሰድ እንደሚገባ ጠቁመው፣ “በዓሉ እየሰፋ እንዲሄድ ክልሉ ድጋፉን ያጠናክራል” ብለዋል።

  “ኤኩሞሞር የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ትስስር የሚያጠናክር እሴት ያለው ክብረ በዓል ነው” ያሉት ደግሞ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ናቸው።

  ክብረ በዓሉ ጎልብቶ ለቀጠናው ትስስርና ለቱሪስት መስህብነት እንዲውል ብሎም ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን እንደመንግስት ተገቢ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።

  በድንበር አካባቢ የተገኘው ሰላም ከአጎራባች አገራት ህዝቦች ጋር በጋራ በመሆን የተሰራው ሥራ ውጤት መሆኑን የገለጹት ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ ናቸው።

  አሁን ያለውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ አስተዳደሩ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመው፣ በተለይም ቀጠናውን የሰላም፣ የልማት እና የቱሪዝም መስህብ ማዕከል ለማድረግ በተቀናጀ መንገድ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

  የፌዴራል መንግስት ከጎረቤት አገራት መንግስታት ጋር በመሆን በድንበር አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦችን በንግድ እና በመንገድ መሠረተ-ልማት ለማስተሳሰር የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አስተዳዳሪው ጠይቀዋል።

  “ኤኩሞሞር ለቀጠናዊ ትስስር” በሚል መሪ ሀሳብ በተከበረው የሰላም ፌስቲቫል ላይ የክልልና የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎች፣ ከምዕራብ ኢትዮጵያና ከደቡብ ክልል የመጡ የክብር እንግዶች በበዓሉ ላይ ታድመዋል።

  በተጨማሪም ከአጎራባች አገራት ከኡጋንዳ-ካራሞጃንግ፣ ከኬኒያ-ቱርካና እና ከደቡብ ሱዳን-ቶፖሳና ጂዬ በመባል የሚጠሩና ከኛንጋቶም ማህበረሰብ ጋር ተመሳሳይ ቋንቋ ተጋሪ የሆኑና ተቀራራቢ ባህል ያላቸው ማህበረሰቦችና የቀጠናው አስተዳዳሪዎች ታድመዋል።

  የኤኩሞሞር በዓል በቀጠናው ህዝቦች መካከል አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ በድምቀት ተከብሯል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

  December 24, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው በለውጥና ልማት ሥራዎች ላይ ካተኮርን ኢትዮጵያን መለወጥ ስለሚቻል በንፁህ ልቦና ለተሻለ ሥራ መዘጋጀት ያስፈልጋል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ።

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ በግል ባለሀብት የለማውን የእርሻ ኢንቨስትመንት በጎበኙበት ወቅት ነው።

  የዛሬ ሁለት ዓመት በረሃ የነበረውን ቦታ ያለሙ ባለሀብቶች ሊመሰገኑ ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ተሞክሮ በማስፋፋት ኢትዮጵያን ለመቀየር ሌት ተቀን መሥራት አለብን ብለዋል።

  የስንዴ ልማት፣ አረንጓዴ ልማትና የፍራፍሬ ልማት በአጭር ጊዜ የተሳኩ ልማታዊ ሥራዎች መሆናቸውን ገልጸው ሌሎች ዕቅዶችም በዚህ ልክ ውጤታማ እንዲሆኑ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

  በጉብኝቱ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ የሠላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም፣ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የውጭ ጉዳይ አማካሪ አቶ አዲሱ አረጋ እና የሚድሮክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ተገኝተዋል።

  December 24, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በአንድ ወቅት ምንም ልማት ባልነበረበት የብላቴ ወንዝ ተፋሰስ፣ የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም የተለያዩ የአትክልትና ፍራፍሬ ዝርያዎች እየተንዠረገጉበት ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አይህመድ።

  በቆራጥ የግሉ ሴክተር ባለሀብቶች የሚለሙትን እርሻዎች የምርታማነት ዐቅም ለማየት ወደ ቦታው በማምራት ጉብኝት አድርገናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጻቸው።

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዚህ አካባቢ ምርታማነት ከክፍፍል ይልቅ ትብብር የሚያስገኘውን ውጤት ማሳያ መሆኑን አክለዋል።

  ይህ ተሞክሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ መስፋፋት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር ዐቢይ አህመድ አሳስበዋል።

  December 23, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በወላይታ ሶዶ ከተማ በቀዳሚዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተገነባው የዳቦና የዱቀት ፋብሪካ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

  የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀዳሚዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽህፈት ቤት ተገንብቶ የተመረቀውን የዳቦና ዱቀት ፋብሪካ ጎብኝተዋል፡፡

  የዳቦ ፋብሪካው በቀን 300 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ለአካባቢው ስራ አጥ ወጣቶች ስራ ዕድል ከመፍጠር አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል፡፡

  ፋብሪካውን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የወሰደው ጊዜ 9 ወር መሆኑንና የተቀመጠውን የግንባታ ጥራት መስፈርት አሟልቶ በመጠናቀቅ ለምረቃ መብቃቱም ተገልጿል።

  በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ሂቤይ ፒንግል ማሽነሪስ አጋርነት የተገነባ መሆኑም ተጠቅሷል።

  የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በ11 ከተሞች ተመሳሳይ አቅም ያላቸው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎችን በጋራ ለመገንባት ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ጋር ተፈራርሞ እያስገነባቸው ካለ ፋብሪካዎች ውስጥ ዛሬ የተመረቀው አንዱ ነው ተብሏል::

  ፅህፈት ቤቱ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በቀን 1 ሚሊየን እንዲሁም በአጋሮ ከተማ 3 መቶ ሺህ ዳቦ የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን አስገንብቶ ማስመረቁ ይታወሳል::

  በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም እና ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

  December 23, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው ጉባኤ ስድስት አባላት ያሉትን የኢዜአ ስራ አመራር ቦርድ ሹመት አጸደቀ።

  ምክር ቤቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቀረቡለትን እጩዎች ዝርዝር በማየት ተወያይቶ ሹመታቸውን አጽድቋል።

  በዚህ መሰረትም ፦ 1. ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ሰብሳቢ 2. አቶ መሀመድ ራፊ አባል 3. አቶ ሙሣ አህመድ አባል 4. ወይዘሮ ሚሊዮን ተረፈ አባል 5. ወይዘሮ ሁሪያ አሊ አባል 6. ረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ አባል

  በማድረግ በአብላጫ ድምጽ የተቋሙ የቦርድ አመራሮች ሆነው ተሹመዋል። የስራ አመራር ቦርዱ አባላትም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ በመፈጸም ሃላፊነታቸውን ተረክበዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

  December 22, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በሚያካሂደው መደበኛ ጉባዔ የምክር ቤቱን 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባኤ መርምሮ በማፅደቅ የሚጀምር ይሆናል፡፡

  በተጨማሪም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባላትን ሹመት መርምሮ የሚያፀድቅ ሲሆን፤ በምክር ቤቱ አዳዲስ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ምደባን አስመልክቶ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይም ተወያይቶ ምደባውን የሚያፀድቅ ይሆናል፡፡

  የመንግስትና የግል አጋርነት እንዲሁም የብሔራዊ ክፍያ ስርዓት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚያቀርበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ አዋጁን በማፅደቅ የዕለቱን ጉባዔ የሚያጠናቅቅ ይሆናል፡፡(ኢ ፕ ድ)

  December 21, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የተመራ ከጤና ሚኒስቴር እና ከሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳሮች የክትባት የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተገኙበት በአገርአቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የኩፉኝ መከላከያ ክትባት ለማካሄድ የተደረገውን አጠቃላይ ቅድመ ዝግጅት ከሰው ሀይል፣ ከግብዓትና ከሌሎች አኳያ በዝርዝር በበይነ መረብ ገምግሟል፡፡ በግምገማዊ መድረኩም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆኑ የተደረጉትን ቅድመ ዝግጅቶች በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የኩፉኝ መከላከያ ክትባት በስኬታማነት ለማጠናቀቅ እንደ አገር በቂ ዝግጅት መደረጉ የተገለጸ ሲሆን የተስተዋሉ መጠነኛ የቅድመ ዝግጅት ውስንነቶችም በፍጥነትና በቅንጅት መፈታት እንዳለባቸው መግባባት ላይ መደረሱን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

  December 19, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአሜሪካ ቆይታ ኢትዮጵያ ያላትን የዲፕሎማሲ አቅም ከፍ ያደረገ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

  የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።

  ሚኒስትር ዴኤታዋ በመግለጫቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና የሉዑካን ቡድናቸው በአሜሪካ የተሳካ ቆይታ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን አስታውቀዋል።

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ አፍሪካ ጉባኤ ተገኝተው ከጉባኤው ጎን ለጎን ከአሜሪካ መሪዎችና ጋር ውጤታማ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

  በውይይቱ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ሰላምን ለማምጣት የወሰደው እርምጃ እውቅና ያገኘበት መሆኑንም አመላክተዋል።

  በተለይ ለስምምነቱ ትግበራ ያሳየው ቁርጠኝነት አድናቆት እንደተቸረው እንዲሁ።

  አሜሪካና ኢትዮጵያ በጋራ የሚሰሯቸውን የልማትና ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን አጠናክረው ለማስቀጠል መስማማታቸውንና ሁለትዮሽ ግንኙነቱን ወደ ቀደመ መልኩ ለመመለስ እንደሚሰራም ገልጸዋል።

  ኢትዮጵያ ሚሊየኖችን አስተባብራ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን መትከል መቻሏና ወደ ሌሎች አፍሪካ ሀገራት ለማስፋት የምታደርገው ጥረት እውቅና የተሰጠበት መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለዋል።

  በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለመልሶ ግንባታ የምታደርገውን ጥረት አለም አቀፍ ድጋፎች የተገኘበት እንዲሁም ለቀጣይ ድጋፎችም መሰረት የተጣለበት ቆይታ መሆኑንም አመላክተዋል።

  በአጠቃላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ ቆይታ በዲፕሎማሲ መስክ ስኬት የተመዘገበበት እና ኢትዮጵያ ያላትን የዲፕሎማሲ አቅም ከፍ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

  ምንጭ፦ ኢዜአ

  December 20, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ታሪካዊ ሪፎርሞች ተከትሎ የአሜሪካ የኢንቨስትመንት ማህበረሰብ አባላት በተለያዩ ዘርፎች ኢንቬስት እንዲያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አበረታትተዋል። ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኦፊሴላዊ ፌስቡክ ገጽ።

  December 17, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ምክር ቤቱ በሀዋሳ ውይይት አካሂዷል። በምርጫ ቦርድ ድጋፍ የተቋቋመውና በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው የጋራ ምክር ቤት ከፓርቲዎች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችለው አሰራር እየዘረጋ መሆኑን አስታውቋል። የጋራ ምክር ቤቱ በዛሬው እለት በቅሬታ አቀራረብና አፈታት፣በአሰራር ደንብና ትግበራ እንዲሁም በቋሚ ኮሚቴዎች እቅድ ትግበራ ዙሪያ በሀዋሳ ውይይት አካሂዷል። የምክር ቤቱ የወቅቱ ሰብሳቢ አካሉ ብዙነህ እንዳሉት ከፓርቲዎች የሚነሱ ቅሬታዎች አለመግባባቶች በሰለጠነ መንገድ በውይይት የሚፈቱበትን ስርኣት እየዘረጋ ይገኛል። ለዚህም የውስጥ ጠንካራ አሰራርና ደንብ በማዘጋጀት፣ቅሬታዎችን በአግባቡ በማስተናገድና የሚፈቱበትን ስርኣት በማበጀት እንዲሁም ምክረ ሀሳቦችን በማቅረብ በኩል ጥሩ ጅምሮች መኖራቸውን አስታውቀዋል ። በተለይ በአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በኩል ገዢው ፓርቲ ጫና ያሳድርብናል በሚል ለሚቀርቡ አቤቱታዎች ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ የምክር ቤቱ አባላት ታች ድረስ ወርደው የማጣራት ስራ እንደሚሰሩ አቶ አካሉ ተናግረዋል ። ምክር ቤቱ ፓርቲዎች በጋራ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች፣ በዴሞክራሲያዊ ስርኣት ግንባታ፣በህግ የበላይነት፣በዘላቂ ሰላምና በህዝብ ልማቶች ስኬት ዙሪያ የበኩላቸውን እንዲወጡ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። ፓርቲዎች በመቀራረብና በመነጋገር ችግሮችን የመፍታት ልምድ ሊያጎለብቱ እንደሚገባም ሰብሳቢው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።

  December 15, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች ቀን በአዳማ ከተማ "በጎ ፈቃደኝነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው። በመርሀ ግብሩ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች፣ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የስራ ባልደረቦች፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ የአጋር ድርጅቶች ተወካዮች እንዲሁም የአዳማ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተሳተፉ ሲሆን በዕለቱ በበጎ ፈቃደኛነት ትሩፋት ዙሪያ ያላቸውን መልዕክት አስተላልፈዋል። እለቱ በጎፈቃደኝነት በተደራጀ አግባብ እንዲካሄድና በጎ ፈቃደኞች ስለሚሰጡት አገልግሎት ለማመስገን ያለመ መሆኑ ተገልጿል። የሴቶችና ማህበታዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ወይዘሮ ሙና አህመድ ባደረጉት ንግግር፤ በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖች የገጠማቸውን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ፣ በጋራ ለመደጋገፍ፣ አብሮነትን ይበልጥ ለማጠናከርና ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት ቀኑ መከበሩን ገልጸዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ የበጎ ፈቃደኝነት እንደሀገር ሳይቆራረጥ ለማካሄድና ተቋማዊ አሰራር ተበጅቶለት እንዲከናወን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሳሚያ አብደላ በክልሉ ለአሰራር ያመች ዘንድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የክረምትና የበጋ በሚል ተከፋፍሎ ቢሰራም የክልሉ ወጣቶች አመቱን ሙሉ በመስራት የአረጋውያንን ቤት እያደሱ ለተቸገሩ ወገኖች አስቤዛ አያቀረቡና ግንባር ለሄዱ ቤተሰቦች ምን እናግዝ ብለው ሲያግዙ እንደነበር በመጥቀስ የክልሉን ወጣቶች አመስግነዋል። በመድረኩ በጎፈቃደኞችና የበጎ ፈቃደኛ አገልግሎት የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚያገናኝ የመረጃ ቋት ተመርቆ በይፋ ስራ የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል። ይሄም በኢትዮጵያ የሚታየውን የበጎ ፈቃደኛና የበጎ ፈቃደኛ ፈላጊዎችን አለመገናኘት በመቅረፍ አገልግሎት ሰጪና ፈላጊን በቀላሉ እንደሚያገናኝ ታምኖበታል። (ኢፕድ)

  December 15, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ቅን እና ውጤታማ ውይይት አድርገናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር የነበራቸውን ውይይት አስመልክቶ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ጋር ቅን እና ውጤታማ ውይይት አድርገናል” ብለዋል። ሰላምን ለማስፈን በምናደርገው ጥረት በአሜሪካ ለተበረከተው አስተዋፅዖ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ ነው ያሉት። ለአስርት አመታት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአሜሪካ ቁልፍ አጋር ሆና ቆይታለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን አጋርነታችንን ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተናል ሲሉ አስታውቀዋል።ኢዜአ እነደዘገበው

  December 14, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ከተባበሩት መንገስታት የንግድ እና የልማት ኮንፈረንስ ፅ/ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ፓውል አኪዉሚ ጋር ተወያዩ። በውይይታቸውም የተባበሩት መንግስታት የንግድ እና የልማት ኮንፈረስ ዋና ፅ/ቤት በተለያዩ አፍሪካ አገሮች ማለትም በአንጎላ፥ ቡርኪና ፋሶና ኒጀር ውስጥ በንግዱ እና በስራ ፈጠራው ዘርፍ እየሰራቸዉ ያሉትን ስራ በአበይትነት ጠቅሰው በኢትዮጵያም ውስጥም በንግድ፥ በስራ ፈጠራ እና ኢንደስትሪ ዘርፍ ለመስራት የተያዙ እቅዶችን አብራርተዋል። በጽ/ቤቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተሩ ፓውል አኪዉሚ ያካሄዱትን የፖሊሲ ጥናትም ለሚኒስትሯ አብራርተዋል ፡፡ ዶ/ር ፍፁም በበኩላቸው የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ፖሊሲዎችን ከማናበብ እና ያሉትን ልዩነቶች ከመፍታት አንፃር በመንግስት በኩል እየተሰራ ያለውን ተግባር ጠቅሰው በዚህ ወቅት ሃገሪቱ ከምትሄድበት የልማት አቅጣጫ ጋር የተናበበ መሆኑንም ገልጸዉላቸዋል ፡፡ ሃላፊዎቹ በቀጣይ በጋራ በመስራት በኢትዮጵያ የልማት ጉዞ ላይ አሻራቸውን ማሳረፋቸዉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

  December 14, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ( ባባ ) የቀብር ስነ ስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ፡፡

  ወጣቱ የፊልም ባለሙያ ታሪኩ ብርሃኑ ባደረበት ህመም ምክንያት ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ሲሆን፥ ሥርዓተ ቀብሩ በዛሬው ዕለት የአርቲስቱ ቤተሰቦች ፣ ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም አድናቂዎች በተገኙበት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል፡፡

  አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ከ40 በላይ በሚሆኑ ፊልሞች በመሪ ተዋናይነት እና በተዋናይነት ተሳትፏል፡፡

  አርቲስቱ ከተሳተፈባቸው ፊልሞች መካከል ላውንደሪ ቦይ፣ 300 ሺህ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ፣ ኢንጂነሮቹ፣ ህይወቴ፣ ከቃል በላይ፣ ህይወትና ሳቅ፣ ሀገርሽ ሀገሬ፣ እዮሪካ፣ ከባድ ሚዛን፣ ወፌ ቆመች፣ በቁም ካፈቀርሽኝ፣ እንደ ቀልድ፣ እርቅ ይሁን፣ ሞኙ ያራዳ ልጅ 4፣ አባት ሀገር እና ወጣት በ97 በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበር።

  December 12, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የኮንስትራክሽን እና ሎጂስቲክስ ምክትል ዳይሬክተር በሆኑት ተስፋዬ ደሜ እና አራት የአገልግሎቱ ሰራተኞች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱ ተገለጸ።

  የስራ ሀላፊው እና ባለሙያዎች ላይ ክስ የተመሰረተው በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ስም 29 ሺ 200 ኩንታል ሲሚንቶ ከሁለት ፋብሪካዎች ገዝተው ለግለሰቦች በመሸጥ ከ30 ሚሊዬን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው በማዋል የተጠረጠሩ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

  ተከሳሾቹም 1ኛ ተስፋዬ ደሜ በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የኮንስትራክሽን እና ሎጂስቲክስ ምክትል ዳይሬክተር፣ 2ኛ አሸናፊ ተስፋዬ የኮንስትራክሽን እና ሎጂስቲክስ ግዢ ዋና ክፍል ሃላፊ፣ 3ኛ ቱጅባ ቀልቤሳ እና 4ኛ ተከሳሽ ሙስጠፋ ሙሳ የግዢ ባለሙያ ሆነው ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውን አስታውቋል።

  ተከሳሾቹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በ2013 እና 2014 ዓ.ም በተለያዩ ወራት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምንም አይንት ሲሚንቶ ግዢ ባልተፈፀመበት ሁኔታ በስሙ ሲሚንቶ ከፋብሪካዎች በአነስተኛ ዋጋ በመግዛትና ገበያ ላይ በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ መጠርጠራቸውን ገልጿል።

  በዚህመ 1ኛ ተከሳሽ አገልግሎቱ የሲሚንቶ ግዢ ፍላጎት ሳይኖረው እንዳለው በማስመሰል ለአገልግሎቱ አስቸኳይ የግንባታ ስራ የሚውል በድምሩ 29, ሺ 200 ኩንታል ሲሚንቶ ሽያጭ ከደርባና ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች እንዲፈፀም ማድረጋቸው ተጠቅሷል።

  የስራ ሀላፊው በ3ኛ እና በ4ኛ ተከሳሽ ስም ደብዳቤዎችን በመፃፍ፣ በተከሳሾች የግል አካውንት ገቢ በማድረግ፣ ወደ ፋብሪካችሁ ገቢ በሆነው ገንዘብ ለመስሪያ ቤታችን የሲሚንቶ ሽያጭ እንድትፈፀሙ በማለት ደብዳቤ በመፃፍ በመስሪያ ቤቱ ስም ግዢ እንዲፈፀም እና ሲሚንቶው ወደ መስሪያ ቤቱ ገቢ ሳይደረግ አየር ላይ ተሸጦ ለግል ጥቅሙ እንዲውል ያደረገ በመሆኑ፤

  2ኛ ተከሳሽም 1ኛ ተከሳሽ ያለምንም ግዢ ፍላጎት በተቋሙ ስም ግዢ እንዲፈፀም የፃፋቸውን ደብዳቤዎች 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ለደርባ እና ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች እንዲያደርሱ እና ተከሳሾች በግል አካውንታቸው ገቢ በሚያደርግላቸው ገንዘብ ከየፋብሪካዎቹ የሲሚንቶ ግዢ እንዲፈፅሙ በመንገርና ደብዳቤዎቹን በመስጠት በተቋሙ ስም የተገዛውን 29 ሺ 200 ኩንታል ሲሚንቶ በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እንዲውል ያደረገ በመሆኑ፤

  3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ደግሞ ለደርባ እና ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ በተቋሙ የሲሚንቶ ግዢ ፍላጎት ሳይኖር ለደርባ እና ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ በ3ኛ ተከሳሽ ስም 7 ሺ 200 ኩንታል፣ በ4ኛ ተከሳሽስም 22 ሺ ኩንታል ሲሚንቶ፣ በድምሩ 29 ሺ 200 ኩንታል ሲሚንቶ ግዢ እንዲፈፀም በተፃፈ የተቋሙ ደብዳቤ አማካኝነት በግል አካውንታቸው በሚገባ ከፍተኛ ገንዘብ ግዢ በመፈፀም ሲሚንቶው ወደ ተቋሙ ገቢ ሳይሆን አየር በአየር በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እንዲውል ያደረጉ በመሆኑ፤

  በአጠቃላይ ተከሳሾች በጥቅም በመመሳጠር ምንም አይነት የግዢ ፍላጎት ሳይኖር በአገልግሎቱ ስም በፃፏቸው ደብዳቤዎች ከዳንጎቴ እና ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች በድምሩ 29 ሺ 200 ኩንታል ሲሚንቶ በመግዛት ወደ ተቋሙ ገቢ ሳያደርጉ ገበያ ላይ በመሸጥ 30 ሚሊዬን 99 ሺ 360 ብር ጥቅም ያገኙ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት በስልጣን አላግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡

  ተከሳሾች የተከሰሱበት ክስ በችሎት ደርሷቸው ክሱ የተነበበላቸው ሲሆን ተከሳሾችም የክስ መቃወሚያ ካላቸው በጽሁፍ እንዲያቀርቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎትም ለታህሳስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

  መረጃው ተከሳሾች ላይ ክስ ስለመመስረቱ ለማሳወቅ የቀረበ ሲሆን የተከሳሾችን ከፍርድ በፊት እንደ ንፁህ የመገመት ህገ-መንግስታዊ መብትን ያከብራል ሲል ባወጣው መግለጫ አሰታውቋል።

  December 12, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • አጠቃላይ ክብደታቸው ስምንት ኪ.ግ የሚመዝኑ ማእድናት በሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በብዬ ቆቢ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ መያዙን የጉመጁሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

  በተመሳሳይ በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለት ሚሊዮን ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የቁም እንስሳት በህገወጥ መንገድ ወደ ሱማሌ ላንድ ሊወጡ ሲሉ በቶጎዉጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

  የጉምሩክ ኮሚሽን በሂደቱ ለተሳተፉ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ሠራተኞችና አመራሮች እንዲሁም ለጸጥታ ተቋማት አመራሮች እና አባላት ምስጋናውን አቅርቧል።

  የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል።

  December 12, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የቄስ በሊና ሳርካ ሥርዓተ ቀብር በአዲስ አበባ ጴጥሮስ ወጳውሎስ የፕሮቴስታንት እና የካቶሊክ መካነ መቃብር ዛሬ ተፈፅሟል።

  በቀብር ሥነስርዓቱ ላይ ቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

  ቄስ በሊና ሳርካ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሕዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ማረፋቸው ይታወሳል።

  ቄስ በሊና ሳርካ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገልጋይ እንደነበሩ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

  በቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአገልግሎት ታሪክ ያላቸውን ትጉህና ታማኝ አገልጋይን በማጣቷ የቤተክርስቲያኒቱ አመራርና ምዕመናን የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልፀዋል ።

  ከቀብር ሥነስርዓቱ አስቀድሞ በወዳጅነት አደባባይ በተከናወነው የአስከሬን ሽኝት ኘሮግራም ላይ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቄስ በሊና በተሰጣቸው ዕድሜ ፍቅር፣ አንድነትንና ተግቶ መስራትን አስተምረውን አልፈዋል ብለዋል። ቄስ በሊና ሳርካ ያባከኑት ጊዜ የለም ያሉት ወ/ሮ አዳነች፤ ትውልዱ ከእርሳቸው ለእውነት መትጋትን መማርና መኖር ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።

  የኢትዮጵያ የከፍታ ጊዜ በሚለው መፅሀፋቸው የኢትዮጵያን ብልፅግና በራዕይ አሳይተውናል ያሉት ከንቲባዋ፤ እስከ መጨረሻው ዕድሜያቸው ድረስ ትውልድ ላይ በመስራት ያለፉ ጀግና አባት መሆናቸውን አክለው ገልፀዋል። ለወዳጁ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለቤተክርስቲያኗ ምዕመናን በመሉ መፅናናትን ተመኝተዋል።

  December 12, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በሀዋሳ ከተማ “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኝበት ወቅት ነው።

  በበዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል “ኢትዮጵያ በድምቀትና በሙላት የምትታይበት የኢትዮጵያዊነት ቀን ነው” ብለዋል።

  ዛሬ ሁላችንም ለኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊ መሆናችንን በኢትዮጵያ ጥላ ስር ሆነን የምናሳይበት ታሪካዊ ቀንም ነው ሲሉ ገልጸዋል።

  ሰላምን መፍጠር ካልቻልን የምንፈልገውን ልናሳካ አንችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁላችንም በአንድነት የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት መስራት እነደሚገባ በመልዕክታቸው አሳስበዋል።

  የትላንት ታሪክ መማሪያ እንጂ መወቃቀሻ ሊሆን አይገባም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኋላ ታሪክ ላይ በመንተራስ መገፋፋትና መጠላለፍ መቆም አለበት ብለዋል።

  “ኢትዮጵያ ትፈተናለች አንጂ አትሸነፍም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሁን የገጠመን ፈተና ምንም አሳዛኝ ቢሆንም ሀገርንና የነገን ትውልድ መገንባት በሚፈልጉ ዜጎች እናሸንፋለን ኢትዮጵያም ትበለጽጋለች ብለዋል።

  ኢትዮጵያ በልጽጋ በከፍታ ማማ ላይ ተቀምጣ ለልጆቻችን የምትሻገር መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ ሲሉ አመልክተው ይህንንም በአዲስ ድል በቅርቡ እንደምንገናኝ ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

  የኢትዮጵያ ማሸነፍ የሚጀምረው ከእውነትና ፍቅር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለእያንዳንዱ አጀንዳ ምላሽ ከመስጠታችሁ በፊት የአጀንዳውን መነሻ ምክንያት በማጣራት መከላከል አለባችሁ ነው ያሉት።

  አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ ከፍታ እውን ይሆናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ አንድነትና ብልጽግና ያላችሁን ሁሉ ሰጥታችሁ በትጋት እንድትሰሩ አደራ ልላችሁ እፈልጋለሁም ብለዋል።

  በዕድገት እስራኤል

  December 8, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ 5 አባላት ያሉት የፀረ ሙስና ኮሚቴ አቋቋሙ።

  በሀገር ደረጃ የፀረ ሙስና ትግሉን የሚያጠናክር ብሄራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አማካኝነት ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በከተማዋ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አማካኝነት አምስት አባላት ያሉት የፀረ ሙስና ኮሚቴ ተሰይሟል፡፡

  በዚህም መሰረት 1. ወ/ሮ ሊድያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ 2. አቶ ጀማል ረዲ የአዲስ አበባ ከተማ የፀረ ሙና ኮሚሽን ኮሚሽነር 3. አቶ ተስፋዬ ደጀኔ የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህ ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ 4. አቶ ጥላሁን ግድየለው የአዲስ አበባ ከተማ አቃቤ ህግ 5. ኮ/ር አህመድ መሃመድ የገቢዎች ቢሮ ም/ቢሮ/ሃላፊ ናቸው፡፡

  ስለሆነም ህብረተሰቡ በ 9977 የነፃ የስልክ መስመር አስፈላጊውን ጥቆማና መረጃ በመስጠት ለፀረ ሙስና ትግሉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ ከኮሚቴው ጎን እንዲቆም የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አቅርቧል።

  የተጀመረውን የፀረ ሙስና ንቅናቄ ለመግታትና ለማሰናከል የተለያዩ ደባል አጀንዳዎችን በመፍጠር በተለይም ትምህርት ቤትን የሁከት ማእከል ለማድረግ የሚከናወነውን እንቅስቃሴ በተቀናጀ አግባብ መከላከል እንደሚያስፈልግም ተገልጿል።

  ህዝቡ ይህንን ሴራ በንቃት በመከታተል እንዲያከሽፍና ለማይቋረጠው የፀረ ሌብነት ትግል ማስረጃዎችንና ጥቆማዎችን በመስጠት ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ መቅረቡን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

  December 7, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በገንዘብ ሚኒስቴርና በአፍሪካ ልማት ባንክ መካከል ለቦረና ዘላቂ ውሃ ልማትና ለተሻሻለህይወት መረሀ ግብር ትግበራ የሚውል የ14 ሚሊዮን ዶላር (756 ሚሊየን ብር) ዕርዳታ ስምምነት ተፈረመ፡፡

  በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአካባቢ ልማት፣ ሥርዓተ ፆታን ያገናዘበ የተቀናጀ ዘላቂ የውሃ ልማት፣ የአካባቢና የግል ንጽህና አገልግሎትን ለማስፋፋትና በውሃ አጠር አከባቢ የሚኖሩ አርብቶ አደሮችን በጤና፣ በማህበራዊ ኑሮ፣ በሥነ-ምግብ እና በምግብ ዋስትና የሚከናወኑ ተግባራትን ለመደገፍ የሚውል ነው ተብሏል።

  የገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እንደተናገሩት የእርዳታ ገንዘቡ በቦረና ዞን በተከታታይ ድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች የከርሰ ምድር ውሀ በማልማት በአርብቶ አደሩ ዘንድ ዘላቂ ልማት ለማምጣትና በተለያዩ ዘርፎች ኑሮን ለማሻሻል እንደሚውል አመልክተዋል።

  የቦረና ዞንን ጨምሮ በቆላማ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭት ሊተነበይ የማይችል በመሆኑ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ለከፋ ድህነት እና ለምግብ እጥረት እየተጋለጠ እንደሚገኝ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልፀው፤ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ በቅርቡ የአርብቶ አደር አካባቢዎች ልማት ፖሊሲ አዘጋጅቶ ስራ ላይ አውሏል ብለዋል፡፡

  ፖሊሲው የአርብቶ አደሩን አገር በቀል ዕውቀት በመጠቀም ዘላቂነት ያለው የውሃ ሀብት አያያዝ ተግባራትን በማሳደግ የእንስሳትን ምርታማነት ለማሻሻል እና ድርቅ የመቋቋም አቅምን ለማጎልበት ቁልፍ ስትራቴጂ ሆኖ ያገለግላልም ብለዋል።

  ድጋፉ የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር (IWRM) አሰራርን በመጠቀም የድርቅ ተፅእኖን በመቅረፍ እና ከውሃ ሀብት ጋር በተገናኘ በዘላቂነት መቋቋም ላይ የሚያተኩር መሆኑ ተገልቷል፡፡ የእርዳታ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰውሰው እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱል ካማራ መሆናቸውን ሚኒስቴር መሠሪያ ቤቱ ገልጸዋል።

  December 6, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ኢትዮ-ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሞተር ሳይክሎችን ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ድጋፍ አደረገ፡፡

  የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ካሉ መሰረተ ልማቶች ትልቁን ቦታ የሚሸፍነው የምድር ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የጅቡቲ የባቡር መስመር መሆኑን ገልፀው ካለው ጠቀሜታ አንፃር በመንግስት ከፍተኛ ወጪ የተገነባውን የባቡር መስመር ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሰበታ እስከ ደዋሌ ያለውን መስመር ትኩረት ሰጥቶ እየጠበቀ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

  ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የተደረገው ድጋፍ የሁለቱን ተቋማት መልካም ግንኙነት የሚያሳይና በጋራ መስራትን የሚያመላክት እንደሆነ ተናግረው በቀጣይም ትብብራቸውን የበለጠ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

  የኢትዮ-ጁቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብዲ ዘነበ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ለክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፉንታ ሲያስረክቡ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሀገራችን እየተገነቡና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ መሰረተ-ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ የማይተካ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

  በመጨረሻም የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር ያለውን ትብብርና አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

  ምንጭ የኢፌፖ

  December 6, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • "ለኢትዮጵያ ልዕልና የምሁራን ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ሀገር አቀፍ የምሁራን የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ከመላ ሀገሪቷ የተውጣጡ ምሁራን እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

  ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የምሁራን አበርክቶ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የምሁራን አስተዋፅኦ ላይ ውይይት እንደሚደረግ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።

  የምክክር መድረኩ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የተዘጋጀ ነው። የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሃነ መስቀል ጠና፤ ምሁራን ሀገር ተረካቢ ትውልድ ከማፍራት ባሻገር በጥናትና ምርምር ለአገር ልማትና እድገት በመስራት ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።

  የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን ለማድረግ፣ ለፖሊሲ ግብአት፣ ለሀገር ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት የመፍትሔ ሀሳብ በማቅረብ ጭምር ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት።

  የሀገርን ጥቅም ማስቀደም ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ሃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው በተለይም ምሁራን ለዚህ ትልቁን ሃላፊነት መውሰድ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል። በየትኛውም ዘርፍ ላይ ያሉ ምሁራን በመቀራረብ፣ በአንድነትና በመተጋገዝ ለአገርና ለህዝብ ጥቅም እንዲሰሩ ጠይቀዋል። በኢትዮጵያ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጫናዎችን በመመከት ረገድም ምሁራን በሰላ ብዕራቸው እና በትክክለኛ ጥናትና ምርምራቸው ሊታገሉ ይገባል ነው ያሉት።

  በምክክር መድረኩ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የምሁራን አበርክቶ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የምሁራን አስተዋፅኦ ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

  December 5, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ስም የተሰራጨውን አቋም ማህበራችን አያውቀውም ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስታወቀ።

  የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ለኢዜአ በላከው መግለጫ ማህበሩ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምሀርት ድረስ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን በማደራጀት በአምስት ዓላማዎች እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጿል።

  ከአምስቱ ዓላማዎች መካከል አንዱ የመምህራን መብትና ጥቅም ማስከበር ነው ያለው መግለጫው በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ መምራን ያነሱትን ጥያቄዎች ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሚመለክታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት እያቀረበ ለመፍትሄው እየሰራ መሆኑንም አመልክቷል።

  አንዳንድ ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ ማግኘት የሚገባቸው መሆኑን ማህበሩ ቢያምንም አንዳንዶቹ ደግሞ ጊዜ የሚፈልጉ መሆናቸው ሊታወቅ እንደሚገባም አስታውቋል።

  የመምህራን ማህበር የትግል ስልት መርህን መሰረት በማድረግ ለሌሎች አርዓያና ትምህርት ሰጪ በሆነ መልኩ መሆን እንዳለበትም የማህበሩ መግለጫ ያመለክታል።

  ይህ በእንዲህ እያለ "የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች የአቋም መግለጫ” በሚል ርዕስ “ከህዳር 26/2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሥራ ማቆም አድማ እናደርጋለን" በሚል ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የማያውቀው ነው በማለት አስታውቋል።

  እውቅና ያለው የማህበሩ መዋቅር ስምም “የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር" መሆኑን ያስታወቀው መግለጫው መምህራንም ማህበራችሁ ጉዳዩን በጥብቅ ይዞ እየሰራ መሆኑን አውቃችሁ የተለመደውን የማስተማር የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት በሙያዊ ኃላፊነታችሁን እንድትቀጥሉ ሲል ጥሪውን አስተላልፏል። ምንጭ፦ ኢዜአ

  December 2, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአካባቢዉ ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎች እየለሙ ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ ፕሮጀክቱ ከዘርፉ የሚገኘዉን ገቢ ለማሳደግ እንሚያግዝ ተናገረዋል፡፡

  በተጨማሪም አካባቢዉን እርስበርስ የሚያስተሳስርና አብሮ ለማደግ ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥር ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የኃይለማርያም እና ሮማን ፋዉንዴሽን ከመንግስት የቀረበዉን ጥያቄ ተቀብሎ ወደ ሥራ በመግባቱ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

  ያገለገሉ ሰዎች ልምዳቸዉን ለሀገራቸዉ ጥቅም ሥራ ላይ እንድያዉሉ የማድረግ ተግባር ቀጥሎ ባሉ ጊዜያትም ሊለመድ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

  ባለሀብቶች፣ ቀና ዜጎችና ሌሎችም ፕሮጀክቱ ስኬታማ እንዲሆን ሀብትና ድጋፍ በማመንጨት ሊደግፉ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

  ሪዞርቱ በኃለማርያም እና ሮማን ፋዉንዴሽን አማካኝነት የሚገነባ ሲሆን ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለዉ ተጠቅሷል፡፡

  በመርሀግብሩም ላይ ከፌዴራል ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት መሪዎችና ሌሎችም ማህበራዊ መሰረቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በተመስገን ተስፋዬ

  December 2, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ያቋቋሙት የፀረ ሙስና ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ በተለይም በአዲስ አበባ በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ተሳትፈው የተገኙ ግለሰቦችና ባለሥልጣናትን በቁጥጥር ሥር የማዋል ተግባር መጀመሩን አስታወቀ።

  የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተመሥገን ጥሩነህ እና ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በጋራ መግለጫውን ሰጥተዋል።

  የኮሚቴው ሰብሳቢ በኢትዮጵያ ሙስና ብሔራዊ የደህንነት ሥጋት የመሆን ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቅሰው መንግሥት ይህን በመገንዘብ ኮሚቴውን ማቋቋሙን ገልፀው፣ ኮሚቴው የተቋቋመው ተቋማትን ለመተካት ሳይሆን የተቀናጀና የተናበበ ሥራ ለመሥራት መሆኑን ተናግረዋል።

  ኮሚቴው በታቀደና በተጠና መልኩ ሥራውን እንደጀመረ ጠቁመው የኮሮና ወረርሽኝና ጦርነትን ተገን በማድረግ ህዝብን ሲያማርሩ የቆዩ ሙሰኞች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አስታውቀዋል። የኮሚቴው አባል ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በበኩላቸው በመሬት፣ በአገልግሎትና በሌሎች መስኮች በርካታ ጥቆማዎችና ማስረጃዎች መቅረባቸውን ተናግረዋል።

  ለአብነትም በአዲስ አበባ መሬት የወረሩ፣ በተጭበረበረ መንገድ ኮንዶሚኒየም የወሰዱ አካላት በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆኑን አስረድተዋል።

  በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ካሉት ውስጥ የመንግሥት ባለሥልጣናትንም የሚጨምር መሆኑን ተናግረዋል ሲል የዘገበው (ኢ ፕ ድ) ነው።

  December 2, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽሬ ላይ እየመከረ ነው።

  በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጀው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ከትናንት ኅዳር 21 ቀን ጀምሮ ሽሬ ላይ ሥራውን ጀምሯል።

  ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ታጣቂዎች የተወጣጣው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሥራውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይታመናል።

  ኮሚቴው የሚያወጣው ዝርዝር ዕቅድ ትጥቅ የማስፈታት፣ ካምፕ የማስገባትና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመልስ ይሆናል። ዝርዝር ዕቅዱን የማውጣት ተግባሩ፣ በቴክኒክ ጉዳዮች ምክንያት መዘግየቱ ይታወቃል።

  ኅዳር 22 ቀን 2015 ዓ/ም
  አዲስ አበባ
  የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

  December 1, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ።

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደህና መጡ ብለዋል።

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይታቸው ኢትዮጵያ ከተመድ ጋር ያላትን ግንኙነትና ትብብር በምታጠናክርበት ተመካክረናል ብለዋል።

  December 1, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ዘርፍ በፈጣን እድገትና ለውጥ ላይ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 17ኛው አለም ዓቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል።

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በአፍሪካ አህጉር ላለፉት 11 ዓመታት ሳይካሔድ የቆየውን የአለም የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ኢትዮጵያ በማስተናገዷ ታላቅ ክብርና ኩራት ይሰማናል ብለዋል። በኢንተርኔት አማካኝነት ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረ በመሆኑ አጠቃላይ ለዘርፉ እድገትና የጋራ ተጠቃሚነት መጎልበት የአለም የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት አራት አመታት በተለያዩ ፈተናዎች ማለፏን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የችግሮች ምክንያት በመሆንና ለመልካም አጋጣሚዎች በማገልገል የኢንተርኔት ድርሻ ተጠቃሽ ነበር ብለዋል።

  ኢንተርኔት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት በኦንላይን ስራዎችን በፍጥነት ለማከናወን የጠቀመውን ያክል በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ግጭት ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የነበረውን አሉታዊ ጎን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

  የኢንተርኔት አገልግሎት በተለይም ለአገር ግንባታና ፈጣን አገልግሎት በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው። የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ለተያዘው የ10 አመት እቅድ የሚኖረውን ፋይዳ አስረድተዋል።

  ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ዘርፍ ፈጣን ለውጥ እያመጣች ስለመሆኑ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለግሉ ሴክተር ጭምር ዘርፉን ክፍት በማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ነው የጠቀሱት።

  የሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገትን ለማሳለጥ፣ ለአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና ሌሎች መስኮች ልዩ ትኩረት በመስጠት አጠቃላይ በቴክኖሎጂ ልማት እየተከናወነ ያለውን ተግባር ዘርዝረዋል። ለማህበራዊ ልማት፣ ለስራ ፈጠራና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ተግባራት የኢንተርኔት ጠቀሜታ ሰፊ መሆኑን አብራርተው የደህንነትና ነፃነት ጉዳይ ግን በብዙ መልኩ ጥያቄ ውስጥ እየገባ መሆኑን አመላክተዋል። በተለይም አፍሪካ ላይ ጫናው የበረታ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ በራስ ፈጠራና ስትራቴጂ ታግዞ በዘርፉ ፈጠራና ልማት ላይ በስፋት መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል።

  በአዲስ አበባ የሚካሄደው 17ኛው አለም ዓቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ ለዘርፉ አድገትና የጋራ ተጠቃሚነት የሚመከርበት ጠቃሚ መድረክ እንደሚሆን ያላቸውንም እምነት ገልጸዋል። በጉባኤው ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ ባስተላለፉት መልክት የኢንተርኔትን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት፣ ደህንነትና የጋራ ተጠቃሚነት መስራት ይገባል።

  ዓለም ዓቀፉ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤ “የማይበገር ኢንተርኔት ለዘላቂና እኩል የጋራ ተስፋ” በሚል መሪ ሃሳብ እስከ ፊታችን አርብ ድረስ ይቆያል።ዘገባው የኢዜአ ነው፡፡

  November 29, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በአርብቶ አደር አካባቢ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስችል የአርብቶ አደር የምግብና ስርዓተ ምግብ ደህንነት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።

  የፕሮግራሙ ማስጀመሪያ በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን፣ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ፣ በአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ልማትና የቢዝነስ አቅርቦት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱል ካማራ ፣ ከፌደራል የተወጣጡ የስራ ሃላፊዎች እና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

  በዚሁ ወቅት እንደተገለጸውም ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ቀንድ የምግብ ደህንነት ችግርን የመቋቋም አቅምን በመገንባት የሴቶች፣ የወጣቶች እና የህዝቡን አጠቃላይ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ይችላል ተብሏል። ፕሮጀክቱ የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን ከማሳደግ ባለፈ በአርብቶ አደሩ አከባቢ ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠርም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑም ተጠቁሟል።

  ፕሮጀክቱ አጠቃላይ የአርብቶ አደሩን ህይወት በማሻሻል በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደህንነት እንዲረጋገጥ ያስችላልም ተብሏል። በምስራቅ አፍሪካ የአርብቶ አደሩን ምርታማነት ከማሳደግ አንጻርም ላቀ ያለ ሚና እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።

  ፕሮጀክቱ ለስድስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በሶማሌ፣ አፋር ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የሚተገበር መሆኑም ተመልክቷል። የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የኢትዮጵያ መንግስት ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውም በስነ ስርዓቱ ላይ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

  November 29, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ከ3 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ተሽከርካሪ በጨረታ አሸንፎ የወሰደው ግለሰብ ያቀረበው ሰነድ ሲረጋገጥ ሐሰተኛ ሆኖ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

  ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን የፈፀመው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለጨረታ ባቀረባቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ተጫራች ሆኖ በመሳተፍ ነው፡፡

  ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው በዚሁ ጨረታ ላይ የተሳተፈው ተጠርጣሪው፤ ለማስያዥያነት በዳሽን ባንክ ስም የተዘጋጀ ሐሰተኛ ሲፒኦ እንዲሁም ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መስቀል ፍላወር ቅርንጫፍ 3 ሚሊዮን 565 ሺህ ብር ገቢ ተደርጓል የሚል ሐሰተኛ ደረሰኝ ለድርጅቱ በማቅረብ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2-B87869 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ ወስዶ ከአካባቢው መሰወሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

  የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰነድ የማረጋገጥ ስራ በሚሰራበት ወቅት ጨረታውን አሸንፎ ተሽከርካሪውን የወሰደው ግለሰብ ያቀረበውን ሰነድ ትክክለኛነት ተጠራጥሮ ለፖሊስ ካመለከተ በኋላ ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ግለሰቡን ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር በማዋል እና የሰነዱን ሐሰተኛነት በማረጋገጥ በህግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል።

  ተቋማት በተለያዩ ምክንያቶች የሚቀርቡላቸውን ገንዘብን ተክተው የሚሰሩ እና ከገንዘብ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ሰነዶች አስቀድመው በማረጋገጥ ሊፈፀምባቸው ከሚችል ወንጀል ራሳቸውን ሊከላከሉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል ስል ኢቢሲ ዘግቧል ።

  November 28, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብርን ቀጣይነት ለማረጋገጥና ለማስፋት ማህበረሰቡን ያሳተፈ ሃገር በቀል የምገባ ስርዓት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

  በሚኒስቴሩ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ለኢዜአ እንደገለጹት በሃገር ደረጃ የተጀመረው የትምህርት ቤት የምገባ መርሀ-ግብር በትምህርቱ መስክ ያበረከተው አስተዋጾ ከፍተኛ ነው፡፡

  በሃገሪቱ ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች በምገባ መርሀ ግብሩ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የተፈጥሮ አደጋና ሰው ሰራሽ ችግሮች ባስከተሉት መፈናቀል ሳቢያ ምገባ የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ቁጥር መጨመሩን አመልክተዋል፡፡

  በመሆኑም ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደረገውን የምገባ ፕሮግራም ቀጣይነት ለማረጋገጥና ለማስፋት ማህበረሰብን ያሳተፈ ሃገር በቀል ስርዓት ማጠናከር ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው አክለው ሃገር በቀል የምገባ ስርዓቱ በየአካባቢው ያሉ የአመጋገብ ባህሎችን የሚያጠናክርና ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

  ሃገር በቀል የምገባ ስርዓት ተማሪዎች በቀላሉ በየአካባቢው የሚገኙ የተመጣጠኑ ምግቦችን እንዲያገኙ የሚያደርግ በመሆኑ ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር ከማድረግ አንጻርም ዕገዛው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ የተዘጋጀው ሃገር በቀል የምገባ ስርዓት ከክልል እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የሚወርድ የአሰራር ስርዓትን ተከትሎ የሚከናወን እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የምገባ ስርዓቱን ማጠናከር የመንግስትንና የድርጅቶችን ድጋፍ ብቻ ከመጠበቅ ህብረተሰቡን ያሳተፈ እንዲሆን በየክልሎቹ በትኩረት እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡

  የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በበኩላቸው በክልሉ አርብቶ አደር ወረዳዎችና ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በሚከናወነው የትምህርት ቤት ምገባ መርሀ-ግብር ከ265 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

  የምገባ መርሀ ግብሩ ተጠቃሚ በሆኑ የደቡብ ኦሞ ዞን ስድስት አርብቶ አደር ወረዳዎችና አሌ ወረዳ በሚገኙ ተማሪዎች ውጤትና መጠነ ማቋረጥ ከማስቀረት ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል፡፡

  “ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አርሶ አደር አካባቢዎች የሚደረገው የምገባ መርሀ-ግብር ወቅትን ጠብቆ እየተከናወነ ነው” ብለዋል፡፡ የተጠቃሚዎች ቁጥር ከተማሪዎች ብዛት አንጻር ዝቅተኛ መሆኑን የገለጹት ሃላፊው ሃገር በቀል የምገባ ስርዓት የአካባቢውን አመጋገብ ልምድ መሰረት ባደረገ መልኩ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

  ሃገር በቀል የምገባ ስርዓቱ ከወጪም ከጤናም አንጻር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸው “ስርዓቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ማህበረሰቡን የማሳተፉ ስራ በትኩረት ይከናወናል” ብለዋል፡፡ የምገባ መርሀ ግብሩን የሚያግዙ የሃይማኖት ተቋማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መኖራቸውን ጠቅሰው የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶችን በመቀስቀስ የትምህርት ቁሳቁስ ለማሟላት በተሰራው ስራ ከ17 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

  በአማራ ክልል ለተፈጥሮ አደጋና ድርቅ ተጋላጭ በሆኑ ሰሜን ወሎ፣ ዋግህምራና ሰሜን ጎንደር የተማሪዎች የምገባ መርሀ-ግብር እንደሚከናወን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሙላው አበበ ናቸው፡፡ የክልሉ መንግስት ለዘንድሮው የምገባ መርሀ ግብር ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን ገልጸው ባለፈው ዓመት 250 ሺህ የነበረው የተጠቃሚ ተማሪዎች ቁጥር ዘንድሮ ወደ 350 ሺህ ማደጉን ተናግረዋል፡፡

  ከችግሩ ስፋት አንጻር ቁጥሩ በቂ አለመሆኑን ገልጸው ሃገር በቀሉ የምገባ ስርዓት መቀንጨርን ጨምሮ መሰል የጤና እክሎችን በመከላከልና ጤናማ ትውልድ በመገንባት ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በክልሉ ባህር ዳርን ጨምሮ በተመረጡ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች የወተት ከብት እርባታን በማከናወን የምገባ መርሀ ግብሩን የሚያግዙ ተግባራት መጀመራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ “በዘንድሮ ዓመትም ሃገር በቀሉን የምገባ ስርዓት ውጤታማ ለማድረግ በትምህርት ቤቶች የጓሮ አትክልቶችን ልማት ማስፋፋት የሚያስችል ስትራቴጅ ተነድፎ ይሰራል” ብለዋል። የምገባ ስርዓቱ በተማሪዎች ውጤት ላይ ከሚያስገኘው ጠቀሜታ ባሻገር ጤናማ ትውልድ ለማፍራትና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑ ተመላክቷል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

  November 26, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሀገር መከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ በመወያየት ለዝርዝር ዕይታ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።

  በዛሬው መደበኛ ስብሰባው የምክር ቤቱን 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ እና 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔዎችን በመመርመርም በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

  ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የገቢዎች ሚኒስትር ሆነው ቀደም ብለው የተሾሙትን ወይዘሮ ዓይናለም ንጉሴ ሹመትም በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

  የመከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን በውሳኔ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 09/2015 ዓ.ም በመመርመር ለዝርዝር ዕይታ ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል።

  የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋምን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 8/2015 ዓ.ም መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ለሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

  በማብራሪያቸውም የዜጎች መብት መከበሩን፣ የሕግ የበላይነትን መሠረት ያደረገ መልካም የመንግሥት አስተዳደርን ለማስፈን የተቋሙን የአሰራርና የሕግ ክፍተት መፈተሽ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።

  ሥራ ላይ የሚገኘውን አዋጅ ቁጥር 1142/2011 በማሻሻል የተቋሙን ኃላፊዎችና አደረጃጀት በማጠናከር ስኬታማ ሥራ እንዲያከናውን ለማድረግ አዋጁን ማሻሻል እንዳስፈለገ አብራርተዋል።

  በምክር ቤቱ የመንግሥት ቋሚ ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ፤ የመከላከያ ሠራዊትን አዋጅ ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ በተመለከተ ለምክር ቤት አባላት አቅርበዋል።

  አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የማሻሻያ እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት መካከል የመከላከያ ሠራዊት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሠራዊቱ አገራዊ ኃላፊነቱን በአስተማማኝ መልኩ እንዲወጣ የሕግ ማዕቀፎችን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።

  ከዚህ በፊት አዋጁ ማሻሻያ እንደተደረገበት አስታውሰው፤ አሁንም ምላሽ የሚሹ ጉዳዮች በመኖራቸው ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

  የምክር ቤቱ አባላትም የቀረቡላቸውን የሹመት የውሳኔ ሃሳብ፣ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጆች እና የፌደራል ዳኛ ስንብትን አስመልክቶ የተለያዩ ሃሳብና አስተያየቶችን በመስጠት በሙሉ ድምጽ ለየቋሚ ኮሚቴው መርተዋል።

  ኢትዮጵያን በመስዋዕትነቱ እያጸና የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተነሳሽነት ለማሳደግ በሚሻሻለው አዋጅ ውስጥ የሠራዊት ቀን እንዲካተትም ጠይቀዋል።

  ሠራዊቱ የሚከፍለውን መስዋዕትነት በሚመጥን መልኩ በሥራ ላይም ሆኖ ከሥራ ሲሰናበት ክብሩን የሚመጥን ሃሳብ በአዋጁ መካተት እንዳለበትም አመላክተዋል።

  በሌላ በኩል የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩት ፋንታሁን ደለለ ሽፈራው፤ በቀረበባቸው የዲሲፕሊን ግድፈት የስንብት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ ለሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን የዘገበው ኢዜአ ነው።

  November 22, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በኦሮሚያ ክልል የሌማት ትሩፋት ንቅናቄን ለመተግበር በትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ።

  የኦሮሚያ ክልል የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተጀምሯል።

  በመርሃ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የክልሉ መንግስት ለግብርና ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል። የግብርና ዘርፉን መለወጥና አሟጦ መጠቀም ሲቻል ክልሉን ማሳደግና አገርን ለማበልጸግ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው መሆኑንም ጠቁመዋል።

  ”የግብርና ዘርፍ ከሰጡት ልክ በላይ የሚሰጥ ዘርፍ ነው” ያሉት አቶ ሽመልስ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ክልሉ ያለውን ሀብት ጥቅም ላይ እንዲያውል እድል ይፈጥራል ብለዋል። በተለይም ክልሉ በእንሰሳት ሀብት ልማት ረገድ ያለውን ሀብት በጥራትና በስፋት ጥቅም ላይ እንዲያውል መንገድ ይከፍታል ነው ያሉት። የሌማት ትሩፋት ንቅናቄው እንዲሳካ የክልሉ መንግስት ምርጥ ዘርን፣ ሌሎች የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችንና ቴክኖሎጂዎችን አሟጦ እንደሚጠቀም አመላክተዋል፡፡

  በተጨማሪም የመኖ እቅርቦትን ማሻሻል እንዲሁም የእንሰሳት ጤንነትን መጠበቅ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ጠቁመዋል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በበኩላቸው መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ ያላትን የእንሰሳት ተዋጽኦ በአግባቡ እንድትጠቀም ያደርጋታል ብለዋል።

  መርሃ ግብሩ የእንሰሳት ተዋጽኦ ጥራትን በማሳደግ የቤተሰብ ስነ ምግብ የማሻሻልና የምግብ ፍጆታን ለማሳደግ ትልቅ ጥቅም አለው ነው ያሉት።

  የግብርና ዘርፍ ባለሙያዎች፣ አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ጠንክረው ከሰሩ አገሪቷ ከዚህ ንቅናቄ ብዙ ታተርፋለች ብለዋል።

  November 22, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በአከባቢው ያለውን ዕምቅ የብዝሃ ህይወት አቅም አውጥቶ ለመጠቀምና ሳይንሳዊ ምርምሮችን ለማዘጋጀት የሚያግዝ የምርምር ማዕከል በኦሞ ሸለቆ አካባቢ ሊቋቋም መሆኑን የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።

  ማዕከሉን ለማቋቋም ከካናዳ፣አሜሪካ፣ ኬኒያ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ማዕከላት የተውጣጡ የብዝሃ ህይወት ተመራማሪዎች በሸለቆው አካባቢ የመስክ ምልከታ እያደረጉ ነው።

  የምልከታው አላማ በአካባቢው "የኦሞ- ቱርካና የምርምር ማዕከል" የተሰኘ የጥናትና የምርምር ማዕከል በጋራ ለመመስረት ያለመ መሆኑን የጂንካ ዩኒቨርስቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ኤሊያስ አለሙ በተለይ ለኢዜአ ገልፀዋል።

  የምርምር ማዕከሉ በአከባቢው ያለውን ያልተነካ ዕምቅ ሀብት መጠቀም የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችን ማበርከት ቀዳሚው ዓላማ መሆኑን አብራርተዋል ።

  በተለይም በእንስሳት፣ በአሳ ሀብት ምርት እንዲሁም በግብርናና በብዝሃ-ህይወት ላይ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ያካሂዳል ብለዋል ዶክተር ኤሊያስ ።

  የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት፣ ብዘሃ-ህይወት፣ ብዘሃ-ባህል እና አግሮ ኢንዱስትሪ ላይ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው የምርምር ማዕከሉ መቋቋም ተጨማሪ አቅም እንደሚሆንም ነው የገለጹት ።

  ከተለያዩ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ማዕከላት ጋር በጋራ መስራት ዩኒቨርስቲው በልህቀት ማዕከልነት የሚሰራቸውን ተግባራት ለማሳካት አጋዥ እንደሆነም ተናግረዋል ።

  በምልከታው ከአገር ውስጥ ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣አዲስ አበባና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ከውጭ ደግሞ ከካናዳ፣አሜሪካ-ሚቺጋን እና ኬኒያ-ማሴኖ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ የብዝሃ ህይወት ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል ።

  ምንጭ:-ኢዜአ

  November 22, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በአዳማ የተገነባው አዲስ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ።

  ተቋሙ ጣቢያውን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለተውጣጡ ጋዜጠኞች አስጎብኝቷል።

  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስፈጻሚ ክብሮም ካህሳይ እንዳሉት ጣቢያው 250 ሜጋ ዋት ሃይል ለማቅረብ የሚያስችል ነው።

  ጣቢያው በዋናነት ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ሃይል እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው እንደሚሉት ለፕሮጀክቱ ግንባታ 13 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ተጨማሪ 150 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን ወጪውን ሙሉ በሙሉ የሸፈነው መንግስት ነው።

  ጣቢያው በአሁኑ ወቅት ሃይል ማቅረብ መጀመሩን አመልክተው የአዳማን ሃይል አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ ነው ብለዋል።የዘገበው ኢዜአ ነው።

  November 22, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ኢትዮጵያውያኑ በሶስት ዙር በረራ ከሳዑዲ አረቢያ ጅዳ መመለሳቸው ተነግሯል።

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

  አምባሳደር ብርቱካን በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ የአረብ ሀገራት በመሄድ በችግር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ለመመለስ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሲሰራ ቆይቷል።

  በዚህም እስከሁን በተለያዩ ዙሮች ከ70 ሺህ በላይ ዜጎችን መመለስ መቻሉን ነው የጠቀሱት።

  በአሁኑ ዙር 30 ሺህ ዜጎችን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁመው ዛሬ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የዚሁ አካል ናቸው ብለዋል።

  November 21, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በቅርቡ የፈነጠቀው የሰላም ሂደት ስር እንዲሰድ ሁሉም በጋራ መስራት እንዳለበት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ጉባዔ አባላት ጋር እየተወያየ ነው።

  የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ከተቋቋመ 8 ወራትን ያስቆጠረው ኮሚሽኑ የዝግጅት ምዕራፉን እያጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።

  በቀጣይ በክልልና በዞኖችና ቅርንጫፎችን የመክፈት፣ አወያይና አመቻቾችን ለይቶ ስልጠና የመስጠትና የአጀንዳ ልየታ ስራዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል።

  ኮሚሽኑ ዓላማው ለኢትዮጵያዊያን ያለመግባባት መንስኤ የሆኑና ለአገር ዕድገት ሳንካ የሆኑ መሰረታዊ ችግሮች ላይ በመመካከር የጋራ አገራዊ መግባባት መፍጠር ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ እስካሁን በኢትዮጵያ ከሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጋር መወያየቱንም በማስታወስ።

  የኢትዮጵያ ሀገር ሽማግሌዎች አገራዊ ስርዓትን ማስቀጠልን ጨምሮ በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ቦታ እንዳላቸው ነው ፕሮፌሰር መስፍን የገለጹት።

  ኮሚሽኑ የሕዝብና የአገር ጥቅም ካስቀደሙ አባቶች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ገልፀዋል። በቅርቡ የፈነጠቀው የሰላም ሂደት በቀጣይነት ስር እንዲሰድ ሁሉም በጋራ መስራት እንዳለበት ጠቁመዋል።

  በውይይቱ መክፈቻ የኢትዮጵያ አገራዊ ኮሚሽኑ የእስካሁኑ ተግባራት እና ቀጣይ ስራዎች አስመልክቶ ለሀገር ሽማግሌዎቹ ገለጻ ተደርጓል።

  November 21, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት አባል ሌፍተናንት ጀነራል ኢብራሂም ጃብር የተመራ ልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ተቀብለው በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ማነጋገራቸው ተገለጸ።

  ሁለቱ ወገኖች በጋራ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

  November 21, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ለትምህርቱ ዘርፍ ማነቆ ናቸው ተብለው በጥናት በተለዩ አራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፡፡

  በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ ባለው 31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ የትምህርት ጥራት ችግርን ለመፍታት እንደ ሃገር የተዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ መሰረት ያደረጉ የለውጥ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው።

  የመምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና በትምህርት ዘርፍ የተሳተፉ አካላትን ሙያዊ ብቃት ማሳደግ ከትኩረት አቅጣጫዎች ቀዳሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

  በዚህም ካለፈው ዓመት ጀምሮ ለ4 ሺህ 300 ርዕሳነ መምህራን ተግባራዊ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ጠንካራ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ለመገንባት ጅምሮች መኖራቸውንም ጠቁመዋል። ፕሮፌሰር ብርሀኑ እንዳሉት ሌላኛው በትምህርት ዘርፉ የታየው ክፍተት የሞራል ስብራት ነው።

  ያለእውቀት የትምህርት ማስረጃ እስከማግኘት የደረሰ ህገወጥነትና ሙስና በዘርፉ እየታየ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህን ለማረም የግብረ ገብ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል።

  የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን በዘንድሮ ዓመት መጀመር፣ በተለያዩ ደረጃ የሚሰጡ ምዘናዎችን ከኩረጃ ነጻ እንዲሆኑ በቴክኖሎጂ ማስደገፍ የሞራል ስብራቱን መጠገኛ መንገድ መሆናቸውንም አስረድተዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

  November 19, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የነዳጅ ድጎማ ማሻሻያ የመንግስትን ወርሃዊ ኪሳራ ከ10 ቢሊዮን ወደ 4 ቢሊዮን ብር ዝቅ ማድረጉን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ገለፀ፡፡

  ባለፉት ሶስት ወራት በነዳጅ ማደያዎች ላይ በተጣለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱንም ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡

  የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ከሶስት ወራት በፊት ተግባራዊ የሆነው የታለመለት ነዳጅ ድጎማ ማሻሻያ በዘርፉ እምርታ እያመጣ ነው።

  ለአብነትም መንግስት በየወሩ በነዳጅ ድጎማ ይደርስበት የነበረውን ኪሳራ ከ10 ቢሊዮን ወደ 4 ቢሊየን ብር መቀነስ መቻሉን ገልጸዋል። መንግስት እስካሁን በነዳጅ ድጎማ 179 ቢሊዮን ብር ዕዳ ወይም ኪሳራ እንዳለበት ጠቅሰው፤ የድጎማው ሂደቶች እየተስተካከሉ ሲመጡ ቀስ በቀስ ዕዳውን መቀነስ ያስችለዋል ብለዋል። መንግስት ለነዳጅ ግዥ የሚያወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ እንደ ፖሊሲ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ማበረታቻዎች ተግባራዊ እንደሚደረግም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

  ቴክኖሎጂን በመጠቀም የነዳጅ ተደራሽነት ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሯ ጠቅሰዋል። በዚህም ነዳጅ በሚያመላልሱ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችና ነዳጅ ማደያዎች ላይ ቴክኖሎጂዎችን በመግጠም ቁጥጥር ስራውን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። መንግስት ከዓለም የነዳጅ ገበያ ዋጋ አንጻር አሁንም ድጎማ እንደሚያደርግ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ለአብነትም በዓለም አቀፍ ዋጋ ቢሆን ኖሮ አሁን ላይ ናፍታ 81 ብር፤ ቤንዝን ደግም 66 ብር በሊትር ይሸጥ ነበር ብለዋል።

  ከድጎማ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ በታሪፍና መሰል ጉዳዮች ላይ አሁንም በተለይ በክልል ዋና ዋና ከተሞች የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ባለስልጣኑ ከክልሎች ጋር እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ተቋሙ በነዳጅና ኢነርጂ ዘርፍ ላይ ብቁ ተቆጣጣሪ ለመሆን ተቋማዊ አደረጃጀት ማሻሻያዎች መደረጋቸው እና የተዘጋጀው ቁጥጥር ማዕቀፍም በካቤኒ ውሳኔ ማግኘቱን ተናግረዋል።

  November 18, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትየጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ያለበትን ደረጃ እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡

  በውይይቱ የፌደራል፣ የክልል፣ የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የንግድ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

  በውይይቱ ኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ አጠቃላይ ገጽታ የሚያሳይ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት መሆኑን የኢዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

  የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል÷ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ጥሩ ውጤት መታየት ጀምሯል ብለዋል።

  በዚህም ወደ ዘርፉ በርካታ ኢንቨስትመንት መሳብና የተዘጉ ኢንዱስትሪዎች እንዲያመርቱ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል።

  November 18, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የኢትዮ- ኬንያ ባለ 500 ኪል ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያ ዛሬ በይፋ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ጀምሯል፡፡

  ኃይል ማስተላለፍ የጀመረው የኢትዮ - ኬኒያ ባለ 500 ኪል ቮልት የማስተላለፊያ መስመር በዓመት እስከ 100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ የማስገባት አቅም ያለው ሲሆን ከኬንያ አልፎ ከታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ላሉት ሀገራት እስከ 2ሺህ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ማስተላለፍ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

  ኢትዮጵያ ቀደም ብላ ከሱዳን እና ከጅቡቲ ጋር የኃይል ሽያጭ የጀመረች ሲሆን፥ ከሶማሌ ላንድ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርማለች።

  በዚህም ባለፈው ዓመት ለሱዳን እና ለጅቡቲ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል 95 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶሊር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ለኢዜአ የላከው መግለጫ ጠቁሟል፡፡

  November 17, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋም ሙስና ሀገርን የሚበላ ነቀዝ ነው፡፡ የሀገርን አንጡራ ሀብት እየቦረቦረ ጥሪቷን ባዶ ለማስቀረት ሌት ተቀን የሚማስን ተባይ ነው። ዋልጌ ባለሥልጣናት፣ በፍቅረ ነዋይ የታወሩ ደላሎች እና ባለሃብቶች አንድ ላይ ሲገጥሙ፤ ከነዚህ የሌብነት ፊታውራሪዎች ጀርባ ብዛት ያላቸው ዜጎች መሰለፍ ሲጀምሩ ሙስና የተባለው ነቀዝ ሀገርን እንደ ወረርሽኝ ያጠቃታል፡፡

  ሙስና በየትኛው ቦታና በየትኛውም ዘመን ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የሀገርን ልማት አጥንቱ ድረስ እስከ መጋጥ ከደረሰ ሙስና አንድ አደገኛ ወረርሽኝ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ሙስና ሀገርን ሊያፈርስ የሚችል የደኅንነት ሥጋት መሆኑን ያስመሰከሩ ሀገሮችን በዘመናችን አይተናል፡፡ የአደንዛዥ ዕጽ፣ የኮንትሮባንድ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ንግድ፣ የንግድ ማጭበርበር ሙስናን ለዓላማቸው ማስፈጸሚያነት ይፈልጉታል፡፡ በዓለማችን የተጀመሩ ጦርነቶች እንዳይጠናቀቁ፤ ግጭቶች እንዳይበርዱ፣ ሕዝቦች እርስ በርስ እንዲጋጩ፣ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች አንዱ ሙሰኞች ከዚህ አይነት ቀውሶች ስለሚያተርፉ ነው፡፡

  ሙስና ዛሬ የሀገራችን የደኅንነት ሥጋት ሆኗል፡፡ ወደ ብልጽግና የምናደርገውን ጉዞ እጅ ተወርች አሥሮ ለመያዝ ከጠላቶቻች እኩል ሙሰኛው እየታገለን ነው፡፡ የተስተካከለ ቢሮክራሲ፣ የተቀናጀ መዋቅርና ዘመናዊ አሠራር ለሙስና ተጋላጭነትን ስለሚቀንሱ፣ እነዚህን ለማጥፋት ወይም ለማሰናከል ሙሰኛው ቀን ከሌት እየሠራ ነው፡፡ሕዝባችን በአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከመሬት ጋር በተያያዙ አሠራሮች፣ በፋይናንስ ዘርፍ፣ በሽያጭና ግዥ ሂደቶች፣ በፍትሕ አደባባዮች፣ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት፣ የልማት ድርጅቶች፣ የህዝብ ተቋማት ወዘተ. በሚያጋጥመው ሙስና እየተማረረ ነው፡፡

  በተለያዩ ጊዜያት ከሕዝብ ጋር በተደረጉ ውይይቶች ከጸጥታ ሥጋቶች እኩል ሙስና የብልጽግና ጉዟችን ዋናው ዕንቅፋት መሆኑን አንሥቷል፡፡

  መንግሥት በየደረጃው የሚገኘውን መዋቅር በመፈተሽ፣ አዳዲስ አሠራሮችን በመዘርጋት፣ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥራዎችን እያሳለጠ ሥራዎችን ከእጅ ንክኪ ነጻ በማድረግ፣ በሙስና ወንጀል የሚሳተፉ አመራሮችንና ሌሎች ተዋንያንን ለሕግ በማቅረብ፣ ሙስና ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠርለት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ሀገራችን ያጋጠማትን ጦርነትና ኮሮናን የመሳሰሉ ወረርሽኞች የመንግሥትን ትኩረት ወስደዋል ብለው ያሰቡ ሙሰኞች፣ በየቦታው ተሠግሥገውና ኔት ወርክ ዘርግተው፣ ኢትዮጵያን ለማጥፋት እየሠሩ መሆናቸውን በዝርዝር የቀረበው የጥናት ሪፖርት ያሳያል፡፡

  መንግሥት በጸጥታው ዘርፍ እንዳደረገው ሁሉ በሙስና ላይ ጠንካራና የማያዳግም ኦፕሬሽን ማድረግ እንዳለበት የጥናቱ ውጤትና የሕዝብ ውይይቱ ግምገማ ያመለክታል፡፡ በአንድ በኩል የመንግሥት ሕጎች፣ደንቦች፣ መመሪያዎችና አሠራሮች ለሙስና ያላቸውን ተጋላጭነት የማጥፋት ሥራ ይሠራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሙስና ተዋንያንን የማጋለጥና በሕግ የመጠየቅ ተግባር ይከናወናል፡፡ መንግሥት በጥናት በደረሰባቸው የመንግሥት ሹመኞች፣ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች፣ አቀባባዮችና ጉቦ ሰጪዎች ላይ ምርመራ እያደረገ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ሙስና በባሕርዩ በረቀቀ መንገድ፣ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ አንዳንድ ጊዜም በሕጋዊነት ሽፋን የሚካሄድ በመሆኑ በመንግሥት ጥናት የተደረሰባቸው አካላትን ብቻ ለሕግ በማቅረብ የሚፈታ አይደለም፡፡

  ሙስናን ከሥር ከመሠረቱ ለመንቀል እንዲቻል ከሕግና ከአሠራር ማሻሻያዎች በተጨማሪ፣ የሙስና ተዋንያን ሁሉ ሙስናን እርም እንዲሉ የሚያደርግ ርምጃ ያስፈልጋል፡፡መንግሥት በሙስና ላይ የሚያደርገውን ዘመቻ የሚያስተባብር፣ በጥናት ተለይተው ከቀረቡት በተጨማሪ ሌሎችንም ተዋንያን የሚለይና ለሕግ እንዲቀርቡ የሚያደርግ ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡

  ብሔራዊ ከሚቴው ሰባት አባላት ያሉት ሲሆን፣ እነርሱም፡- 1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ 2. ዶ/ር ጌዴዎን ጢሞቴዎስ 3. አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ 4. አቶ ሰሎሞን ሶቃ 5. አቶ ደበሌ ቃበታ 6. ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ 7. አቶ አብዱሃሚድ መሃመድ ናቸው፡፡ ይህ የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣትና ትርጉም ያለው ውጤት ለማምጣት እንዲችል የኅብረተሰቡ ሙሉ ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ኅብረተሰቡ በሙስና ላይ በሚደረገው ዘመቻ ሊሳተፍ እንደሚገባ በተለያዩ መድረኮች ሲያነሣ ቆይቷል፡፡ መንግሥትም ይሄንን የሕዝብ ተሳትፎ በእጅጉ ይፈልገዋል፤ ምክንያቱም ሙስና በዋናነት የሚጠፋው ሕዝብ አምርሮ ሲታገለው ነውና፡፡

  በመሆኑም ኅብረተሰቡ የሙስና ተዋንያንን በተመለከተ ያለውን መረጃ፣ ከቂምና ከበቀል ነጻ በሆነ መንገድ፣ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አድራሻዎች ለብሔራዊ ኮሚቴው በመላክ ሙስናን ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን፡፡

  የሚቀርቡ ጥቆማዎች የጠቋሚዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እና ሚስጥራዊነት በጠበቀ መንገድ ተይዘው ይመረመራሉ። ብሄራዊ ኮሚቴው የሚወስዳቸው እርምጃዎች እና የእንቅስቃሴው ውጤት በየጊዜው ለህዝብ ይፋ ይደረጋል። የየክልሉ ርእሳነ መስተዳድሮች በየደረጃው የሚሠሩ ክልላዊ ኮሚቴዎችን በቅርቡ እንደሚያቋቁሙ በዚሁ አጋጣሚ እንገልጣለን።

  November 17, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሰብዓዊ ድጋፍን በፍጥነት ለማድረስ እንዲቻል አራት ቡድኖች ተቋቁመው ወደ ተግባር መሸጋገራቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

  የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
  የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ በሰጡት መግለጫ በሰላም ስምምነቱ መሰረት ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል በአፋር በኩል ካለው መንገድ በተጨማሪ ሌሎችም መከፈታቸውን ገልጸዋል።

  የሰብዓዊ ድጋፉ በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆንም በአራት አቅጣጫ በኩል ድጋፉን የሚያስተባብሩ አራት ኮሚቴዎች ተቋቁመው ወደ ተግባር መግባታቸውንም ተናግረዋል። የሰብዓዊ ድጋፉን በፍጥነት ለማድረስም በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልፀው በአሁኑ ጊዜም በተለያዩ ቦታዎች ተደራሽ በመሆን ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

  ከጥቅምት 20 ቀን እስከ 27 ድረስም በመጀመሪያ ዙር በሽሬ፣አክሱም ፣ ሰለክለካ እና በዚህ አቅጣጫ ለሚገኙ ሌሎች አካባቢዎች ለ108 ሺ ዜጎች ስንዴ እና አልሚ ምግቦች ድጋፍ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

  በተጨማሪም በአላማጣ በኩል ባሉ የተለያዩ አከባቢዎች በመጀመሪያ ዙር ለ287ሺህ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ መደረጋቸውን ጠቁመዋል።

  በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው መሰረት ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እና አገልግሎት ለማስጀመር መንግስት ቁረጠኛ ነው ብለዋል። በዚህም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ባልተጀመረበት አከባቢዎች ለማስጀመር እየተሰራ ነው ብለዋል።

  አሁን ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ካገኙ ከተሞች በተጨማሪ በቅርቡ በርካታ አከባቢዎች ላይ ተደራሽ ለማድረግ የጥገና ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

  November 10, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳና ገላና ወረዳዎች እንዲሁም በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ አጎራባች ቀበሌዎች ህዝቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን የጸጥታ ችግር ከሁለቱም ወገን በተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት ነው በእርቅ የመፍታት ስነ ስርዓት እየተካሔደ የሚገኘው።

  ከዚህ ቀደም በሁለቱ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የቀጠናውን ሰላም ለማወክ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሀይሎች በፈጠሩት ችግር ለበርካታ ዜጎች ሞት፣ለአካል ጉዳት፣ለንብረት ውድመት እና ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኖ መቆየቱ ተጠቁሟል።

  ከምዕራብ ጉጂ እና ከአማሮ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌያት የተውጣጡ የመርሐ ግብሩ ታዳሚዎች እንደገለጹት የጉጂ ኦሮሞ እና የኮሬ ህዝቦች ለዘመናት የቆየ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ናቸው። የሁለቱ ህዝቦች የቆየ መልካም ግንኙነት ያላስደሰታቸው አካላት የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።

  በዛሬው እለት የሚካሔደው እርቅ በጉጉት ሲጠብቁት እንደነበር የተናገሩት ነዋሪዎቹ የቀጠናውን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ላይ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል። በጉጂ እና በኮሬ ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም ማስፈንን መሰረት ባደረገው በዚህ የእርቅ ፕሮግራም የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የጸጥታ አካላት ተገኝተዋል።

  November 10, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • አለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ለሰላም ስምምነቱ ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ አጋርነቱን እያሳየ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጸ።

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ መለሰ አለም በሳምንታዊ መግለጫው እንዳስታወቁት÷ በአለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ በሳምንቱ የተሰሩ አንኳር ጉዳዮችን ዳሰዋል።

  አለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በመንግስትና በህወሓት መካከል በተፈረመው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ በዚህም የተለያዩ ሀገራት፣የአለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ክፍለ አህጉራዊ ድርጅቶች፣ አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት መንግስትና ህወሓት ግጭቱን ለመፍታት የደረሱበትን ስምምነት በአዎንታ እንደሚቀበሉና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጡ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል።

  በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደሚያደርጉም መግለጻቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

  November 9, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የክብር ዶክተር አርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ሽኝት መርሐግብር በወዳጅነት አደባባይ በመካሄድ ላይ ነው።

  አስክሬኑ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተሸኝቶ በአሁኑ ሰዓት ወዳጅነት አደባባይ ደርሷል።
  በመርሐግብሩ ላይ የፌዴሬሽን አፈ-ጉባኤ አገኘው ተሻገር፣ የብልጽግና ፖርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሃር እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሞያ አጋሮቹ ተገኝተዋል።

  የክብር ዶክተር አርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ዛሬ ማለዳ ቢሾፍቱ ከሚገኘው ቤቱ ሽኝት ተደርጎለታል። ከወዳጅነት አደባባይ የክብር ሽኝት በኋላ ለአስክሬኑ በድሬዳዋ ከተማ አቀባበል የሚደረግ ሲሆን፤ በድሬዳዋ ስታዲየም የጸሎት ፕሮግራም ተደርጎ ስርዓተ ቀብሩ በከተማዋ ለገሀሬ እስላም መቃብር እንደሚፈጸም ተገልጿል።

  ክብር ዶክተር አርቲስት ዓሊ ቢራ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በ75 ዓመቱ ከትናንት በስቲያ ሕይወቱ ማለፉ ይታወቃል።

  አርቲስቱ ስለአንድነት ፣አብሮነት ፣ፍቅር ፣ሰላምና ፍትህን ጨምሮ በበርካታ ስራዎች ላይ አቀንቅኗል።

  November 8, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ለአርቲስት አሊ ቢራ አስክሬን በነገው ዕለት የጀግናና የክብር ሽኝት እንደሚካሄድ ብሄራዊ የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴው አስታወቀ።

  ለታላቅ አርቲስት አሊቢራ የጀግና ሽኝት እንደሚደረግለት የተገለጸ ሲሆን ፤ ለዚህም ከፌዴራል ፣ከኦሮሚያ ክልል፣አዲስ አበባ እና ከድሬደዋ ከተማ የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሟል ።

  የኮሚቴው አባል አቶ ሞገስ ኢዳኤ እንዳሉት ነገ ጠዋት ከመኖሪያ ቤቱ ከቢሾፍቱ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ከተደረገ በኋላ በወዳጅነት አደባባይ የሽኝት ፕሮግራም ይደረጋል ። ቀጥሎም በድሬዳዋ አቀባበል ከተደረገ በኋላ በድሬዳዋ ስታዲየም የጸሎት ፕሮግራም በማድረግ ስረዓተ ቀብሩ በከተማዋ ለገሀሬ እስላም መቃብር ይፈጸማል ብለዋል።

  የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒሰትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው አርቲስቱ ለ60 ዓመታት በአርቱ ላሳለፈው ትልቅ ስራ የጀግና ሽኝት ይደረግለታል ነው ያሉት ።

  አርቲስቱ ስለአንድነት ፣አብሮነት ፣ፍቅር ፣ሰላምና ፍትህን ጨምሮ በበርካታ ስራዎች ላይ ማቀንቀኑን አስታውሰዋል።

  November 7, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ ታጣቂዎች አዛዦች ናይሮቢ ላይ ተገናኙ።

  በሰላም ስምምነቱ ውስጥ በ5 ቀን ውስጥ ወታደራዊ አመራሮች እንዲገናኙ በሚያዘው መሠረት አዛዦቹ ውይይት ዛሬ በናይሮቢ ተጀምሯል ።
  እስከ አሁን በስምምነቱ ሂደቱ በመልካም ሁኔታ እየሄደ ነው።

  November 7, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡

  ከ50 ዓመታት በላይ በሚዚቃው ኢንዱስትሪው የቆየው ድምጻዊው ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

  በዛሬው ዕለትም የአርቲስቱ ህልፍተ ህይወቱ መሰማቱን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚህም ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በአርቲስቱ ህልፈተ ህይዎት የተሰማውን ሃዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡

  November 6, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሁለት ወር የግንባር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጠቅላይ መምሪያ ቢሯቸው እንደተመለሱ ተገልጿል።

  መንግሥት ከህወሓት ጋር ያደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ነው የግንባር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮአቸው የተመለሱት።

  የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በማሕበራዊ ትስስር ገጹ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከውጊያ ኮማንድ ፖስት ወደ መደበኛ ማዘዣ ቢሮአቸው ከተመለሱ በኋላም በመንግሥት እና በህወሓት በተደረገው ስምምነት መሰረት በጥቂት ቀናት ውስጥ ከህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ አመላክቷል።

  November 5, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ኢትዮጵያ ለስንዴ ልማት የሰጠችው ትኩረት ከአገር ውስጥ ባለፈ በዓለም ገበያ ያለውን የስንዴ ምርት እጥረት ለመቅረፍ እገዛ እንደሚያደርግ በኢትዮጵያ የፈረንሳይና የብርታኒያ አምባሳደሮች ተናገሩ፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በአዲስ አበባ ከሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በምእራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ እየተካሄደ ያለውን የስንዴ ምርት አሰባሰብ ሂደት ጎብኝተዋል።

  በጉብኝቱ ከተሳተፉት መካከል በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር አልስቴር ማክፔል፣ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን ኦዎር እንዲሁም በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አውጉስቲኖ ፓሌስ እና ሌሎች የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ይገኙበታል፡፡

  በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ ኢትዮጵያ ለስንዴ ልማት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኗን በጉብኝታቸው መመልከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

  በዓለም የጂኦ ፖለቲካ መለዋወጥ ምክንያት ሰንዴን ጨምሮ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ እጅግ እየናረ መምጣቱን ጠቅሰው፤ይህም ለዓለማችን ወቅታዊ ፈተና ሆኗል ነው ያሉት፡፡

  ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ ለስንዴ ምርት ትኩረት ሰጥታ መስራቷ የሚደገፍ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ የፈረንሳይ ኩባንያዎች በተለይ በኢትዮጵያ በቢራ ገብስ ምርት ላይ መዋለ ንዋያቸውን በግብርናው ዘርፍ እያዋሉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

  በኢትዮጵያ የብሪታኒያ አምባሳደር አልስቴር ማክፔል በበኩላቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ የስንዴ ምርት እጥረት መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህም እንደ ኢትዮጵያ ሌሎች ሀገራት በራስ አቅም ስንዴን በማምረት ለወጪ ንግድ ለማቅረብ ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

  ብሪታኒያ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርናው መስክ የተሻለ ትብብር እንዳላት ጠቅሰው፤ በቀጣይ ይህ ትብብር ሊጠናከር ይገባል ነው ያሉት፡፡ ከዚህ አኳያ በርካታ የብሪታኒያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ሊሰማሩ እንደሚገባ መክረዋል፡፡

  በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በግብርና መካናይዜሽን ወጤታማ ስራ እያከናወነች መሆኗን ተናግረዋል፡፡ የግብርና መካናይዜሽን በተለይ በምርት ወቅት የሚከሰትን የምርት ብክነት በመከላከል ምርታማነትን እንዲጨምር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነት ወደተሻለ ደረጃ እያደገ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡

  ኢትዮጵያ ከመኸር በተጨማሪ ለበጋ ስንዴ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ሲሆን፤ በዘንድሮው የበጋ ወቅትም በአገር አቀፍ ደረጃ በ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ በኩታ ገጠም ስንዴ በማልማት 52 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እቅድ ተይዟል፡፡ በዘንድሮው ዓመትም የስንዴ ምርትን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

  November 5, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ሀገሪቱ የጀመረችው የፀረ ሙስና ትግል ፍሬያማ እንዲሆን የተቋማት የሥራ ሃላፊዎች ቁርጠኝነት እና ተሳትፎ ሊጎለብት እንደሚገባ የፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ የፌደራል የመንግስት ባለስልጣናት የሥነ-ምግባር ረቂቅ ደንብ እና የባለስልጣናት የጥቅም ግጭትን ለመከላከል፣ ለማስወገድ እና ለማስተዳደር የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል። ረቂቅ ደንቦቹ ባለስልጣናቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በአግባቡ እና ስነ-ምግባርን በተላበሰ መልኩ እንዲወጡ የሚያስችሉ መሆናቸው በውይይቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡ በተጨማሪም የሥራ ሃላፊዎች የሀገር እና የህዝብን ሀብት ከሙስና በፀዳ መልኩ እንዲጠቀሙ እና ተጠያቂነትን ለማስፈን መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡ የፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ፤ ሙስና በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህራዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህንም ለመቅረፍ መንግስት እንደ ሀገር ትኩረት አድርጎ እየሰራ ካለባቸው ጉዳዮች አንዱ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በፀረ ሙስና ትግሉ የስራ ሃላፊዎችን ንቁ ተሳታፊ ለማድረግ የባለስልጣናት የሥነ-ምግባር ረቂቅ ደንብ እና የባለስልጣናት የጥቅም ግጭትን ለመከላከል የሚያግዙ ረቂቅ ደንቦች መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡ የኮሚሽኑ የሕግ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሻው ረቂቅ ደንቦች በሀገሪቱ የሚስተዋሉና ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ያግዛሉ ብለዋል፡፡ በረቂቅ ደንቡ ሁለት አዳዲስ ድንጋጌዎች መካታተቸውን በመጥቀስ፤ ባለስልጣናት ከሃላፊነት ከለቀቁ በኋላ ሊኖራቸው ስለሚገባ ስነምግባር እና ሚስጥር ጠባቂነት የሚዘረዝር ድንጋጌ መኖሩን አመላክተዋል። ሌላኛው የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች የተሰጣቸውን ሀገራዊ ግዴታ ከፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው ጋር አስታርቀው መሄድ የሚችሉበትን መንገድ የሚደነግግ ስለመሆኑም ጠቁመዋል። በውይይቱ የተሳተፉ የተቋማት ተወካዮች፤ ረቂቅ ደንቦቹ ሃላፊነት ላይ የተቀመጡ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ህዝብ እና መንግስት የጣሉባቸውን አደራ በአግባቡ እንዲወጡ ያስችሏቸዋል ነው ያሉት፡፡ የወጡት ሁለት ረቂቅ ደንቦች ጸድቀው ወደ ተግባር እንዲገቡ በመጠየቅ፤ ለዚህ ደግሞ የተቋማት የሥራ ሃላፊዎች ቁርጠኝነትን ይጠይቃል ነው ያሉት። ረቂቅ ደንቦቹ ተቋማቸው በየጊዜው ለሚያደርገው የቁጥጥር ስራ አጋዥ መሆናቸውን ያነሱት ደግሞ የፌደራል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሰረት ዳምጤ ናቸው ስል ኢዜአ ዘግቧል።

  October 31, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ

  በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረው የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተጠናቋል።
  ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በሁለት ዙር ሲሰጥ በነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ900 ሺህ በላይ ተማሪዎች በ130 የፈተና ጣቢያዎች ተፈትነዋል።

  ፈተናው በመጀመሪያዉ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሂደት ካጋጠሙና በመጀመሪያዉ ዙር ማጠቃለያ ከተገለጹ ችግሮች ዉጪ በታቀደው መሰረት በስኬት የተጠናቀቀ ሲሆን የሁለተኛ ዙር ተፈታኞችም ከዛሬ ጀምሮ ወደ የአካባቢያቸው መመለስ ጀምረዋል። ዩኒቨርስቲዎች ለፈተናው ውጤታማነት ያደረጉት ዝግጅት እና በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ የነበራቸው አስተዎፆ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን ተፈታኞችም የፈተና ስርዓቱን ባከበረ መልኩ ፈተናቸውን ሲወስዱ ቆይተዋል።

  ለዚህም የትምህርት ሚኒስቴር ለወላጆች፣ ተፈታኝ ተማሪዎች እና ፈታኝ መምህራን ፣ጣቢያ አስተባባሪዎች ፣ሱፐርቨይዘሮች ፣ የጸጥታ አካላት እና በየደረጃው ለፈተናው ስኬታማነት የበኩላቸውን ለተወጡ አካላትም ላቅ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።

  የዘንድሮው የፈተና አሰጣጥ ሂደት የፈተና ስርቆት እና ኩረጃን በማስቀረት ሂደት የነበረው አስተዎፆ ውጤታማ መሆኑ የታየበት እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል።

  በቀጣይም የፈተና አሰጣጥ ስርዓቱን በማሻሻል የተሻለ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድን ለመፍጠር በትኩረት የሚሰራ ይሆናል።

  ከየኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ኦፊሰላዊ ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ

  October 21, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ከውጭ በሚገቡ 38 ምርቶች ላይ ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንዳያገኙ ገደብ መጣሉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።

  ባንኩ ውሳኔውን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
  የባንኩ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት ፍቃዱ ደግፌ እንደገለጹት ቅድሚያ የማይሰጣቸውና ከውጭ ለሚገቡ 38 ምርቶች የውጭ ምንዛሬ እዳይፈቀድ ተወስኗል።

  ውሳኔው ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ መሆኑን ጠቁመው ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

  የውጭ ምንዛሬ እገዳ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል ለስራ አገልግሎት የማይውሉ መኪናዎች፣ ሰው ሰራሽ ጸጉር፣ ጌጣጌጦች፣ የቡስኩትና የመሳሰሉ ምርቶቸን ይገኙበታል።

  እገዳ የተጣለባቸውን ምርቶች ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ መጠየቅ እንደማይቻል ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስቱ ተናግረዋል።

  October 14, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በክረምቱ የእረፍት ጊዜ ከ2 ሺህ 200 በላይ መዛግብት የውሳኔ እልባት እንዲያገኙ ማድረጋቸውን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ ተናገሩ።

  በእረፍት ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ዝግ ሆኖ የቆየው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት የፌዴራል የመጀመሪያ፣የከፍተኛና የጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

  የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ፤ የዳኝነት አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት መልእክት አስተላልፈዋል።

  በ2014 ዓ.ም ስራ ዘመን 25 ሺህ 480 መዛግብት ቀርበው 18 ሺህ 979ዎቹ ውሳኔ ማግኘታቸውን አስታውሰዋል። በዳኝነትና አስተዳደር ስራ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚረዱ በርካታ መመሪያዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን ተናግረዋል። ባለፈው የስራ ዘመን 6 ሺህ በላይ መዝገቦች ለ2015 እንዲተላለፉ ቢወሰንም ዳኞች በክረምቱ የእረፍት ጊዜያቸው በሰጡት አገልግሎት ከ2 ሺህ 200 በላይ መዝገቦች እልባት እንዲያገኙ አድርገዋል ነው ያሉት።

  በዛሬው እለት እየተካሄደ ባለው የ2015 የስራ ዘመን ችሎት ማስጀመሪያ ስነ ስርአት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ከ270 በላይ መዝገቦች እንደሚታዩ ገልፀዋል።

  የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሰለሞን አረዳ፤ ባለፈው በጀት ዓመት የዳኝነት አገልግሎት ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ እንዲሆን በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል። በ2015 የስራ ዘመንም ዳኞች በነፃነትና ያለምንም ጣልቃገብነት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ፤የዳኝነት ጥራትን የማሳደግ ስራም ልዩ ትኩረት ይደረግበታል ብለዋል።

  የዳኝነት ዕውቀትና ክህሎት ማሳደግ፣ በስነ ምግባርን የተሞላ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት በመስጠት ውጤታማ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

  October 11, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄደበት በዛሬው ዕለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በመወያየት አጽድቆታል።

  እቅዱን አስመልክቶ ከተከበሩ የምክር ቤት አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጥላሁን ከበደ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በተለይም ከማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎች ከበርካታ አካባቢዎች የሚቀርቡ ቢሆንም አብዛኛዎቹ ጥያቄዎች የክልሎችን መፍትሄ አሟጥጠው እንደማይመጡ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በምክር ቤቱ ውሳኔ ተሰጥቶባቸው እያለ በውሳኔው ባለመርካት በድጋሚ ጉዳያቸውን ይዘው የሚመጡ መሆኑን ጠቅሰው አንዳንዶቹ ግን ውሳኔ አግኝተው በአፈጻጸም መዘግየት ምክንያት የሚቀርቡ መሆኑን አስታውሰዋል።

  የተከበሩ ሰብሳቢው ከሰላም ግንባታ ጋር በተያያዘም ለቁርሾ ምክንያት የሚሆኑትን በመለየት መቅረፍ እንደሚገባና ሰላምን የሚያደፈርስ የውጭ ጣልቃ ገብነት ሲያጋጥም መላውን ኢትዮጵያውያን በማስተባበር በጋራ መመከት አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመው ችግሮችን ከመሠረታቸው ለመፍታት መወያየት፣ መመካከርና መናበብ እንደሚያስፈልግና በሕዝቦች መካከል ከልዩነት ይልቅ ወንድማማችነትን፣ አንድነትና ልዩነትን በማጉላት መሥራት እንደሚገባ አብራርተዋል።

  በመጨረሻም የተከበሩ አቶ ጥላሁን የሰላም ግንባታ ሥራ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሰፊ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ክልሎች በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል ።

  October 11, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • መንግስት የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የተጀመሩ ጥረቶችን በአዲሱም በጀት ዓመትም እንዲሚቀጥል የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።
  አሁንም የአፍሪካ ሕብረት ለሚያደርገውን የሰላም የጥረት መንግስት ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ብለዋል።
  6ኛው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን መክፈቻ ስነ-ስርዓት የጋራ ስብሰባ ተካሂዷል።
  በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የ2015 ዓ.ም ዋና ዋና የመንግስት አቅጣጫዎችን የሚያመላክት ንግግር አድርገዋል።

  መንግስት በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል ያለው ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ የገለጹት ፕሬዝዳንቷ፤ መንግስት ከሕወሓት ጋር የሰላም ውይይት የማድረግ ጥረቱን እንደሚገፋበት ጠቁመዋል።
  የሰላም ሂደቱን ለማስተጓጎል ለሚደረጉ ትንኮሳዎች መንግስት የማስታገሻ እርምጃ እንደሚወስድ ሊሰመርበት ይገባል ብለዋል።
  በአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አማካኝነት እየተደረገ ያለውን የሰላም ጥረት ስኬታማ እንዲሆን መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ከግጭት አዙሪት ወጥታ ዘለቄታዊ ሰላም እንድታገኝ ሁሉም ወገን የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ፕሬዝዳንቷ ጥሪ አቅርበዋል።
  የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሚያከናውነው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ሁሉን አሳታፊ ያደረገ እንዲሆን አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግለት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

  October 10, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • በዋቸሞ፣ በወልዲያ ፣ በጎንደር ፣በወላይታ ሶዶ እና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲዎች 69 ሺህ 238 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመፈተን ላይ ናቸው።
  በዩኒቨርሲቲዎቹ ፈተናው ሰላማዊ በሆነ መልኩ መሰጠት መጀመሩን የኢዜአ ሪፖርተሮች በስፍራው ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

  October 10, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚፈተኑ ተማሪዎች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል

  የሀገራችን የነገ ተስፋዎች ሆይ
  ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት። ይህ የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ። እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል። ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነው።
  የተሰጣችሁን መመሪያ አክብሩ፤ ተረጋግታችሁ ፈተናችሁን ሥሩ፤ በምንም አትሸበሩ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ።

  October 9, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በጅግጅጋ ማካሄድ ጀመረ።

  ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይገኛል።

  ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተወያይቶ የተለያዩ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

  ዘገባው የኤፍ ቢ ሲ ነው

  October 7, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞችን መቀበል ጀምሯል።

  የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ማጠናቀቂያ ፈተና እንዲወስዱ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመደቡ የመጀመሪያ ዙር የሶሻል ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በመግባት ላይ ናቸው።

  ከዩኒቨሪሲቲዉ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘዉ መረጃ እንደሚያመለከረተዉ ለተፈታኞች የመፈተኛ ክፍል፣ የምግብ እና የመኝታ፣ የሕክምና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን በበቂ ሁኔታ በማዘጋጀት ነው ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን መቀበል የጀመረው። መስከረም 30/2015 ዓ.ም ለሚጀመረው ብሔራዊ ፈተና ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገቡ ላሉ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች በፀጥታ አካላት ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገም ይገኛል።

  ዩኒቨርሲቲው ከመስከረም 27/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 28/2015 ዓ.ም ከወላይታ ዞን እና ከሀድያ ዞን የተመደቡ ከ19 ሺህ የሚበልጡ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎችን ይቀበላል። ተፈታኝ ተማሪዎች በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የሚኖራችሁ ቆይታ ያማረ፣ የሰመረ እንዲሁም በመልካም ውጤት የታጀበ እንዲሆን እንመኛለን።

  October 7, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • “የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት መጀመር አይሲቲን የብልጽግና ጉዟችን ሞተር አድርገን የመንቀሳቀሳችን ማሳያ ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

  የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት መጀመር ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን የብልጽግና ጉዟችን ሞተር አድርገን የመንቀሳቀሳችን ማሳያ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

  የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል።

  በመርሐ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የኩባንያው አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

  October 7, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከሚመራው የኬንያ ሪፐብሊክ ልዑካን ቡድን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ሁለቱ መሪዎች ተናግረዋል።

  October 6, 2022

  | ሀገራዊ ዜና

 • ሁልጊዜም ከመንጋቱ በፊት ድቅድቅ ጨለማ ይሆናል። በምሽትና በንጋት ሽግግር ውስጥ ያላለፈ ሀገርና ትውልድ የለም። ብርቱው ጨለማ የንጋቱ ጸዳል አብሳሪ ስለሆነ፣ መቼም ቢሆን “ይኼ ምሽት እንደ ጨለመ ቢቀርስ?” ወይንም ‘ንጋት ባይመጣስ?’ ብለን አንሠጋም።

  ንጋቱ አይቀሬ ነውና አስደንጋጩ ጨለማ በማለዳው የብርሃን ጸዳል ይዋጣል። የአዲሱ ቀን ጎሕ ሲቀድድ አስፈሪዎቹ አውሬዎች ወደየጎሬያቸው መግባታቸው፣ የሌሊቱም ቁር ለቀኑ ሙቀት ሥፍራ መልቀቁ አይቀሬ ነው። በቀን የተሰወሩት ከዋክብትም ቢሆኑ ከመቼውም ይልቅ ደምቀውና ጎልተው የሚታዩት ጨለማው ሲበረታና ሌሊቱ ከመንጋቱ በፊት ነው።

  በሕይወት ጉዟችንም ከጠበቅነው የተስፋ ንጋት ቀድሞ ጨለማ የሚመስል ፈተና ከፊታችን እንደ ጅብራ ሊደነቀር ይችላል። ፈተናው አዲስ እየመሰለን የስሜት መረበሽ ያጋጥመናል። በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በአስተዳደርና በሌሎች ማኅበራዊ ሂደቶች ሁሉ፣ ተግዳሮትና ፈተና ውስጥ ገብተን ራሳችንን እናገኛለን። ግለሰቦችና ቤተሰቦች፣ መንግሥታትና ሀገራት በጥፋት ሥጋት የህልውና ጥያቄ ውስጥ ገብተው በአጣብቂኝ ውስጥ ያልፋሉ።

  ጥያቄው ‘ይህ ጊዜ ያልፋል ወይስ አያልፍም?’ ሳይሆን ‘እንዴት ይታለፋል?’ ነው? ይህ ችግርና ተግዳሮት በጨለማው ውስጥ ደምቀውና አሸናፊ ሆነው ብዙዎችን አስከትለው ለሚወጡ ከዋክብት የድምቀትና የጀግንነት እድልም ነው።

  ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀደምት ታሪኳ ብዙ ክረምትና በጋዎችን፣ ጨለማና ብርሃንን ያፈራረቁ ውጣ ውረዶችንና እንቅፋቶችን አሳልፋለች። በገባችበት የክረምት አረንቋና የውድቅት ሌሊት የፈተና ሰዓት የቁርጥ ቀን ልጆችዋ “በክፉዎች ሤራ ተጠልፋ ትወድቅ ይሆን?” የሚል ሥጋት ቢገባቸውም፣ እጃቸውን አጣጥፈው ከመቀመጥ ይልቅ በተስፋ ጽናት በሕይወታቸው ተወራርደው ችግሯን ተጋፍጠውላታል። ጠላቶቿን ለማሳፈር አንገታቸውን ለሰይፍ፣ ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተዋል። በዚህም እንደ ጨለማ የበረቱት ጠላቶችዋ ሲወድቁ፣ እሷ አንገቷን ቀና አድርጋለች።

  ብዙ የዓለም ሀገራትም እኛ ዛሬ የምናልፍበት በሤራ የመጠለፍ አደጋና የመበታተን ሥጋት፣ በአንድ ወይንም በሌላ ዘመን ገጥሟቸው ያውቃል። እንደ ዩጎዝላቪያና ሶሪያ፣ ሶማልያና ሊቢያ ያሉ ሀገራት በሥጋታቸው ተጠልፈው ወድቀዋል። እንደ ጀርመንና ጃፓን፣ ኮርያና ቬየትናም ያሉት ሀገራት ደግሞ በተመሳሳይ ቀውስ ውስጥ አልፈው፣ ፈተናቸውን ፊት ለፊት ተጋፍጠው፣ ለጋራ ድል በአንድነት ሠርተው፣ ለስኬት ከበቁ ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ።

  እነዚህ ሀገራት ዛሬ በኢኮኖሚ ዐቅማቸውና በዘመናዊ የፖለቲካ አስተዳደራቸው፣ በቴክኖሎጂ ምጥቀታቸውና በማኅበራዊ ዕሴታቸው እጅግ ዘመናዊ ከሚባሉት ሀገራት መካከል የሚመደቡ ሆነዋል። አስቀያሚና ፈታኙን ቀውስ አይተው ተሻግረውታል። የገጠሟቸውን እንቅፋቶች እንደ መስፈንጠሪያ ነጥብ እየተጠቀሙ አሁን ካሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

  ለምሳሌ ጀርመን በሁለተኛው ጦርነት ማግሥት ወድቃና ተንኮታኩታ ነበር። ምሥራቅና ምዕራብ ጀርመን እየተባለች ለሁለት ተከፍላ ለመቆየት ተገድዳለች። ጊዜው ቢረዝምም በመጨረሻ ሕዝቦቿ ተባብረው የለያቸውን የድንጋይና የርዕዮተ ዓለም ግንብ አፍርሰውታል፡፡

  በ1860 አካባቢ ደም አፋሳሽ በሆነው የርስ በርስ ጦርነት ገብታ ሁለት ከመከፈል ለጥቂት የተረፈችው አሜሪካ ራሷ ከደረሰባት ጥፋትና የመበታተን አደጋ የዳነችው በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የልጆቿን ሕይወት ዋጋ ከፍላ ነው።

  በድህነት ላይ የእርስ በእርስ ጦርነትና የውጭ ጣልቃ ገብነት ክፉኛ ፈትኗት ሳትረታና ሳትፈታ በድል ያለፈችው የደቡብ ኮርያ ታሪክ ከሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በእጅጉ ተዛማጅ ነው። ዛሬ እኛ እያለፍን በምንገኝበት መንገድ ውስጥ ያለፉ፤ ችግርና እንቅፋት የሩቅ ሳይሆን የቅርብ ጊዜ ትዝታቸው የሆኑ፣ ሌሎች ሀገራትም ቁጥራቸው ጥቂት አይደሉም።

  ኢትዮጵያ በታሪኳ ያልገጠሟት ፈተናዎች፣ ያላለፈችበት ተግዳሮቶች የሉም። ሁሉንም የቀለበሰችውና ድል አድርጋ የወጣችው በአንድነት፣ በብልሐትና በመደመር ነው። ከውጭ የመጣ አደጋም ሆነ ከውስጥ የተነሳባት ፈተና፣ የቱንም ያህል የበረታ ቢሆን ልጆቿ በኅብረት ሲቆሙ ከዐቅማቸው በላይ ሆኖ አያውቅም።

  በሌላ በኩል ደግሞ “እኔ ከሞትኩ” ባዮች፣ ለግል ጥቅም ሲሉ እናታቸውን በሚሸጡና ሀገራቸውን አሳልፈው በሚሰጡ፣ ጠላት እንደፈለገው በሚጋልባቸው ከንቱ ልጆችዋ ምክንያት ኢትዮጵያ ከአንዴም ብዙ ጊዜ ብርቱ ፈተና ውስጥ ገብታለች።

  ዛሬም ኢትዮጵያ በደኅናው ቀን እፍታዋን ያጎረሰችው፣ የማጀቷን ምርጥ በልቶ የጠገበው የጁንታው ኃይል፣ ሀገርን ለጠላት አሳልፎ ለመስጠት ዐይኑን የማያሽ ውስጥ ዐዋቂ ባንዳ በመሆኑ ምክንያት ፈተናው ጠንክሮብን ይሆናል። በአንድነት ከቆምንና ተደምረን ከተጋን ግን ይኽን ፈተና አሸንፈን፣ ችግሩን ወደ ዕድል፣ ዕድሉንም ወደ ታላቅ ድል ለውጠን፣ ሀገራችንን ወደ አየንላት የሰላምና የብልጽግና ከፍታ ማማ ላይ እንደምናደርሳት ለአፍታም ልንጠራጠር አይገባም።

  ለዘመናት በሀገራችን የሰራ አካል ውስጥ ተሰግስጎ የኖረው ሕወሓት አለ፡፡ የህ ቡድን ራሱን እያፋፋ፣ ኢትዮጵያን በአንጀት – በደም ሥርዋ ሰርጎ ሲጣባ – ሲመርዛት ኖሯል፡፡ አሸባሪው ሕወሐት አሁን ተጠራርጎ ሊወጣ አፋፍ ደርሶና ጣዕረ ሞት ይዞት በመንፈራገጥ ላይ ይገኛል። እድሜውን ለማራዘም የመጨረሻ መፍጨርጨርና የሞት ሽረት ትግል ላይ ነው። የአልሞት ባይ አትርሱኝ መወራጨቱ በዝቷል።

  ከግብአተ መቃብሩ በፊት ልትወጣ ያለች ነፍሱ እስካለች ድረስ መንፈራገጡና የሰላም ደንቃራ መሆኑ አይቀርም። ክፉ መርዙን ተክሎ ጥገኝነቱን ከመሠረተበት የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተነቅሎና ተጠራርጎ እስኪወጣ ድረስ ደዌ ነውና ሕመሙን ችለን፣ የማሻሪያ መድኃኒት እየወሰድን እንቆያለን።

  “ኮሶ ሊያሽር ይመራል” እንደሚባለው፣ የማያዳግም ፀረ ሽብር መድኃኒቱ የጎን ጉዳት የሆነውን ምሬትና ሕመም ታግሠን ከቆየን፣ ሕወሓትም ሆነ ማንኛውም እናቱን ለመሸጥ የሚደራደር ኃይል የሀገራችን ክፉ ትዝታ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ ላይኖረው በቅርቡ ለዘለዓለሙ ይሰናበታል።

  ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በብዙ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አሻጥሮች ውስጥ አልፈናል። ዛሬ በዲፕሎማሲያችን ላይ የሚታየው ከፍተኛ መንገራገጭ ከሦስትና ከአራት ዓመታት በፊት በሁሉም ዘርፎች ላይ የሚታይ የየዕለት ስቃያችን ነበረ። በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማኅበራዊው ዘርፍ፣ በአስተዳደር፣ በሕግ ሥርዓቱ፣ በጸጥታና ደኅንነት ሥርዓቱ፣ ከክልል እስከ ወረዳ በሁሉም ቦታ ይሄ ቀውስ ነበር። በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ ፈውስ እስኪገኝ ስቃይ ነበር፤ ሕመም ነበር። ስለዚህ አሁንም በዲፕሎማሲያችን ውስጥ ቀውስ ውስጥ ገባን ብለን መበርገግ አይገባም። ጠላት ሁሌም በማስፈራራትና በፕሮፓጋንዳ ቀድሞ ሊያሸንፈን ሲጥር ተሸንፈን አንጠብቀው።

  የምንዋጋው ኃይል ዋነኛ ትጥቁ ውሸት ነው። ማኅበራዊ ትስስርን ጨምሮ በየሚዲያው አንድ ውሸት በተኮሰ ቁጥር የምትበረግጉ ሰዎች ባለማወቅ የጁንታው ተባባሪዎች እየሆናችሁ እንደሆነ ዕወቁ።

  ሰው አንድና ሁለት ጊዜ ይሸወድ ይሆናል፤ ባለፉት ብዙ ዓመታት የተሸወዳችሁት ሳያንስ ዛሬም በፕሮፓጋንዳው በመደንበር፣ የሀገራችሁን ጥቅም ከማሳጣት በዘለለ ምንም የሚፈይድላችሁ ነገር የለም። በተለይ ጥቃቅን ነጥቦችን በመገጣጠም የሤራ ትንታኔ ለመስጠት የምትነሡ ሰዎች፣ ሤራ በመተንተን የምሁርነት ጊዜው አልፏል። አሁን የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር ተገቢው ቦታ ላይ መሰለፍ የሚጠይቅበት ጊዜ ላይ ነን።

  የኢትዮጵያ ጠላቶች ድሮ በድብቅ የሚያደርጉትን አሁን በግልጽ በሁለት ግንባሮች ላይ ጦርነት ከፍተዋል፤ በጦር ግንባር እና በዲፕሎማሲ ግንባር። ስለዚህ የኢትዮጵያ ህልውና ግድ የሚለው ሁሉ ከሤራ ትንታኔና ከአጉል መበርገግ ወጥቶ ሁለቱን ግንባሮች በይፋ ይቀላቀል።

  ጁንታው ቀሩኝ የሚላቸውን የክፋት ካርዶች ሁሉ ተጠቅሞ ሊያሸብረን፣ ሊያበጣብጠንና ሊለያየን የሚችለውን ድንጋይ ፈንቅሏል። በገንዘብ ኃይል ሕዝባችን ላይ እሳት እየለኮሰና እርስ በእርስ እያጋጨ እሱ በምቾት እሳት ሲሞቅና ሕዝባችን ላይ ሲሳለቅ ነበር። የሽብር ነጋሪቱን እየጎሰመ ጀሌዎቹን አስከትሎ ዘምቷል። አሁን በተቃራኒው ተሳዳጅና የሞት ሽረት ሩጫ ውስጥ ነው። ጀንበሩ እየጠለቀች ነው። በሞት ሽረት ሩጫ ውስጥ የቀበረውንና የቀረውን የመጨረሻ ጥይቶቹን እየተኮሰ ነው።

  ከመጨረሻዎቹ ምሽጎቹ የጣር ድምጹንና የተስፋ መቁረጥ ቀረርቶውን ስሙልኝ ብሎ ነጋ ጠባ ያላዝናል።የሀገራችንን እጅ ለመጠምዘዝ የሚፈልገው የምዕራቡ ዓለም ዲፕሎማሲና የሚዲያ ጩኸትም የጁንታውን ድምጽ በማስተጋባት ደጀን ሊሆን ጥረቱን ቀጥሏል።

  ተባብረን ጫናውን ለመቋቋምና ለመመከት ከቆረጥን ይኼ ኃይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያልቅለታል።

  ዲፕሎማሲና የውጭ ግንኙነት “ሰጥቶ በመቀበል” መርሕ የሚመራ የፖለቲካ ዳንስ ነው። በትክክለኛ የግንኙነት መሥመር በተቃኘ ዲፕሎማሲ በዋናነት ተጠቃሚ የምትሆነው ሀገራችን ለመሆኗ ምንም ጥርጥር የለውም።

  በተቃራኒው የሀገራችንን ጥቅምና ሉዓላዊነታችንን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ የሚቃኝ ግንኙነት ለጊዜው ፋታ የሚሰጥ ቢመስልም ዘላቂ ጉዳቱ አመዛኝ ነው። ይኼን ለማስተከለል መንግሥት የበኩሉን እያደረገ ነው፤ ወደፊትም አቋሙን አጽንቶ ይቀጥላል።

  በዚህ አንጻር መታወቅ ያለበት አንድ ቁልፍ ሐቅ አለ፡፡ በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ላይ ዋነኛ ተጽዕኖ የሚፈጠረው በመደበኛው መንገድ ብቻ አይደለም። ለምሳሌ የምዕራቡ ዓለም ጫና ሊያደርጉባቸው በሚፈልጓቸው ሀገራት ላይ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም መጠነ ሰፊ ልዩ ልዩ ዘመቻዎችን እንደሚያደርጉ የአደባባይ እውነት ነው። ዛሬም ሆነ ትናንት የሚደርስብንን ጫና “አይሆንም” ማለት ስንጀምር አፍራሽና ስም አጠልሺ የሆኑ የሚዲያና የመረጃ ዘመቻዎች ይከፈቱብናል።

  እነርሱ ትልልቅ ዐቅምና ሽፋን አላቸው፣ የዓለም ሕዝብ የተሳሳተ ምስል እንዲኖረው የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ የሚዲያ መሣሪያዎችና የዳበረ ኃይል በበቂ አላቸው። ስለዚህም በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን የሚዲያና የዲፕሎማሲ ጫና ለመመከት ሁሉም ሀገር ወዳድ ወገን መረባረብ ይጠበቅበታል። ተደምረን ያለንን የተጽዕኖ በርና ዕድል ሁሉ በመጠቀም የተከፈተብንን ዘመቻ መመከት አለብን። በማኅበራዊና በዋናው ሚዲያ፣ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር፣ በግልና በጋራ፣ በተናጠልና በመናበብ ሀገራችንን የሚጎዱ የውሸት ዜናዎች መቃወምና ማምከን ያስፈልጋል። እውነት በትክክልና በበቂ ከተነገረች ውሸትን ታሸንፋለች፤ እናም ሁሉም ዜጋ ለሀገሩ እውነት ዘብ በመሆን ሐቃችን እንዲያሸንፍ ማድረግ አለበት።

  በዚህ አስፈላጊ ወቅት ሁሉም ሀገር ወዳድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆኖ እንዲቆም እናት ሀገሩ ጥሪ ታቀርብለታለች። እስካሁንም ጥቂት የማይባሉ የሀገር ልጆች ቀደም ብለው ትግሉን በመቀላቀል ለሀገራችን ብርቱ ፍልሚያ በማድረግ ላይ ናቸው። እነዚህ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ጀግኖች፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ እስከዛሬ አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ የቆየችው በልጆቿ ብርቱ ጥረትና ትብብር እንጂ፣ እጅን አጣጥፎ በመቀመጥና ወሬ በመሰለቅ እንዳልሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ወደ ሌላ ሰው ጣት ከመቀሰር ይልቅ “ሀገሬ የገጠማትን ችግር ለመመከት ከእኔ ምን ይጠበቃል?” በሚል መንፈስ ጠዋትና ማታ ሳይታክቱ ይፋለማሉ። በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ቢኖሩ፣ የሀገራችንን ችግር በመጋፈጥ ያገኟትን ዕድል ወደ ድል ለመለወጥ ነጋ ጠባ በመዋደቅ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ከማበርከት አልቦዘኑም። ኢትዮጵያም ለሚያደርጉት ትግል ታመሰግናቸዋለች።

  በተመሳሳይ ጥሪዋን ተቀብለው በዱር በገደሉ የሕይወት መሥዋዕትን በመክፈል የሀገራችንን ህልውና ለማስጠበቅ ተጋድሎ የሚያደርጉ ብርቅዬ ኢትዮጵያውያንንም ታሪክ ለዘላለም ይዘክራቸዋል። እነዚህ ሁሉ ሀገር በጨለመባት በዚህ ሌሊት የአንድነት ደማቅ ኮከቦቿና የነጻነት ፋና ወጊዎቿ ናቸው።

  የውሸት ፀሐይ ሲጠልቅ የሤረኞች ወጥመድ መበጠሱ፣ እውነትም አንገቷን ቀና አድርጋ መታየቷ አይቀርም። ጨለማው ይነጋል፤ ክረምቱም ያልፋል፤ ይኼም ፈተና ሰብሮን ሳይሆን አጠንክሮን በድል ይጠናቀቃል። ያለን አማራጭ ወደ ፊት፣ ወደ ብልጽግና፣ ወደ ነጻነትና ወደ ሰላም መገስገስ ነው።

  ካለፈው ትውልድ የተረከብናትን ሀገር የተሻለችና የተመረጠች አድርገን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ በጋራ እንነሣ። ጠላት ወደ ወጥመዳችን እየገባ ነው፡፡ የማሸነፍ ዐቅማችን ተደራጅቶና ተጠናክሮ እየወጣ ነው፡፡ ቃል እንደ ገባነው እጅን በአፍ የሚያስጭን ገድል መፈጸማችንን የምናበሥርበት ጊዜው ቅርብ ነው፡፡

  የያዝነው የኢትዮጵያን አምላክ ነው፤ የምንታገለው ለኢትዮጵያ ነው፣ የሚዋጋው የኢትዮጵያ ጦር ነው፡፡ በመጨረሻም ታሪክ እንደሚነግረን አሸናፊዋ ኢትዮጵያ ናት፡፡መሆን ይችላል፡፡

  ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

  ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

  August 16, 2021

  | ሀገራዊ ዜና

 • በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሳምንታዊ አማካይ የሞት መጠን በእጥፍ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለፀ፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ÷ ወደ ህክምና ተቋማት የሚገቡ የህሙማን ቁጥርም የ 2 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

  ሳምንታዊ አማካይ የሞት መጠን ደግሞ ከ13 ወደ 36 አድጓል ያሉ ሲሆን÷ በፅኑ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። እንደ ሚኒስትሯ ገለፃ የቫይረሱ ስረጭት እየጨመረ ቢሆንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የሚቀሙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው፡፡ በዚህም በአዲስ አበበ 59 በመቶ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ ከተሞች ደግሞ 20 በመቶ ብቻ ናቸው የአፍና አፍንጫ ማስክ የሚጠቀሙት ብለዋል ሚኒስትሯ።

  አሁን ቫይረሱ ያለበት ስርጭት 3ኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ የስርጭት ማዕበል የጀመረ መሆኑን ያመለክታል ያሉት ዶክተር ሊያ ህብረተሰቡ ቫይረሱ የሚያደርሰውን ከፍተኛ ጉዳት ከሌሎች ሀገሮች በመማር ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል ከመጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን 2 ሚሊየን 254 ሺህ 270 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን ወስደዋል። ከ 300 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ሁለተኛ ዙር ክትባት መውሰዳቸውን የተናገሩት ሚኒስትሯ ቀሪውን የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ስራ እይተሰራ ነው ብለዋል።
  በአዲስ አበባ ቫይረሱ ካለው የስርጭት አሳሳቢነት በመነሳት ከዚህ ቀደም የኮሮና ቫይረስ ክትባት ያልወሰዱ እድሜያቸው ከ 35 አመት በላይ የሆኑ ፣በሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ደግሞ እድሜያቸው ከ 55 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ክትባቱ ይሰጣቸዋል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው እድሜያቸው ከ 18 አመት በላይ የሆኑ በአዲስ አበባም ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ ሰዎች እንዲሁም በስራቸው ምክንያት ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችም ክትባቱ ይሰጣቸዋል።

  August 16, 2021

  | ሀገራዊ ዜና

 • የውጭ ሀይሎች ደካማና ተላላኪ መንግስት እንዲመሰረት ለማድረግ እያደረጉት ያለው ከንቱ ምኞት በፍጹም ሊሳካ አይችልም ሲሉ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ገለፁ፡፡

  ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት በደቡብ ክልል በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ነው፡፡ የሽብር ቡድኑ በንጹሀን ዜጎች ላይ የፈጸመውን የጭፍጨፋ ተግባር የክልሉ መንግስት በጽኑ ያወግዛልም ነው ያሉት፡፡
  ይህ ሀይል የመላው ኢትዮጵያን ጠላት መሆኑን ተገንዝበናል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ ወጣቶች ለሀገራችን ሉአላዊነት መስዋዕትነት ለመክፈል ከጀግናው የመከላከያ ሀይላችን ጎን ሆነዋል። የክልሉ የጸጥታ ሀይሎች አሸባሪው ቡድን የክልሉን ሰላም ለመንሳት እያደረገ ያለውን ሴራ ከማክሸፍ ባለፈ ለሀገራዊ ግዳጅ ወደ ግንባር አቅንተዋል።

  ሀገርን የማዳኑ ተግባር በድል እስኪጠናቀቅ በዘርፉ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የክልሉ ህዝብ ለመከላከያ ሀይሉ ማጠናከሪያ ከ200ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል። የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ለህልውና ዘመቻው የ1ወር ደመወዝ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል። የመንግስት ሰራተኛውም ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ ለማድረግ ቃል እየገባ ነው ብለዋል።
  ጠላቶቻችንን አሳፍረን ድል እናደርጋለን ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ደካማና ተላላኪ መንግስት እንዲመሰረት የሚፈልጉ የውጭ ሀይሎችን ሴራ አምርረን እንታገላለን ማለታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

  August 16, 2021

  | ሀገራዊ ዜና

 • በአፋር ክልል ካሊጎማ አሸባሪው ህውሃት ላስከተለው ቀውሰ የተነሳ ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ሰዎች የሚውል የእርዳታ እህል ወደቦታው መንቀሳቀስ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገለጸ።

  አሸባሪው ህወሃት በአፋርና በአማራ ክልል በንፁሃ ላይ ባስከተለው ቀውስ 300 ሺህ ሰዎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡
  መንግስት አሁን ላይ እያካሄደ ያለው ዘመቻ በትግራይ ክልል መሽጎ በሚገኘው አሸባሪ ቡድን ላይ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል።
  መንግስት ለመላው ህዝብ ጥሪ ያደረገው ዜጎች አካባቢያቸውን ማህበረሰባቸውን ነቅተው እንዲጠብቁ እና መከላከያው ሌሎች ድንገተኛ ጥሪዎችም ስላለበት መሆኑን መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
  ወደ ትግራይ እስካሁን 277 እርዳታ የጫኑ መኪኖች መግባታቸውንም አስታውሰዋል። የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሃትን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ወደ ማድመጡ ማዘንበሉን የፕሬስ ሴክሬቴሪያት ሃላፊዋ ጠቁመዋል።

  August 16, 2021

  | ሀገራዊ ዜና

 • በባህሬን የኢትዮጵያ ቆንስል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አምባሳደር ጀማል በከር ከባህሬን የኢንዱስትሪ ንግድና ቱሪዝም ሚኒስትር አቶ ዜይድ አልዜይን ጋር በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

  በውይይቱ አምባሳደር ጀማል በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ የህግና የአሰራር ማበራታቻዎች ዙሪያ በተለይም በግብርና፣በማኑፋክቻሪንግ፣አግሮፕሮሰሲንግ፣ በኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣በቱሪዝምና አገልግሎቶች መስክ ያሉትን ዕድሎች በተመለከተ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ የግብርና፣የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦና የአግሮፕሮሳስንግ ምርቶች በባህሬን ገበያ በሚቀርቡበት ሁኔታ ዙሪያም ተዋያይተዋል፡፡
  አያይዘውም አምባሳደር ጀማል ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

  አቶ ዜይድ አልዜይን በበኩላቸው÷ የሁለቱ አገራት የኢንቨስመንት፣ የንግድና የቱሪዝም ትስስር እንዲጠናከር እና የኢትዮጵያ የግብርና፣ የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች በባህሬን ገበያ እንዲገቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡
  ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን እንዲጐበኙ የቀረበውን የግብዣ በመቀበል የፈረንጆች አመት ከመጠናቀቁ በፊት ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሃብቶችንና የኩባንያ ኃላፊዎች በመያዝ ጉብኝት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

  August 16, 2021

  | ሀገራዊ ዜና

 • የመከላከያ ሠራዊትንና የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይል የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ዛሬ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ።

  በሰልፉ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ እና ምክትል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ በጅግጅጋ ከተማ እስታዲየም በተካሄደው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ ላይ የከተማው ነዋሪዎች ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍና አሸባሪውን የህወሓት ጁንታ የሚያወግዙ የተለያዩ መልክቶችን አስተላልፈዋል። በጅግጅጋ ከተማ ከሚገኙ 20 ቀበሌዎች የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ በመውጣት አሸባሪውን የህወሓት ጁንታ ቡድን ሀገር የማፍረስ ተግባር የሚቃወምና የሀገር መከላከያ ሠራዊትንና የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይልን የሚደግፍ የድጋፍ ሰልፍ ነው ያካሄዱት፡፡ የከተማው ነዋሪዎች የተለያዩ መፈክሮችን አንግበው ለመከላከያ ሠራዊትና ለሶማሊ ልዩ ሀይል ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል፡፡ አሸባሪው ቡድን ባለፉት 30 አመታት በሶማሊ ክልል ህዝብ ላይ የፈፀመው አስከፊ በደሎች ከህሊናችው መቼም እንደማይጠፋ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

  በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለረጅም ጊዜ ሲሰራ የቆየውን ኢትዮጵያዊያን የማፍረስ እቅድ ለማሳካትና ዳግም የማእከላዊ መንግስት ስልጣን ላይ ለመውጣት የተለያዩ የጥፋት ተግባር እየፈፀመ ነው ብለዋ፡፡

  ጁንታው ሀገር የማፍረስ አቅም የለውም ያሉት የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ይህንን የጥፋት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግብአተ መሬቱን በመፈፀም የሀገሪቱን ሰለም ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልፀዋል።

  የሶማሌ ህዝብ ባለፉት 30 አመታት በጁንታው የተጎዳ ህዝብ መሆኑን የጠቆሙት ርእሰ መስተዳደሩ የክልሉ ህዝብ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለማጥፋት ከመላው የሀገሪቱ ህዝብ ጎን ተሰልፎ የሚጠበቅበትን ተጋድሎ ያደርጋል ብለዋል።

  ወቅቱ የመላው የሀገሪቱ ህዝቦች አንድነት የሚያስፈልግበት ወቅት በመሆኑ ህብረተሰቡ በየአከባቢው ግጭትና መከፋፈል የሚፈጥሩ ሀይሎችን እኩይ ሴራ በማክሸፍ በፍቅርና በአንድነት መንቀሳቀስ እንደሚገባ መናገራቸውን የሶማሊ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

  August 16, 2021

  | ሀገራዊ ዜና