ዋናዋና ዜናዎች

| የወላይታ ዞን ዜና


 • የህግ ታራሚዎች ጤንነታቸው የተጠበቀና አምራች ዜጎች እንዲሆኑ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ ስፖርት ለሁሉም በሁሉም ሥፍራ በሚል መሪ ቃል የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ተቋም የህግ ታራሚዎች በጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሄዱ። የ2016 ዓ.ም የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ተቋም የህግ ታራሚዎች ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድር ተካሂዷል። የወላይታ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ደረጀ የስፖርት ውድድሩን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያስጀመሩ ሲሆን ታራሚዎች ጤንነታቸው የተጠበቀና አምራች ዜጎች እንዲሆኑ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወሳኝ ነው ሲሉ ገልጸዋል። አቶ ወንድሙ አክለው ስፖርት አንድነትና እርስ በርስ ያለን ግንኙነት እንዲጠናከር የሚያደርግ እንደሆነ በማስረዳት የሥራ መፍጠሪያም ዘርፍ በመሆኑ የህግ ታራሚዎች ከዚህ ሲወጡ በተሰጥኦዋቸው በመሳተፍ የነገ ተወዳዳሪ ዜጎች ለመሆን በተዘጋጁ ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል አቶ ደለለኝ ደቻሳ በመምሪያው የስፖርት ዘርፍ ቡድን መሪ ሲሆኑ በስፖርት ፖሊሲው ማንኛውም ዜጋ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ መሥራት እንዳለበት በተቀመጠው መሠረት ለህግ ታራሚዎች ስፖርታዊ ውድድሮች መዘጋጀታቸውንና ስፖርት በመሥራት ጤናቸውን እንዲጠብቁ አንስተዋል። በቀጣይ ቀናትም የመረብና የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድሮች እንዲሁም ከባህል ስፖርት የገበጣና ገመድ ጉተታ ውድድሮች የተዘጋጁ መሆናቸውን የገለፁት አቶ ደለለኝ የህግ ታራሚዎች በዞኑ በሚደረጉ ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮናዎች በመሳተፍ ከተቋሙ በሚወጡበትም ጊዜ አምራችና ጤናማ ዜጎች እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው አብራርተዋል። በተቋሙ የስፖርት ዘርፍ ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር መስፍን ጀጎሌ በተቋሙ ያሉ ዜጎች ነገ ኅብረተሰቡን ሲቀላቀሉ ጤንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ስፖርት አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ላመቻቸው የዞኑ ስፖርት ምክር ቤት ምስጋና አቅርበዋል። ስፖርት ሰላም፣ ፍቅር አንድነት ነውያሉት ኢንስፔክተር መስፍን ነገ ለሀገር ልማት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ወጣቶች እንዲወጡም ያስችላል ብለዋል። ስፖርት በጤና ላይ የሚመጡ በሽታዎችን እንደሚከላከልላቸው ያነሱት ታራሚዎች ታርመን ስንወጣም በልማቱ እንድንሳተፍ ያስችለናል ሲሉ ገልጸዋል። የስፖርት እንቅስቃሴ ከሱሰኝነት፣ ከስሜታዊነትና ከወንጀል ነፃ እንዲሆኑ እንደሚያደርግም ስፖርት ሲሠሩ የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ያነጋገራው ታራሚዎች ገልጸዋል።

  October 15, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት የተዘጋጁ መፃህፍት ማስተዋወቂያ ስልጠና የተሳተፉ መምህራን የቀሰሙትን ዕዉቀት ወደ ታች በማዉረድ ትዉልድ የመቅረፅ ኃላፊነታቸዉን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ፡፡ ስልጠናዉን በክልሉ የሚገኙ ከ22 ሺህ በላይ መምህራንን ለመድረስ በቁርጠኝነት ይሠራልም ብለወዋል፡፡ ባልተሟላ በጀትና ቁሳቁስ በሚደረገዉ ርብርብ መምህራን የግል ጥረታቸዉን በማከል የዜግነት ግዴታቸዉን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡ ከትናንት ተምረን ለነገ ለዉጥ መስራት ይኖርብናል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የሁሉምነም ሴክተር ተግባራትን ለመምራት ትምህር ቁልፍ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ስምኦን በበኩላቸዉ ከ1500 በላይ ለሚሆኑ መምህራን የተሰጠዉ የመጀሪያዉ ዙር ስልጠና የተፈለገዉን ግብ ያሳካ ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡ መምህራን ይህንን ስልጠና በአግባቡ ካልወሰዱ መሠረት ላይ ችግር ሊፈጥር ስለሚችል ሁሉም መምህራን በየትምህርት ቤቱ ያሉ መምህራንን የማሰልጠን ኃላፊነታቸዉን በአግባቡ እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የክልሉ መንግስትም አፈፃፀሙን በቅርበት እንደሚከታተልም ተጠቁሟለ፡፡

  October 15, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ዳሞታ ተራራን በማልማት ለቱሪስት መሲህብነት ምቹ በማድረግ ከቱሪዝም ዘርፍ የሚጠበቀውን ጥቅም ለማግኘት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ልሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት አጠቃላይ የወረዳውን አመራር አካላት በማስተባበር የዳሞታ ተራራ ቱሪስት ማዕከል ጎብኝቷል፡፡ የወላይታ ሶዶ ከተማ ራስገ ላይ ሆኖ ለከተማው ግርማ ሞገስ የሆነው ዳሞታ ተራራ ከራሱ በተጨማሪ በርካታ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ መሲህብ ቦታዎችን በውስጡ በመያዝ ለጎብኚዎች ምቹ የሆነ ተፈጥሮ ያደለችን ገፀ በረከት ነው፡፡ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ መስከረም ብርሃኑ ወረዳው ከሚመለከታቸው አካት ጋር በመሆን ተራራውን የማልማት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ተጽዕኖች ተራራው የተጋጋጠበና ለጉዳት የተዳረገበት ሁኔታ ነበረ ያሉት አፈ ጉባኤዋ ወረዳው ልዩ ከለላና ጥበቃ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ እንዲመጠ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ ተራረው ውስጥ ካሉ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ የመሲህብ ቦታዎች በተጨማሪ ለመዲሃኒትነት የሚያገለግሉ እጽዋት፣ ለወላይታ ሶዶ ከተማ መጠጥ ውሃ ምንጭነት የሚያገለግሉ ከ30 በላይ የውሃ ምንጮችና ሌሎች የተፈጥሮ ፀጋዎችን የያዘ መሆኑ ተገልጿል፡፡ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የግል ባለሀብቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካት ይህንን ታሪካዊ ተራራ በተሻለ ሁኔታ በማልማት ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም የማሳደግ ኃላፊት ሊወጡ ይገባል አሉ ወ/ሮ መስከረም፡፡ የጠፉ ምንጮችና ወንዞች እንደገና መፍለቅ፣ የተለያዩ እጽዋት መብቀል እና የጠፉ አዕዋፍት ተመልሰው መምጣት ወረዳው ተራራውን የማልማት ስራ ከጀመረ ወዲህ የመጡ ለውጦች ስለሆኑ አሁንም የሚመለከታቸው አካላት ተጨማሪ ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል ያሉት አፈ ጉባኤዋ ገብኚዎችም የነገስታት መናገሻና ሌሎች ታሪካዊ መሲህቦችን የያዘውን ዳሞት ተራራን በመጎብኘት ስለአካባቢው ያላቸውን ዕውቀት

  October 13, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የግብርና ባለሙያዎች ለአርሶ አደሮች በቂ ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ምርት እንዲታገኝ ሚናቸውን መወጣት ያስፈልጋል አለ የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ። ባለሙያዎች ከማሳ አዘገጃጀት ጀምሮ ምርቱ እስከሚሰበሰብ ድረስ አርዓያ በመሆን አርሶ አደሮችን ለማገዝ መዘጋጀታቸውን የተናገሩት ደግሞ የመምሪያው ባለሙያዎች ናቸው። የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ለመምሪያው ባለሙያዎች ከመስከረም 30 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሙያዊና ተግባር ተኮር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት ለማሳደግ የሰለጠነ ብቁ ባለሙያ ድጋፍ ወሳኝ ነው ብለዋል። ባለሙያዎች በግብርናው ዘርፍ ተምረው መመረቅ ብቻ ሳይሆን የአርሶ አደሩን ምርታማነት ማሳደግ የሚያስችል ድጋፍ እንዲሰጡ የሚያስችል ስልጠና በየጊዘው መውሰድ እንደሚያስፈልግም አቶ መስፍን ተናግረዋል። ለአርሶ አደሩ በቂ ድጋፍ በማድረግ ምርታማነትን ለማሳደግ ለስልጠናው ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን በስልጠናው እየተሳተፉ የሚገኙ ባለሙያዎች ተናግረዋል። የግብርና ባለሙያዎች አርሶ አደሩን በመልካም ስነ ምግባር በማገልገል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ምርት እንዲታገኝ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገልጿል።

  October 12, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በዘንድሮ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወላይታ ሊቃ ትምህርት እንደ ሀገር ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 10 ትምህርት ቤቶች ተርታ ተመድቧል፡፡ በትምህርት ቤቱ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 623 ቢሆንም በትምህርት ቤቱ የላብራቶሪና እና ሌሎች ቤተ ሙከራዎች ቁሳቁሶች እጥረት በመኖሩ ውጤታቸው ሊያንስ መቻሉን ተፈታኝ ተማሪዎች ጠቁመዋል፡፡ ተማሪዎቹ የሚያነሷቸው ችግሮች እና ሌሎች ማነቆዎች በመኖራቸው ከወትሮ ያነሰ ውጤት መመዝገቡን የሚያነሱት የትምህርት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማ ደነቀ ችግሮቹን በመቅረፍ በቀጣይ ዓመት ውጤቱን ለማሻሻል እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡ የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ/ም 76 ተማሪዎችን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን አስፈትኖ በት/ቤቱ ከፍተኛ ውጤት 623 በማስመዝገብ ብሎም ካስፈተናቸው ተማሪዎች 72ቱ 50 ከመቶ በላይ ውጤት በማስመዝገባቸው በሀገሪቱ ከሚገኙ 10 ት/ቤቶች ከፍተኛ ውጤት በማምጣት አንዱ መሆን ችሏል፡፡ በብዙ ችግሮች ውስጥ አልፈው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የሊቃ ት/ቤት ተማሪዎች በበኩላቸው ባስመዘገቡት ውጤት ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ በቀጣይ ትልቅ ደረጃ ደርሰው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ተናረዋል፡፡ ምንም እንኳን ት/ቤቱ በመማር ማስተማሩ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ይንቀሳቀስ እንጂ ማነቆ የሆኑ ችግሮች እንዳሉ ተማዎቹና መምህራኖቹ አንስተዋል፡፡ በትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማሩን ሊያስተጓጉሉ የሚችሉ ችግሮችን ከመቅረፍ አኳያ በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን በአካባቢው ሌሎች አዳሪ ት/ቤቶች ቢገነቡ መልካም ነው ተብሏል፡፡ በከፍተኛ ውጤት ያለፉ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በቀጣይ በውጭ ሀገር ነጻ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ከመንግስት ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ የሊቃ ት/ቤት ስራ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

  October 11, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የዎላይታ ዞን ከፍተኛ የመንግስት ሰራ ኃላፊዎች "ካረታ አንስተኛ መስኖ ፕሮጀክት" ግንባታ ሂደት ያለበት ደረጃ እየጎበኙ ነው የመስኖ ግንባታው በሁምቦ ወረዳ አንካ ኦቻ ቀበሌ እና አበላ አበያ ወረዳ አበላ አጀጃ ቀበሌ አዋሳኝ የሚገኝ ሲሆን 150 ሄ/ር መሬት ማልማት የሚችል እንደሆነ ተገልጿል። ግንባታው ከ55 ሚሊዮን በላይ ውጪ የሚገነባ እንደሆነና ቀጣይ ሳምንት ርክብክብ ተደረጎ ለህብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ብልጽግና ፓርቲ የህዝባችን መሠረታዊ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ እሙን ነው። ከዚህም አንዱ ዘመናዊ የመስኖ ግንባታዎችን በመከናወን አርሶአደሩ በዓመት ሶስቴ እንዲያመርት በማስደረግ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና አርሶአደሩ በምግብ ራሱን እንዲችል ለማስቻል ነው። በትናንትናው ዕለት በበጋ መስኖ ልማት አርሶአደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን ዞናዊ የበጋ መስኖ ልማት ንቅናቄ መድረክ መካሄዱ ይታወሳል። በጉብኝቱ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ፣ የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ተመስገን አለማየሁን ጨምሮ ሌሎች የዞኑና የሁምቦ ወረዳ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

  October 5, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ማህበራዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ጤናው የተጠበቀ ዜጋን መፍጠር እጅግ ወሳኝ ነው፦ አቶ ሳሙኤል ፎላ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ የ2015 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸም ግምገማና የ2016 ዓ.ም ንቅናቄ መድረክ በኦፋ ወረዳ አካሂዷል። በንቅናቄው የተገኙ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ጤናውን የተጠበቀለት ህብረተሰብ በመፍጠር የምንመኘውን ማህበረሰብ ብልጽግና ማረጋገጥ እንችላለን ብለዋል። መከላከልና አክሞ የማዳን መሠረት ያደረገ ጤና ስርዓት መዘርጋትና የኅብረተሰቡን ጤናማነት ማስጠብቅ ለልማት መሠረታዊ ጉዳይ እንደሆነም ገልጸዋል። አመራሩ በተቀሰቀሰው ልክ ውጤት ይመጣል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው መላው ህዝባችንን በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን እንዲሳተፍና ተጠቃሚ እንዲሆን ለአመራሩ ቀዳሚ አጀንዳ ሊሆን ይገባል ብለዋል። በገንዘብ እጥረት ምክንያት በተለያዩ በሽታዎች የሚሞቱ አቅመ ደካሞችን ባለሀብቶችና አቅም ያላቸው ማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ሀብት የማሰባሰብ ስራ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል። የማዕጤመ የአባልነት መዋጮ በጊዜ በንቅናቄ መሰባሰብ እንደሚገባ ያሳሰቡት ዋና አስተዳዳሪው ግቡን ለማሳካት አመራሩ የመሪነት ሚናውን መውጣት እንዳለበትም አሳስበዋል። የወላይታ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ ባለፉት ዓመት በጤና ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎች ተስፋ ሰጪ እና ህዝባችንን ተጠቃሚ ያደረገ ነው ብለዋል። ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ የሚቻለው በጤናው ዘርፍ መሠረታዊና ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ስችል ብቻ እንደሆነም አስገንዝበዋል። በጤና ተቋማት የሚስተዋሉ ችግሮችን ማረምና መቆጣጠር ያስፈልጋል ያሉት አቶ አሳምነው ጤናማ ማህብረሰብን ለመፍጠር ቁጭት ፈጥረን መስራት ይጠብቅብናል ብለዋል። የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ፣ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ እንዲሆንል በአጽንኦት አሳስበዋል። የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ በበኩላቸው በዞኑ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ለህብረተሰቡ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ያሉት ኃላፊው በዘርፉ በቀዳሚነት ተጠቃሚ መሆን ያለባቸውን ዜጎች በአግባቡ በመለየት በማዕጤመ የሚታቀፉ የአባላትን ቁጥር ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

  October 5, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ቴሌቪዥን በሚሰጣቸው የሚዲያ አገልግሎት ቅሬታ ካለዎት በስልክ ቁጥር: 0911260234 ይደውሉ ወይም በኢሜል አድራሻ: [email protected] በመጻፍ ፓብልክ አዲተሩን ያሳውቁ

  October 5, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ቀጥታ ከወላይታ ሶዶ_ ዲላ የትራንስፖርት ስምሪት መጀመሩ ተገለጸ ከባለ ሰባት በር መግቢያና መውጫ ከተማ አንዱ የሆነው ከወላይታ ሶዶ ጌዲኦ ዞን ዲላ ከተማን በቀጥታ የሚያገናኝ መንገድ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመረ። ከዚህ ቀደም ከወላይታ ሶዶ ሀዋሳ ከዛም ዲላ ይደረግ በነበረው ጉዞ የሚያጋጥሙ መጉላላቶችን ይቀንሳል የተባለለት አዲሱ መስመር 179.50 ሳንቲም ብር ታሪፍ ተቆርጦለታል። መነሻውን ከመናኅሪያ አድርጎ ከወላይታ ሶዶ በአዋሳ መስመር በሞሮቾ በሚወስደው መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ አገልግሎት ወይም ትራንስፖርት ለመስጠት የተከፈተው መንገድ 168 ኪሎ ሜትር ይረዝማል። ይህም ከዚህ ቀደም በ3 የተለያየ ተሽከርካሪ የሚደረገውን ጉዞ አንድ ያደረገና ርቀት የሚቀንስ መንከራተትን የሚያስቀር በመሆኑ ወደ ዲላ ከተማ ከዎላይታ ሶዶ በቀጥታ መጓዝ መጠቀም ይችላሉ ። ለዘገባው ጥንቅር የዎላይታ ሶዶ ከተማ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ታጠቅ ምትኩ መረጃዎች በመስጠት የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

  September 27, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የ1498ኛውን የነቢዩ መሀመድ የመውሊድ በዓል በማስመልከት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ያስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ። የተወደዳችሁና የተከበራችሁ መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ እንኳን ለ1498ኛው የመውሊድ በአል በሰላም አደረሣችሁ/አደረሰን! ነብዩ መሐመድ(ሰዓወ) በእስልምና ሀይማኖት በነበራቸው አስተምህሮት የሰው ልጆች ያለ ዘርና ሃይማኖት ልዩነት የምድር ፍጡራን ሁሉ እኩል መሆናቸውን ሲያስተምሩ ቆይተዋል። የመወሊድ በዓል የመቻቻልና የመከባበር ተምሳሌት የሆነ በዓል በመሆኑ አርአያነቱን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል። እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሐ ሀይማኖት፣ ቋንቋና ታሪክ ሀገር ናት። ብዝሀነታችን ውበታችን ብቻ ሳይሆን የጥንካሬያችንና የታላቅነታችን ምንጭ በመሆኑ እንደዓይናችን ብሌን ልንንከባከበው ይገባል። በኢፌዴሪ የተረጋገጠው የሀይማኖት እኩልነት በአክራሪነትና ጽንፈኝነት እንዳይሸረሸር ቅንጅታዊ እንቅስቃሴያችንን አጠናክረን መቀጠል ያስፈልጋል። ሀይማኖቶች ሁሉ በመሠረታዊነት የሠላም አምባሳደር በመሆናቸው የሰላም ፣ የመቻቻልና የመከባበር ዕሴቶቻቸው ቀጣይ እንዲሆኑ የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል። የሀይማኖት ፅንፈኝነት ውጤቱ እየተናቆሩ መጠፋፋት በመሆኑ ከድርጊቶቹ መታቀብ ብቻ ሳይሆን በእኩይ ተግባራቱ የሚሳተፉትን ማስገንዘብ፣ መገሰፅና ማረም ወቅቱ የሚጠይቀው ቁልፍ ጉዳይ ነው። በዓሉን ስናከብር የበዓሉ እሴቶች የሆኑ ተግባራት በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ እና ለአደጋ የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በላቀ ተነሳሽነት የመርዳት፣ የወደቁትን የማንሳት፣ የታረዙትን የማልበስና የተራቡትን የመመገብ በጎ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በዞናችን አስተዳደርና በራሴ ስም ላሳስብ እፈልጋለሁ። ኢድ ሙባረክ -መልካም በአል። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ! አመሠግናለሁ። ሳሙኤል ፎላ -የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

  September 27, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታ የአብሮነት ተምሳሌት መሆኑን የሚያሳይ ስጦታ ከተለያዩ ወንድም ሕዝቦች ተበርክቷል። ሰንጋ በሬ እና የተለያዩ የሕዝቦች የጋራ እሴቶችን የሚያንጸባርቁ ስጦታዎች ለወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ ለወላይታ የሀገር ሽማግሌ ተወካይ አቶ ሰይፉ ለታና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ዮዮ ጊፋታ በማለት አስረክበዋል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የወላይታ የሀገር ሽማግሌ ተወካይ አቶ ሰይፉ ለታና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም ጊፋታ ዮዮ፤ ለጋሎካ በማለት በወላይታ ሕዝብ ስም አመስግነው ስጦታውን ተቀብለዋል።

  September 24, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • "የጊፋታ በዓል ከኃይማኖትና ከባዕድ አምልኮ ሥርዓት ጋር በፍጹም የማይገናኝ የህዝቡ የዘመን መለወጫ በዓል ነው።" -የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ በጊፋታ በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ጊፋታ የደስታ እና የምስጋና በዓል፤ከአሮጌው አመት ወደ አዲሱ አመት የመሻገር ማብሰሪያ በዓል ነው ሲሉም ተናግረዋል ። የጊፋታ በዓል ከኃይማኖትና ከባዕድ አምልኮ ሥርዓት ጋር በፍጹም የማይገናኝ የህዝቡ የዘመን መለወጫ በዓል ነው ሲሉ አቶ ሳሙኤል ፎላ ገልጸዋል። ጊፋታ የአንድነት፣ የአብሮነት፣ የዕርቅና የይቅር ባይነት አንዱ ከሌላው ጋር በመተሳሰብ የሚያከብረው በዓል ነው ብለዋል አቶ ሳሙኤል። ጊፋታ ላለፈው ስኬት ፈጣሪን የሚያመሰግኑበት ለቀጣይ ተግባር ምክክር የሚደረግበት እንዲሁም ያለውን ጨርሰን የምናባክንበት ሳይሆን ቁጠባን የምናዳብርበት ድንቅ እሴቶች ያሉት በዓል ነው በማለትም አብራርተዋል ዋና አስተዳዳሪው። የወላይታ ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል ፖሌቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ልንንከባከበው ይገባል ሲሉ ፋይዳውንም ገልጸዋል። እኛ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በታሪክ፣ በሥነ ልቡናና በሌሎች ማህበራዊ መስተጋብሮች በማይበጠስ መልኩ የተጋመድን ተሳስረን የምንኖር ስለሆነ አንዱ የሌላውን ባህል ልናከብር ልናደንቅ ይገባል ሲሉ የተናገሩት አቶ ሳሙኤል አንድነታችንን ለመጠበቅ የህዝብ ለህዝብ ትስስርና ግንኙነታችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል። ባህላችንንና ታሪካችንን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር በህትመትና በኤሌክትሪክ ሚዲያዎች በማከማቸት ልንጠብቅና ልንንከባከበው ይገባል ሲሉም አስረድተዋል። የሚመለከታቸውም አካላት የጊፋታ በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የምናደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል። ኢንቨስተሮችም በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማሩ እንዲሁም ጎብኚዎችም በአካባቢያችን ያሉ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል ።

  September 24, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • "ጀግንነት ባህል ነው፣ የወላይታ ህዝብ ጀግንነትን ባህል አድርጎ የተቀበለ ህዝብ ነው።"-ቀጄላ መርዳሳ የኢፌዴሪ ባህል ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የወላይታ ብሔር እንደ ሌሎች ብሔሮች ሁሉ በርካታ አኩሪ ባህሎች ባለቤት ብለው ቅርሶችን ጠብቀው ላቆዩ አባቶቻችን ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ አቶ ቀጄላ ተናግረዋል። ጠንካራ ወታደራዊ ውጊያ ከመደራጀቱ በፊት የፈረስ ውጊያ ነበር ያሉት አቶ ቀጄላ የወላይታ ህዝብ በፈረስ የሚዋጋ ጀግና ህዝብ ነው ብለዋል። የወላይታ ህዝብ የራሱ ባህላዊ አለባበስ፣ የሙዚቃ መሣሪያ፣ የቆየ የዘመን መቁጠሪያ ሥልጣኔ፣ የሀገር በቀል ዕውቀት፣ የፈጠራ ክሂሎት ባለቤት ናችሁ ብለዋል ለታዳሚዎች ባሰሙት ንግግራቸው። ጀግንነት ባህል ነው ያሉት ሚኒስትሩ የወላይታ ህዝብ ጀግንነትን ባህል አድርጎ የተቀበለ ህዝብ ነውበማለት ገልጸዋል። በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ላደረጉት ምስጋና ያቀረቡት አቶ ቀጄላ የጊፋታ በዓል በማይዳሰስ ቅርስ እንዲመዘገብ የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊና የርዕሰ መስተዳደሩ ተወካይ አቶ ወገኔ ብዙነህ የህዝባችን የአደረጃጀት ጥያቄ ተመልሶ የኢትዮጵያ ተምሳሌት የሆነውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተመሠረተበት የሚከበር መሆኑን ተናግረዋል። ወላይታ የብዙ ታሪኮችና ትውፊቶች ባለቤት ነው ያሉት አቶ ወገኔ የኢትዮጵያ መገለጫ የወላይታ ህዝብ ሀብት የሆነው የጊፋታ በዓል በዩኔስኮ እንዲመዘገብ የመንግስት ድጋፍ እንደማይለይ አረጋግጠዋል።

  September 24, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን አስተዳደር የሕዝቡ ባህላዊ እሴቶች እንዲጠበቁና እንዲታወቁ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ገልጸዋል የጊፋታ በዓል የወላይታ ባህልና ቋንቋ ስምፖዚዬም በወላይታ ጉታራ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል። የወላይታ ዞን አስተዳደር የሕዝቡ ባህላዊ እሴቶች እንዲጠበቁና እንዲታወቁ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በርካታ ስራዎችን መስራቱን የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ገልጸዋል። በዓሉ ከዩኒሰኮ ድንጋገ ጋር የማይቃረን፣ ከማን ኛውም ሀይማኖት ጋር የማይገናኝና በሌሎች አካባቢዎች የማይገኝ በመሆኑ በዓለም የሰው ዘር ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚሰራው ስራ መልካም ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል። በዓሉ የታራራቁ የሚገናኙበት፣ የተጣሉት የሚታረቁበት አብሮነትና አንድነት የሚጎለብትበት የሕዝብ መድመቂያ ነው ብለዋል አቶ ሳሙኤል። የወላይታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ ኃብቴ ለታዳሚዎች ባስተላለፉት መልዕክት ወላይታ የራሱ ቋንቋና የዘመን መለወጫ ድንቅ በዓል ያለው መሆኑን ጠቅሰው በአፀ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት ሕዝቡ የራሱን ማንነት የሚያሳይበት ዕድል ተነፍጎ መቆየቱን ተናግረዋል። በዓሉ ከማነኛውም ሀይማኖት ጋር የማይገናኝና የመላው የወላይታ ሕዝብ በራሱ አቆጣጠር አሮገውን ዓመት አልፎ አዲሱን ዓመት የሚቀበልበት የዘመን መለወጫ መሆኑን ተናግረዋል። በአለም ሕዝብ ወካይ ቅርስነት ለማስመዝገብ በሀገራችን የመጀመሪያ ደረጃ ተሰጥቶ በመጠባበቅ ይገኛል፤ ለዚህም አስተዋጽኦ ላበረከቱና እያበረከቱ ለሚገኙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የኢፌዴሪ ባህልና ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ተወካይ አቶ ደምረው ዳኜ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሚልኪያስ ካልታሳ፣ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎል እና ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ስምፖዚዬሙን እየታደሙ ይገኛሉ።

  September 23, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ጊፋታ አብሮነት፣ ሠላም፣ ፍቅርና አንድነት የሚገለጽ በዓል በመሆኑ የበህብረተሰቡን መቻቻልና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ተባለ። በወላይታ ሶዶ ከተማ "ጊፋታ ለሠላምና ለአብሮነት" በሚል መሪ ቃል የተካሄዳው ታላቅ የጊፋታ ዋዜማ ሩጫ ውድድር በሠላም ተጠናቋል። በውድድሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የወላይተ ዞን ምክርቤት ቤት ዋና አፌ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ ጊፋታ ደሃ ሀብታም ሳይል ሁሉም ሰው እኩል የሚያከብርበት ታልቅ በዓል ነው ብለዋል። በዛሬው ዕለት በጊፋታ ዋዜማ የተካሄደው ሩጫው የጊፋታ አካል አንዱ መሆኑን የተናገሩት ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት በዓሉ አንዱ ከአንዱ ጋር በፍቅር፣ በመተሳሰብና በመቻቻል የሚከበርበት እንደሆነም ጠቅሰዋል። ጊፋታ አብሮነት፣ ሠላም፣ ፍቅርና አንድነት የሚገለጽ በዓል እንደሆነ የገለጹት ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት በዓሉ በህብረተሰቡ ዘመን መቻቻልና አብሮነትን እንደሚያጠናክር አስታውቀዋል። የወላይታ ዞን ባህልና ቱርዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ ሀብቴ የጊፋታ እሴቶች አንዱንና ዋነኞቹ ሰላምና አብሮነት እንደሆነ ገልጸዋል። ጊፋታ በዓል ሀይማኖታዊ አይደለም ያሉት አቶ ተሾመ ጊፋታ የወላይታ ህዝብ የዘመን መለወጫ እንደሆነም ገልጸዋል። በዛሬው ዕለት የተካሄደው የጊፋታ ሩጫ በሠላም እንዲጠናቀቅና ያማረ እንደሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትን ምስጋና አቅርበዋል። የወላይታ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደሰ ተክሌ በበኩላቸው ጊፋታ የክረምት ጭጋግ እና ጨለማ አልፎ ብርሃን ወጋገን በሚወጣበት ጊዜ የሚከበር ታላቁ ባህላችን ነው ብለዋል። በመጨረሻም በሩጫ ውድድሩ በፆታ መሠረት አንድ እስከ ሶስት የወጡ ሯጮች የማበረታቻ ሽልማት ገንዘብና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

  September 22, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ዳሽን ባንክ የወላይታ ዲስትሪክት የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብን በገቢ ለማጠናከር ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያሰራውን የደጋፊዎች ማልያ ለክለቡ ደጋፊ ማህበር አስረከበ ክለቡም ባንኩ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናውን በማቅረብ ሌሎች ድርጅቶችም በመሰል ስራዎች ላይ በመሳተፍ የክለቡን አቅም ለማጎልበት ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባም ጥሪ አቅርቧል።

  September 22, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • መርሳ ሚዲያ እንስትቲዩት የተሰኘ ለሚዲያ ልማት የሚሰራና ለትርፍ ያልተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለወላይታ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና ለአስተዳደር ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ የባለሙያዎችን ሙያዊ ብቃት በማሳደግ ሚዲያውን የበለጠ ተወዳዳሪና ተመራጭ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የወላይታ ቴሌቪዤን ሥራ አስኪያጅ አቶ ሴባ ናና ገለጹ፡፡ የመርሳ ሚዲያ እንስትቲዩት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ የአብስራ አማረ እንዳሉት ድርጅቱ በሀገራችን ሚዲያ አቅም ለማጎልበት ለባለሙያዎች ሙያዊ ስልጠና መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ የወላይታ ቴሌቪዢንን ጨምሮ በሀገራችን በአራት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ራሳቸው ባወጡት የሚዲያ ህግ የሚተዳደሩበትን አሰራር በሙከራ ደረጃ ለማስጀመር ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን እሰራ እንደሚገኝም አክለው ገልጸዋል፡፡ ሚዲያዎች ያለሙትን አላማ ግብ እንዲመቱ ጠንካራ መተዳደሪያ ደንብና ኢድቶሪያል ፖሊሲ ሊኖራቸው ይገባል ያሉት ወ/ሮ የአብስራ ወላይታ ቴሌቪዥንም ለጠንካራ ህግና ኢድቶሪያል ፖሊሲ ተግባራዊነት የሰጠው ትኩረት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡ መርሳ ሚዲያ እንስትቲዩት ለወላይታ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና አስተዳደር ሰራተኞች ኢድቶሪያል ፖሊስን ጨምሮ በሌሎች ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ጠቃሚ ስልጠና በመስጠቱ ያመሰገኑት ደግሞ የወላይታ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅ አቶ ሴባ ናና፡፡ ለጣቢያው ባለሙያዎች አስፈላጊ ስልጠናዎችን በመስጠት በሙያና በስነ ምግባር የተካኑ ጋዜጠኞችን ለማፍራት የተጀመሩ መልካም ጅምሮች ለወደፊትም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ የተቋሙ ባለሙያዎች ዕውቀት፣ ክህሎትና ልምድ በማዳበር ሚዲያውን ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራልም ብለዋል። ወላይታ ቴሌቪዥን ገና የሁለት ዓመት ዕድሜ ያለው ተቋም ቢሆንም አሁን ያለው የተመራጭነት ደረጃው የተሸለ ነው ያሉት የወላይታ ቴሌቪዢን ቴክኒክ ኪሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ተሻለ ተገኔ ጣቢያው ተመራጭነቱ የበለጠ እንዲጨምርና የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ከፍ እንዲል ተንካራ ህግና ፖሊሲ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ አንድ ጋዜጠኛ የመረጃ ትክክለኛነት፣ የመረጃ ምንጮች ታማኝነትና እና ሌሎች የሙያ ስነ-ምግባር ደንቦችን ጠብቆ ለህበረተሰቡ ሁለንተናዊ ዕድገት ፋይዳ ያለውን መረጃ ተደራሽ የማድረግ ግዴታውን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ በስልጠናው የተሳተፉ ጋዜጠኞችና የአስተዳደር ባለሙያዎችም ከተሰጠው ስልጠና ጠቃሚ ዕውቀት ማግኘታቸውን ጠቅሰው ቀጣይም መሰል ስልጠናዎችን የማግኘት ሰራ ተጠናክሮ እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡

  September 22, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የሁምቦ ወረዳ አስተዳደር ለ50 አቅም ደካሞችና 480 በላይ ወላጅ አጥ ተማሪዎች የመማርያ ቁሳቁስ፣ አልባሳትና የተለያዩ ድጋፍ አድርጓል በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ ከሁሉም ቀበሊያትና ታዳጊ ማዘጋጃዎች ለተወጣጡ ለ50 አቅም ደካሞችና ወላጅ አጥ 480 በላይ ተማሪዎች የመማርያ ቁሳቁስ፣ አልባሳትና የተለያዩ ድጋፍ ተደርጓል። የሁምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፀጋዬ ቀልታ በዛሬው ዕለት የሚደረገው ድጋፍ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል መሆኑን ገልጸው፣ በወረዳው በክረምት ወራት በረካታ ማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደረገ ሥራ በሁሉም ትኩረት መስኮች መከናወናቸውን ገልጸዋል። በጎ ሥራ ከፍተኛ የአእምሮ እርካታ የሚሰጥ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በዛሬው ዕለትም አንድም ተማሪ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ ያለመ ተግባር ተከናውኗል ብለዋል። በጎ ፍቃድ አገልግሎት በክረምት ወራት ብቻ ሳይሆን በበጋም እንዲሁም ባህል ሆኖ እንዲቀጥል እየተሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። የወላይታ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ም/ኃላፊና ወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ደረጀ በወረዳው በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተሰሩ ሥራዎች በጣም ተስፋ ሰጪና ለሌሎች አካባቢዎች ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል። ወላጅ አጥና የአቅም ደካማ ቤተሰብ ልጆች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ ለማድረግ የተሰራው ሥራ እጅግ በጣም ጥሩ በመሆኑ ወረዳውን አመስግነው፣ ይህ ተግባር የአእምሮ እርካታ የሚሰጥና ከፈጣር ዘንድም ዋጋ ያለው ተግባር ነው ብለዋል። የሁምቦ ወረዳ ዋና የመንግሥት ተጠሪና የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አመኑ ጎአ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚመራ ዐቢይና ቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ ተግባሩን መምራቱን ገልጸዋል። አቶ አመኑ አክለውም በሁሉም ቀበሊያት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በትኩረት መሰራቱን ጠቁመው፣ በዝህም በረካታ ወጣቶች መሳተፋቸውን ጠቁመዋል። በዛሬው ዕለትም የመማርያ ቁሳቁስ እጥረት ላለባቸው ተማሪዎች የተለያዩ የመማርያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ጠቁመው በቀጣይም በጎ ፍቃድ አገልግልት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።

  September 22, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ከህብረተሰቡ የሚኑሱ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ድጋፍና ክትትል አንደሚያደርጉ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የከተማ መሰረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ቋም ኮምቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ገለፁ። በመድረኩ የቦሎሶ ሶሬ ምርጫ ክልል-2 በመወከል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልና የከተማ መሰረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ቋም ኮምቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባል ወ/ሪት መስከረም ደገፉ በቦሎሶ ሶሬወረዳ በምርጫ ክልሉ ከተካተቱ 10 ቀበሌያት ነዋሪዎች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በወረዳው በመሠረተ ልማት ዘርፍ አሉ ያሏቸውን ችግሮች አንስተዋል። በተለይም የመንገድ መሠረተ ልማት ያለመሟላትና ብልሽት በቀዳሚነት አንስተዋል። በወረዳው ተጀምረው የቀሩ የንፀህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን የጠቆሙት ተሳታፊዎች እንደወረዳም በዘርፉ ያለው ችግር እንዲፈታላቸውጠይቀዋል። በማጠቃለያውም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባል ወ/ሪት መስከረም ደገፉ ጥያቄዎችን ለመመለስ በየደረጃው ያሉ አስፈፃሚ አካላት በቁርጠኝነት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል። የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የከተማ መሰረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ቋም ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው ለህዝቡ መመለስ ያለባቸው የመልካም አስተዳደር እና መሠረተ ልማት ጥያቄዎች በጊዜ ምላሽ እንዲያገኙ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄውን እንደሚያደርሱ ተፈፃሚነቱንም እንደሚከታተሉ አስረድተዋል።

  August 31, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ሶዶ ከተማ ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 2ኛ ዙር 11ኛ የሥራ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ወ/ሮ አልማዝ ባንጫን የወላይታ ሶዶ ከተማ ዋና አፌ ጉባኤ እና አቶ አበራ አዋሾን የወላይታ ሶዶ ከተማ ም/አፌ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።

  August 30, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የፌዴራልና የክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በልማትና በመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተወያዩ ናቸው የፌዴራል እና የክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የክረምት የህዝብ ውክልና ሥራ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። በፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የልዑክ ቡድኑ መሪ አቶ መለሰ መና የመድረኩ ዋና ዓላማ የህዝብን ማዳመጥና ለህዝቡ መመለስ ያለባቸው ጉዳዮች በጊዜ ምላሽ እንዲያገኙ ማስቻል ነው ብለዋል። በቀጣይነት መሰል መድረኮች እስከታችኛው መዋቅር የሚወርድ መሆኑን የገለጹት አቶ መለሰ መና በመድረኮቹ የህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የህዝብን ቅሬታ በሚፈታ መልኩ እየተፈጸሙ ስለመሆናቸው እያረጋገጥን የምንገመግምበት ነው ሲሉም ተናግረዋል። በዞን ደረጃ እየተካሄደ ባለው መድረክ የአስፈጻሚ መ/ቤቶች አፈጻጸም ቀርቦ ግምገማ ይደረግበታል፣ በአፈጻጸሙ መነሻም ግብረ መልስ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል::

  August 30, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በይፋ ስራ አስጀመሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በአዲሱ ቢሮ ተገኝተው ስራ አስጀምረዋል። ርዕሰ መስተዳደሩ ወላይታ ህዝብ ላደረገው ለደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል። ርዕሰ መስተዳደሩ አዲስ ቢሯቸውን የጎበኙ ሲሆን የሰንደቅዓለማ መርሃግብርም አካሂደዋል።

  August 29, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወንማማችነትና እህትማማችነትን የበለጠ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሆኖ እንዲመሠረት ሕዝቡ ላበረከተው አስተዋጽኦ የክልሉ ዋና ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ አመስግነዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ይፋዊ ስራ ማስጀመሪያ የወላይታ ሕዝብና የዞኑ አስተዳደር ላደረገው ደማቅ አቀባበል አድንቀዋል። አስጨናቂውን ፈተና በድል ተሻግረን ተውበንና ደምቀን እንድንታይ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲጎለብት ስላደረጉ በክልሉ በጋራ የተደራጁ የሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ሕዝቦችን አመስግነዋል። ፈተናዎች የበዙት አብሮነታችንና አንድነታችንን በመቅናት የመነጨ የክፋት ያመጣው ውጥን ቢሆንም በበሳል አመራር ሰጪነትና በአስተዋይ ህዝብ ጥረት ያማረ ውጤት ለማየት ችለናል ብለዋል። በመገፋፋትና በሕቦች መካከል ልዩነት በመስበክ ማንም አይጠቀምም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተመሠረተው የህብረብሔራዊ ተምሳለት በሆነው ክልል በርትተን ሰርተን የለውጥና የእድገት ተምሳለት መሆን አለብ ብለዋል። በክልሉ 6 የክላስተር ከተሞች የተመረጡ ስሆን በርዕሰ መስተዳድሩ መቀመጫ በሆነችው በወላይታ ሶዶ ከተማ ስራ ለመጀመር አቅደን ስንጀምር ለተደረገው ደማቅ አቀባበል እንግዳን በመቀበል ከጥንትም የሚታወቀውን የወላይታን ሕዝብ አመስግነዋል። በማስመሰል ስሜት ሳይሆን ከልብ በሆነ ፍቅር ለክልሉ ዕድገት በአንድነት እንነሳ፤ ቀንና ማታ ሰርተን ሕዝባችንን ተጠቃሚ እናድርግ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል። ክልሉን የብልጽግና ተምሳለት የሆነ ክልል ለማድረግ ሕዝቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

  August 29, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ርዕሰ መስተዳድር ለአቶ ጥላሁን ከበደና ለክልሉ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። ህብረብሔራዊነት ተምሳለት ለሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ታዳሚዎችን እንኳን አደረሳችሁ ብለው ክልሉ በተሳካ ሁኔታ እንዲመሰረት የወላይታ ሕዝብና ሌሎች የክልሉ ሕዝቦች ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል። ወላይታ ሶዶ ርዕሰ መስተዳድር መቀመጫ ሆና በመመረጧም በወላይታ ሕዝብ ስም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። የወላይታ ሕዝብ ከሌሎች የክልሉ ሕዝቦች ጋር ያለውን ባህላዊ፣ስነልቦናዊና ቁሳዊ አብሮነትን በማጠናከር በጋራ ለመስራትና በፍትሃዊነት ለመጠቀም ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል። በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አመራር ሰጪነት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የዞኑ አስተዳደር በትጋት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

  August 29, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ትምህርት ለትውልድ በሚል የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ገለፁ ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልል የዞን እና የከተማው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና በጎ አድራጊ አካላት ትምህርት ለትውልድ በሚል የቄራ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የግንባታ ስራ በይፋ አስጀምረዋል ። ትምህርት ትውልድ ተሻጋሪ ልማትን ለማረጋገጥ መሰረት መሆኑን የገለፁት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ለግንባታው ስራም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። እንደሀገር የትምሀርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ህፃናት ላይ በማተኮር እና ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተጀመረው ንቅናቄው ቀጣይነት እንደሚኖረው አቶ ተስፋዬ ገልፀዋል። የቄራ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ በህብረተሰቡ ፣ ባለሀብቶች ፣ በጎ አድራጊዎች እና የመንግስት እገዛ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ሲሉም ተናግረዋል። የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ትምህርት በዎላይታ ቀደምት እና ሁሌም ተፈላጊ የህዝቡ የልማት ጥያቄ መሆኑን አስታውቀዋል። በተለምዶም መዋለ ህፃናት የሚባለው የቅድመ መደበኛ ትምህርት በመንግሥት ማእቀፍ ለህዝቡ እየቀረበ እና እየተጠናከረ እንደሚሄድም አቶ አክሊሉ ገልፀዋል። አቶ አክሊሉ ለጨቅላ ህፃናት ትምህርት ቤት ለመገንባት እና የልማት አቅሞችን በላቀ ተነሳሽነት በማስተባበር ለውጤት ያበቁትን የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አመስግነዋል ። የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን አለማየሁ አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት የእውቀትን ሀብት ለዜጎች ለማስጨበጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል። በከተማ ደረጃ ትምህርት በስታንዳርድ መሰረት እንዲሰጥ እና ጥራትን ለማስጠበቅ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሚገኙ ክቡር ከንቲባው አብራርተዋል። ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቱ ግንባታ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋሉ ሲሉ ከንቲባው አቶ ተመስገን ተናግረዋል። ትምህርት ለትውልድ የቄራ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤትን ቼንትሮ አዩቲ ኢትዮጵያ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመቀናጀት የሚከናወን ሲሆን ከተቋሙ በኩል መልዕክታቸውን ያስተላለፊት ሀላፊ ህብረተሰቡ ለትምህርት ያለውን ተነሳሽነት አድንቀዋል። የግንባታ ስራውን የሚያከናውነው መሀንዲስ ረድኤት ገብረዮሀንስ በ5 ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልፀዋል። በስፍራው የተገኙ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል።

  August 17, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የሚመሰረተው አዲሱ ክልል ብዙ ብዝሃነት ያለበት በመሆኑ የተዘጋጀው ረቂቅ ህገ መንግስት ፍትሃዊነትና እኩል ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ እንዲሆን ኃላፊነት እንወጣለን አሉ የወላይታ ዞን ምክር ቤት አባላት። ዛሬ በተካሄደው የዞኑ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ምክር ቤቱ የአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ሕቦች ክልል ህግ መንግስት አርቃቂ ኮሚሽን አባላትን መርጧል። በሀገራችን 12ኛ ክልል ሆኖ የሚመሰረተው አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ብዙ ብዝሃነት ያለበት በመሆኑ የተዘጋጀው ረቂቅ ህገ መንግስት የህዝቦችን ፍትሃዊነትና እኩል ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንዲሆን ሁሉም ሰው የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል። የወላይታ ዞን አፈ ጉባኤ ወ/ካሰች ኤልያስ ከዚህ በፊት የነበረው ህገ መንግስት ህዝቦችን በስፋት ከማሳተፍ አንጻር የነበረውን ክፍተት በዚህ ረቂቅ ህገ መንግስት ለማሻሻል በሁሉም ምክር ቤቶችና ማህበራዊ መሰረቶች ውይይት ከማድረግ አንጻር የተሻለ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የሁሉም ብሔሮችና ብሔረሰቦች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግና የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክሬሲያዊ መብት የሚያረጋግጥ ህገ መንግስት እንዲዘጋጅ እየተሰራ ባለው ስራ የዞኑ ምክር ቤትም ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት አክለው ገልጸዋል። ጉባኤው የብሔረሰቦች ምክር ቤት አባል የነበሩት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ወደ ፌድሬሸን ምክር ቤት የገቡ በመሆናቸው በእርሳቸው ምትክ ወ/ሮ ጤናዬ ትራንጎን ለብሔረሰቦች ምክር ቤት መርጧል። በመጨረሻም ጉባኤው የአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ህግ መንግስት አርቃቂ ኮሚሽን አባላትን በመምረጥ ተጠናቅቋል።

  August 11, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተዛባ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው አሉ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ መትከል ብቻ ሳይሆን ችግኞች በአግባቡ እንዲጸድቁም ህብረተሰቡ በትኩረት መንከባከብ እንዳለባቸው የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ አሳሰቡ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ እና የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በዞኑ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ተገኝተው ችግኝ ተክለዋል:: እንደወላይታ ዞን በአንድ ጀንበር 21.6 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ከጧቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተዛባ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ለማስተካከል ጊዜው አሁን በመሆኑ ሁላችንም በጠንካራ ወነ መነሳት ያስፈልጋል አሉ ። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ እየተቸገረች ባለችበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ችግኞችን በመትከል በተከታታይ አመታት ያስመዘገበችው ውጤት ለመላው አለም ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ብለዋል:: የአካባቢው ነዋሪዎችም በማለዳው ለችግኝ ተከላ ወደተዘጋጀው ቦታ ደርሰው ተከላ እያከናወኑ ይገኛሉ። ለተከላ ከተዘጋጁ ችግኞች መካከል ለጥምር ደን፣ ለእንስሳት መኖ፣ ለምግብነት የሚያገለግሉ ፍራፍሬዎች፣ የውበትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች የሚሰጡ ሀገር በቀል ዝርያ ያላቸው ችግኞኝ ይገኙበታል ። በዛሬው ዕለት በመላው ሀገሪቱ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪክ ለመስራት የታቀደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጀምሯል።

  July 17, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 21 ሚሊየን 653ሺ 333 ችግኞች ዝግጁ መሆናቸውን የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቋል ወላይታ ሶዶ፣ ሐምሌ 9/2015(ወቴቪ)የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ እና ተፈጥሮ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን መድህን በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 96 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ 91 ነጥብ 4 ሚሊየን ችግኝ መዘጋጀቱን ገልፀው ከዚህም ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 21 ሚሊየን 653ሺ 333 ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል። የታቀደውን ከግብ ለማድረስ በተለያዩ ወረዳዎች ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ መስፍን መድህን ጠቁመው ከ1 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፋ ገልፀዋል። የችግኝ መትከያ ጉድጓድ ዝግጅት ምዕራፍ መጠናቀቁንም ተናግረዋል። ሐምሌ 10 ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አጠቃላይ የዞኑ ህዝብ አሻራውን ለማሳረፍ ኃላፊነት እንዲወጣ ምክትል ኃላፊው መልዕክታችን አስተላልፈዋል።

  July 16, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • Wolaita TV | ወላይታ ቲቪ: ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 21 ሚሊየን 653ሺ 333 ችግኞች ዝግጁ መሆናቸውን የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቋል ወላይታ ሶዶ፣ ሐምሌ 9/2015(ወቴቪ)የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ እና ተፈጥሮ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን መድህን በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 96 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ 91 ነጥብ 4 ሚሊየን ችግኝ መዘጋጀቱን ገልፀው ከዚህም ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 21 ሚሊየን 653ሺ 333 ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል። የታቀደውን ከግብ ለማድረስ በተለያዩ ወረዳዎች ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ መስፍን መድህን ጠቁመው ከ1 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፋ ገልፀዋል። የችግኝ መትከያ ጉድጓድ ዝግጅት ምዕራፍ መጠናቀቁንም ተናግረዋል። ሐምሌ 10 ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አጠቃላይ የዞኑ ህዝብ አሻራውን ለማሳረፍ ኃላፊነት እንዲወጣ ምክትል ኃላፊው መልዕክታችን አስተላልፈዋል። ምንጭ ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/ የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/wolaitatelevision ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ https://twitter.com/WolaitaTV?s=09 ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን የግብርናና ሥራ ዕድል ፈጠራና የቱሪዝም ሥራ እንቅስቃሴ ለመጎብኘት ወደ ወላይታ ዞን የመጣው የፌደራል መንግስት ድጋፍና ክትትል ቡድን በዞኑ በ3 መዳረሻዎች ደርሰው ባዩት ነገር ላይ ከዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል። ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ብዝሃ ኢኒስቲትዩት እና ከቱሪዝም ኢኒስቲትዩት የተወጣጣው የድጋፍና ክትትል ቡድን በዳሞት ሶሬ፣ ሁምቦ ወረዳና ወላይታ ሶዶ ከተማ ቱሪዝምን ጨምሮ በሌሎች በተጠቀሱት ዘርፎች ባዩት ነገር ያገኙትን ግብረ መልስ በጥንካሬና በውስንነት ለይተው አካፍለዋል። የድጋፍና ክትትል ቡድኑን የሚያስተባብሩት የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ በዞኑ ልማታዊ ሥራዎችን በንቅናቄ ለመምራት እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰዋል። በአካባቢው ከሌሎች አካባቢዎች በተሻለ ሁኔታ ያለው ሠላምና ጸጥታ የተለየ ነገር በመስራት ቀድሞ ለመሄድ ምቹ አጋጣሚ የመሆኑን ያክል አጋጣሚውን በሚገባ መጠቀም እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው አርሶ አደሩና ወጣቱ ዘንድ ያለው የለውጥ ፍላጎት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል። ኃላፊዎቹ አክለው በተጀማመሩ ልማታዊ ሥራዎች ላይ እሴት ጨምሮ መስራትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎችን ማበራከት እንደሚያስፈልግ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አሲዳማ አፈር ያለበትን አካባቢ አክሞ መጠቀሙ ላይ አፅንኦት መስጠት እንደሚያስፈልግም አስምረውበታል። አረንጓዴ አሻራ ላይ የተጀመረው ነገር የሚበረታታ ነው ያለው ቡድኑ አካባቢው ተዳፋታማ የመሆኑን ያክል በልዩነት መሥራት ያስፈልጋል ብሏል። የማዳበሪያ እጥረት በሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ለመተካት የሚደረገው ጥረት አበረታች ለውጥ በዞኑ ማምጣቱን ተናግረው ሥራ ዕድል ፈጠራን የፖለቲካ ትርጉም ሰጥቶ መምራትና በቱሪዝም ዘርፍ ያለውን የመቀዛቀዝ ችግር በመቅረፍ ዘርፉን ማነቃቃት እንደሚያስፈልግ በግብረ መልሳቸው ጠቁመዋል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በበኩላቸው ቡድኑ የሰጠው ግብረ መልስ ዞኑ በቀጣይ ለመስራት ለሚያቅዳቸው ነገሮች አቅም ስለሚሆን ጠንካራ ነገሮችን ይበልጥ ለማጎልበትና ውስንነቶችን ለማረም እንሠራለን ብለዋል። የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በዞኑ ተጀምሮ የተቋረጠውን የአየር ማረፊያ ግንባታ ጉዳይ የቤት ሥራ አድርጎ እንዲወስድም ዋና አስተዳዳሪው ጠይቀዋል። ለልማት ቦታ ወስደው ያላለሙ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም ጉዳይ በመድረኩ ተጠይቋል። የቡድኑ አባላትም ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል እንደሚያደርሱትና ቀጣይ የቤት ሥራ አድርገው እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

  July 16, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት ኢንሸቲቭ እንደወላይታ አመርቂ ውጤት አያመጣ ነው አሉ የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መስፍን ዳዊት በግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ የተመራው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቡድን በዞኑ በዳሞት ሶሬ በተለያዩ ቀበሌያት የሌማት ትሩፉት ስራዎችን ተዘዋውረው በጎበኘበት ወቅት ነው አቶ መስፍን ይህንን የተናገሩት። በዳሞት ሶሬ ወረዳ አርሶ አደሮች በሰብል መንደር፣ በወተት መንደር በስራስርና በሌሎች መንደሮች ወጥ በሆነ መልኩ በሰሩት ስራ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አንጻር አመርቂ ውጤት መታየቱነሰ አቶ መስፍን ተናግረዋል። በማያያዝም ወላይታ ቡናን በስፋት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተያዘውን ዞናዊ ዕቅድ ለማሳካት አርሶ አደሮች የተፈጥሮ የማምረት ዘዴን በመጠቀም እየሰሩ ያሉት ስራ ለሌሎች አካባቢዎችም ተሞክሮ የሚሆን ስለሆነ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። ለርካታ ስራ አጥ ወጣቶች ስራ ዕድል የተፈጠረው በግብርና ዘርፍ ነው ያሉት አቶ መስፍን በሰብል ልማት፣ በዶሮ እርባታ እና በሌሎች የስራ ዘርፎች ከከፍተኛ የት/ተ ተቀበማት የተመረቁ ወጣቶች ከዚህ በፊት የነበረውን የተዛባ አመለካከት በማስተካከል ሰርቶ ወደመለወጥ ተግባር በመግባታቸው የተሻለ ውጤት መታየቱን አያይዘው ተናግረዋል። ይህ ውጤት ሁሉም አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ አርሶ አደሮችና ወጣቶች በትጋት ሰርተው ያመጡት ውጤት በመሆኑ ይህንን መነሳሳት በማጠናከር የህዝቡን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ በቅንጅት መትጋት ያስፈልጋልም ብለዋል።

  July 15, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በወላይታ ዞን ሐምሌ 10/2015 ዓ/ም በአንድ ጀምበር ከ21 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ይህ መርሃ ግብር በሀገራችን በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል የተያዘው ዕቅድ አካል መሆኑንና በዚህም ሀገራችን አዲስ ታሪክ የሚታስመዘግብበት መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ገለጹ፡፡ አቶ አክሊሉ በጉዳዩ ዙሪያ ትናንት ማታ በሰጡት ገለጻ በሀገራችን በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ፣ በክልላችን ደግሞ 110 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በታቀደው መነሻ በወላይታ ዞን 1.3 ሚሊዮን ሰው በማሳተፍ 21 ሚሊዮን 653 ሺህ 353 ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን አመላክተዋል፡፡ ችግኝ ተከላውን ለማሳለጥ በተለያየ የዕድሜ ክልል በመመደብ ለመስራት መታቀዱን የጠቆሙት አቶ አክሊሉ ዕድሚያቸው ከ12 ዓመት ጀምሮ ያሉ ዜጎች በተሰጣቸው ቁጥር ልክ ይተክላሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ የዘንድሮውን ችግኝ ተከላ ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው የተተከሉ ችግኞች በተፋሰስ ተለይተው ቁጥራቸው በየሰዓቱ በሳታላይት አማካኝነት በሀገር-አቀፍ መረጃ ቋት ውስጥ የሚገቡ መሆናቸውን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው ለዚህም 127 ንዑሳን ተፋሰስ የተዘጋጁ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በዚህ መርሃ ግብር ለዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተዘጋጁ ከ393 ሺህ በላይ ወጣቶች እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች በንቃት እንደሚሳተፉ አቶ አክሊሉ ተናግረዋል፡፡ ለችግኝ ተከላው በቂ ጉድጓድ መቆፈሩና እስከትላንትና ማታ ድረስ 38 ከመቶ የሚሆን ችግኝ ወደሚተከልበት ስፍራ መጓጓዙ ተገልጿል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው በዚህ አዲስ ታሪክ በሚናስመዘግብበት ቀን ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አርሶአደሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ነጋዴዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የመንግስት ስራ ኃላፊችና ሌሎችም በነቂስ ወጥተው የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  July 15, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በሀገራችን እየሸረሸረ የመጣውን የበጎነት እሴት ለመመለስ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ለውጥ እያመጣ ነው አሉ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ። የደቡብ ክልል ወጣቶች ክልላዊ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በወላይታ ሶዶ ከተማ ተጀመረ። የደቡብ ክልል ወጣቶች ክልላዊ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በሀገራችን እየሸረሸረ የመጣውን የበጎነት እሴት ለመመለስ በወጣቶች በጎ አገልግሎት እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው አሉ ። ወጣቶች በበጎ ፈቃድ በመሳተፍ ባህላቸውን በማወቅና የምራል ልዕልናቸውን በማሳደግ የሀገራችንን ከፍ ለማድረግ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል በዓለም ደረጃ ሀገራችንን ከፍ ለማድረግ በግልና በቡድን መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል። የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘርሁን እሸቱ ወጣትነት እውቀትና ጉልበት በማጣመር ውጤት ለማምጣት የሚያስችል ወርቃማ ጊዜ በመሆኑ ለማህበረሰብ ጥቅም ተግቶ መበስራትና ከተለያዩ አሉባለ ተግባር በመቆጠብ ለተሻለ ለውጥ ተግተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ባለፈው ዓመት ከ1.8 ሚሊዮን ወጣቶች በመሳተፍ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ስራ መፈጸሙን ገልጸዋል። በክልሉ በዘንድሮው የወጣቶች የክረምት በጎ አገልግሎት 2.4 ሚሊዮን ወጣቶች ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት በመስጠት ከ7.6 ሚለዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል። በክልሉ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚሳተፉና የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣ የከተማ ጽዳት እና የአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚፈጸሙ ገልጸዋል። ወጣቶቹ በ11 ዋና ዋና መስኮች እንደሚሳተፉና 2.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት በመስጠት ከ7.6 ሚለዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ወደተግባር መገባቱ ተገልጿል። በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ በወጣቶች አገልግሎት ተሳትፎ በክልል ደረጃ ከ5 ሺህ 300 በላይ የአቅመ ደካሞች ቤት ጥገና እንደሚካሄድና ከ110 ሚሊዮን በላይ ለተለያዩ ጥቅሞች የሚዉሉ ችግኞች እንደሚተከሉ ተናግረዋል። በዞኑ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ393 ሺህ በላይ ወጣቶችን በ11 ዋና ዋና መስኮች በማሳተፍ የህዝቡን ማህበራዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኙ የገለጹት ደግሞ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ናቸው። በመርሃ ግብሩ ላይ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጊባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሱርሜሎን ጨምሮ ሌሎች የፌድራል፣ የክልልና የተለያዩ ዞኖች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

  July 13, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የህዝባችንን ማህበራዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ማስፋት ያስፈልጋል- የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ የ2015 ዓ/ም የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በወላይታ ሶዶ ከተማ በተለያዩ መስኮች ተጀምሯል።

  July 13, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በሀገራችን እየሸረሸረ የመጣውን የበጎነት እሴት ለመመለስ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ለውጥ እያመጣ ነው አሉ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ። የደቡብ ክልል ወጣቶች ክልላዊ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በወላይታ ሶዶ ከተማ ተጀመረ። የደቡብ ክልል ወጣቶች ክልላዊ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በሀገራችን እየሸረሸረ የመጣውን የበጎነት እሴት ለመመለስ በወጣቶች በጎ አገልግሎት እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው አሉ ። ወጣቶች በበጎ ፈቃድ በመሳተፍ ባህላቸውን በማወቅና የምራል ልዕልናቸውን በማሳደግ የሀገራችንን ከፍ ለማድረግ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል በዓለም ደረጃ ሀገራችንን ከፍ ለማድረግ በግልና በቡድን መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል። የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘርሁን እሸቱ ወጣትነት እውቀትና ጉልበት በማጣመር ውጤት ለማምጣት የሚያስችል ወርቃማ ጊዜ በመሆኑ ለማህበረሰብ ጥቅም ተግቶ መበስራትና ከተለያዩ አሉባለ ተግባር በመቆጠብ ለተሻለ ለውጥ ተግተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ባለፈው ዓመት ከ1.8 ሚሊዮን ወጣቶች በመሳተፍ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ስራ መፈጸሙን ገልጸዋል። በክልሉ በዘንድሮው የወጣቶች የክረምት በጎ አገልግሎት 2.4 ሚሊዮን ወጣቶች ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት በመስጠት ከ7.6 ሚለዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል። በክልሉ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚሳተፉና የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣ የከተማ ጽዳት እና የአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚፈጸሙ ገልጸዋል። ወጣቶቹ በ11 ዋና ዋና መስኮች እንደሚሳተፉና 2.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት በመስጠት ከ7.6 ሚለዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ወደተግባር መገባቱ ተገልጿል። በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ በወጣቶች አገልግሎት ተሳትፎ በክልል ደረጃ ከ5 ሺህ 300 በላይ የአቅመ ደካሞች ቤት ጥገና እንደሚካሄድና ከ110 ሚሊዮን በላይ ለተለያዩ ጥቅሞች የሚዉሉ ችግኞች እንደሚተከሉ ተናግረዋል። በዞኑ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ393 ሺህ በላይ ወጣቶችን በ11 ዋና ዋና መስኮች በማሳተፍ የህዝቡን ማህበራዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኙ የገለጹት ደግሞ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ናቸው። በመርሃ ግብሩ ላይ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጊባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሱርሜሎን ጨምሮ ሌሎች የፌድራል፣ የክልልና የተለያዩ ዞኖች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

  July 13, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በወላይታ ዞን ዞናዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀመረ በወላይታ ዞን 2ኛ ምዕራፍ ዞናዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መርህ ቃል በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ ተጀምሯል። ዞናዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብሩን የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ እና የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ በይፋ አስጀምረዋል። የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ በሀገር ደረጃ በሁለተኛው ምዕራፍ 25 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውቀዋል። አረንጓዴ አሻራችን ዛሬ ላይ ለነገያችንን መትከል እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ሀይለማርያም ችግኝ መተከል ምቹ፣ ውብና አረንጓዴ አከባቢውን ለመፍጠር የጎላ ሚና እንዳለውም አስገንዝበዋል። ችግኝ ተከላ ለመርሃ-ግብር ብቻ ሳይሆን ፀድቆ ያለምነውን ዓላማ እንዲያሳካልን ለማድረግ ከዚህ በፊት የተተከሉትንም አሁን የምንተክላቸውን መንከባከብ እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርበዋል። የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ በበኩላቸው ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን መተከል የአየር ንብረት ለውጥና ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል። ለነገው ትውልድ ቅርስ የሚሆን ስራን ዛሬ ላይ ሆነን አሻራችንን የምናሳርፍበት ስለሆነ ሁሉም ዜጎ ለቀጣይ ትዉልድ አሻራዉን በማኖር ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል። ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን እንዲጸድቅ ለማድረግ እንክብካቤ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዮሐንስ በሁሉም መዋቅሮች የሚገኙ አመራሮች በስልጠናው ማጠቃለያ አረንጓዴ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ አሳስበዋል። ዘንድሮ በወላይታ ዞን ከ96 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ መያዙን ከመምሪያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

  June 28, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በመኸር እርሻ ከ104ሺ 700 በላይ ሄክታር ማሳ በማልማት ከ13 ሚሊዮን 193 ሺህ 800 ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱን የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ። በዞኑ የ2015/16 የመኸር እርሻ ሥራ ፈጻሚ ማዘጋጃ ንቅናቄ መድረክ ተካሂዶ የተግባር ግብ ስምምነት ተደርጓል። በመድረኩ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ሁሉም መዋቅሮች ጥራት ያለውን ዕቅድ አቅደው መንቀሳቀስ አለባቸው ብለዋል። በመኸር ዕቅድ አተገባበር ላይ የግብርና ባለሙያዎች አርሶ አደሩን በብቃት ለመደገፍ የሚያስችል በቂ የተግባርና ንድፈ ሀሳብ ውይይትና ሥልጠና ሊሰጥ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። በመቀጠልም ከዋናው ፈጻሚ አርሶ አደርም ጋር በየደረጃው በቂ ውይይት ተደርጎ መግባባት መፈጠር አለበትም በማለት ሥራዎች በተደራጀ አግባብ እየተገመገሙ መመራት አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል። የልማታችን ነቀርሳ የሆነው የአፈር ማዳበሪያ የግብአት ዕዳ መፈታት እንዳለበት የገለጹት አቶ አክሊሉ ሌሎች ለሥራ ዕድል ፈጠራ የተሠራጩ ዕዳዎችም በትኩረት መመለስ አለባቸው ሲሉ አበክረው አሳስበዋል። የወላይታ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ አመራሩ ወስኖ ከተነሳ የትኛውንም ተልዕኮ ማሳካት እንደሚችል ካለፈውና ዳግም ከተደረገው ህዝበ ውሳኔ ማረጋገጥ መቻላቸውን ገልጸው ሁሉንም ተግባራት በጊዜ የለንም መንፈስ መፈጸም አለብን ብለዋል አመራሩ መኸርን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ተግባራት አቀናጅቶ ለመምራት ዝግጁ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል። ከመኸር እርሻ ሥራም አንጻር የወል መሬቶች ጾም ማደር እንደሌለባቸውም አሳስበዋል። የወላይታ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት ሁሉንም አማራጮች አሟጠን በመጠቀም የመኸር ሥራን ለማሳካት ርብርብ መደረግ እንዳለበት በመግለፅ ባለሙያው አርሶ አደሩን በትኩረት መደገፍ እንዳለበትም አብራርተዋል። የአረንጓዴ አሻራ ልማት ሥራም ዘንድሮ የሚከናወነው የ30-40-30 ፕሮጀክት አካል የሆነው በአርሶ አደር 40 ችግኝ የማስተከልና የምርጥ ዘር ግብአት መግዣ ገንዘብ በትኩረት ተሰብስቦ ለእርሶ አደሩ ግብአት በጊዜ እንዲቀርብ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል። የምርጥ ዘር እና የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግር ታቅዶ ካልተሠራበት በአፈጻጸሙ ላይ እክል ሊያጋጥም እንደሚችል ተሳታፊ የወረዳ አመራሮች ስጋታቸውን አንስተዋል። በግብአት ስርጭት የሚስተዋሉ ህገ ወጥነቶችን መቆጣጠር ያስፈልጋል ያሉት ተሳታፊዎች የግብአት ችግሮች ከተፈቱ የመኸር ተግባራትን ማሳካት እንደሚችሉ አረጋግጠዋል። በመድረኩ የተግባር ግብ ስምምነት የፊርማ ሥነ ሥርዓት ተደርጓል።

  June 22, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ትምህርት መሠረታዊ ሰብአዊ መብት በመሆኑ ሁሉ ዜጋ በአካባቢው ባሉ ትምህርት ቤቶች ጥራት ያለውን ትምህርት ማግኘት ይኖርበታል ተባለ። ይህንን ዓላማ ገቢራዊ ለማድረግ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ። ቢሮው በአዲሱ ትምህርት ሥርዓት አተገባበር ላይ ተግዳሮት የሚሆኑ ችግሮችን በመቅረፍ ሥርዓተ ትምህርቱ ውጤታማ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን አስታወቋል። የትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የሥርዓት ትምህርት ዝግጅት ትግበራና ቴክኖሎጂ አቅርቦት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ስምኦን በአዲሱ ስረዓተ ትምህርት ትግበራ ወቅት የመማሪያ መጸሕፍት ችግር ማጋጠሙን ተናግረዋል። በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ወቅት የትምህርት መሳሪያ ግብዓት እጥረት መኖሩን የጠቆሙት አቶ ስንታየሁ ጥራቱን የጠበቀ ስርዓተ ትምህርትን ለማምጣት የግብአት እጥረቱን መቅረፍ ያስፈልጋል ብለዋል:: የትምህርት ግበአትን ለማሟላት ደግም የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑንም ገልጸዋል። የትምህርት ስራዓቱን በቴክኖጂ በማስደገፍ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ መሆኑንም ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለው ገልፀዋል። ለ8ተኛ ክፍል ተማራዎች ልዩ ድጋፍ ኘሮግራም እየተሰጠ መሆኑ አበራታች ነው ያሉት የስራዓት ትምህርት ትግበራ ባለሙያ አቶ ደጉ ዘውዴ የትምህርት ቁሳቁስ ግበዓት እጥረት መኖሩን ጠቁመዋል። የተዘጋጁ የመማሪያ መጻሕፍት ጥራት ላይም በቀጣይ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልፅዋል። የአዲሱ ስረዓተ ትምህርት ሙሉ ትግበራ ቀጣይ አቅጣጫ እንዲሚቀመጥም ይጠበቃል።

  June 22, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የጠረጴዛ ልማት ማህበር የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት ለሀገራዊ አረንጓዴ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ። የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማልማት በተሰሩ ቅንጅታዊ ስራዎች ለሀገራዊ አረንጓዴ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ልማት ማህበሩ አስታወቀ፡፡ ልማት ማህበሩ በወላይታ ዞን በሚገኙ በተለያዩ አካባቢዎች ከ 2500 ሄክታር በላይ የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙ ያስቻለ የተፈጥሮ ሀብት ሥራ ማከናወኑን የልማት ማህበሩ ኮሚዩኒኬሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ማኔጀር አቶ ታምራት ማቴዎስ ገልፀዋል፡፡ በ1994 ዓ.ም. የተቋቋመው የጠረጴዛ ልማት ማህበር ሁለንተናዊ አገልግሎት ለሰው ልጆች ሁሉ በሚል መርህ የሚሰራ ሲሆን በእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ፤ ትምህርት እና የጤናና ስነ-ምግብ ዘርፎች የዜጎችን ህይወት የለወጡ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በሀገራችን በትኩረት እየተሰራ ያለው የአረንጓዴ አሻራ ስራን ልማት ማህበሩ አስቀድሞ በመጀመር ለውጥ ማምጣት መቻሉንና በዚህም በዞን የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ጊዜያት በተለያዩ ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ከምርታማነት ውጭ የነበረውን ከ 2 ሺህ 5 መቶ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በመንከባከብ አረንጓዴ በማልበስ ወደ ምርታማነት መመለስ ተችሏል ፡፡ ማህበሩ በአረንጓዴ ልማት በሚሰራቸው ስራዎች ለፍራፍሬ ዝርያዎች ትኩረት እንደሚሰጥ የገለፁት አቶ ታምራት የግብይት እሴት መጨመር ፤የድህረ-ምርት አያያዝ ፤ ቴክኖሎጂ ማስተዋወቅ ፤ የገበያ ትስስር መፍጠር እና ሌሎችም የማህበሩ ተጨማሪ የትኩረት መስኮች ናቸው ብለዋል፡፡

  June 22, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በድጋሚ የተካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን በማስመልከት ለዞኑ ሕዝብ ምስጋና አቀረቡ። በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥና ቆጠራው ያለምንም ጸጥታ ችግር በሠላማዊ መንገድ መጠናቀቁን ጠቁመዋል ። በምርጫው ወቅት ብዙ መራጮች ረዥም ሠልፍ ላይ ሳይሰላቹ ተሰልፈው በሠላማዊ መንገድ መምረጣቸው ትልቅ ኃላፊነት መሆኑነሰ ጠቁመው የምርጫ ድምጽ ቆጠራው ተጠናቅቆ ጊዚያዊ ውጤት በየምርጫ ጣቢያው ይፋ መሆኑን አስረድተዋል ። በመራጩ ቁጥር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደረው ጉዳይ ከመታወቂያ ጋር የተፈጠሩ ክፍተት መሆኑንና አንድ ዜጋ በአከባቢው ከቆየ በኋላ አድስ መታወቂያ መያዝ ከምርጫ ማግለል በመራጩ ቁጥር ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረና በሂደት መስተካከሉን ጠቁመዋል። በመጀመሪያው ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ድምጽ የምርጫ ሕግ ተጥሷል ተብሎ ምርጫው ተሰርዞ ዳግም መመረጡ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ ያደርጋል ብለዋል። የሕዝቡ ጨዋነትና ለምርጫ ሕግ ተገዥነት የምርጫ ቦርድ በራሱ የመወሰንና የማድረግ ኃላፊነት ተግባራዊ ያደረገበት ሁኔት መሆኑን ገልጸዋል ። የምርጫ ሂደት ተከትሎ የሕግ ተጠያቂነት በአንድ ቀን ተመዝግቦ በአንድ ቀን ድምፅ የሰጠ ሕዝብ ወላይታ መሆኑና በኢትዮጵያ ደረጃ በታሪክ የሚታወስ ሕዝብ መሆኑን ጠቅሰዋል ። በምርጫ ቦርድ በኩል የዲሞክራሲ ልምምድ አንጻር ቀዳሚ ሥፍራ የሚይዘው ሥራ የሠሩ የዞኑ ሕዝብ ትዕግሥትና ጽናት አመስግነዋል ። ሚዲያዎች ፣የጸጥታ መዋር፣ ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ ያሉ አመራሮችና ምርጫ ታዛቢዎች ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረት በማድረጋቸው በዞኑ አስተዳደር ስም አመስግነዋል ። ዋና አስተዳዳሪው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም.በወላይታ ዞን ያስፈጽመው የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ ምርጫ በታቀደለት ጊዜ ሠለዳ መሠረት መራጩ ሕዝብ ምርጫው ሠላማዊና ታአማኒ እንዲሆን በማድረጉ ያለው ሂደት በመከተል የሚወጣውን ውጤት እንዲጠብቁ አሳስበዋል። በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥና ቆጠራው ያለምንም ጸጥታ ችግር በሠላማዊ መንገድ መጠናቀቁን ጠቁመዋል ።

  June 22, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ከካዎ ጦና ምርጥ ስብስብ ውስጥ የተመረጡ ታታሪዎች ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በመሰለፍ የተሻለ ነገር ለመስራት ዝግጅት ላይ መሆናቸዉን ይናገራሉ፡፡ ግብ ጠባቂዉ ቢኒያም ገነቱ እና አማካዩ አበባየሁ ሃጅሶ በአሰልጣኝ ዳንኤል ገ/ማርያም ለሚመራዉ ብሄራዊ ቡድን መጠራታቸዉ ይታወሳል፡፡ ሁለቱም መሻታቸዉ ከ23ቱ አልፈዉ ለምርጥ 11 ተመራጭ መሆን ነዉ፡፡ ተጨማሪ ነገሮችንንና የወደፊት ራዕያቸዉን በዝርዝር ይናገራሉ፡፡ በወላይታ ቴሌቪዥን የዕለተ ሰኞ ሰኔ 5/2015 ዓ.ም ዜና ሰዓት ላይ ተጨማሪ ዝርዝር ታገኛላችሁ፡፡ ለማንኛዉም የወላይታ ዲቻ ፍሬ ለሆኑት ለነኝህ ተስፈኞች መልካሙን ተመኙላቸዉ፡፡ የወላይታ ቴሌቪዥን መልካም ምኞቱን ከወዲሁ ይገልጻል፡፡

  June 12, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በህብረተሰቡ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጡ ይገባል አሉ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በዞኑ የተጀመሩ የድህነት ቅነሳ ስራዎች የሰፊውን ማህበረሰብ ህይወት የሚለውጡ እንዲሆኑ የመንግሰና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማቀናጀት በትኩረት እየሰራሁ ነኝ ያለው ደግሞ የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ነው የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ 17ኛ ዙር የመንግሰና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የጋራ ምክክር ፎረም በወላይታ ጉታራ እያካሄደ ይገኛል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ እንዳሉት መንግስት ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምቹ የሆነ አዋጅ በማውጣት የተለያዩ ድህነት ቅነሳ ስራዎች እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። በመሆኑም በሁሉም ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በህብረተሰቡ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማሞጣት አለባቸው ብለዋል። ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዞኑ 3.4 ቢለዮን ብር በመመደብ እየሰሩ ያሉት ስራ የሚበረታታ ነው ብለው ቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማምጣትና በድህነት ቅነሳ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጡ ተቀራርቦ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቱ ጳውሎስ በዞኑ የድህነት ቅነሳ ስራዎች ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዞኑ ከሁሉም መዋቅሮች አመራር አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ ብለዋል። በዞኑ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እየተሰሩ ያሉ 83 ፕሮጀክቶች አሉ ያሉት አቶ መብራቱ በእነዚህም የሕዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል። በምክክር ፎረሙ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እየሰሩ ያሉት ስራ የዞንና የወረዳ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሮች አመራር አካላት እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

  May 24, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በህብረተሰቡ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጡ ይገባል አሉ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በዞኑ የተጀመሩ የድህነት ቅነሳ ስራዎች የሰፊውን ማህበረሰብ ህይወት የሚለውጡ እንዲሆኑ የመንግሰና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማቀናጀት በትኩረት እየሰራሁ ነኝ ያለው ደግሞ የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ነው የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ 17ኛ ዙር የመንግሰና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የጋራ ምክክር ፎረም በወላይታ ጉታራ እያካሄደ ይገኛል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ እንዳሉት መንግስት ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምቹ የሆነ አዋጅ በማውጣት የተለያዩ ድህነት ቅነሳ ስራዎች እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። በመሆኑም በሁሉም ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በህብረተሰቡ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማሞጣት አለባቸው ብለዋል። ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዞኑ 3.4 ቢለዮን ብር በመመደብ እየሰሩ ያሉት ስራ የሚበረታታ ነው ብለው ቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማምጣትና በድህነት ቅነሳ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጡ ተቀራርቦ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቱ ጳውሎስ በዞኑ የድህነት ቅነሳ ስራዎች ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዞኑ ከሁሉም መዋቅሮች አመራር አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ ብለዋል። በዞኑ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እየተሰሩ ያሉ 83 ፕሮጀክቶች አሉ ያሉት አቶ መብራቱ በእነዚህም የሕዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል። በምክክር ፎረሙ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እየሰሩ ያሉት ስራ የዞንና የወረዳ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሮች አመራር አካላት እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

  May 24, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ልማት ማህበር መላውን የወላይታ ህዝብና ደጋፊዎቹን በማስተባበርና ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ገለጹ። የማህበረሰቡ ኑሮ ዘላቂ በሆነ መልኩ እንዲሻሻል ሁሉም አባላትና ደጋፊዎች ከልማት ማህበሩ ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ሊሰራ እንደሚገባም ተገልጿል። የወላይታ ልማት ማህበር 22ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን በወላይታ ጉታራ እያካሄደ ይገኛል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ እና የወላይታ ልማት ማህበር የበላይ ጠባቂ አቶ አክሊሉ ለማ ባደረጉት መክፈቻ ንግግር ልማት ማህበሩ ለዞናችን ብሎም ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማምጣት እየተጋ ይገኛል ብለዋል። ማህበሩ ሰንቀው የተነሳውን ራዕይ ለመሳካት መላው የልማት ማህበሩ፣ አባላትና ደጋፊዎች ተቀናጅተውና ተባብረው በትጋት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። የሕዝባችን የኑሮ ዋስትና በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ከልማት ማህበራችን ጋር ልንሰራ ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስና ፈጣንና ዘላቂነት ያለው ዕድገትን ለመገንባት አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። ልማት ማህበሩ የጀመራቸውን ታላላቅ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቅ በአካባቢው የሚገኙ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል እንደሚፈጥርና በኢኮኖሚ መነቃቃት ላይም የሚጨምረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸዋል ። የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪና የልማት ማህበሩ የቦርዱ ም/ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ፎላ ልማቱ ማህበሩ በአካባቢያችን ሥር የሰደደውን ድህነት ለመቀነስና የህብረተሰቡ የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ አዎንታዊ ሚናም ሲወጣ ቆይቷል ብለዋል። ማህበሩ ከተመሠረተበት ጀምሮ የመንግሥት አጋር በመሆን የልማት ክፍተቶችን በጥናት በመለየት፤ ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ ችግሮችን በመቅረፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለመድረግ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፤ እያከናወነም ይገኛል ብለዋል። ዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጥ እንዲመዘገብ ልማት ማህበሩ የተጫወተው ሚና ቀላል እንዳይደለም ጠቅሰዋል። በአገር ደረጃ እየገጠመን ያለውን የምርጥ ዘር ጥራትና አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ልማት ማህበሩ በአበላ አባያ እርሻ ልማት በ28 ሄ/ር ማሳ ላይ በማልማት 556 ኩ/ል የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜት ማካሄዱ ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በትምህርት ልማት ዘርፍ ሁሌም የምንኮራበትን አንጋፋውን "ሊቃ ትምህርት ቤት" በመገንባት በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን በማፍራት አሻራ አሳርፏል፤ እያሳረፈም ይገኛል ብለዋል። ልማት ማህበሩ ላስመዘግባቸው ድሎች ቀጥተኛ የአባላቱ፣ የአጋሮቹ፣ የደጋፊዎቹ እንዲሁም ታላቅና ሥራ ወዳዱ ህዝባችን ሙሉ ድጋፍ በመሆኑ በዚህ ረገድ ላሳያችሁን ድጋፎች ሁሉ በራሴና በሥራ አመራር ቦርድ ስም ልባዊ ምስጋናን አቅርበዋል፡፡ የልማት ማህበሩ ሰብሳቢ አቶ አሰፋ ናና በበኩላቸው ልማት ማህበሩን ጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት የማህበሩ አባላት፣ አጋሮችና ደጋፊዎች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።

  May 22, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የአየር ንብርት ለዉጥ ለማስተካከል ችግኝ መትከልና መንከባከብ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ በዳሞት ወይዴ በቶራ ሳዴቦ ቀበሌ በቀይ መስቀል ማህበር አዘጋጅነት የተለያዩ ችግኞች ተተክለዋ። ይህ መርሃ ግብር የተካሄደው 56ኛው የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀንን ምክንያት በማድረግ ነው። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጻድቁ ፈለቀ የአረንጓዴ አሻራ ተግባር ከተጀመረ ወዲህ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰው ተግባሩ እንዲቀጥል ሁሉም አካል ችግኝ መትከል እና መንከባከብን ባህል ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል። ቀይ መስቀል ማህበሩ ለአካባቢው ህብረተሰብ ምቹ የአየር ንብረት እንዲኖር ለማስቻል እና የህዝቡን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦ በዞኑ መንግስት ስም በማመስገን የአከባቢው ምህዳር ይበልጥ እንዲቀየር ችግኝ መትከልና በዘላቂነት መንከባከብ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅ ቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል። የወላይታ ዞን ቀይ መስቀል ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማኑኤል አይዛ በበኩላቸው ቀይ መስቀል ማህበሩ የአየር ንብርት ለዉጥ በመሠረታዊነት ለመቆጣጠር በአካባቢው እየሰራ ያለዉ ስራ የሚበረታታ እና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመጠቆም የአየር መዛባት ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ማነቆ ስለሚሆን የአካባቢው ህብረተሰብ ችግኝ በመትከል እንዲሁም ከእንስሳት ንክክ በመጠበቅ ችግኙ እንዲፀድቅ ከፍተኛ ሚና መጫወት አለበት ብለዋል። ቀይ መሰቀል ማህበር በአከባቢው የአየር ንብርት ለዉጥ በመሠረታዊነት ለመቆጣጠር የሰራው ሥራ የሚደነቅ መሆኑን በመጠቆም የወረዳው መንግስት እያደረገ ያለውን አሰፈላጊ ድጋፍ አጠናክሮ እንድቀጥል ጠይቀዋል። የዳሞት ወይዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላላንዳ ዶዳ እንደገለጹት ህብረተሰቡ ለአካባቢው ደህንነት ዋስትና መሆን የሚችሉ የተለያዩ የችግኝ ዓይነቶችን በመትከልና በመንከባከብ ለነገው ትውልድ ማስረከብ እንደሚገባ አሳስበዋል። በረሃማ አካባቢና የተጎዳ ቦታ ላይ ቀይ መስቀል ማህበሩ በራሱ ችግኝ ጣቢያ ችግኝ ከማፊላት አልፎ በመትከል እንዲሁም የአካባቢውን ህብረተሰብ በማስተባበር የአየር ንብረት ለመቆጣጠር ለሰራው እና እየሰራ ላሌው ሥራ በማመስገን የወረዳው መንግስት አስፈላጊ ድጋፍና ትብብር ያደረጋል ብለዋል። እንደ ሀገር የተጀመረውና ውጤት የተመዘገበው የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር ሲታሰብ የአየር ንብረት ለውጥ ይታሰባል፣ የተስተካከለ አየር ንብረት ሲኖር ደግሞ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የምናደርገው የግብርናው መስክ ትኩረታችንን ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል። በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጻድቁ ፈለቀን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የወላይታ ዞን ቀይ መስቀል ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማኑኤል አይዛና የቦርድ አባላት፣ የወረዳው አጠቃላይ አመራሮችና የአከባቢው ህብረተሰብ አካላት ተገኝተዋል።

  May 11, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የ1 ሺህ 444ኛውን የኢድ አል-ፈጥር በአል በማስመልከት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የወላይታ ዞን ነዋሪ እና መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች። እንኳን ለዚህ ታላቅ በአል በሰላም አደረሣችሁ አደረሰን! እያልኩ በዚህ ታላቅ ኩነት ላይ መልዕክት ለማስተላለፍ ዕድል በማግኘቴ የተሠማኝን ታላቅ ደስታ በዞናችን አስተዳደርና በራሴ ስም ለመግለፅ እወዳለሁ። የዘንድሮው ኢድ አል-ፈጥር በዓል ቀደም ሲል በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተፈጥሮ የነበረው የሰላም እጦት በሰላም ወዳዱ የህዝብ ልጆች ፍላጎት ተቀርፎ በሀገራችን አንጻራዊ ሰላም በሰፈነበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ኩነቱን ልዩ የሚያደርገው ሲሆን ዘላቂ ሰላም በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች እንዲረጋገጥ ሁላችንም በቁርጠኝነት በቀጣይነት ልንሰራ ይገባል፡፡ በበዓሉ የሚንጸባረቁ እርስ በእርስ የመጠያየቅና የመደጋገፍ፣ የአብሮነትና የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የርህራሄና የደግነት ዕሴቶች የበለጠ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል፡፡ ኢትዮጵያችን ለዘመናት በአብሮነት የዘለቁ የብዝሀ ሀይማኖት፣ የቋንቋዎች፣ ባህሎችና ታሪኮች ሀገር ናት። የሀገራችን ህዝቦች ዘመናትን ያስቆጠረ በማይበጠስ መልኩ የተጋመዱ የጋራ ሀገረ_መንግስት ግንባታ ታሪክና የማይሸርሸር የሥነ ልቦና አብሮነት የተጎናፀፉ ህዝቦች ናቸው። ሀገራችን እየገጠሟት ያሉት ፈተናዎች የበለጠ እንድንተጋና እንድንታትር የሚያደርጉን እንጂ ከተስፋ ሰጪና ዘላቂ ጉዟችን ለአፍታም ፈቀቅ ሊያደርጉን አይችሉም። ይልቅ በሚያጋጥሙን ጊዜያዊ ፈተናዎች ሳንሸበር ለዘላቂ ህዝባዊ ጥቅም መረጋገጥ ተግተን መስራት ይጠበቅብናል። ጠላቶቻችን በየጊዜው የሚደቅኑብንን ተለዋዋጭ ፈተናዎች ቀልብሰን የጀመርነውን እልህ አስጨራሽ የልማት ጉዞ በማሣካት የበለፀገች ሀገር ለልጆቻችን የማውረስ ራዕያችንን ዕውን ለማድረግ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን መንቀሳቀስ ይኖርብናል። የብልፅግና ግቦቻችንን ዕውን ለማድረግ ሠላማችን እንዳይታወክ የድርሻችንን በተነሳሽነት ልንወጣም ይገባል። አንድነታችንና አብሮነታችን ዕድገታችንን ለሚጠሉ ጠላቶቻችን ዕንቅልፍ የሚነሣ በመሆኑ በሚችሉት መንገድ ሁሉ ለማደናቀፍ የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ በመገንዘብ በንቃት በመመከት ከግባችን ለመድረስ መትጋት አስፈላጊ ይሆናል። የማይቻሉ የሚመስሉ የተወዛዘፋ የተለያዩ ፕሮጀክቶቻችንን በፈታኝ ሁኔታዎች መካከል እያሣካን የመጣንበት ትልቁ ምስጢር በየደረጃው የሚገኘው ህብረተሰባችን አብሮነት በመሆኑ ሂደቱን በማይናወጥ መሠረት መገንባት የህዝባችንን ተጠቃሚነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል ጠቋሚ ቁልፍ መሣሪያ ነውና ህብረ_ብሄራዊ አንድነታችን እንዳይሸረሸር መሥራት ይገባል። በኢፌዴሪ ህገ_መንግስት የተደነገገው የሀይማኖት እኩልነትና ነፃነት ለአፍታም እንዳይሸሪረፍ የህግ ጥበቃው ተጠናክሮ ይቀጥላል። የሀይማኖት ፅንፈኝነትና የብሄር አክራሪነት ፍፃሜው እየተናቆሩ መጠፋፋት በመሆኑ ከድርጊቶቹ መታቀብ ብቻ ሳይሆን ተጋላጮቹን ማስገንዘብ፣ መገሰፅና ማረም ወቅቱ የሚጠይቀው ቁልፍ ጉዳይ ነው። ፈጣሪ የቸረንን ተዝቆ የማያልቅ የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን ለህዝባችን የላቀ ተጠቃሚነት ማዋል የምንችለው በስግብግብነትና እረስ በርስ በመናቆር ሳይሆን ይልቅ እይታችንን፣ ክንዶቻችንንና ክህሎታችንን ፣ ዕውቀታችንንና ጉልበታችንን፣ ሀብታችንንና ቀልባችንን በማስተባበር ነውና ቸል ልንል አይገባም። በሰው ላብ በአቋራጭ የመክበር ፀያፍ አባዜ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያቀጭጭ እኩይ ምግባር በመሆኑ ከድርጊቱ መራቅ ብቻ ሳይሆን የድርጊቱ ተዋናዮችንና ተባባሪዎችን ማጋለጥ፣ ማውገዝና ለህግ አካላት የመጠቆም ጉዳይ ለአፍታም ሊዘነጋ አይገባም። ጠብን በፍቅር ስናሸንፍ፣ ከወደቅንበት ተጋግዘን ለመነሳት ስንጣጣር፣ እንደ አገር አስበን ስናደርግ ሁላችንንም በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ስለሚያደርገን ለሀገራችን ነጻነት፣ ለህዝቦቿ ሰላምና አንድነት በአንድነት ተግተን ልንሰራ ይገባል ። የተወዛዘፉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ ሲሆን ቀሪ ተግባራትን በሁሉም ዘርፎች የ90 ቀናት ዕቅድ ተደርጎ በልዩ ትኩረት እየተሰራ በመሆኑ ለተፈጻሚነቱ የድርሻችንን በተነሳሽነት እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ በመጨረሻም የኢድ አል ፈጥር በአል ስናከብር በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ እና ለአደጋ የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንደ ወትሮው ሁሉ በላቀ ተነሳሽነት የመርዳት፣ የወደቁትን የማንሳት፣ የታረዙትን የማልበሰና የተራቡትን የመመገብ በጎ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በዞናችን አስተዳደርና በራሴ ስም ላሳስብ እፈልጋለሁ። ኢድ ሙባረክ ። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ። አመሠግናለሁ።

  April 21, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በከተሞች መሬት ዘርፍ የሚስተዋለዉን ህገወጥነት በመቅረፍ የህዝብ ተጠቃሚነት ለማስፋት የባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ ይገባል አለ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር። የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር በከተማ መሬትና ፕላን ዙሪያ ከደቡብ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎች ለተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቅቆ አስመርቋል፡፡ በስልጠናው ከተሳተፉ 200 ሰልጣኞች መካከል 34ቱ ሴቶች ሲሆኑ 166ቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው። እነኝህ ሰልጣኞችም የቀሰሙትን ዕዉቀት ወደ ተግባር በመቀየር በከተሞች መሬት ዘርፍ የሚስተዋለዉን ችግር ለመቅረፍ በአፅዕኖት ሊሰሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል።

  April 4, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • 29 ሚሊየን ዶላር ወጪ በማድረግ በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የሶዶ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ባስገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። ወርልድ ቪዥን በኢትዮጵያ የሶዶ ፕሮግራም ማስተባበሪያ በወላይታ ዞን 5 ወረዳዎች ላይ ያስገነባቸውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ጉብኝት አደረገ። የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ እንደዘገበው የወርልድ ቪዥን በኢትዮጵያ የካንትሪ ዳይሬክተር ካርመን ቲል እንዳሉት ዉሃ ምን ያህል አስፈላጊና ህይወት ቀያሪ እንደሆነ በተሰሩት ፕሮጀክት ተጠቃሚ ከሆኑት ሰዎች ሁኔታ መረዳት ችያለሁ ብለው ወርልድ ቪዥን የህጻናት ጉዳይ በጣም አስፈላጊና አንገብጋቢ ስለሆነ ሁሌም ከመንግስት ጎን በመሆን እንሰራለን ብለዋል። በወርልድ ቪዥን የጌሽያሮ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ እንድሪያስ ሾቤው በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በወላይታ ዞን በውሃ፣ በጤና፣ በትህምህርት፣በማህበረሰብ ዙሪያ በርካታ የልማት ስራዎችን ሰርቷል። ከ29 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ በተገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ከ6 መቶ ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል። የወላይታ ዞን ዉሃና ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ ሀላፊ አቶ ተስፋሁን ታዲዎስ እንዳሉት ወርልድ ቪዥን በኢትዮጵያ የሶዶ ፕሮግራም ማስተባበሪያ በዞኑ 5 ወረዳዎች በመንግስት በጀት ብቻ መስራት የማይችሉ ትላልቅ የልማት ስራዎችን በመስራቱ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። የተሰራው ስራ በከፍተኛ ወጪ የተገነባ ስለሆነ ህብረተሰቡ በእኔነት ስሜት ሊጠብቀውና ሊንከባከበው እንደሚገባ አቶ ተስፋሁን አሳስበዋል። የዳሞት ሶሬ ወረዳ የሻያምባ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ታመሩ ፈለሀ በበኩላቸው በአካቢያባቸው ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የውሀ ችግር እንዳለ ያብራራሉ። በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በሶዶ ማስተባበሪያ በጌሽያሮ ፕሮጀክት በተገነባው የንጹህ መጠጥ ውሀ ሙሉ ለሙሉ እንደተቀረፈና ተጠቃሚ እንደሆኑ ተናግረዋል። በዳሞት ሶሬ ወረዳ የሻያምባ ቀበሌ ጤና ጣቢያ የጤና መኮንን አቶ አብረሃም ቡንዳሳ እንዳሉት ከዚህ ቀደም በውሀ እጦት ምክንያት በጤና ጣቢያቸው ታካሚ ለመምጣት እንደማይፈልጉ በተለይ ወላድ እናቶች ከዚያ የተነሳ ውሀ ፍለጋ እስከ ወንዝ እንደሚሄዱ አብራርተዋል። ተማሪ ቃልኪዳን አለሙ በበኩሏ ወርልድ ቪዥን በኢትዮጵያ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በጋራ ጎዶ ቀበሌ የመጀመሪያ ደረጃ ተምህርት ቤት ከዚህ ቀደም በወሀ እጦት ምክንያት በርካታ ይደርስ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ችሏል። ወርልድ ቪዥን በኢትዮጵያ በሶዶ ማስተባበሪያ በጌሽያሮ ፕሮጀክት በተሰሩ የልማት ስራዎች ጉብኝት የመንግስት ከፍተኛ አመራር,የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

  April 4, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በደቡብ ክልል የህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከአንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ገለፀ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የህዳሴ ግድብ 12ኛ ዓመት በዓል አከባበር በተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ተካሂዷል፡፡ በመርሃግብሩ ካነጋገርናቸው ተሳታፊዎች መካከል ወ/ሮ በላይነሽ ጡናሞና ወጣት አማኑኤል ኤንከሸ የህዳሴ ግድብ የህብረ ብሔራዊነት መገለጫ የትውልድ አሻራ መሆኑን ተናግረዋል። የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ በቦንድ ግዢና በ8100 አጭር የጽፍ መልዕክት መሳተፉ አሰፈላጊ መሆኑን የሚናገሩት ተሳታፊዎች በዛሬው ዕለት የሁለት ሺህ እና የአንድ ሺህ ብር ቦንድ መግዛታቸውን ተናግረዋል። በከተማው ነጋዴዎች፣ መንግስት ሥራተኞች እንዲሁም የተለያዩ የህበረተሰብ ክፍሎች ቦንድ ግዢ ፈጽመዋል፡፡

  April 1, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ የወላይታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቋል። በዚህም ምክር ቤቱ የዞኑን አስፈጻሚ፣ የምክር ቤቱን እና የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት አድርጓል። የምክርቤት አባላት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ የገበያ ንረትን፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የህዝቡን እርካታ በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲመለስ ጠይቀዋል። ባለፉት ዓመታት ተወዝፈው የመጣው የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ በዞኑ በጀትና ዕድገት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖን እያሳደረ ይገኛል ያሉት የምክርቤት አባላት ቀጣይ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት መፍትሔ እንዲበጅለትም ጠይቀዋል። በዘንድሮ የተማሪዎች ውጤት ዞኑን የማይመጥን መሆኑን በመጠቀስ በትምህርት ዘርፍ ያጋጠመው የሞራል ውድቀት ለመቅረፍ ስር ነቀል ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ልዩ ትኩረት እንደሚሻ አንስተዋል። ህብረተሰቡ በምግብ ራሱን እንዲችልና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ምርትና ምርታማነቱንም ለመጨመር በግብርናው ዘርፍ ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም አመላክተዋል። ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ እና ከሚመለከታቸው አስፈፃሚ ሴክተር መስራያ ቤት ኃላፊዎች ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ዋና አስተዳዳሪው በምላሻቸው በግማሽ ዓመቱ በሁሉም ዘርፎች የዜጎች ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። ምክር ቤቱም በግማሽ ዓመቱ በተሻለ የተከናወኑ ተግባራት እንዲጠናከሩና በጉድለት የተገመገሙ ጉዳዮች በቀጣይ ጊዚያት መስተካከል እንዳለበትም አሳስቧል። የቀረቡ ሪፖርቶችን መነሻ በማድረግም መስተካከል ያለባቸውን አፈጻጸሞች እንዲስተካከሉ ዋና አስተዳዳሪው አቅጣጫ በመጠቆም የጋራ መግባባት ላይም ተደርሶ ጉባዔው ተጠናቋል። በመጨረሻም የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት ምክር ቤት ተጠናቋል ።

  March 22, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የዞን ምክር ቤት አባላት በቀጣይ ጊዜያት የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና የኑሮ ዉድነት ተግዳሮቶችን ለመቀነስ የሚያስችሉ ሥራዎችን መስራት እንዳለባቸው የወላይታ ዞን ምክር ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ተናገሩ። ዋና አፈ ጉባኤዋ ይህን የተናገሩት ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 10ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በወላይታ ጉተራ እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው። የዞኑ ምክር ቤት ባለፉት ጊዜያት የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል፣ የቀበሌ ምክር ቤቶችን ለማጠናከርና አቅመ ደካሞችን የመርዳቱን ሥራ በስፋት ያከናወነ ቢሆንም የተፈለገው ውጤት ገና አለመምጣቱን ገልፀዋል። በመሆኑም በቀጣይ የምክር ቤት አባላት የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና የኑሮ ዉድነት ተግዳሮቶችን ለመቀነስ የሚያስችሉ ሥራዎችን መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በምክር ቤቱ ጉባኤም ሰፊ ውይይት በማድረግ ቀጣይ ችግሮችን ለመሻገር የሚያስችል አቅጣጫ ማስቀመጥ አለባቸውም ሲሉ ተደምጠዋል።

  March 10, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በወላይታ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት በመኸርና በመስኖ ልማት 41 ሺ 2 መቶ 78 ሄክታር መሬት በተለያዩ ምርቶች ለመሸፈን ታቅዶ ከ40 ሺ 8 መቶ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት መቻሉ ተገለፀ። ይህ የተገለጸው የወላይታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በወላይታ ጉተራ በተካሄደበት ወቅት ነው። በጉባኤው የዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ያለፉትን ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ የዕቅዱ አፈጻጸም 99 ከመቶ መሆኑን አስታውቀዋል። በዞኑ በተለያዩ ሴክተሮች ያለው ዕቅድ አፈጻጸም በአንጻራዊነት የተሻለ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የዞኑን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ሲሉም አሳስበዋል። የምክር ቤቱን ጉባኤ የተከታተለው ተመስገን ተስፋዬ ተጨማሪውን እንደሚከተለው አዘጋጅቷል።

  March 10, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ጎጂ ልማዳዊ ድረጊት ለማስቀረት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባ የወላይታ ዞን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ አሳሰቡ። 20ኛው የወላይታ ዞን ም/ቤት የወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የጋራ ምክክር ፎረም መድረክ ተካሂዷል።። በሁሉም መዋቅሮች የሚገኙ ምክር ቤቶች ከመራጩ ህዝብ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ የወላይታ ዞን አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ገለጹ። ወ/ሮ ካሰች አክለውም ሁሉም ምክር ቤቶች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተቀመጠው የአሰራር ደንብ መሠረት መፈጸም አለባቸው ብለዋል ። ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ባሉ ምክር ቤቶች የተቋቋሙ ቋሚ ኮሚቴዎች በምንም ሳይገደቡ ለሕዝብ ተጠቃሚነት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ወ/ሮ ካሰች አክለዋል። ጫፍ የወጣ የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት ምክንያት ሳንደረድር መስራት ይጠበቃል ብለዋል። በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ጎጂ ልማዳዊ ድረጊት ለማስቀረት በተለይ ለመሬት ለምነት ጠንቅ የሆነው ባህር- ዛፍ ተክል እንዲወገድና ከለቅሶ ስርዓት ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን መጠ ባህልን ለማስቆም ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባ ወ/ሮ ካሰች ተናግረዋል። በምክክር ፎረሙ ላይ የዞን ም/ቤት አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት እና የሁሉም ወረዳዎችና ከተማዎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጽ/ቤቶች የ6 ወር ተግባር አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። በታቸኞቹ መዋቅሮች ባለፉት 6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በሪፖርቱ የተመላከተ ሲሆን በአንዳንድ መዋቅሮች መደበኛ የምክር ቤት ጉባኤ በታቀደው መሠረት አለማካሄድ፣ ትክክለኛ የኦዲት ግኝት መረጃ ሪፖርት በጊዜ ያለማቅረብ እና የምክር ቤቶችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ጉድለቶች እንደክፍተት ተነስቷል። ቋሚ ኮሚቴዎች ፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ገምግሞ አቅጣጫ በማስቀመጥ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ለአመራሩ አቅም ስለምሆኑ በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመድረኩ ተነስቷል። በጋራ ምክክር ፎረም መድረኩ ላይ የወላይታ ዞን ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ፣ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ጤናዬ ትራንጎ፣ የወረዳዎች አስተዳዳሪዎችና የከተማ አሰተዳደሮች ከንቲባዎች፣ የሁሉም መዋቅሮች አፈ ጉባኤዎች እና የዞኑ ምክር ቤት የሶስቱ ኮሚቴዎች አባላት ተገኝተዋል።

  March 6, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ጎጂ ልማዳዊ ድረጊት ለማስቀረት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባ የወላይታ ዞን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ አሳሰቡ። 20ኛው የወላይታ ዞን ም/ቤት የወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የጋራ ምክክር ፎረም መድረክ ተካሂዷል።። በሁሉም መዋቅሮች የሚገኙ ምክር ቤቶች ከመራጩ ህዝብ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ የወላይታ ዞን አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ገለጹ። ወ/ሮ ካሰች አክለውም ሁሉም ምክር ቤቶች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተቀመጠው የአሰራር ደንብ መሠረት መፈጸም አለባቸው ብለዋል ። ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ባሉ ምክር ቤቶች የተቋቋሙ ቋሚ ኮሚቴዎች በምንም ሳይገደቡ ለሕዝብ ተጠቃሚነት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ወ/ሮ ካሰች አክለዋል። ጫፍ የወጣ የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት ምክንያት ሳንደረድር መስራት ይጠበቃል ብለዋል። በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ጎጂ ልማዳዊ ድረጊት ለማስቀረት በተለይ ለመሬት ለምነት ጠንቅ የሆነው ባህር- ዛፍ ተክል እንዲወገድና ከለቅሶ ስርዓት ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን መጠ ባህልን ለማስቆም ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባ ወ/ሮ ካሰች ተናግረዋል። በምክክር ፎረሙ ላይ የዞን ም/ቤት አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት እና የሁሉም ወረዳዎችና ከተማዎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጽ/ቤቶች የ6 ወር ተግባር አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። በታቸኞቹ መዋቅሮች ባለፉት 6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በሪፖርቱ የተመላከተ ሲሆን በአንዳንድ መዋቅሮች መደበኛ የምክር ቤት ጉባኤ በታቀደው መሠረት አለማካሄድ፣ ትክክለኛ የኦዲት ግኝት መረጃ ሪፖርት በጊዜ ያለማቅረብ እና የምክር ቤቶችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ጉድለቶች እንደክፍተት ተነስቷል። ቋሚ ኮሚቴዎች ፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ገምግሞ አቅጣጫ በማስቀመጥ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ለአመራሩ አቅም ስለምሆኑ በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመድረኩ ተነስቷል። በጋራ ምክክር ፎረም መድረኩ ላይ የወላይታ ዞን ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ፣ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ጤናዬ ትራንጎ፣ የወረዳዎች አስተዳዳሪዎችና የከተማ አሰተዳደሮች ከንቲባዎች፣ የሁሉም መዋቅሮች አፈ ጉባኤዎች እና የዞኑ ምክር ቤት የሶስቱ ኮሚቴዎች አባላት ተገኝተዋል።

  March 6, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • "እንሰት የመጪው ጊዜ የአገራችን የምግብና የስነ ምግብ ዋስትናችን ተስፋ" በሚል መሪ ቃል የግብርና ሚኒስቴር ከደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ጋር በመቀናጀት በእንሰት ልማት ድህረ ምርትና በሽታ መከላከል ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል። በንቅናቄ መድረኩ የግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዞንና ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የእንሰት ልማት ድህረ ምርት ተመራማሪዎች፣ ግብርና መምሪያና ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ። በመድረኩ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ የእንሰት ምርት ለበሽታ በመጋለጡ ምክንያት ከአርሶ አደሩ ማሳ እየጠፋ መሆኑን ተናግረዋል። ሰብሉ በዞኑ ለበርካታ ዜጎች የምግብ ዋስትና ሲደግፍ የቆየ የመሆኑን ያክል በሽታውን ለመከላከል በምርምር የታገዘ ሥራ ቀድሞ መጀመሩንና ተስፋ ሰጪ ውጤት መታየቱን ጠቅሰዋል። ባለፈዉ ዓመት በዞኑ 20 ሚሊዮን የእንሰት መተከሉን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው የንቅናቄ መድረክ ምርቱን ለማሻሻል የተጀመረውን ጥረት ይበልጥ ያበረታታል ብለዋል። የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነው የማህበረሰብ ክፍል በዋነኝነት በየቀኑ የሚጠቀመው የእንሰት ሰብል በከፍተኛ ሁኔታ ለአደጋ መጋለጡን በመድረኩ ገልፀዋል። የንቅናቄው ዋና ዓላማ በሀገር አቀፍ ደረጃ እያደገ ያለውን የምግብ ፍላጎት ለማርካት የሰብሉን ቁጥርና ሽፋን ከ3 እስከ 5 እጥፍ ማሳደግ መሆኑንና በቀጣይ በምስራቅ አፍሪካ ተምሳሌታዊ ሰብል ሆኖ እንዲገኝ ከማድረግ አኳያ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ቃል ኪዳን የሚገባበት መሆኑን አስታውቀዋል። ይህን ለማሳካት አመራሩ፣ ሙያተኞችና ምሁራን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል። የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መለሠ መኮንን የእንሰት ሰብል በሀገሪቱ ከ3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ በሚሆን መሬት እየለማና ከ25 ሚሊዮን ለሚበልጥ የማህበረሰብ ክፍል የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እንደሌሎች የትኩረት መስኮች ሁሉ የአመራር የትኩረት አጀንዳ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ተደምጠዋል። የተጀመረው ንቅናቄ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ሲሉ መልዕታቸውን አስተላልፈዋል። የንቅናቄ መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የደቡብ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ የህዝባችን የጋራ እሴት ለሆነው የእንሰት ምርት የሚሰጠውን ትኩረት ይበልጥ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። በተለይ የክልሉ አመራር ያሉ ችግሮችን በጋራ በመፍታት ምርቱ ወደ ሌሎች ክልሎች እንዲስፋፋ ለማድረግ ሚና መጫወት አለበት ብለዋል። "የሶዶ የእንሰት ልማት ዲክላሬሽን 2015" ሀገራዊ የልማት አጀንዳ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

  March 6, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • "ቸንትሮ አይ ዩቲ ፔርሌ ኢትዮጵያ" የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በወላይታ ዞን በእናቶችና ህጻናት ዙሪያ በተለይም ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአረጋውያን፣ ለደሃ ደሃ ወገኖች እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ገለጹ። ድርጅቱ በወላይታ ዞን በተለያዩ ማህበራዊ ምክንያቶች ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለአካል ጉዳተኞች እያደረገ ባለው ድጋፍ የአመራር ትኩረት በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ድርጅቱ በዞኑ እያከናወነ ያለውን እንቅስቃሴ፣ በማህበራዊ ልማትና የተቸገሩትን ለመረዳት በሚደረገው ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል። አመራሩ ፕሮጀክት ተደራሽ ና ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባም አመላክተዋል። አያይዘውም ድርጅት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የፕሮጀክቱን ተፈጻሚነት አመራሩ እየተከታተለ መምራት እንዳለበትና ስራውም በጥራት፣ በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ እንዲመራ አሳስበዋል። የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ሮበርቶ ራባቶኒ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ከ40 ዓመት በላይ መቆየቱንና በእነዚህ ዓመታት በወላይታና አከባቢው የበጎ አድርጎት ስራዎችን መሰራቱንና እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። ድርጅቱ ትምህርታቸውን ለመማር ፍላጎት እያላቸው በተለይም በማህበራዊ ምክንያት ለተጋለጡና መማር ያልቻሉ ዕድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ህጻናትን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። እንደዞን ከ13 ሺህ በላይ ህጻናት በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጹት ሚስተር ሮበርቶ በዚህም ለእያንዳንዳቸው በየወሩ ስምንት ሺህ ብር ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። በአንድ ዓመት ብቻ "በስፖንሰርሽፕ" አማካይነት ድርጅት ከ100 ሚሊዮን ገንዘብ በላይ ድጋፍ ማደረጉን ተናግረዋል። በድርጅቱ የተመደበው ሀብት መጠቀም የሚገባቸው አካላት ሁሉ እንዲጠቀሙ ከማድረግ አንጻር ችግር አጋጥሟል ያሉት ሚስተር ሮበርቶ ለዚህም አመራሩ ኃላፊነት በመወሰድ ህብረተሰቡ በአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል። በቀጣይም ለአካል ጉዳተኞች ድጋፍ ለማድረግ ድርጅቱ ዝግጁ መሆኑን የገለጹት ሚስተር ሮበርቶ ዓላማውም ይህ እንደሆነም ገልጸዋል። በተነሱ ጉዳዮች ላይ ሀሰብ የሰጡት የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ድርጅቱ በዞኑ የቆየ መሆኑን ገልጸው በዚህም ሰፋፊ የድጋፍ ስራዎችን ማከናወኑን አስታውቀዋል። ድርጅቱ በእናቶችና ህጻናት ዙሪያ በተለይም በማህበራዊ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ ለደሃ ደሃ ወገኖች ልዩ ድጋፍ እያደረገ መቆየቱንም አስረድተዋል። ድርጅቱ እየሰራ ያለው እና ለመሰራት ያቀዳቸው ፕሮጀክቶች ትልቅ ዕውቅና የሚያሰጡ ናቸውም ብለዋል ለዚህም በቅርበት መከታተልና መደገፍ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል። በመድረኩ የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ፣ የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እና የወረዳና ከተማ አስተዳዳሪዎችና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

  March 1, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የከተማ መሬት አጠቃቀምና አደረጃጀት ለማዘመን የካዳስተር ሲስቴም በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የፌድራል ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፌንታ ደጀን ገለጹ። የፌድራል ከተማና መሬት ልማት ሚኒስቴር ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በከተማ መሬትና ፕላን ዘርፍ የተዘጋጀ የሙያ ደረጃዎች እና የብቃት ማረጋገጫ ሥልጠና በዩኒበርሲቲው ተጀምሯል። ስልጠናውን ያስጀመሩት የፈድራል ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፌንታ ደጀን ከተሞች ለአንድ ሀገር ዕድገት ምሰሶ በመሆናቸው የመሬት አጠቃቀምን ለማዘመን የካዳስተር ሲስቴም ተግባራዊ ማድረግና የዘርፋ ባለሙያዎች የማስፈጸም አቅም ማጎልበት እንደሚገባ ተናግረዋል። የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በበኩላቸው ውስን የሆነውን የከተማ መሬት በአግባቡ ለመጠቀምና አሰራሩን ለማዘመን የአስፈጻሚ ባለሙያዎች አቅም ለማጎልበት ሥልጠናው በመዘጋጀቱ ሠልጣኞች ሥልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው ማጠናቀቅ እንደሚገባቸው አሳስበዋል። ስልጠናው ከሲዳማ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እና ከደቡብ ብሔር ብሔረሶቦችና ህዝቦች ክልል ለተወጣጡ ባለሙያዎች የሚሰጥ ሲሆን ለ45 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ እንደሚቆይም ታውቋል።

  February 28, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን አስተዳደር ለወላይታ ልማት ማህበር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ገለጹ የወላይታ ዞን አስተዳደር ለልማት ማህበሩ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሁለት የእርሻ ትራክተሮችን ድጋፍ አድርጓል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ የእርሻ ትራክተሮችን ለልማት ማህበሩ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት የልማት ማህበሩ ከቀድሞ የአሚባራ እርሻ ልማት የተረከበው ከ1200 በላይ ሄ/ር መሬት ቢኖረውም በአቅም ችግር ምክንያት በሙሉ አቅሙ ሳይለማ ቆይቷል። ይህንን ችግር ታሳቢ በማድረግም የዞኑ ካቢኔ ልማት ማህበሩን ለመደገፍ በማሰብ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ ለልማት ማህበሩ የእርሻ ትራክተሮች ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት አቶ አክሊሉ ለማህበሩ የሚደረገው ድጋፍ የዞን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግና ለወጣቱም የሥራ ዕድል የሚፈጥር እንደሆነ አስረድተው ድጋፉ ቀጣይነት ያለው እንደሆነም አረጋግጠዋል። በወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊና የልማት ማህበሩ ም/ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ፎላ ልማት ማህበሩ የዞናችንን የልማት ክፍተቶችን እየሞላ ህዝብን ሲደግፍ የቆየ ተቋም እንደሆነ ተናግረው በዞናችን አዲስ የገቢ ማመንጫ የሆነውን የእርሻ ዘርፉን ለመደገፍ የዞኑ አስተዳደር ችግሩን በመረዳት የሰጠው ድጋፍ ነው ብለዋል። ልማት ማህበሩ የአባያ እርሻ ልማትን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም በዞኑ ያሉ እርሻዎችን ይደግፋል ያሉት ኃላፊው ለተደረገው ድጋፍ የዞኑን አስተዳደር አመስግነው ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። አቶ ሳሙኤል አክለውም ልማት ማህበሩ በሰው ሀብት ልማት በዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ ሥራዎችና በተቀናጀ ጤና ልማት የሚሠራ በመሆኑ ትልቅ የፋይናንስ አቅም የሚያስፈልገውና የገቢ አቅም ከሚፈጠርባቸው የድጋፍ ዘርፎች አንዱ ነውም ብለዋል። ከአለም ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን የገንዘብ ዕጥረት ለመቅረፍም የብዙዎችን ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረው መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፤ የመንግስት ተቋማት ፤ የግል ባለሀብቶች እና ግለሰቦች ማህበሩን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል አቶ ሳሙኤል። የልማት ማህበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ናና በበኩላቸው የዞኑ አስተዳደር ካለው ውስን ሀብት ለልማት ማህበሩ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ድጋፉ አቅም የሚፈጥር እንደሆነም ተናግረዋል። ልማት ማህበሩ ከዞኑ መንግስት የተረከበውን ከ1200 በላይ ሄ/ር ሙሉ በሙሉ በማልማት ለወጣቱ የሥራ ዕድል በመፍጠርና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ሥራዎችን በመሥራት ከአካባቢ አልፎ ለሀገር የሚተርፍ ሥራ እንደሚሠራም ተናግረዋል ሲል ወ/ዞ/መ/ጉ/ መመሪያ ዘግቧል።

  February 28, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በከተሞች የዜጎችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት – አቶ ተስፋዬ ይገዙ የደቡብ ክልል የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም/UIIDP/ 6 ወር አፈጻጸም በስትሪንግ ኮሚቴ ግምገማ እየተካሄደ ነው። የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በክልሉ ከተሞች ሁሉም አመራር አካላት በቅንጅት በመስራት በሀገር ደረጃ ከኦሮሚያ በመቀጠል ክልሉ ሁለተኛ ደረጃ መያዙን ገልጸዋል። አመራሩ በክልሉ ከነበረው ከክልል የማደራጀት ስራ ጋር የተጣለውን ተደራራቢ ኃላፊነት በብቃት በመወጣት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ በመቻሉ ለመኩራራት ሳይሆን ቀጣይም ተበረታትተን ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚያነሳሳ ስለሆነ ተግተን እንሰራለን ብለዋል። በክልሉ ያለውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በከተሞች የዜጎችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ርብርብ ሁሉም መዋቅር በቁርጠኝነት ልመራ እንደሚገባ አቶ ተስፋዬ አሳስበዋል። በተጀመሩ የጌጠኛ ድንጋይ ማንጠፍ፣ የድልድይ፣ የፈሳሽ ማስወገጃ ቦዮችና የሌሎች መሰረተ ልማቶች ከጥራት መጓደል፣ ከመዘግየትና የተበላሹትን ከመጠገን ጋር ተያይዞ አንዳንድ ከተሞች ላይ የሚተዋለው ችግር በፍጥነት መፈታት አለበት ተብሏል። ከከተሞች ፕላን፣ ከመሬት አስተዳደርና ከገቢ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ በአብዛኞቹ ከተሞች የሚታይባቸውን ድክመቶች በማረም ለከተሞች ዘላቂ ልማት መረባረብ እንደሚገባ ምክትል አስተዳደዳሪው አሳስበዋል። በቀረበው የ6 ወር በዘርፉ ሪፖርት ላይ በአንዳንድ ከተሞች የተስተዋሉ የሙስና አዝማሚዎች የተነሱ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ቶሎ እርምጃ ተወስዶ ማረም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። በግገማ መድረኩ ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ፤ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ይልማ ሱንታ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክን ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እንቁ ዮሐንስ፣ የክሊሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበባየሁ ኤርሚያስ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

  February 20, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት መምሪያ ከህገወጥ ቅጥርና ከደረጃ ዕድገት ጋር ተያይዞ ልባክን የነበረውን ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ገለጸ። መምሪያው የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በተገኙበት ያለፋት 6 ወራት የዞኑን ሴክተር መስሪያ ቤቶች ስራ አፈጻጸም ገምግሟል። በተለያዩ መንግስት መስሪያ ቤቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ለሚስተዋለውን የተገልጋዮች እሮሮ እልባት ለመስጠት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተገልጿል። ባለፉት 6 ወራት በዞኑ የሚገኙ መስሪያ ቤቶች የተገልጋይ እርካታን ከማረጋገጥና መልካም አስተዳደርን ከመፍጠር አንጻር የተመዘገቡ ወጤቶችና የታዩ ድክመቶች በስትሪንግ ኮሚተው ተመልክተዋል። የሰው ኃብት አስተዳደር መመሪያ ተጥሶ የተሰሩ ስራዎች መኖራቸውን የገለጹት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ እና የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ኃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፀጋ ችግሩን ለመቅረፍ እየተወሰደ ባለው እርምጃ ከቅጥርና ከደረጃ ዕድገት ጋር ተያይዞ በደስክ ኦዲት በማጣራት ከ11 ሚለዮን ብር በላይ ከብክነት ማዳን መቻሉ ጥሩ ጅምር ነው ብለዋል። ከቅጥርና ድርጃ እድገት ጋር ተያይዞ ግለሰቦች አለግባብ ለመጥቀም በተሰራው ስራ በዞን ደረጃ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ በደስክ ኦዲት መለየቱ ተገልጿል። የሰው ኃብት አስተዳደር መመሪያ ተጥሶ የተሰራው ስራ ዞኑ ደመወዝ ለመክፈል እስከሚቸገር ያደረሰ በመሆኑ ፈተናውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመሻገር ከከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ጀምሮ የትምህርት ዶክሜንት የመፈተሽና እርምጃ የመውሰድ ስራ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክልሉ ለማ ተናግረዋል። ከአገልግሎት አሰጣጥ ተያይዞ በቅርቡ በተደረገው ጥናት በርካታ አገልጋዮች እሮሮ የሚያሰሙበት መሆኑን ያሳየ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊዎቹ ሁሉም ባለሙያ የገባውን መኃላ በማክበር ህብረተሰቡን ማገልገል እንዳለበት አሳስበዋል። በዞኑ ህገወጥነትን ለማረም የተጀመረው ስራ ውጤት እንዲያመጣ ሁሉም የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ቀርቧል።

  February 20, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በሰላም በመፈታቱ የተሰማቸውን ደስታ ገለጹ። በቤቴክርቲያኒቱ አባቶች መካከል የተደረሰው መግባባት ለሀገራችን አንድነት፣ ሠላምና ፍቅር የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑንም ነዋሪዎቹ አክለዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በሰላም ከመፈታቱ ጋር ተያይዞ ለሚዲያችን አስተያየት የሰጡ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ቤቴክርቲያኒቱ ፈተናዎችን በድል በማለፍ ለእርቅና ሠላም መድረሷ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል። ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በጣም ከባድና ስጋት የፈጠረ እንደነበረ የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ አሁን የተፈጠረው መግባባት ለሀገር ሠላምና አንድነት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የፍላጎቶች መበራከትና መለያየት ምክንያት አልፎ አልፎ አለመግባባት ሊፈጠር ይችላል ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች አለመግባባት ሲፈጠር በመነጋገር መፍታት እንደሚቻል ሁሉም የሀይማኖት ተቋማትና ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤቴክርስቲያን አባቶች መማር እንደሚገባ ተናግረዋል። በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችና በሌሎች አማራጮች መረጃ የሚያደርሱ አካላትም ከሚያለያዩ ነገሮች በመራቅና አንድነትና ሰላምን በማሰራጨት ለሀገራችን ሰላምና አንድነት የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ አስተያየት ሰጪዎቹ አሳስበዋል።

  February 17, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የሕዝብ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ ላበረከተው አስተዋጽኦ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፉዬ ይገዙ አመስግነዋል። ምርጫው በስኬት መጠናቀቁ ለሕዝቡ ጠቃሚ አጀንዳ በማቅረብና በማሳተፍ በቅንጅት ከሰራን በሁሉም ዘርፎች ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ያሳየ ነው ተባለ። የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፉዬ ይገዙ የፌዴራል፣ የከክልል የዞንና የወረዳ አመራር አካላ ሕዝቡን በማሳተፍ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። የምርጫ ስራ እንዲደናቀፍ የሚፈልጉ ኃይሎች ያልጠፉ መሆኖቸውን የጠቆሙት አቶ ተስፋዬ ምርጫው በተካሄደበት አካባቢዎች ሁሉም ማህበረሰብ ላደረገው ከፍተኛ ትብብር አመስግነዋል። ሕዝቡ በሁሉም አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ልክ ድምጽ ሰጥቷል ያሉት አቶ ተስፋዬ በዚህም መንግስት ግልጽ የሆነና ጥራት ያለውን አጀንዳ ካቀረበ ሕዝቡ ተቀብሎ ለመፈጸም ፈቃደኛ መሆኑን፣ አርቆ አሳቢነቱንና ትልቅነቱን ያሳየ በመሆኑ አመስግነዋል። የፖለቲካ አመራሩ ከላይ እስከታች ያለምንም ቀስቃሽ በራሳቸው ጥረትና በቅንጅት ሰርተው ላስመዘገቡት ውጤት አቶ ምስጋና አቅርበዋል። በተለያዩ አፍራሽ አላማ ባላቸው ሚዲያዎች አማካይኝነት በሕዝብ መካከል የተለያዩ ስጋቶችን የሚያሰራጩ አካላት ቢኖሩም የጸጥታ አካላት ሕዝቡን ያሳተፈ ጠንካራ የጸጥታ ስራ ሰርተው ምርጫው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ በማድረጋቸው አመስግነዋል። የሚዲያ ተቋማት ስለምርጫ በሰሩት ጠንካራ የማስተማርና የማንቃት ስራ ሕዝቡ እውነታውን ተርድቶ በምርጫው እንዲሳተፍና ሂደቱም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ የምርጫ ሂደት በስኬት እንዲጠናቀቅ የዞኑ ሕዝብና አጠቃላይ አመራር አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል። አንዳንድ ያነጋገርናቸው የመንግስት ስራ ኃላፊ የሆኑ መራጮች ህዝቡ በሁሉም ቦታ የመምረጥ መብቱን በአግባቡ ተጠቅሞ በዲሞክራሲያዊና በሰለጠነ አኳሃን መምረጣቸውን ገልጸዋል።

  February 7, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ሁሉም ሰው የሀገር አንድነትና ሰላም ለማስጠበቅ ድርሻውን መወጣት እንዳለበት የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ሎሚ በዶ አሳሰቡ። የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ከፌደራልና ከክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ጋር በአጠቃላይ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂደዋል። ''የኅብረተሰባችን ተሳትፎ ለህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና የእህትማችነት መጠናከር ለሀገራችን ሠላም ጉልህ ሚና አለው" በሚል መሪ ቃል ነው መድረኩ የተካሂደው። የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ሎሜ በዶ እንዳሉት ከለውጡ ወዲህ ጽንፈኛ ሀይሎች ሀገርን ለማፍረስ ብዙ ቢሰሩም በህዝብ ተሳትፎ እቅዳቸውን ማክሸፍ ተችሏል ብለዋል። የለውጡ ትሩፋቶችን ብቻ ሳይሆን የገጠሙን ተግዳሮቶችንም በመረዳት በቀጣይ ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመቆም ለሀገር ሰላምና ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ወ/ሮ ሎሚ አሳስበዋል። ሁሉም ሰው ጽንፈኝነትንና አፍራሽ አጀንዳዎችን በመቃወም ለሀገር አንድነትና ሰላም ድርሻውን መወጣት እንዳለበት ዶክተር አህመዲን መሀመድ አሳሰቡ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሀመድ በበኩላቸው ሁሉም ሰው ጽንፈኝነትን በመቃወም በወንድማማችነትና በህትማማችነት መንፈስ ለሀገር አንድነትና ሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት አለበት ብለዋዋል ። የወላይታ ህዝብ ሰላምና የሀገር አንድነት ትርጉም ከረዥም ታሪክ ጀምሮ የሚያውቅ ህዝብ ነው ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው። ከመድረክ ተሳታፊዎች መካከል የሀገር ሽማግሌን በመወከል የተሳተፉት አቶ ሴታ ጭናሾ እንዳሉት የሀገር አንድነት ማስቀጠል ከሁሉም ሰው የሚጠበቅ ተግባር ነው። ወጣቱ ትውልድ የሀገር አንድነት ከሚሸረሽሩ አጀንዳዎች ተላቅቀው ለሠላም ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ እንደ ሀገር ሽማግሌ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ አቶ ሴታ አረጋግጠዋል። ወጣት መልካሙ ኢያሱ የወላይታ ወጣቶች ለሀገር አንድነት ብዙ ዋጋ መክፈላቸውን ጠቅሶ ቀጣይም ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል። ወይዘሮ ለምለም ቡሼ በበኩላቸው ሰላም የሚጀመረው ከራስ ነው ብለው ለዚህም ከልጆቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው መነሻ አድርገው በመምከርና በማስተማር የሀገር አንድነትና ሰላም ከማስጠበቅ አኳያ ንቁ የሆነ ማህበረሰብ ለመፍጠር ድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። ሀገርን ለማፈራረስና የዜጎችን ሰላም የሚጎዱ ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያራግቡ ሚዲያዎችን መንግስት በሆደ ሰፊነት ማለፍ የለበትም ብለዋል የውይይቱ ተሳታፊዎች። በውይይቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ -ጉባኤ ሎሚ በዶ፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ እና የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት፣ አባቶችና የተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

  January 31, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በዞኑ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ሥራ ገብተዋል በተያዘው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ ከ1 ቢሊዮን 349 ሚሊዮን በላይ ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን የወላይታ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በተያዘው ዓመት ስድስት ወራት በኢንዱስትሪው ዘርፍ 49 ኢንቨስትመንቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት ታቅዶ 34 ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል። በዚህም በዞኑ አንድ ቢሊዮን 349 ሚሊዮን በላይ ብር ያስመዘገቡ ኢንቨስተሮች ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡ አቶ አክሊሉ እንደገለፁት፣ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ሁለት ቢሊዮን የሚጠጋ ካፒታል ያላቸውን ባለሀብቶች ወደ ዞኑ ለመሳብ ሲሠራ የቆየ ሲሆን፤ ከ1 ቢሊዮን 349 ሚሊዮን ብር በላይ ኮፒታል ያስመዘገቡ ኢንቨስተሮች ወደ ሥራ መግባት ችለዋል። ወደ ሥራ ገብተዋል ከተባሉት 34 ኢንቨስትመንቶች 18 ያህሉ በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸውን ያብራሩት አቶ አክሊሉ፤ ሌሎች 11 የአገልግሎት እና 5 የሚሆኑ ደግሞ በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፎች ወደ ሥራ ገብተዋል ሲሉ አስረድተዋል። በገጠሩ አካባቢ 500 ሄክታር መሬት ለኢንቨስተሮች ለማቅረብ ታቅዶ ከአንድ ሺህ 500 በላይ ሄክታር መሬት ማቅረብ መቻሉንና በከተማው አካባቢ በካሬ የነበረውን ወደ ሄክታር በመቀየር አምስት ሄክታር መሬት ለማቅረብ ዕቅድ ተይዞ ከስምንት ሄክታር በላይ መሬት ለኢንቨስተሮች አቅርቦት መዋሉንም አክለው አብራርተዋል፡፡ የኢንቨስትመንት ሌላኛው ዓላማ የሥራ ዕድል መፍጠር ነው ያሉት አቶ አክሊሉ፤ ለ10 ሺህ 51 ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የታቀደ ሲሆን፤ ከስድስት ሺህ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል አግኝተዋል ሲሉ አስረድተዋል። መሬት ከተሰጣቸው በኋላ የተለያዩ ምክንያቶችን በማንሳት በሚፈለገው ፍጥነት ወደ ሥራ የማይገቡ ኢንቨስተሮች እንዳሉ በመግለጽም፤ ወደ ሥራ ገብተው ማልማት ከጀመሩ በኋላ የሚያቋርጡ መኖራቸውን ጠቅሰዋል። ይህን ድርጊት በሚፈጽሙ ባለሀብቶች ላይ የማስጠንቀቂያና የተቀበሉትን መሬት በመንጠቅ በተገቢ ሁኔታ ለሚያለሙ ባለሀብቶች እየተሰጠ መሆኑን አስረድተዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

  January 28, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚያስገነባው ህንጻ ግንባታ ሥራ ለማስጀመር ግንባታውን ከሚያከናውነው ተቋራጭ ጋር የሳይት ርክብክብ ተደረገ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወላይታ ሶዶ ከተማ የቅርንጫ መ/ቤቱን ህንጻ ለመገንባት ካሸነፈው China Civil Enginering Construction JV with China Rail Way Construction Group Co.Ltd. ከተሰኙ የውጪ ሀገር ግንባታ ተቋራጮች ጋር የሳይት ርክብክብ ያደረጉ ሲሆን የግንባታ ስራውን የኢትዮጽያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት የተሰኘ የሀገር በቀል አማካሪ ድርጅት የሚያማክረው እነደሆነ ታውቋል። ተቋራጩ ሥራውን ከተሰጠው ጊዜ ገደብ ቀድሞ ለመጨረስ የከተማ አስተዳደሩ ወሰን የማስከበር፣ የካምፕ ሳይትና የተለያዩ አገልግሎቶች የውሃና የመብራት አቅርቦት እንዲያመቻችላቸው የጠየቁ ሲሆን ሳይቱን ከተረከቡበት እስከ ጀምሮ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ ማሽነሪዎችንና የሰው ሀይል ማስገባት የሚጀምሩ መሆናቸውን ገልጸው ለተደረገላቸው አቀባበል የከተማ አስተዳደሩን አመስግነዋል። በሳይት ርክብክቡ ስፍራ የተገኙት የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን አለማየሁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በከተማው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ህንጻ ግንባታ ማከናወኑ ለከተማው ለዞኑና ለአጎራባች ዞኖች የፋይናንስ ዘርፉ ዕድገት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው ባንኩ ከከተማ አስተዳደሩ መሬት ከተረከበ በርካታ ዓመታትን ማስቆጠሩ እና ፕሮጀክቱ ወደ ግንባታ ባለመግባቱ በከተማው ህዝብ ዘንድ ቅሬታ ሲያስነሳ የቆየ መሆኑን አስታውሰዋል። ፕሮጀክቱ ወደትግበራ እንዲገባ የከተማ አስተዳደሩ ከዞን አስተዳደር ጋር በቅንጅት ሲከታተል መቆየቱን አንስተው ባንኩ ተቋራጭና አማካሪ ለይቶ ወደ ግንባታ ለመግባት ሳይት ርክብክብ በማድረጉ አመስግነዋል። በቀጣይም ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከከተማ አስተዳደሩ የሚጠበቁ ድጋፎችና የቅርብ ክትትል የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጠዋል። በርክብክብ ቦታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተወካዮች፣ የከተማ ማዘጋጃ ስራ አስኪያጅና ሌሎች የቀበለ አመራሮችና የማዘጋጃ ቤቱ ባለሙያዎች መገኘታቸውን የከተማው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ዘግቧል።

  January 28, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቦርድ አባላት የሶስት ወር ሥራ አፈጻጸም ገምግሟል። አንደኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈጻጸም ላይ እንደ ክፍተት የተነሱ ጉዳዮች መሻሻላቸውንና ከአሁን በኃላ የሆስፒታሉን አቅም እያዳከመ ያለዉን የሌብነት ሰንሰለት ለማጥፋት በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ ተገልጿል። አባላቱ ተቋሙ ዉስጥ ያሉ የእናቶችና ህጻናት የአዋቂዎች ጥብቅ ጥንቃቄ እንዲሁም የአስክሬን ሙሉ ምርመራ የሚደረግበት ክፍሎችንና የመምህራን መኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታን ጭምር መስክ ምልከታ ወቅት ጎብኝተዋል። ከዚህ በፊት ያልተሰሩ የህጻናት ቀዶ ህኪምና ክፍልና የአስክሬን ቤት ዘመናዊ በሆነ መልኩ መሠራቱ የሚበረታታ ተግባር መሆኑን የቦርድ አባላት አመላክተዋል። አባላቱ አክለዉም የመድኃኒት አቅርቦትን ለማሻሻልና ለአካባቢ ማህበረሰብ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ ያለዉ ሥራ ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል። በተጨማሪም የመምህራን መኖሪያ ቤት የተካለለው ቦታ ላይ ያሉ ሰዎችን አግባብ በሆነ መልኩ በማስነሳት ባለሙያዎች ከተቋሙ አቅራቢያ ሆኖ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ለማድረግ ቀጣይ በትኩረት እንደሚሠራ ተገልጿል። ይህ ብቻ ሳይሆን ሌብነትን በመከላከል የተቋሙ የዉስጥ ገቢ ለማሳደግ ሊሠራ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

  January 23, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የ2015 ዓ/ም የጥምቀት ከተራ በዓል በወላይታ ሶዶ ከተማ በከፍተኛ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በበዓሉ ከፍተኛ የወላይታ ዞንና የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖቱ መሪዎች፣ ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ምዕመናን በተገኙበት በኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ግቢ እየተከበረ ይገኛል።

  January 19, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ኦሞ ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ባለፉት 6 ወራት ከ1 ቢሊዮን 213 ሚሊዮን ብር በላይ ቁጠባ መሰብሰብ መቻሉን ገለጸ። ዲስትሪክቱ ባለፉት 6 ወራት አፈጻጸምና በቀጣይ የ6 ወር ዕቅድ ዙሪያ ከሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ጋር ምክክር መድረክ አካሂዷል። በኦሞ ባንክ የወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ያይና እንዳሉት ባለፉት 6 ወራት በተፈጸሙት ተግባራትና በቀጣይ ግማሽ ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በዲስትሪክቱ ስር ካሉት 24 ቅርንጫፎች ስራ አስኪያጆች ጋር ውይይት ተካሂዷል። ዲስትሪክቱ በቁጠባ አሰባሰብ፣ በብድር ስርጭትና በዕዳ ማስመለስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በዚህም በ2015 ዓ/ም ግማሽ ዓመት ከ1 ቢሊዮን 213 ሚለዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉንና አፈጻጸሙም 167 ከመቶ መሆኑን አክለዋል። ብድር ስርጭቱ 253 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑንና ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ነው ብለዋል። በብድር ማስመለስ ረገድ ስትሪንግ ኮሚቴ በማዋቀር በተሰራው ስራ ከፍትህ ተቋማት ጋር በመሆን ከ231 ሚሊዮን ብር በላይ ማስመለስ መቻሉንና አፈጻጸሙ የተሻለ እንደሆነ ገልጸዋል። ደንበኛች ከብድር መመለስ ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን ችግር መቅረፍ እንዳለባቸውም አሳስበዋል። የዳሞታ፣ የኪንዶ ኮይሻና ዳሞት ፑላሳ ቅርንጫፎች የተሻለ ውጤት በማስመዝገባቸው አመስግነው በተቃራኒው ቦሎሶ ቦምቤ፣ አረካ እና ዳሞት ወይዴ ቅርንጫፎች ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ በመሆናቸው ከድክመታቸው ፈጥነው እንዲወጡ ስራ አስኪያጁ አሳስበዋል። በውይይት መድረኩ ላይ አስተያየት ከሰጡት መካከል የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡት በወ/ሶዶ ከተማ የሚገኘው የዳሞታ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ መተኪያ ዳካ ባለፉት 6 ወራት 23 ሚሊዮን የተጣራ ቁጠባ መሰብሰቡን፤ ከ38 ሚለዮን ብር በላይ ብድር ማሰራጨቱንና ከ30 ሚለዮን ብር በላይ ዕዳ ማስመለሱን ገልጸዋል። በተቃራኒው ከ24 ቅርንጫፎች መካከል ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገበው ቦሎሶ ቦምቤ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ኤርሚያስ እንዳሉት ቅርንጫፉ በሁሉም ዘርፎች ዝቅተኛ አፈጻጸም ማስመዝገቡንና ከድክመቱ ለመውጣት ልዩ ዕቅድ አውጥቶ ለመስራት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

  January 18, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የ2015 ዓ.ም የከተራ እና ጥምቀት በዓል አከባበርን አስመልክቶ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ያስተላለፉት መልዕክት የተከበራችሁ የወላይታ እና የሀገራችን ክርስትና ዕምነት ተከታዮችና መላው ህዝቦች ለከተራ እና ጥምቀት በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የደስታ በዓል እንዲሆንልን በዞኑ አስተዳደር እና በራሴ ስም እመኛለሁ። በዚህ አጋጣሚ በዚህ ታላቅ በዓል አከባበር ላይ የወላይታን ዞን አስተዳደር ወክዬ የ'እንኳን አደረሳችሁ' የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ለማስተላለፍ ዕድል በማግኘቴ የተሠማኝን ልባዊ ደስታ በዞናችን አስተዳደርና በራሴ ስም ለመግለፅ እወዳለሁ። አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ ለሠው ልጅ ራስን ዝቅ ማድረግን ለማስተማር በዮሐንስ እጅ ተጠምቋል። ከዚህም የኛን አገልግሎት ለሚፈልጉ ራሳችንን ዝቅ በማድረግ በቅንነት፣ በታማኝነትና በትህትና ልናገለግልና የሚጠበቅብንንም ልንወጣ ያስፈልጋል። በጥምቀቱም ከክፋት በመራቅ የተግባር እና የአስተሳሰብ ንፅህናን እንድንጎናፀፍ መክሮናል፤ ሠላማችን እንዲበዛም አበክሮ ሰርቶልናል። እኛም የሌላውን ስብዕና፣ አካልና ህሊና፣ ሀብትና ንብረት ከሚጎዱ እኩይ ተግባራት ራሳችን ብቻ ሳንሆን ቤተሰቦቻችን፣ ጎረቤቶቻችን፣ አካባቢየችንና ማህበረሰባችን መታቀብ ይጠበቅብናል። ጥላቻ፣ ሀሰተኝነትና ፅንፈኝነት በምድር ብቻ ሳይሆን በአምላክ ፊትም የሚኮነኑ መጥፎ ምግባሮች በመሆናቸው ከድርጊቶቹ መቆጠብ ይጠበቅብናል፤ ድርጊቶቹ በአምላክ ፊት ብቻ ሳይሆን በሀገራችን ህግም ተጠያቂ እንደሚያደርጉ ሌሎችንም ማስገንዘብ ይገባል። የዘንድሮ የጥምቀት በዓል በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተከሰተው ጦርነት እንዲያከትም መሠረት የጣለው የደቡብ አፍሪካ የሠላም ስምምነት ተፈርሞ ወደ ትግበራ በገባበት እና ተስፋ ሠጪ ውጤት መታየት በጀመረበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ኩነቱን ልዩ ያደርገዋል። በሰላም ስምምነቱም ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆናለች፤ አሸናፊና ተሸናፊ ወይም ተጎጂና ተጠቃሚ የሚባል ፍረጃም አይኖርም፤ በመሆኑም ስምምነቱ ሁለቱንም ወገን ብሎም የኢትዮጵያን ህዝቦች በሙሉ ተጠቃሚ አድርጓልና፤ከሠላም ስምምነቱ ሁሉም አትርፏልና። በዚህ አጋጣሚ ለሠላማችን ታላቅ ዋጋ ለከፈሉ አካላት ታላቅ አክብሮት፣ አድናቆት እና ምስጋና በዞናችን አስተዳደር እና በራሴ ስም ዳግም እየገለፅኩ ለሠላሙ ዘላቂነት ሁሉም የድርሻውን በላቀ ተነሣሽነት እንዲወጣ ላሣሥብ እፈልጋለሁ። የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ጊዜያዊ ናቸው፤ በሌላ በኩል በፅናት እና በቁርጠኝነት ከተንቀሣቀስን ዘላቂ እና ፈጣን ድል ማስመዝገብ እንደሚቻል የደቡብ ኮሪያ፣ የቻይና፣ የጃፓን እና የሌሎች እስያ ሀገራት ተሞክሮ ይመሠክራልና ጠንክረን መሥራት ይጠበቅብናል። ኢትዮጵያ ሀገራችን የረጅም ዘመናት አኩሪ የነፃነት ታሪክ፣ የድንቅ ቅርሶችና ጥበብ፣ ተዝቆ የማያልቅ የተፈጥሮ ሀብትና ማራኪ መስህቦች ባለቤት፣ የሚቻቻሉና የሚወራረሱ የብዝሀ ሀይማኖት፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪክና እምነቶች ሀገር ናት። የኢትዮጵያ ህዝቦች ከረጅም ክፍለ ዘመናት በፊት ጀምሮ በጋብቻ፣ በባህል፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በታሪከ ፣በሥነ ልቦናና በመልክአ ምድራዊ መሥተጋብሮች ሊበጠስ በማይችል መልኩ የተጋመዱ የአንድ ፖለቲካ ማህበረሰብ አካላት ናቸው። ዘመን ተሻጋሪው የሀገራችን ሉአላዊነት፣ የግዛት እና የህዝቦቿ አንድነት ውስብስብ ፈተናዎችን በድል አድራጊነት እየተሻገረ የዘለቀበት ቁልፉ ምስጢር አባቶቻችን እና እናቶቻችን ለመቻቻል እና ለአብሮነት ዕሴቶቻችን ታላቅ ዋጋ በመክፈላቸው ነውና ትውልድ ፈለጋቸውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል። ምክንያቱም ከመበታተን ይልቅ አንድነት አቅም ነውና። ብልሀትና ጥበብ በተሞላበት የዲፕሎማሲ እና ጠንካራ የህዝብ እና የመንግሥት ትግል መነሻነት የሀገራችን ገፅታ በዓለም በአዎንታ እየተቀየረ ይገኛል። የሀገራችንን ህዝቦች ፍላጎት ተከትሎ ከሦሥትና አራት አመታት ወዲህ የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ በሀገራችን የህዝቡን ህይወት ወሣኝ በሆነ መልኩ ሊያሻሽሉ የታለሙ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች በጠንካራ ድጋፍና ክትትል ውጤታማ እየሆኑ ይገኛሉ። ለአብነት ያህል ለአመታት ሲጓተት የነበረው የመላው ኢትዮጵያዊያን አሻራ ያረፈበት እና ለአብዛኛው ህብረተሰባችን የብርሀን ምንጭ ከመሆን በተጓዳኝ ዳጎስ ያለ የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስገኝልን ታምኖበት እየተገነባ ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት 3ኛ ዙር የውሀ ሙሌት በስኬት ተጠናቆ ሁለት ቴርባይኖቹ የምሥራች የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ጀምረዋል። የስኳር፣ የባቡር፣ የአየርና የየብስ መንገድ፣ የመስኖ ልማት፣ የቱሪስት መዳረሻ እና ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች በጠንካራ ድጋፋዊ ክትትል ውጤታማ እየሆኑ ይገኛሉ። የሀገራችንን የውጭ ስንዴ ምርት ጥገኝነት በማስቀረት ለምግብ ዋስትናችን መረረጋገጥና በወጪ ምርትነት የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኝልን ታቅዶ እየተሠራ ያለው ሥራ ተስፋ ሰጪ ውጤት እየታየበት ይገኛል። የዞናችን ህብረተሰብ የረጅም ጊዜ ጥያቄ ሆኖ የቆየው በሶዶ ከተማ ከሌዊ ሪዞርት _ ግብርና ኮሌጅ _ ሆርባቢቾ ማዞረያ የ13 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ማስፋፊያ ግንባታ ፕሮጀክት በኢፌዴሪ መንግሥት በተመደበ ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ግንባታው እንዲካሄድ በኢፌዴሪ የመንገዶች ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት እና በቻይና ተቋራጭ ድርጅት መካከል ፕሮጀክቱን ከሁለት ዓመት ባነሠ ጊዜ ለማጠናቀቅ ያለመ ውል ተገብቷል። እናም ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት ጊዜ እና ጥራት እንዲጠናቀቅ አስተዳደራችን የተጠናከረ ክትትል እንደሚያደርግ እየገለፅኩ ለስኬታማነቱ ህብረተሰቡም የድርሻውን በላቀ ተነሣሽነት እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ። በፌዴራል መንግስት በጀት በዞኑ ከዲምቱ ከተማ እስከ ቢላቴ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ማሠልጠኛ ካምፕ የሚገነባው የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክትም በዕቅዱ መሠረት እየተከናወነ ይገኛል። እንዲሁም በፌዴራል መንግሥት በጀት በዞኑ የአይሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት ዲዛይን ደረጃው ከፍ እንዲል በመንግስት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ለሚሻሻለው ዲዛይን አተገባበር ምቹ የቦታ መረጣ እየተካሄደ ሲሆን በፕሮጀክቱ አፈፃፀም ሂደት የህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዳይለይ ጥሪዬን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። ለዞኑ የምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና የገበያ መረጋጋት ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ታምኖ በኢፌዴሪ መንግሥት በተመደበ ከ 2 ቢሊየን ብር በላይ በጀት በዞኑ ቦሎሶ ሶሬ እና ቦሎሶ ቦምቤ የሚገነባው የመሥኖ ልማት ግድብ ግንባታ በታቀደው መሠረት በማስፈፀም ረገድ የህዝቡም ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ላሳስብ እወዳለሁ። ብዝሀነትን ማስተናገድ የዴሞክራሲያዊ ሥርአት ግንባታ መገለጫ ነው። እናም ለውጡን ተከትሎ በሀገራችን ብዝሀነትን የማስተናገድ እና ተያያዥ የሀሳብ ነፃነትና ልዕልና እየጎለበተ ይገኛል። በሌላ በኩል ራስን በማግዘፍና በማሳበጥ የሌላውን ደግሞ በማንኳሰስ፣ በማጠልሸትና በማሳነስ የመፈረጅ አመለካከትና ጥላቻ የፅንፈኝነት መገለጫ በመሆኑ ልንኮንነው ይገባል። ፅንፈኞች 'የእገሌ ወገን ነን' በሚል የሀሰት ትርክት ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚያደርጉት የሽንገላ መረብ በመሆኑ ልንሸከማቸው አይገባም። ለመከበር የሌላውን ማክበር፣ መረን ከለቀቀ ራስ ወዳድነት ይልቅ የአብሮነት ዕሴቶችን በማጎልበት፣ ከመጠላለፍ ይልቅ በመገነባባትና ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን በማሳደግ ሰጥቶ የመቀበል ዕሴቶችን ይበልጥ ልናጎለብት ይገባል። በማህበራዊ ሚዲያ የምንለቃቸው መረጃዎች ፅንፈኝነትንና ጥላቻን የሚረጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ለአብሮነታችን የማይበጁ በመሆናቸው ልንኮንናቸው ይገባል። የምንለቃቸውና የምናጋራቸው መረጃዎች ከሚዛናዊነት በተጓዳኝ ማንነትን ብቻ ሳይሆን የጋራ ዕሴቶቻችንን በማጉላት ትውልድን የሚያንፁ ሊሆኑ ይገባል። ለብጥብጥና ለጥፋት የሚዳርጉ የጥላቻ ንግግሮችና ሀሰተኛ መረጃዎች የህግ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትሉ ማስተዋል ይገባል ። በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች የጋራ መግባባት ለመፍጠር ብሎም ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ቁልፍ ግብአት እንደሚሆን ታምኖበት እየተተገበረ የሚገኘው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አላማ እንዲሣካ ሀሣብ ከማዋጣት ጀምሮ ግብአቶችን በሰከነ መንፈስ በማከል በህብረ-ብሄራዊ ሀገር ግንባታ ሂደት የሚጠበቅብንን መወጣት ይጠብቅብናል። የአገልግሎት አሠጣጣችን ጥራት፣ ፍጥነትና ተደራሽነት በላቀ ደረጃ ህዝቡን እንዲያረካ ሀላፊነታችንና ተግባሮቻችንን በተነሣሽነት ልንወጣ ይገባል። ዜጎች ህገ መንግሥታዊ መብታቸውን በመጠቀም ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደው የአዲስ ክልል ምስረታ የህዝበ ውሣኔ የመራጭነት ድምፅ እንዲሠጡ ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ። በመጨረሻም በዓሉን ስናከብር ጦርነትን ጨምሮ በተለያዩ ሠው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ ወገኖቻችንን በመርዳት ሊሆን ይገባል። በድጋሚ በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የደስታ በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ! አመሰግናለሁ።

  January 18, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የኤግዚቢሽንና ባዛር በይፋ ተጀምሯል።

  በከተማው ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የምርት ማሳያ ኤግዚቢሽንና የክልል፣ የዞንና የቦዲቲ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል ።

  በባዛር መክፈቻ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ክልል ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ታደለ ወ/ሚካኤል እንደገለፁት የወላይታ ዞን በደቡብ ክልል ከሚገኙ ኢንተርፕራይዞች 25 በመቶ የሚገኝበት ነው አካባቢ እነደመሆኑ ይህ ኤግዚቢሽንና ባዛር በዚህ ጊዜ መካሄዱ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

  የኤግዚቢሽን ባዛር ዝግጅት ዋና አላማው በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ምርቶቻቸውን ለገበያ ከማቅረብ ባለፈ የአከባቢውን ህብረተሰብ ለማስተዋወቅ የጎላ ሚና ያላቸው መሆኑን አቶ ታደለ አስረድተዋል ።

  በባዛሩ አማካኝነት በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ምርቶቻቸውን ለገበያ አቅርበው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስራዎቻቸውን ከማስተዋወቅ አንፃር የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም እንዲታወቅ የማድረጉ ስራ ከሚመለከታቸው የሚጠበቅ እንደሆነ ተጠቁሟል።

  የወላይታ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምርያ ኃላፊ አቶ ማንደፍሮ ግርማ በበኩላቸው ኤግዚቢሽንና ባዛር ዝግጅት በየጊዜው ማድረግ ማህበራት ምርቶቻቸውን በአንድ ማዕከል በማምጣት የገበያ ትስስር እንድፈጥሩና የገበያ ዕድሎችን እንዲያገኙ ይረዳል ብለዋል ።

  በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት በስራዎቻቸው ከአካባቢያቸው አልፈው በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የክልሉ መንግስት እያደረገ ያለውን ስራ ያደነቁት አቶ ማንደፍሮ የዞኑ መንግስትም ለኢንተርፕራይዞች ከዚህ ቀደም የሚያደርገውን ሁሉ አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን አረጋግጠዋል።

  የቦዲቲ ከተማ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጌታሁን ዳና ባዛሩ ከዛሬ ጀምሮ ለ5 ቀናት ደምቆ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረው በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማኑፋክቸሪንግ ማህበራት የእጅ ሰራ ውጤት የሆኑ ጥራት ያላቸውን ምርቶች የአከባቢው ህብረተሰብ ወደ ቦታው ድረስ በመምጣት እንደገዙ ጥሪ አቅርበዋል።

  አቶ ጌታሁን ዘርፉን የሚመሩ አካላት ሂደቱን ከማስተዋወቅ አንፃር በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበው የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ኢንዳስተሪ ደረጃ ለመድረስ ምሶሶ ናቸውና በተለያዩ መንገድ ማህበራትን መደገፍ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

  January 3, 2023

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • Wolaytta Sooddo ambbaa zoreta keettaa 2ntto yuusho 10ntto ooso layttaa 2ntto gophphe konssoonoy doomettiis.

  Ha konssoonuwan zoreta kettay koyro sikko laytta oosuwa poloy yigettin ginay widhdhiyoogadan naagettees.

  Ambaa zoreta keettaa huuphphe dere doona gidiya bonchchettida godattiya Taaddasa Talggora konssoonuwa doomettan haasayidogadan kawotettaa oosoynne poloy dere asaa achchan qoncce gidanaadan wudidi ootteetees giidosona.

  Ambban halchchettida oosoti polettidona aggidona giyaaga minttidi yiggidooga qonccissida dere doonentti hegaassika heezzu eqo komitetakka galatidosona.

  Ambban dere asaassi immiyo haggazaa gujjin boolumiiddi yiida polota minttiyoganinne lefa miyeta giigissiyoogan deriya oyshshaa zaaranawu loytti oottanawu bessees giidosona.

  Ha konssoonuwan ambbaa zoreta keettaa 2015 bajete laytta 1ro sikko laytta oosuwa poloynne heezzu gophphe komiteti yiggi xeellido ubba ooso keettatu poloykka shiiqin ginay wodhdhiyoogadan naagettees.

  Ha konssoonuwan wolaytta sooddo ambbaa ayso gadaawaa mantta Alamayo Tamazggini, ubba ooso keettata kaalettiya gadawatinne zoreta keettaa yarati beettidosona.

  December 31, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ባለፉት ሦስት ቀናት 194,736 ሺህ የሚጠጉ ህጻናት የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ተጠቃሚ መሆናቸውን የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ  አስታወቀ።

  መምሪያው ዞናዊ የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ የ3 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።

  የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አሳምነው አይዛ በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት በየጊዜው የኩፍኝ በሽታ በወረርሽኝ መልክ በመከሰት የህጻናት ጤናን በመፈታተን ላይ በመሆኑ ዘመቻው ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተመራ ይገኛል ።

  በመሆኑም ባለፉት 3 ቀናት ብቻ የእቅዱን 60% ማሳካት ተችሏል ብለዋል።

  ዘመቻው በአብዘኛው አካባቢ በተቀመጠለት እቅድ መሰረት እየተመራ ነው ያሉት የመምሪያው ኃላፊ የማህበረሰቡ ተሳትፎም በጣም የሚበረታታ እንደሆነ ገልፀዋል።

  በዘመቻው ሌሎች ትኩረት የሚሹ ተግባራት በቅንጅት እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው  168 ሺህ ህጻናት የምግብ እጥረት ልየታ በማድረግ 385 የሚሆኑት የምግብ እጥረት ችግር ያለባቸውን ህጻናት ከጤና ተቋማት ጋር የማስተሳስር ሥራ ተሰርቷል ብለዋል።

  በቅንጅት በሚሰሩ ተግባራት እና በኩፍኝ ዘመቻ የአፈጻጸም ችግር ያለባቸው አካባቢዎች የማህበረሰብ ንቅናቄ መድረክ፣ የድጋፍ፣ ክትትል፣ ግምገማና ግብረመልስ ስርዓቱን የየእለት አጀንዳ አካል ሆኖ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የጤና መምሪያው ኃላፊ አሳስበዋል።

  በዘመቻው አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የፈዴራል፣ የክልል ጤና ቢሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የዞኑ ጤና መምሪያ ሠራተኞች እና የአጋር ድርጅት ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

  ምንጭ፦ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ

  December 29, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ጥር 29 የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ሂደት ፍጹም ሰላማውዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መላው የዞኑ ህዝብ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቀረቡ ።

  ዋና አስተዳዳሪው ጥር 29 ለሚካሄደው ህዝበ ዉሳኔ ድምፅ ለመስጠት የምርጫ ካርድ ወስደዋል።

  የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ጥር 29 ለሚካሄደው ህዝበ ዉሳኔ ድምፅ ለመስጠት የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ በዳሞት ወረዳ ወረዳ ተገኝተው ወስደዋል።

  ዋና አስተዳዳሪው የምርጫ ካርድ በወሰዱበት ወቅት እንደገለጹት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ውስጥ የሚገኙ 11 የዞን እና ልዩ ወረዳ መዋቅሮች የሚመሰርቱት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በፌዴሬሽን ምክር ቤት ይሁንታ አግኝቶ የህዝቦች መስተጋብር ባጠናከረ መልኩ ህዝበ ውሳኔ እንደሚካሄድ ገልፀዋል።

  የህዝበ ውሳኔው ሂደት ፍጹም ሰላማውዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መላው የዞኑ ህዝብ የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲወጡና መራጮችም በነቂስ ወጥቶ ካርድ መውስድ እንዳለባቸው አቶ አክሊሉ አሳስበዋል።

  በዞኑ የመራጮች ምዝገባ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል።

  December 23, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የምርጫ ካርድ ሲወስዱ ያገኘናቸው የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ማርቆስ ማቴዎስ ህብረተሰቡ በወከለው ምክር ቤት በአምስት ዞኖችና ስድስት ልዩ ወረዳዎች ለመደራጀት በተስማማው መሠረት የመራጭነት ካርድ መውሰድ እንዳለበት አሳስበዋል።

  የመምረጥ መብትን ለመጠቀም መቅደም ያለበት ተመዝግቦ ካርድ መውሰድ ነው ያሉት ከንቲባው በከተማው ባሉ 98 የምርጫ መመዝገቢያ ጣቢያዎች ሕብረተሰቡ በአደረጃጀት በነቂስ ወጥቶ እንዲመዘገብ አሳስበዋል ።

  በከተማው በሚገኙ የተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች ህብረተሰቡ በመመዝገብ ካርድ እየወሰደ እንደሚገኝም ለመመልከት ችለናል።

  December 21, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር አዲሱ "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል" ለመመስረት የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ምርጫ መራጮች ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በነቂስ በመውጣት ካርድ በመውሰድ ሲመዘገቡ ውለዋል።

  ከከተማው ነዋሪዎች ጋር ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም የዞን እና የከተማ ቁልፍ አመራሮች የምርጫ ካርድ ወስደዋል::

  የመራጭነት ካርድ ሲወስዱ የነበሩት የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ዮሀንስ በየነ በሰጡት አስተያየት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ውስጥ የሚገኙ 11 የዞን እና ልዩ ወረዳ መዋቅሮች የሚመሰርቱት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በፌዴሬሽን ምክር ቤት ይሁንታ አግኝቶ የህዝቦች መስተጋብር ባጠናከረ መልኩ ህዝበ ውሳኔው እንደሚካሄድ አስረድተዋል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን አለማየው በምርጫ ጣቢያ በመገኘት የመራጭነት ካርድ ወስደዋል ፡፡

  በዚህን ወቅት ክቡር ከንቲባው እንዳሉት በወላይታ ሶዶ ከተማ 106 የምርጫ ጣቢያዎች ለህብረተሰቡ አመቺ በሆኑ ቦታቸዎች ተዘጋጅተዋል፡፡

  የህዝበ ውሳኔው ሂደት ፍፅም ሰላማውዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የዎላይታ ሶዶ ከተማ እና አካባቢው የህብረተሰብ ክፍሎች የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲወጡ አቶ ተመስገን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

  የመራጭነት ካርድ የወሰዱ የሕብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት ደግሞ የዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው በመጨረሻዎቹ ቀናት ከሚፈጠር መጨናነቅ ለመዳን ከወዲሁ መመዝገብ ይገባል ብለዋል፡፡ ዘገባው የከተማው መን/ኮሙኒኬሽን ነው።

  December 21, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • “አቅምን በዉጤት፤ ፈተናን በስኬት” በሚል መሪ ቃል እየተሰጠ ባለዉ ስልጠና አጠቃላይ የዞን አመራሮች፣ ምክትል የመምሪያ ኃላፊዎችና የክልል ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

  የአመራር ስልጠና መድረኩ አመራሩ በወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ላይ አዳዲስ ግንዛቤዎችን እና እይታዎችን እንዲጨብጥ ከማስቻል ባሻገር፣ አመራሩ ተቀራራቢ አረዳድ በመፍጠር የተጠናከረ ፓርቲና መንግስት እውን እንዲሆን የሚያግዝ መሆኑን ተመላክቷል።

  የስልጠና መድረኩ በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት ህዝቡ የሰጠውን አደራ በብቃት መወጣት የሚያስችለዉን የአመራር ስርዓት ለመገንባት እንደ አንድ የአመራር ማብቂያ አማራጭ ተደርጎ መወሰዱም ተነግሯል።

  ስልጠናዉ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ የተገለጸ ሲሆን ተመሳሳይ ስልጠና በወላይታ ዞን ባሉ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ላሉ አመራሮች እየተሰጠ ነዉ፡፡

  December 20, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ሶዶ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት በስነ- ተዋልዶ እና የፆታ ጥቃት መከላከል ዙሪያ የአቻ ለአቻ ስልጠና ለትምህርት ቤቶች እንዲሁም ከትምህርት ቤት ውጪ ለሚገኙ የስነ-ተዋልዶ ጤና ክበብ አባላት እና መሪዎች ነው በዛሬው እለት የተሰጠው፡፡ በስነ ተዋልዶ ጤና እና ፆታ ተኮር ጥቃት መከላከል ላይ ሁሉን አቀፍ እና አካታች ስልጠናዎችን በተከታታይ በመስጠት ጤንነቱ የተጠበቀ እና በስነምግባር የታነፀ ትውልድ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የዎላይታ ሶዶ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ፅህፈት ቤት ምክትል እና የወጣቶች ዘርፍ ሀላፍ ወጣት መድህን አደለ ተናግረል፡፡ ወጣት መድህን የህይወት ክህሎትን በማዳበር ትውልድ ተሻጋሪ አስተዋፆ የሚያበረክቱ ወጣቶችን ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ስልጠናውን የወላይታ ሶዶ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ፅህፈት ቤት እና ከባለድርሻ ተቋማት የመጡ የዘርፍ ባለሙያዎች የሰጡ ሲሆን ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የመጡ ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡ በተለይም ወጣት ተኮር የአሰለጣጠን ዘይቤን በመከተል ዛሬ የሰለጠኑ ወጣቶች ወደ ትምህርት ቤቶች በመውረድ የቀሰሙትን እውቀት ለአቻወቻቸው እንዲያስተላልፉ ወጣት መድህን መክሯል፡፡ የወላይታ ሶዶ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ፅህፈት ቤት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወጣት መድህን አስታውቋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት በተፈጠረላቸው ግንዛቤ ራሳቸውን እና ወገኖቻቸወን ከፆታ ተኮር ጥቃት ለመከላከል እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የወ/ሶዶ ከተማ መንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

  December 15, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ሶዶ ከተማ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ከከተማው ፖሊሴ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ''ፍጥነት ይገድላል፤ ሁሌም ሲያሽከረክሩ የፍጥነት ወሰንዎን ያክብሩ! '' በሚል መሪ ቃል ለአሽከርካሪዎች ለ3 ቀን የሚቆይ የተሃድሶ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል።

  የወላይታ ሶዶ ከተማ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ታጠቅ ምትኩ እንደተናገሩት እንደ ሶዶ ከተማ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በየዓመት የአሽከርካሪዎች የስነ-ምግባር ተሃድሶ ሥልጠና እየተሰጠ መቆየቱን ጠቁመው ዘንድሮም ለበርካታ አሽከርካሪዎች ሥልጠና ለመስጠት ታቅዶ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል።

  የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ደሳለኝ ዘውዴ በበኩላቸው የትራፊክ አደጋ ዘር፣ ቀለምና ጾታ ሳይለይ ሁሉንም የሚጎዳ በመሆኑ አደጋውን ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎችን በቅንጅት ለመስራት ይህ ስልጠና ሚና አለው ብለዋል። አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንብ ጠብቆ ማሽከርከር አለባቸው ያሉት አዛዡ የከተማው ፖሊስ የትራፊክ ደንብ የምጥሱ አሸከርካሪዎችን ወደ ህግ ለማቅረብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል። አዛዡ አክለውም የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ሁሉም ህብረተሰብ ድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

  የሥልጠናውን መርሃግብር በንግግር ያስጀመሩት የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን አለማየሁ እንደገለፁት እጅግ አደገኛ ከሚባሉት በሽታዎች ባልተናነሰ መልኩ ገዳይ የሆነውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ተብሎ ለአሽከርካሪዎች የሚሰጠውን የተሃድሶ ሥልጠና አሽከርካሪዎች በትኩረት እንድሰለጥኑ አሳስበዋል። አቶ ተመስገን አክለውም ህይወት ምትክ የለለው መሆኑን አውቃችሁ ስታሽከርክሩ የፍጥነት ወሰን በማክበርና በጥንቃቄ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ለአሽከርካሪዎች የተሃድሶ ሥልጠና መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ በሶዶ ከተማ ለሚገኙ አሽከርካሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እንደሚሰጥም ተገልጿል።

  በዚህ ዙር አሽከርካሪዎች ተሃድሶ ሥልጠና በቁጥር 3000 የሚጠጉ አሽከርካሪዎች ሥልጠና ይወሰዳሉ ተብሏል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ሥራ አመራሮች ፣የዘርፉ ባለሙያዎችና የትራፊክ ፖሊሶች እንዲሁም አዛዦች በተገኙበት ሥልጠናው መጀመሩን ባልደረባችን ሰይፉ ሳሙኤል ዘግቧል።

  December 7, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በፕሮግራሙ የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ ከንቲባ አቶ ወንድሙ ደረጀ፣ የዳሽን ባንክ ወላይታ ዲስትሪክት ማኔጀር አቶ ታዴዎስ ተስፋዬ እና ሌሎች የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ስራ ኃላፊዎችና በክብር የተጠሩ እንግዶች ተገኝተዋል።

  የባንኩ መከፈት በአካባቢው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲጨምር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

  በትዕግስት ክፍሌ

  December 6, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ሶዶ ከተማ ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ፅህፈት ቤት ከቃለህይወት የልማት ኮሚሽን የኤችአይቪ መከላከል እና ህክምና አገልግሎት ጋር በመተባበር ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ድጋፍ አድርጓል።

  የከተማ ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ በረከት ቶማስ በኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ላይ በማተኮር ከአንድ ሺ ሁለት መቶ በላይ ተጋላጭ ቤተሰቦችን በማቀፍ ድጋፍ መደረጉን አስረድተዋል።

  ከእነዚህም ውስጥ ለከፋ ችግር የተዳረጉ አንድ መቶ ዘጠና በላይ ሴቶች፣ እናቶች ፣ ህፃናትና አቅመ ደካሞች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ከእርዳታ ጠባቂነት ተላቀው ወደ ስራ እንዲሰማሩ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚደረግ ኃላፊዋ ወይዘሮ በረከት ገልፀዋል።

  የቁጠባ ባህልን ለማጎልበትና ዘመናዊ የፋይናንስ ስርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተዘጋጀውን የባንክ ደብተር ወይዘሮ በረከት ለተጠቃሚዎች ሰጥተዋል። ወይዘሮ በረከት አክለውም በዚሁ ፕሮጀክት አማካይነት የመማር ቁሳቁስ፣ የምግብ ድጋፍ እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ክፍያ በመፈፀም ዘላቂ የልማት አጋር መሆኑን አረጋግጧል ብለዋል።

  በቃለህይወት የልማት ኮሚሽን የኤችአይቪ መከላከል እና ህክምና አገልግሎት የፕሮጀክቱ ባለሙያ የሆኑት ሲስተር ሙሉነሽ ሜጋ በበኩላቸው የቤተሰብ አቅም ግንባታ የሚሰሩ ተቋማትን በጎ ፈቃደኞች እና የማህበረሰብ አገልግሎት ሰጪዎችን በማስተባበር የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እየተሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የተገኘውን ጥሪት በአግባቡ በጠቀም የሚጠበቀውን ለውጥ ማምጣት እንደሚባ ሲስተር ሙሉነሽ መክረዋል።

  ቁልፍ ባለድርሻ አካል የሆኑት የጤና ተቋም ኃላፊዎች ለቅንጅታዊ አሰራር ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል ሲል የዘገበው የወላይታ ሶዶ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

  December 2, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ የዘንድሮውን የብሔር ብሔሰቦች ቀንን ልዩ የሚያደርገው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለሁለት አመታት ገደማ ሲካሄድ የነበረው ጦርነትና ሰላም ማጣት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ስምምነት በተደረገበትና ከጦርነት ተላቅቀን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥና በምግብ ራስን ለመቻል "የሌማት ትሩፋት" መርሐ ግብር በተጀመረበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

  በደም የተከበረችን ሀገራችንን በላብ ለማጽናት እንዲሁም በብዙዎች የህይወት መስዋዕትነት የተገኘው ነፃነት እንዳይቀለበስ ለማድረግ ሠርተን ለመለወጥና ለመልማት ያለንን አቅም አሟጠን መጠቀም ይኖርብናል ያሉት ክብርት አፈ ጉባኤዋ በበጋ መስኖ ስንደ ልማት አጠናክረን በመቀጠል በምግብ ራሳችንን ለመቻል ከምናደርገው ጥረት ባሻገር ስንዴን ኤክስፖርት በማድረግ የሚደርስብንን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም መሥራት ያስፈልገናል ብለዋል።

  የብሔር ብሔረሰቦች ቀንም ሲከበር በዋናነት የብሔር ብሔሰቦችን መብት መከበር የሚያረጋግጥ ህገ መንግስት የጸደቀበትን ቀን እያሰብን ነው ብለው በተለይ ሴቶች ድርብ ድል የተጎናጸፍንበት ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጫናዎች የተላቀቅንበትና በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች እስከቀበሌ ምክር ቤቶች በኃላፊነት ለመምራትም ጭምር ዕድል ያገኘንበት ነው ብለዋል።

  እንደኢትዮጵያ ብዝሐ ብሔር ቋንቋና ባህል ያለን ቢሆንም በልማትና አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች በአንድነት መቆም ይቻላል ያሉት ወ/ሮ ካሰች ለህገ መንግስት መከበርና ፌደራሊዝም መጎልበት ሁሉም የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

  አክለውም ከፌዴራሊዝም ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ብዥታዎችን ለማጥራት ከ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ እንዲያውቁና እንዲለማመዱ ለማድረግ የተለያዩ ዝግጅቶች መደረጋቸውን በዚም መድረክ የፌደራሊዝም ጽንሰ ሀሳብ ለማስጨበጥ የሚያስችል ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ብለዋል ክብርት አፈ ጉባኤዋ።

  November 30, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ 17ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል "ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል።

  የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል መከበሩ ኢትዮጵያ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአንድነትና በመቻቻል የሚኖሩባት ተምሳሌት መሆኗን ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
  በዓሉ በህዝቦች መካከል አብሮነትና አንድነት እንዲጎለብት የላቀ አሰተዋጽኦ እንደሚያበረክት የመንግስት ወና ተጠር አቶ ዮሐንስ አብራርተዋል።

  ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮችና ብሔረሰቦች በራሳቸው ቋንቋ፣ ባህልና አለባበስ ተውበው በዓሉን ሲያከብሩ ለሀገር ሠላም ያለው ሚና እያደገ እንደሚሄድ አክለዋል።

  የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን አለማየሁ በበኩላቸው፣ በዓሉ የሚከበርበት ዋና ዓላማ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የእርስበርስ ትስስር በማጠናከር በብዛሃነት ላይ የተመሠረተ ሕብረ - ብሔራዊ አንድነት ሥር እንድሰድ ለማድረግ የገቡትን ቃል ኪዳን በማደስ በአድስ መንፈስ ለሠላም፣ ለልማትና ለዴሞክራሲ ግንባታ እንድነሳሱ እንደሆነ አረጋግጠዋል። በህዝቦች መካከል አብሮነትና መተሳሰብ በመፍጠር ጠንካራ አንድነት እንዲጎለብት ማድረግ የበዓሉ ዋና ግብ መሆኑን ክቡር ካንቲባው ገልጿል።

  በዓሉ በተለያዩ ከነቶች በጽዳት ዉቤት ሥራ በችግኝ ክብካቤ እና በደም ልገሳ የተለያዩ በጎ ሥራዎችን በመሥራት እየተከበረ ይገኛል።
  የዞኑ አጠቃላይ አመራሮችና ባለሙያዎች የሶዶ ዙሪያ እና የወላይታ ሶዶ ከተማ አጠቃላይ አመራሮች እና ባለሙያዎች በክብረ በዓሉ ላይ ተሳትፈዋል ። ዘገባው የሶ/ከ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነዉ።

  November 26, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ14ኛ ጊዜ በተለያዩ የጤና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 234 ተማሪዎች በህክምና ዘርፍ አስመርቋል።

  በምረቃ ስነ ስርዓቱ የተገኙት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስተር ዲኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት ህብረተሰብን ማገልገል ክብር ህይወትን መታደግ ደግሞ ድርብ ክብር በመሆኑ ተመራቂዎች ለዚህ ኃላፊነት ራሳቸውን ማዘጋጀት ይገባቸዋል ብለዋል።

  ዶ/ር አየለ ተሾመ አክለውም ቀጣይነትና ጥራት ላለው የጤና ስርዓት ማጎልበት በክህሎትና በዕውቀት የበቃ ባለሙያ ጉልህ ሚና ስላለው ሚኒስቴሩ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

  የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታ ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም ህብረተሰቡን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል እንደሚገባቸው አሳስበዋል። በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ወኪል ወልዴ በበኩላቸው ከተመራቂ ተማሪዎች 188 በቅድመ መደበኛና 46 በሁለተኛ ድግሪ የሰለጠኑ ናቸው ብለዋል።

  ኮሌጁ በማስተማርና ማህበረሰብ አገልግሎት የራሱን አሻራ ለማኖር የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ15 ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍል የካንሰር ህክምናን ጨምሮ ሌሎች ጥራት ያላቸውን አገልግሎቶች እየሰጠ ይገኛልም ብለዋል። ተመራቂ ተማሪዎች በሜዲካል ላብ፣ በፐብሊክ ሄልዝ፣ በህብረተሰብ ጤና፣ በፓርማሲ፣ በአንስቴዥያ፣ በሚድ ዋይፈሪና በሌሎች ዘርፎች የሰለጠኑ ሲሆን በየትምህርት ክፍሎችና በኮሌጁ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተመራቂዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

  በሰብለወርቅ ኤልያስ

  November 26, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ በአረካ ከተማ በጥቅምት 12 /2015 ዓ/ም በገበያ ማዕከል በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

  በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ንብረት ውድመት ለደረሰባቸው ወገኖችን 5 ሺህ 1 መቶ ኪሎ ግራም አልባሳትና 130 ፓኬት ሚስማር ድጋፍ አድርጓል።

  የተደረገዉ ድጋፍ የአረካ ከተማ አስተዳደር በድንገት በተከሰተው እሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ባቀረበው ጥሪ መሰረት እንደሆነም ተገልፀዋል፡፡

  ድጋፉን የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ዋና ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት ያበረካቱ ሲሆን በደረሰው ጉዳት መጠን መረጃ መሰረት ድጋፉ በቂ እንዳልሆነም አስታውቀዋል።

  በድጋፉ ቦታ ከፍተኛ የዞንና የከተማ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ድጋፉን የተረከቡ ወገኖች ለተደረገላቸው ወገናዊ ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል ። ዘገባው የከተማ አስተዳደሩ መ/ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

  November 23, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ ባስተላለፉት መልዕክት ከተባበርን የማንወጣው ዳገት የለም ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ድህነትን ማሸነፍ የሚቻለው ከመስራት ባለፈ እርስ በእርስ መደጋገፍ ሲቻል እንደሆነ ገልፀዋል ።

  አቶ ደስታ ዳና የቦዲቲ ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በቦዲቲ ከተማ ይህን መሰል ትልቅ ተግባር በመፈጸሙ እጅግ መደሰታቸውን በመግለፅ በከተማው ህዝብና መንግስት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

  አቶ ደስታ አክለውም በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ሌሎች አቅመ ደካማ የሆኑ ነዋሪዎችን ለማገዝ የከተማው አስተዳደር ሰፊ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ በበጎ ተግባራት ላይ ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

  ቤቱን የተረከቡት ወ/ሮ አስቴር ዶዳ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

  በመርሀግብሩ ላይ የክልል፣ የዞን መምሪያ ኃላፊዎችና የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ጠቅላላ አመራሮች ተገኝተዋል ። ዘገባው የከተማው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

  November 22, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በምረቃ ስነስርዓቱ ከኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ከወላይታ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ እንዲሁም ከበሌ ሐዋሳ ከተማ የተለያዩ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

  በርክክብ ስነ-ስርዓቱ የበሌ ሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ስምዖን ሳፓ እንዳሉት በሚኒስቴር መ/ቤት የተጀመረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ የዘገየ ቢሆንም ተጠናቆ ርክክብ በመፈጸሙ ምስጋና አቅርበዋል።

  በሚኒስቴር መ/ቤት ድጋፍ የተደረገው ድጋፍ በተገቢ ሁኔታ በሥራ ላይ እንዲውል የከተማ አስተዳደሩ የፊት አመራሮች ተግባራትን ተከፋፍለው በመውሰድ በቁርጠኝነት መምራታቸውን ገልጸዋል። የከተማው የሀይማኖት አባቶችና ሀገር ሽማግሌዎች ለሥራው ስኬታማነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

  የወላይታ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሪት ድርሻዬ በለጠ እንዳሉት ሚንስቴር መ/ቤቱ በበሌ ሐዋሣ ከተማ ለ5 አቅመ ደካማ ሴቶች ቤት ሠርቶ በማስረከባቸው መደሰታቸውን ገልጸው ይህ በጎ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል። በኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቋማዊ አደረጃጀት ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ትዕግሥት በይሳ ሚኒስቴር መ/ቤቱ የጀመረው የበጎ አገልግሎት ሥራ ተቋማዊ አደረጃጀቱን ለማስተካከል ጥረት ሲደረግ የተገባው ቃል መስተጓጎሉን ተናግረዋል።

  አሁን በከተማ አስተዳደሩና በዞኑ የታየው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ። ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቀጣይነት በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል ። ድጋፍ የተደረገላቸው አቅመ ደካማ ሴቶችም ከዚህ ቀደም ሲል ባሉት ጊዜያት ቀን ጨልሞባቸው የኖሩ መሆናቸውን በመግለጽ ስለተደረገላቸው ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል ።

  ማን ይደርስልናል እያልን ወደ ፈጣሪ እየጸለይን እያለን ፈጣሪ ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱን በማነሳሳት አምጥቶ ቤታቸንን ሰርቶ እንዲያስረክብልን አድርጓል ብለዋል ።

  በታደለ ፎላ

  November 19, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ልማት ማህበርሩ ዳግም ከተቋቋመበት ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ ጊዜያትን በት/ት፣ በጤና፣ በሰዉ ኃይል ልማትና እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የዞኑን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

  ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወድህ ስራዉን በትክክል እንዳያስኬድ የሀብት (ገንዘብ) እጥረት፣ የአባላት መዋጮ ወጥ አለመሆን፣ ከዓለምአቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የለጋሾች አጋርነት መቋረጥ እና ሌሎችም ጉዳዮች ፈተና ሆኖበታል፡፡

  ይህንን የተረዳዉ የዞኑ አስተዳደር የልማት ማህበሩን አቅም ማሳደግ ላይ ያተኮረ ውይይት የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት በሐዋሳ ከተማ አካሂዷል፡፡

  በልማት ማህበሩ የሐዋሳ ቅርንጫፍ አባላት በተገኙበት በተካሄደ በዚህ መድረክ ማህበሩ እስከአሁን የሰራቸዉ ልማቶችና ተግዳሮቶችን የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደርገባቸዉ ይገኛል።
  በማስረሻ ሀብታሙ

  November 19, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ እና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በዛብህ ሻንካ በቦታው ተገኝተው እንደገለፁት የዳላ ባህል በእንስሳት እርባታ ዘርፍ የሚሰማሩ አርሶ አደሮችን የሚያበረታታ ተግባር እንደሆነ ተናግሯል።

  በወላይታ ባህል ትልቅ ሥፍራ ከሚሰጣቸው ሀብት ማብሰሪያ ስነ-ስርዓቶች መካከል አንዱ የሆነው የዳላ ስርዓት የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚ ተጠብቆ እንድቆይ የሚያደርግ ቢሆንም እንስሳት በበሽታና በሌሎች ምክንያቶች የሚሞቱ ስለሆነ ወደ ቋሚ ሀብት ተቀይሮ እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

  አቶ በዛብህ አክለው በወላይታ አከባቢ የተለመዱትን የእንሰሳት ዝርያ በማሻሻል ቢሆን ደግሞ ይበልጥ አሁን ከአንድ መቶ ሀምሳ በላይ ከብቶችን ያስቆጠረው አቶ ይገዙ ነጋን ጨምሮ ሌሎች አርሶ አደሮች ውጤታማ እንደሚሆኑ መክረዋል።

  የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አበበች ሻሬቾ በበኩላቸው ይህ የሀብት ማብሰሪያ ሥነ-ሥርዓት የሆነው ይህ "ዳላ" ስርዓት በወላይታ ህዝብ ዘንድ መተጋገዝ እና ተባብሮ አብሮ የማደግ ባህልን የሚያንፀባርቅ ቱባ ባህል እንደሆነ ተናግረዋል። በተጨማሪም የወላይታ ህዝብ ባህል ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውልድ እንዲሻገር ታታሪ አርሶ አደሮች አሁንም በዚህ ዘርፍ ላይ ጠንክረው እንድሰሩ እና እርስበርስ እየተጋገዙ የማደግ ባህልን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

  ወ/ሮ አበበች የዳላ ስነ-ስርዓት የወላይታ ህዝብ የኢኮኖሚያዊ ከፍታ የሚሳይ እና ከአባቶቻችን ጋር ተያይዘው የመጣ ቱባ ባህል ብቻ ሳይሆን የወላይታ ህዝብ ማንነት የሚገልጽ እና የህዝቦች አኗኗር ለዓለም የሚያስተዋውቅ ባህል ስለሆነ ለቀጣይ ትውልድ ሊተላለፍ ይገባል ብለዋል።

  የዳላ ስነ-ሥርዓት ያበሰሩት አርሶ አደር አቶ ይገዙ ነጋ ከአንድ በሬ ተነስተው ወደ አንድ መቶ ሀምሳ ከብቶችን ማርባት እንደቻሉ ተናግረዋል።

  አቶ ይገዙ አያይዞም የእንስሳት ዝርያን በማሻሻል ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን እንደምሰሩ እና በቀጣይ ከብቶችን ወደ አንድ ሺህ አድርሶ በሊቃ ሥርዓት ሀብታቸውን ለማስተዋወቅ ዕቅድ እንዳላቸው ገልፀው በቅርቡ ዘመናዊ የእህል ወፍጮ ማሽን ለመትከል ዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

  በሰይፋ ሳሙኤል

  November 19, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በወላይታ ዞን በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋጃ ቀሮ ቀበሌ በግል ባለሀብት ወ/ሮ ምትኬ ባልቻ የተገነባው ነዳጅ ማደያ በዛሬው ዕለት ተመርቋል። የነዳጅ ማደያውን የክልልና የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች መርቀው ከፍተዋል።
  በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ዘነበ ዛራ እንዳሉት በሀገራችን እያደገ የመጣውን የነዳጅ ፍላጎትን ለማጎልበትና የአቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ የራሱ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

  የኢንቨስትመንት መስኮችን ተሳትፎ በጥራትና በብዛት በማረጋገጥ የብልጽግና ጉዟችን እውን እናደርጋለን ሲሉም ተናግረዋል። የነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ ምርት ግብይትን ጤናማ በማድረግ የገበያውን ጉድለት ልደፍኑ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

  የወላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት ለዞኑ ብሎም ለአጎራባች ዞኖች ትልቅ የኢኮኖሚ ፋይዳ ያለውን ዘመናዊ ሞቴል በአጭር ጊዜ ገንብተው ለምረቃና አገልገሎት በማብቃታቸው ልባዊ ደስታና አድናቆት ገልጸዋል።

  በዞኑ በሶስት የኢንቨስትመንት መስኮች 323 ባለሀብቶች 9.93 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማስመዝገባቸውን ጠቅሰው በዚህ ለ39 ሺህ ዜጎች በቋሚነትና በጊዜያዊነት የስራ ዕድል መፍጠሩን አስታውቀዋል። በዞኑ በመጀመሪያ የሴት ባለሀብት ተጀምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት የበቃ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት መሆኑን ከሌሎች ለየት ያደርገዋል ብለዋል። የግሉ ሴክተር ለኢኮኖሚ ዕድገት ሞተር ነው ያሉት አቶ መስፍን ለጂዲፒ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑንም ገልጸዋል። የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኃይለ ሥላስ የኢኮኖሚ ብልጽግና ለማረጋገጥ የብዝሃ ዘርፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እጅግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

  በወረዳው ላለፉት ለአንድ አመታት ምንም የነዳጅ ማደያ እንደሌለ የጠቆሙት በዛሬው ዕለት ከተመረቀው ጋር ሁለት መድረሱንም አስታውቀዋል።

  የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚ ዘርፍ ያለው ሚና የጎላ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የግል ባለሀብቶች የአንበሳውን ድርሻን በመያዝ የስራ ዕድልና ገበያ ጉድለቶችን በማሟላት ረገድ አይተከ ሚናውን ይጫወታሉ ብለዋል። የማደያ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ምትኬ ባልቻ በበኩላቸው በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

  የነዳጅ ማደያው ከ34 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ መሆኑን ገልጸው ለ35 ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠሩን አስታውቀዋል ሲል የዘገበው የዞኑ ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ነው።

  November 19, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በጀት ዓመቱ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልገሎቱን በመጠንና በጥራት ከፍ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ አስታወቁ።

  የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የማቀጣጠያ ንቅናቄ መድረክን በቦዲቲ ከተማ እያካሄደ ነው።

  በ2015 በጀት ዓመት 400 ሺህ የሚጠጋ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላትን ለማፍራት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ የመምሪያ ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ አስታውቀዋል።

  ከዚህም 91 ሺህ የሚጠጉት የመክፈል አቅም የሌላቸው የማህበረሰብ ክፍል መሆናቸውን አስረድተዋል። በ2014 በጀት ዓመት 229 ሺህ የሚጠጉ አባወራዎችና እማወራዎች የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባል ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

  አያይዘውም 1.2 ሚሊዮን የሚበልጥ ገንዘብ የተሰበሰበ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው 7.2 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ከዞንና ወረዳዎች ለአቅመ ደካማዎች የድጎማ በጀት መመደቡን ገልጸዋል።

  በጤና መድህን ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎቱን ለሁሉም ማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ በማድረግ የህዝቡን ጤናና ደህንነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የተሰሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውንም አስረድተዋል። በመድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳዳሪዎችና የዘርፉ አመራሮች ተገኝተዋል።

  በታረቀኝ ተስፋዬ

  November 18, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የበጋ መስኖ ስንዴ ሥራ በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በጉሩሞ ኮይሻ ኢጣና መስኖ በይፋ ተጀምሯል።

  ይፋዊ የበጋ መስኖ ልማት ዘር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በስድስቱ ቀበሌያት የዞን ከፍተኛ የሥራ አመራሮችን ጨምሮ የወረዳው ደጋፊዎች እና የወረዳ ፊት አመራሮች በተገኙበት ነው የተጀመረው።

  በ170 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማው ይህ የበጋ መስኖ ስንዴ 7 ሺህ 650 ኩንታል ለማግኘት እየተሰራ ነው። በዚህ በጋ መስኖ ስንዴ ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የወላይታ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም እንደገለፁት የሀገራችንን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚናረጋግጠው በሌሎች ላይ ተደግፈን ሳይሆን በራሳችን ጠንክረን ሰርተን ነው ብለዋል። የበጋ ስንዴ የማልማት ስራ የወረዳውን አርሶ አደሮችን ኑሮ ከማሻሻል በላይ የዞናችን ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍ ለማድረግ ጉሊህ ሚና አለው ብለዋል።

  ሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተና ውስጥ ሆናም ይህንን የበጋ መስኖ ስንዴ በመዝራት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻሏንም ወ/ሮ እታገኝ አንስተው ዘንድሮም 1 ሺህ 926 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴን በማልማት 35.5 ኩይንታል ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ወ/ሮ እታገኝ ተናግረዋል።

  የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ም/ኃላፊና የቡና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ታውሌ በበኩላቸው የዞናችን አርሶ አደሮች ኑሮ ለመለወጥ በሁሉ አቀፍ ግብርና ዘርፍ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው የበጋ መስኖ ስንዴ የማልማት ሥራ የዚህ ትልቁ ማሳያ ነው ብለዋል።

  የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዋና አሰተዳደሪ አቶ አክሊሉ ፍልጶስ ከዚህ በፊት የአከካባቢው አርሶ አደሮች የበጋ መስኖ ስንዴ ለምቶ ፍሬ እንደሚሰጥ ብዙ ግንዛቤ እንዳልነበራቸው ገልጸው አሁን ላይ ውጤቱን ካዩ በኋላ የውሃ አማራጭ ያለባቸው አከካባቢ አርሶ አደሮች ስንዴ እየዘሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

  አስተዳዳሪው አክለውም አርሶ አደሩ 71 ከመቶ ምርት ለአካባቢ ፍጆታ ተጠቅመው 29 በመቶ ለውጭ ገበያ ለማቅረብም ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል። የዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ሥራ በወረዳው በ6ቱ ቀበሌያት በ170 ሄክታር መሬት እንደምለማ የተናገሩት የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማን ከበደ ከዚህ 7 ሺህ 650 ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል።

  አቶ አማን አክለውም ከአምናው ምርት ዘመን ጋር ሲነጻጸር ዘንድሮ የተሻለ የስንዴ ምርት ለማግኘት በሙሉ ፓኬጅ የመስኖ ሥራ በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

  በሰይፉ ሳሙኤል

  November 16, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ከአንድ ሄክታር 35 ኩንታል ምርት ለማግኘት የታቀደው የበጋ መስኖ ስንዴ ሥራ በወላይታ ዞን በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በይፋ ተጀምሯል።

  በይፋዊ የበጋ መስኖ ልማት ዘር ማስጀመሪ መር ግብሩ ላይ የወላይታ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ፎላን ጨምሮ ሌሎች የዞኑና የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎችና የአካባቢው አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

  November 16, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • መርሃ ግብሩን የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ዋና ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት አሰጀምረዋል፡፡

  በ2015 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በመስኖ በማልማት 50 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማምረት እቅድ ተይዟል፡፡

  እንደ ደቡብ ክልል የተጀመረው ስንዴን በመስኖ የማልማት ተግባርን በማስፋፋት ዘንድሮ በ22 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት ሥራ እንደሚካሄድ ከክልሉ ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ የ2015 ዓ.ም በበጋ መስኖ ስንዴን የማልማት ሥራ በወላይታ ዞን ባሉ 13 የወረዳ መዋቅሮች ይፉዊ የማሰጀመሪያ መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል፡፡

  የወላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ዋና ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት እንዳሉት በወላይታ ዞን የተጀመረውን ስንዴን በመስኖ የማልማት ተግባር በማስፋፋት ዘንድሮ በ1926 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ስንዴን በመስኖ የማልማት ሥራ የተጀመረ ሲሆን ከዚህም 67 ሺህ ኩንታል ምርት ይጠበቃል፡፡ አምና በተሰሩ ጅምር ስራዎች የተሻለ ውጤት መገኘቱን ተከትሎ ዘንድሮ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሀገራዊ ብልፀግናን ለማፋጠን እና የውጭ ገበያ ታሳቢ ባደረገ መልክ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

  እንደ ወላይታ ዞን ከአንድ ዓመት በፊት በበጋ መስኖ ስንዴን የማልማት ሥራ አለተለመደም ነበረ ያሉት አቶ መስፍን ተግባሩ አዲስ ከመሆኑ የተነሳ አርሶ አደሮች ለመቀበል ያሰስቸገሩ ቢሆንም በተገኘው መልካም ውጤት ዘንድሮ ሁሉም አርሶ አደሮች በራሳቸው ተነሳሽነት መጀመራቸውን ተናግረዋል ፡፡

  ይህም ድህነትን ለማሸነፍ የሚደረግ ትግል ውጤታማ የሚያደረግ ነው ብለዋል፡፡
  በአማኑኤል ጃግሶ

  November 16, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በወላይታ ዞን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ይፋዊ የዘር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

  በ2015 የምርት ዘመን በዞን ደረጃ በሚከናወነው የበጋ የስንዴ ዘር ልማት ውጤት በታቀደው ልክ ለማከናወን እየተሰራ ይገኛል ።

  በዚህም ከ67 ሺህ ኩንታል ምርት በላይ ለማግኘት መታቀዱን ከዞን ግብርና መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

  በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማን ጨምሮ ሌሎች የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎችና አርሶ አደሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

  November 16, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሪት ድርሻዬ በለጠ ''ሴቷ መቼም ቢሆን የሚደነቅ ማንነት አላት፤ ይህን ደግሞ ወደ ተግባር ለመቀየር ሥልጠናው ወሳኝ ነው'' ብለው ሴቷን ከቤተሰብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በኢኮኖሚ አቅሟን ማሳደግ ወሳኝ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

  ነጋዴ ሴቶች በሚገጥሟቸው ፈተናዎች ፈርተው ወደ ኋላ እንዳይመለሱ አቅም የሚፈጥር ሥልጠና ነው ብለው ዋናው ነገር መሠልጠን ብቻ ሳይሆን የወሰዱትን ሥልጠና ወደ ተግባር መለወጥ እንዳለባቸውም አሳስበዋል ኃላፊዋ።

  የሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን በመቀበል እንደዞን ከፓርቲ አመራሮችም ጋር በመሆን አቅም በፈቀደ መጠን ለመደገፍ ጥረት ይደረጋል ብለው በእጃችን ያለውን ገንዘብ በውጤታማነት ለመጠቀም ዕውቀትና ክሂሎት ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

  ሴቶች ቁጠባን ባህላቸው እንዲያደርጉም ያሳሰቡት ኃላፊዋ ለተጀመረው ሥራ ፕሮጀክቱንና አሠልጣኞችን አመስግነዋል።

  የክሂሎት ሥልጠናውን የሰጡት አሰልጣኝ ዶ/ር ወልደማርያም ልሳኑ ሰዎች ወደ ስኬት ማማ ላይ እንዲደርሱ ያስቻሉ ብቃቶች አሉ በማለት ሰልጠኞችም እነዚህን ብቃቶች በመጎናጸፍ የንግድ ሥራቸውን እንዲሠሩ ሥልጠናው እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል።

  በኢንተርፕሪኔርሽፕ ዴቬሎፕመንት ኢንስቲትዩሽን የሴት ኢንተርፕሪኔርሽፕ የከተማ ፕሮጀክት አስተባባሪ ወ/ሪት ማህሌት ሰሎሞን በበኩላቸው የወላይታ ዞን በፕሮጀክቱ የተመረጠው በዞኑ ብዙ ነጋዴ ሴቶች በመኖራቸው እንደሆነ ተናግረው ሥልጠና መስጠት ብቻ ሳይሆን ኢንስቲትዩቱ የማማከር አገልግሎትና ብድር የማመቻቸት ሥራም ከባንኮችና ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር በመሆን ይሠራል ብለዋል።

  ስልጠናው በሶስት ዙር ከ750 በላይ ለሚሆኑ ነጋዴ ሴቶች እየተሰጠ መሆኑንም ወ/ሪት ማህሌት አክለዋል።

  የወላይታ ዞን ነጋዴ ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሽታዬ አስረስ በበኩላቸው የነጋዴ ሴቶችን በሥልጠና አቅማቸውን ለማሳደግ ማህበሩ አጠናክሮ ይሠራል ብለዋል።

  የሥልጠና ተሳታፊዎችም ሥልጠናው በሚገባን ቋንቋ የተሰጠና ሌሎችንም ለማብቃት የምንችልበት አቅም የፈጠረልን ነው ያሉ ሲሆን ለሰልጣኞቹ በሥልጠና ማጠቃለያ የዕውቅና ሴርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
  የዞኑ መ/ኮ/ጉ መምሪያ ዘግቧል።

  November 10, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሪት ድርሻዬ በለጠ በጉባኤው ባስተላለፉት መልዕክት የሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለታካዊ ተጠቃሚነት ጉዳይ የሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶችን የሚመለከት ጉዳይ ነው ብለዋል።

  በ2014 ቀበጀት ዓመት ''ምግቤን ከጓሮዬ ጤናዬን ከምግቤ`` በሚል ሀገራዊ መርሃ ግብር በተለይም በሶዶ ከተማ የሽቅብ እርሻ ስራ ተግባራዊ በማድረግ በርካታ ሴቶች ጠቃሚ መሆናቸውን ወ/ሪት ድርሻዬ ገልጸዋል።

  ሴቶችን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ለማላቀቅ ከጾታ አቻወቻቸው ጋር በተለያዪ ኅብረት ስራ ማህበራት ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል።

  በጉባኤው የ2014 በጀት አፈጻጻምና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል። በጉባኤው የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማን ጨምሮ የዞን፣ የወረዳና የከተማ ስተዳደሮች የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

  በመለሰ ኦልኮ

  November 8, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ለወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ አመራሮች፣ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች የሪፎርም ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስ መምሪያ ሥልጠና ሰጠ።

  የወላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ዋና ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት በየሴክተሩ የሪፎርም ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የታቀዱ ዕቅዶች በአገባብ እንዲከናወኑ የባለድርሻ አካላትና የአመራሮች ቁርጠኝነትን እንደሚጠይቅ ተናግረዋል ።

  ለግብርና ዘርፍ ከተሰጠው ትኩረት አንጻር በዘርፉ ያሉ አመራሮች፣ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች በዘርፉ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ውጤታማነትን ለማረጋገጥ በዕቅድ በመመራት የጋራ ውጤት ከማስመዝገብ ረገድ ሥልጠናው አቅም እንደሚሆን አቶ መስፍን ዳዊት አስረድተዋል ።

  ባለድርሻ አካላት ኃላፊነቱን በተሰማሩበት ዘርፍ በአግባቡ ለመወጣትና የሪፎርም ሥራ ማጠናከር ስልጠናው ወሳኝ መሆኑን በማንሳት በዋናነት የሰክተር ተኮር ሪፎርም አተገባበር እና የሠራተኛው የሥራ ሥነ ምግባር ደንብ ላይ ያተኮረ ሥልጠና መሆኑን የዞንኑ ፐብሊክ ሰርቪስ ባለሙያ የሆኑት አቶ አሥራት ንጋቱ አስረድተዋል ።

  በግብርና መምሪያ ውስጥ ያሉ አጠቃላይ ሠራተኛውም ሥልጠናውን ከተከታተሉ መካከል ከተቋሙ የተጣለበት ኃላፊነት አንፃር የየራሱን የሥራ ድርሻ በኃላፊነት መንፈስ ለመፈፀም ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ በአስተያየታቸው ገልጸዋል ።

  በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ዕቅድ ላይ ሴክተር ተኮር ዕቅዶችን ውጤታማ ለማድረግ በቲም የሪፎርም ሥራ ለማሳለጥ የመዋቅሩን ራዕይና ተልዕኮን ከግብ ለማድረስ በአንድነት በመቀናጀት እንደሚንቀሳቀሱ በሥልጠናው አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመዋል። ተመሳሳይ ሥልጠና በወረዳና በከተማ አስተዳደር ባሉት በግብርና ሴክተር እንደሚሰጥም ተጠቁሟል። (ወ/ዞ/መ/ኮ መምሪያ)

  November 7, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ''ወባን መከላከል ከኔ ይጀምራል'' በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የወባ ሳምንት በሚመለከት ከተለያዩ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከተወጣጡ የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚያካሂደው የንቅናቄ መድረክ ተጀምሯል።

  ባለፉት አስርት አመታት እንደ ሀገር ለዘርፋ በተሰጠው ትኩረት በወባ በሽታ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር 50% እና 60% መቀነስ ተችሏል፡፡

  የወባ በሽታ ከረዥም አመታት ጀምሮ ከህዝቡ ጋር የቆየ በሽታ ነው፡፡ በሽታውን ለመከላከል እንደ ወላይታ ዞን ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ያሉት የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ ወቅቱን ጠብቆ ከመስራት እና ከመምራት አኳያ ሰፊ ጉድለቶች መኖራቸውን አንስተው እነዚህን ጉድለቶች ለመፍታት በአግባቡ መመራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

  ምንም እንኳን የወባ በሽታ ለመከላከል በርካታ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም በ2015 ዓ/ም ግን የስርጭቱ መጠን ጨምሯል ብለዋል፡፡ ወባን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል፡፡

  የተቀዛቀዘው የጤና ኤክስቴንሸን ስራዎች በተጠናከረ ሁኔታ ሊሰራ ይገባል ተብሏል፡፡ በተለይም አመራሩ በትኩረት መምራት እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

  በተጨማሪ የሞዴል ቀበሌያትን ከመፍጠር እና የማህበረሰብ ጤና መድህን አፈፃጸም በተመለከተም ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

  በአማኑኤል ጃግሶ

  November 7, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባስመዘገባቸው ዋና ዋና ስኬቶችና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ የስራ አመራር ቦርድ ከጽ/ቤቱ ማኔጅመንት አካላት እና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

  ጣቢያው ያሉ ተግዳሮቶችን በትጋት በማለፍ እየሰራ በሚገኘው ጥራት ባለው ስራ ሰፊ አድማጭ ተመልካች ማህበረሰብ ክፍሎችን ማፍራት መቻሉ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

  ሚዲያው ያለውን ውስን የሰው ኃይልና ቁሳቁስ በአግባቡ በመጠቀም የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ የተጠቆመ ሲሆን ቀጣይ ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርስ አዳድስ አቀራረቦችን በመጠቀም በርትቶ መስራት አለበት ተብሏል።

  ሚዲያው የሕዝብ ሚዲያ እንደመሆኑ መጠን በሀገር በቀል ዕውቀት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበትም ተመላክቷል።

  'አኔ ኤራን' የመሳሰሉ እያዝናኑ የሕዝቡን ቋንቋና ባህል ማሳወቅ የሚችሉ ይዘቶች ሚዲያው ከተቋቋመበት አላማ አንጻር ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ በመሰል ይዘቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ተጠቁሟል።

  ሚዲያው ወቅቱን የሚመጥን ስራ እንዲሰራ ለማስቻል የፋይናንስ አቅም ያስፈልጋል ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች የአካባቢው ባለሀብት፣ የተለያዩ ተቋማት እና ሰፊው ማህበረሰብ በባለቤትነት የሚሳተፉበት አሰራር ተዘርግቶ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

  የጣቢያው ስራ አስኪያጅ፣ ማኔጅመንት አካላትና ባለሙያዎች ሚዲያው በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሻለ ተቀባይነት እንዲያገኝ እያደረጉ ላሉት አስተዋጽኦ የውይይቱ ተሳታፊዎች አመስግነው ይህ ትጋት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

  በጣቢያው የሚተላለፉ ፕሮግራሞች ጥራትና ጠቀሜታቸው ጊዜውን የሚመጥን እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት ያሉት ተወያዮቹ ለዚህም የጋዜጠኞችና የባለሙያዎች አቅም ግንባታ ስራ መሰራት አለበት ብለዋል።

  የውይይቱ ተሳታፊዎች በተለይም የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በተለያዩ ተቋማት በኃላፊነትና በባለሙያነት እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን በሙያቸው ጣቢያው የሚፈልገውን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

  የወላይታ ቴሌቪዥን ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኤልያስ አዋቶ ያለንን ትልቅ አቅም በመጠቀም ጣቢያውን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቶ ወዲያው ወደስራ መግባት አለበት ብለዋል።

  በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት ጣቢያው ራሱን እንዲችል አቅም ለመፍጠር የሚያስችል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

  የወላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ ስራ አስኪያጅ አቶ ሴባ ናና በበኩላቸው ጣቢያው ብዙ ተግዳሮቶችን እየተጋፈጠ አሁን ወደደረሰበት ደረጃ መድረሱን ጠቁመው ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመስግነዋል።

  ጣቢያው ከዚህም የበለጠ ተመራጭ እንዲሆን የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን ያሉት አቶ ሴባ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በእኔነት መንፈስ እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ አቅርበዋል።

  በመጨረሻም ጣቢያውን በይዘት ዘርፍ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ ቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

  በመለስ ኦልኮ

  November 5, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ በ79 ሄ/ር መሬት ላይ በወጣቶች እየለማ ያለ የጤፍ ሰብል በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት ወጣቶች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው በሀገራቱ ኢኮኖሚ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚችል አቅም አላቸው ብለዋል። የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበዉ ወጣት አዲሱ በለጠ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም በመጀመሪያ ዲግሪ መመረቁን ጠቁሟል።ከሌሎች አቻ ጓደኞቹ ጋር በመሆን በመንግስት ተቋም ተቀጥሮ መስራት ውጤታማ እንደማያደርግ በመረዳት በ3 ነጥብ 5 ሄ/ር መሬት ላይ ጤፍ እያለሙ መሆኑን ተናግሯል። ወጣቶች ጊዜና ጉልበታቸውን በአግባቡ በመጠቀም በተገኘው የስራ አማራጭ ከራሳቸው አልፈው ሀገርን እና ህዝብን ማገልገል ይገባቸዋል ብሏል። በወላይታ ዞን በ1050 ሄ/ር መሬት ላይ 2ሺ700 ወጣቶች በልዩ ልዩ የግብርና ስራዎች ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተጠቁሟል።

  October 31, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በመሐል ቀበሌ በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ምርቶች ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ እና የዘርፉ ባለሙያዎች ባደረጉት ክትትል በሰው ጤና ላይ ጉዳት ከማድረሱ አስቀድሞ ማስወገድ እንደተቻለ ነው የተገለጸው። የመሀል ቀበሌ ንግድ እና ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑ አቶ ነዋዝ ናስር እንዳሉት የምግብ ውጤቶች ፣ የለስላሳ መጠጦች ፣ የሴቶች ውበት መጠበቂያ እና የታሸጉ የህፃናት ምግቦች መወገዳቸውን አስረድተዋል። ኃላፊው አያይዘው በሰዎች ጤና ላይ ካንሰርን ጨምሮ የተለያዩ ችግሮችን የሚያስከትሉ ምርቶች የገበያ ዋጋ ቢተመን ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጡ ቢሆኑም በማስወገዱ ተግባር መከላከል መቻሉን ገልፀዋል። በቀጣይም ህብረተሰቡ የፋብሪካ ምርቶችን ሲጠቀም የተመሰረተበትን ቀን እና አገልግሎት የሚያበቃበትን ቀን በአግባቡ እንዲያጣራም አቶ ነዋዝ መልክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል የዘገበው የከተማው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነዉ፡፡

  October 31, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በአረካ ከተማ ገበያ ማዕከል ጥቅምት 12/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 2:30 በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ በመንግስት እና በህብረተሰብ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የዞን ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት አካሄዱ።

  ወ/ሶዶ፥-ጥቅምት 14/2015 ዓ/ም(ወቴቭ) በአረካ ከተማ ገበያ ማዕከል በተከሰተው እሳት ቃጠሎ በመንግስትና በህብረተሰብ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የወላይታ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ፥ የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳደሪ አቶ መስፍን ዳዊት፥ የወላይታ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፥የወላይታ ዞን የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛን ጨምሮ ለሎች ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው ዕለት ጉብኝት ያካሄዱ ሲሆን በተከሰተው ድንገተኛ እሳት አደጋ ለተጎዱ ህብረተስብ ክፍሎች ማዘናቸውን ገልጸዋል፡

  October 24, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በአረካ ከተማ ገበያ ማዕከል ጥቅምት 12/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 2:30 በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ በመንግስት እና በህብረተሰብ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የዞን ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት አካሄዱ።

  ወ/ሶዶ፥-ጥቅምት 14/2015 ዓ/ም(ወቴቭ) በአረካ ከተማ ገበያ ማዕከል በተከሰተው እሳት ቃጠሎ በመንግስትና በህብረተሰብ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የወላይታ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ፥ የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳደሪ አቶ መስፍን ዳዊት፥ የወላይታ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፥የወላይታ ዞን የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛን ጨምሮ ለሎች ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው ዕለት ጉብኝት ያካሄዱ ሲሆን በተከሰተው ድንገተኛ እሳት አደጋ ለተጎዱ ህብረተስብ ክፍሎች ማዘናቸውን ገልጸዋል፡

  October 24, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ለሰልፈኞች ባስተላለፋት መልዕክት ኢትዮዽያ ህወሃት የሽብር ቡድን ከሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር የግል ጥቅም ፍላጎት ለማሟላት በመፈለግ የሀገራችንን ሉአላዊነት የደፈረ ከሃዲ ቡድን ነው ብለዋል።

  የህወሃት ሽብር ቡድን ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ድጋፍ በማድረግ የሀገራችንን ሉአላዊነት ለመድፈር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ብለዋል። ህወሃት የሽብር ቡድን ሶስተኛ ዙር በከፈተው ጦርነት ሀገራችንን ያልተፈለገ ዋጋ እያስከፈለ ያገኛል ያሉት አቶ አክሊሉ ድርጊቱን በመቃወም በቅርቡ የትግራይ ተወላጆች ያካሄዱትን ሰልፍ አውስተው በማመስገን ይህ አብሮነት የሀገራችንን ከሉአላዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ነዉ ብለዋል ።

  ከ16 የወረዳና 7 ከተማ አስተዳደር የተሳተፉ ሰልፈኞችን አመስግነው ሀገራችን በፈተና ውስጥም ሆና የህዳሴ ግድብ ሁለት ታርባኖች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጩ ማድረግን ጨምሮ አንኳር የልማት ስራዎች ለሀገራችን በለውጡ የመጡ ትልቅ ተስፋዎች ናቸዉ ብለዋል። የወላይታ ህዝብ ከሌሎች ወንድም የሀገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አጽንቶ ማቆየቱንና ያወሱት ዋና አስተዳዳሪው አሁን ሀገራችን በገጠማት ፈተናም እስከ ግንባር ድረስ በመዝመትና በሚፈለገው ሁሉ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል ።

  የሀገራችን ሉአላዊነት ለማረጋገጥ በግምባር በጀግንነት እየተፋለመ ለሚገኘው ለጀግናው የኢፌዴሪ መከላከያና የፀጥታ ሀይሎቻችን ያለንን አድናቆት፣ ክብርና አጋርነታችንን እየገለፅን የምናደርግላቸዉን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። የወላይታ ህዝብ ከሌሎች ወንድም የሀገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አጽንቶ ማቆየቱንና ያወሱት ዋና አስተዳዳሪው አሁን ሀገራችን በገጠማት ፈተናም እስከ ግንባር ድረስ በመዝመትና በሚፈለገው ሁሉ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል ።

  ሰልፈኞቹ የትግራይ ሕዝብ ወገናችን ነዉ፤ ጁነታዉ ጠላታችን ነው!፣ህወሐት የችግሩ ምንጭ ነው! በሉዓላዊነታችን አንደራደርም!፣ ለዘላቂ ሠላም ህወሐት ትጥቅ ትፍታ!፣ የትግራዋይ ልማትና ብልጽግና የሚረጋገጠው ከእኛ ከወገኖቹ ጋር ነው! እና በሰብአዊ ዕረዳታ ስም ጣልቃ ገብነቱ ይቁም! የሚሉ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡

  October 31, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የወላይታ ዞን ኅብረት ስራ ጽ/ቤት የ2015 የሴክተር ጉባኤና የወላይታ ዳሞት ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኢንዱስትሪ ምስረታ ፕሮግራም በወላይታ ጉታራ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

  የወላይታ ዞን ኅብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሠላማዊት ሳሙኤል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት አንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀምና አርሶ አደሮችን በማስተባበር የተሻለ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

  ለዞኑ አርሶ አደር ምርጥ ዘርና የአፈር ማዳበሪያ የማዳረስና ገበያን የማረጋጋት ስራዎች የጽ/ቤቱ ቁልፍ ተግባራት ናቸው ያሉት ወ/ሮ ሠላማዊት በ2014 በጀት ዓመት 500 የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራትን በመመስረት የሚታይ ተግባር መፈጸሙን ተናግረዋል። የዞኑ መንግስት ሰራተኞች በማህበር ተደራጅተው የፍጆታ ዕቃ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ከዞኑ አስተዳደር ጋር በመተባበር አባላቱ የካፍቴሪያ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

  በላፈው በጀት ዓመት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባሳየው ቁርጠኛ አቋም በግለሰቦች ተመዝብሮ የነበረውን ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ የወላይታ ዳሞታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ሃብት ማስመለስ መቻሉን ወ/ሮ ሠላማዊት ገልጸዋል። የኅብረት ሥራ ማህበራትን ማጠናከር ለኢንዱስትሪ ሽግግር መሠረት መሆኑን ኃላፊዋ ተጠቁመዋል።

  በዞኑ የምግብ ዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ ለማቋቋም ወደ ስራ እንገባለን ያሉት ወ/ሮ ሠላማዊት በዞኑ አስተዳደር ጠንካራ ድጋፍና በወላይታ ዳሞታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዪኒየን አባል አርሶ አደሮች ቁርጠኝነት ውጥናችንን ስኬታማ እናደርጋለን ብለዋል።

  በጉባኤው የጽ/ቤቱ የ2014 አፈጻጸምና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግና በወላይታ ዳሞታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን የሚያስገነባው ዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ ረቂቅ ዕቅድ ውይይት ተካሂዶ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

  የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የወላይታ ዞን ኅብረት ስራ ጽ/ቤት ስራ ኃላፊዎች እና ዳሞታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ቦርድ አመራሮች በጉባኤው እየተሳተፉ ይገኛሉ።

  በመለስ አልኮ

  October 18, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ጀግኖች አባቶቻችን በደማቸውና በአጥንታቸው ያስረከቡንን ሰንደቅ ዓላማ ለአንድነታችንና ለህብረታችን ምሳሌ ነው- የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ።

  የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ለበዓሉ ታዳሚያን ባስተላለፉት መልዕክት ጀግኖች አባቶቻችን በደማቸውና በአጥንታቸው ያስረከቡንን ሰንደቅ ዓላማ ለአንድነታችንና ለህብረታችን ምሳሌ ነው ብለዋል።

  የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የትላንት የጋራ ታሪካችን፣ የዛሬ ጥረታችንን እና የነገ ተስፋችንን እንዲሁም ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጣምሮ የያዘ የክብራችን እና የማንነታችን አርማ ነው፡፡ የሰንደቅ ዓላማ በዓል ስናከብር ሀገራችንን የገጠማትን የውጭና የውስጥ ፈተናዎችን ለመሻገር በባንድራች ጥላ ስር በህብረትና በአንድነት መቆም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ሰንደቅ ዓላማችን የማንነታችን መገለጫ በመሆኑ ሁሉም የሀገራችን ዜጎች ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር መስጠት አለበት ብለዋል።

  የበዓሉ ታዳሚያን በመንግስት ቅድሚያ ተሰጥቶ የታቀዱ ዕቅዶችን ለህዝብ ጥቅም በፅናትና በትጋት ለመፈጸም ቃል መሃል በወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት አቶ መርደኪዮስ ዴአ መሪነት ገብተዋል።

  በበዓሉ የወላይታ ዞን ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ባለሙያዎች እና የዞኑ ፀጥታ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

  በመለስ ኦልኮ

  October 17, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ መክረዋል።

  በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የወላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ የምንመኘው ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ሠላም እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።

  የትግራይ ህዝብ ለዚች ሀገር ያበረከተው አስተዋጽኦ ቀላል የማይባል አይደለም ያሉት አቶ ሳሙኤል የትግራይ ተወላጆች አሸባሪው ህወሓት ትንኮሳን ማውገዝ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

  አሸባሪው ህወሓት ለተከታታይ ሶስት ጊዜ በሀገራችንና በህዝባችን ላይ ጦርነት መከፈቱን ያስታወሱት አቶ ሳሙኤል ይህን ድርጊት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እያወገዘ ይገኛል ብለዋል።

  ሠላም ይበጀና፤ ጦርነት አውዳሚ ነው ያሉት አቶ ሳሙኤል የፖለቲካ ልዩነትና ስብራት አዋጪ መንገድ የሠላምን መንገድን መከተል ብቻ እንደሆነም ገልጸዋል።

  መንግስት አሁንም ብሆን ለሠላም በር ከፍት አድርጎ እየጠበቀ ይገኛል ያሉት አቶ ሳሙኤል አሁንም አሸባሪው ህወሓት ትንኮሳውን መቀጠሉንም አስረድተዋል።

  አሸባሪው ህወሓት አሁንም ከፍተኛ የሰብዓዊ ጥሰት እየተፈጸመ ይገኛል ያሉት አቶ ሳሙኤል ለዚህ መላው የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ለሀገራችን አንድነት የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

  በሁሉም ኢትዮጵያ ሀገራት የሚገኙ ከትግራይ ክልል ተወላጆች ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ሳሙኤል ይህም ለትግራይ ተወላጆች የባይታዋርነት ስሜት እንዳይሰማቸው የሚደረግ የምክክር መድረክ እንደሆነም ገልጸዋል።

  ከጦርነት ትርፍ የለም ያሉት አቶ ሳሙኤል ሠላምን ለማስጠበቅ ህዝቡ የሠላም ባለቤት መሆን ይገባል ሲሉም አሳስበዋል። አሸባሪው ወደ ሠላምና ድርድር እንዲመጣ ማውገዝና መቃወም ያስፈልጋል ብለዋል።

  የሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን አለማየሁ በበኩላቸው ሠላም ከሌላ የትኛውም እንቅስቃሴን ማድረግ አይቻልም ብለዋል። ህዝባችን አንድ ነው ያሉት አቶ ተመስገን የህወሐት ክፉ ድርጊት የትግራይ ህዝብ ማውገዝ አለበትም ብለዋል።

  የዞኑ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት

  October 14, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • "ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሃነታችን መገለጫ፤ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው!" በሚል መሪ ቃል የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ጥቅምት 7/ 2015 ዓ.ም በድምቀት ይከበራል

  ወላይታ ሶዶ:ጥቅምት 2/2015 (ወቴቪ) በአገራችን ለ15ኛ ጊዜ "ሰንደቅዓላማችን የብዝሃነታችን መገለጫ፤ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው!" በሚል መሪ ቃል ሰኞ ጥቅምት 7 ቀን የሚከበረውን የሰንደቅዓላማ ቀን በዓል አስመልክቶ በድምቀት ማክበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ የበዓሉ አከባበር አስተባባሪ ኮሚቴ ውይይት እያካሄደ ነው።

  በዓሉ በዞን ማዕከል፣ በወረዳና ከተማ አስተዳደር ማዕከሎች ሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች በተገኙበት በቀን 04/02/2015 ዓ.ም ሰንደቅ ዓለማ ዙሪያ በፓናል ውይይትና በሌሎች ዝግጅቶች እንደሚከበር ከወላይታ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

  የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ካሰች ኤልያስ በዓሉን በድምቀት ለማክበር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅ አስረድተዋል። ዘገባው የወላይታ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው፡፡

  October 12, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአፋር፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ከጋምቤላ ክልሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር እየተወያየ ይገኛል።
  ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንደገለፁት፤ በአገራዊ ምክክር ሒደት ውስጥ ሁሉም ክልልና ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እንዲሳተፉ ለማድረግ የተጠናከረ ተግባር እየተከናወነ ነው።

  ኮሚሽኑ አገራዊ ምክክሩን በይፋ ከመጀመሩ በፊት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል።
  በዛሬው እለትም ከአፋር፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ከጋምቤላ ክልሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። ኢትዮጵያ የትኛውንም ተቃርኖና አለመግባባት ለመፍታት በርካታ እሴቶች ያሏት ሀገር መሆኗንም የተናገሩት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ለአገራዊ ምክክሩ ስኬት የሁሉም ዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።

  ህዝቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ለህዝብ ቅርብ የሆኑ አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። ዛሬ ከሶስቱ ክልል የህዝብ ተወካዮች ጋር የሚደረገው የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክም የዚሁ አላማ አንዱ አካል ነው ብለዋል።
  ተወካዮቹ ስለ አገራዊ ምክክር አስፈላጊነትና ሂደት የአካባቢያቸውን ማህበረሰብ በማንቃትና በማስገንዘብ ረገድ በሀላፊነት መስራት እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።
  በዋናነት በአገራዊ ምክክሩ ሁሉም የሚመለከተው አካል እንዲሳተፍ ለማድረግ እየተከናወነ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ኮምሽነሩ አረጋግጠዋል።

  ኮሚሽኑ ወደ ህዝቡ ወርዶ ከማወያየቱ በፊት ዛሬ የሚገኘው የሀሳብ ግብዓት በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ነው ያሉት። በውይይት መድረኩ የሶስቱም ክልሎች የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጀቶች ተገኝተዋል።

  October 10, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • "መንግስት የሴቶችን ትምህርት ለመደገፍ ያወጣውን ግብ እውን ለማድረግ ተማሪዎች የያዙትን ዓላማ ለማሳካት ጠንክሮ መማርና መትጋት አለባቸው"፡- አቶ ዮሐንስ በየነ

  ሊንክ ኢጁኬሽን ኢትዮጵያ በሌ ሐዋሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙ ከ1 ሺህ 3 መቶ በላይ ለሴት ተማሪዎች የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
  በድጋፉ የተገኙ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ በየነ እንዳሉት ሊንክ ኢጁኬሽን ኢትዮጵያ በዞናችን ላለፉት 14 ዓመታት በትምህርት ስራ ላይ ትልቅ አሻራን ያሳረፈ ትልቅ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
  ድርጅቱ መንግስት ትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ አቅዶ በምሰራበት ሂደት ላይ ያለውን ክፍተቱን በማሟላት ሲሰራና ሲደግፍ እንደቆየም አስታውቀዋል።
  የተማሪዎች መጠነ ማቋረጥና መደገም ላይ የነበሩ ችግሮችን በማጥናት ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ድርጅቱ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
  በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩና ትምህርታቸውን እንዲማሩና እንዲከታተሉ ዘርፈብዙ ድጋፍ በማድረጉ በዞኑ አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል።
  ተማሪዎች ድርጅቱ ያበረከተውን ድጋፍ በተገቢው በመገንዘብ ግቡን ለማሳካት ጠንክሮ መማርና መትጋት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
  ከዚህ በፊት የሴት ተማሪዎች ቁጥር እጅግ አነስተኛ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዮሐንስ ዛሬ ላይ የሴት ተማሪዎች ቁጥር ከወንድ መብለጡንም ጠቅሰዋል።
  የሴት ተማሪዎች ቁጥርን ከፍ ማድረግ ብቻውን ግብ አይደለም ያሉት አቶ ዮሐንስ ትምህርታቸውን በአግባቡ ተከታትለውና ተምረው ዓላማቸውንና ግባቸውን ለማሳካት በቅተው መውጣት እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
  አቅዶ መስራት፣ ለዓላማ መትጋት፣ ለትምህርት ጊዜን የመስጠት እና ትምህርትን እንደሁለተኛ ስራ አለመያዝ ከተማሪዎች የሚጠበቅ ስራ ስለሆነ ተማሪዎች መልካም አጋጣሚዎችን መጠቅም እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
  አሁን ያለንበት ጊዜ ስራ የምንፈልግበት ሳይሆን ስራ የምንፈጥርበት ጊዜ ላይ ስለምንገኝ ተማሪዎች ከወዲሁ መዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

  የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደሴ ኩማ በንግግራቸው ድርጅቱ እንደወላጅ አባትና እናት በመሆን ለሴት ተማሪዎች ሁሉ አቀፍ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
  በዞኑ የተሻለና ጎበዝ ተማሪን ለማፍራት በኢኮኖሚ በመደገፍና የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ አቅም የማጎልበት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።
  ድርጅቱ በዞኑ ለሚገኙ ለአጠቃላይ ሱፐርቨይዘሮች በአስተዳደር ሲስተም፣ በማስተማር ስነ-ዜዴና በስትራቴጂክ ዕቅድ አቀዳድ ላይ አቅም የማጎልበት ስልጠና መስጠቱንም ገልፀዋል።
  እንደኃላፊው አገላለጽ ድርጅቱ በዞን ደረጃ አጠቃላይ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ውጪ በማውጣት 147 ትምህርት ቤት የሚገኙ ከ61 ሺህ በላይ ሴት ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
  የዞኑ ትምህርት መምሪያው በሚያስፈልገው ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ከጎኑ እንደምቆምና ከመንግሥት የሚጠበቀውን ሃላፊነት ለመውጣት የድርሻውን እንደሚወጣም አረጋግጠዋል፡፡
  የበሌ አዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ስሞዖን ሳፓ ድርጅቱ እንደኪንዶ ኮይሻና በሌ አዋሳ ከተማ መዋቅሮች ላላፉት 11 ዓመትት ድርጅቱ የትምህርት ስራን ሲያሳልጥ እንደቆየም አስታውቀዋል።
  ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስን ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰው ለተደረገው ድገፉ በወረዳው ህዝብና አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል።

  በሰይፉ ሳሙኤል እና ከዞኑ ህዝብ ግንኙነት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተወሰደ

  October 6, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የዎላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ ቦርድ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሥራ አስኪያጁ ወንድሙ ሳሙኤል ከመስከረም 25/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ እንዲታገድ እና ከኃላፊነት እንዲነሳ ወስኗል።

  ቦርዱ ከአስቸኳይ ስብሰባ በሁዋላ መግለጫ የሰጠ ሲሆን የቦርድ ፕሬዝዳንት እና የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ መስፍን ዳዊት ቦርዱ ሥራ አስኪያጁን ከኃላፊነት እንዲነሳ ሲወስን 3 መሠረታዊ ጥፋቶችን ማግኘቱን አስታውቋል።

  1ኛ. የስም ለውጥ በተመለከተ የተጻፈው ደብዳቤ የቦርድ እና የሥራ አስፈጻሚ እውቅና የለውም
  2ኛ. ማስተካከያ ተብሎ የተጻፈው ደብዳቤ በራሱ ስህት ያለበት ነው
  3ኛ. ከዚህ ቀደም የነበረውን ስህተት የማረም ዕድል አለመጠቀሙ እና ክለቡ ደጋፊ የለውም ከማለቱ ጋር ተያይዟል።

  በግለሰብ ተነሳሽነት የተጻፈው ደብዳቤ በህዝብ ዘንድ ጥያቄ መፍጠሩን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ሰፊውን የወላይታ ህዝብ እና የክለቡን ደጋፊዎች ይቅርታ ጠይቀዋል። የክለቡ መጠሪያ ዎላይታ ዲቻ ሆኖ እንደሚቀጥል የገለፁት አቶ መስፍን በቀጣይ በቦርዱ ፕሬዝዳንት ፊርማ ለእግር ኳስ ፌደሬሽን የስም ለውጥ መሻሪያ ደብዳቤ እንደሚጻፍ በመግለጫቸው ተናግረዋል።
  በሥራ አስኪያጅ ቦታ በግዚያዊነት የህዝብ ግንኙነት ሥራ ሲሠሩ የነበሩት አቶ ምትኩ ሀይሌ መወከላቸውንም አስታውቀዋል።

  በተመስገን ተስፋዬ

  October 6, 2022

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • መላው ኢትዮጵያዊያን በጋራ የጀመሩትና ለሀገራችን የባንድራ ፕሮጀክት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የተሰማኝን ላቀ ያለ ደስታ በራሴና በዞኑ አስተዳደር ስም እገልጻለሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!

  የግድቡን ግንባታ ሰርተን እንዳናጠናቅቅ በርካታ ተግዳሮቶች የገጠሙን ቢሆንም በአይበገረነት መንፈስ በአሸናፊነት ስሜት አባይ የእኔ ነው በማለት በህብረ ዝማሬ ከዳር እስከ ዳር ተነቃንቀን አይችሉም ብለው በንቀት የተመለከቱንን በተባባረ ክንዳችን በማሳፈር ለዛሬው ድል በቅተናል።
  እኛ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት መንፈስ ቆርጠን በመነሳት ታሪክ መስራት እንደሚንችል ያሰመሰከረንበትና ከአድዋ ድል ቀጥሎ የዚህ ትውልድ ሁነኛ ገድል የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለኢትዮዮጵያዊን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የይቻላል መንፈስን ዳግም ያጎናፀፈ ልዩ ገፀ በረከት ነው።
  የወላይታ ሕዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወንድም ህዝቦች ጋር በመሆን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከታወጀበት ማግስት ጀምሮ ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙት እስከ ከፍተኛ ባለሀብት፣ ከመንግስት ሰራተኛ እስከ ጡረተኛ፣ ከነጋዴ እስከ አርሶ አደር ከአስተማሪ እስከ ተማሪ ቦንድ በመግዛትና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ግድቡ ለዚህ ደረጃ እንዲደርስ የበኩሉን ድርሻ ተጫውቷል።
  አንዳንድ የሀገራችን ለውጥና ዕድገት የማያስደስታቸው የውጭ ሀገራትና የአለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ ኢትዮጵያ ግደቡን እንዳተገድብ ብርቱ ተቋውሞ ያሰሙ ቢሆንም እኛ ኢትዮጵያዊያን ያንን አመለካከት ቀልብሰን አዲስ ታሪክ እየጻፍን የሚንገኝ ጀግና ህዝቦች ስለሆነን ቀጣይም መላው የዞናችን ህዝብ ለሀገራችን ሰላም የቻለውን ሁሉ በማድረግ ለሀገራችን ሉአላዊነትና ብልጽግና በትጋት እንዲቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ።
  የዛሬው የሕዳሴ ግድብ ስኬት እኛ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ከተነሳን ከባድ የሚባሉ ተግዳሮቶችን ማሸነፍ እንደሚንችል ትልቅ ትምህርት ያገኘንበት በመሆኑ ሁሉም የዞናችን ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊን ጋር በመሆን በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን የገጠማትን ተግዳሮት ለመሻገር በጋራ እንዲነሳ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
  በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር! እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

  August 18, 2021

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የእውቅና ሽልማቱ የበለጠ እንዲያገለግሉ አቅም የፈጠረና አደራ ጭምር መሆኑ የተገለጸው። ይህ ውጤት ለአካባቢው ማህበረሰብና ለዩኒቨርስቲው በትጋትና በታማኝነት በመሥራት ያመጡት ውጤት በመሆኑ ለዞናችን ኩራት፣ ዝና እና ስኬትን ያጎናጸፈ እጅግ የላቀ ገጸ በረከት መሆኑን የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር እንድርያስ ጌታ ተናግሯል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ከአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በአመራር ብቃት 1ኛ በመውጣት እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከአጠቃላይ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች 2ኛ በመውጣት የተመዘገበው ውጤት የዞናችንም ኩራት በመሆኑ ይህ ዕውቅና ሽልማት ተሰጥተዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር እንድርያስ ናቸው። ዋና አስተዳዳሪው ዩኒቨርስቲው ለማህበረሰቡ የያዛቸው ልማቶችን በማፋጠንና በውስጥ የነበሩ ችግሮችን በማስተካከል ይህንን ትልቅ ውጤት ያለውን ሥራ በመስራታቸው የሥራ አመራሩና ቦርዱ እጅግ ሊመሰገኑ እንደሚገባ አስረድተዋል። ዩኒቨርስቲው በቴክኖሎጂ የተደገፈና በዕውቀት የሚመራ ነውና ጥራት ያለውን ትምህርት ተደራሽ በማድረግ ለማህበረሰቡ አገልግሎት ላይ የዋለ ግዙፍ ዩኒቨርስቲ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። ፕ/ር ታከለ ታደሰ ጠቅላይ ሚኒስተራችን በሀገር ደረጃ ያስጀመሩትን አረንጓዴ አሻራን ተሞክሮ በየቦታው በድምቀት በማስፋፋት እየታየ ያለውን ዕድገት መምጣቱንና ዩኒቨርሲቲው ችግሩን በቀላሉ ሊፈታ የቻለና የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ ያለ ተቋም እንደሆነም ገልጸዋል። ዩኒቨርስቲው በማህበረስብ አግልግሎትና በሌላም መንገድ የሠራቸውን ሥራዎችና የያዙዎቸውን ዕቅዶች እጅግ የሚያኮሩ ናቸው ብለዋል። እነዚህ ሥራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉና ዩኒቨርስትው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም አካላት የበኩላቸውን አስተዎፅኦ ሊያደጉ እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህ ውጤት የመላው የወላይታ ህዝብ ነው እንጅ ብቻዬ ሰርቼ ያመጣሁት አይደለምና በጋራ ሠርተን ወላይታ አሁን ያለችበትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት ዘውትር ተግተን ሠርተን ከዚህ የበለጠ ውጤት እናስመዝግባለን ያሉት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ናቸው። ለህዝቡ አገልግሎት ላይ እንዲውል እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን ለማሳለጥ የእውቅና ሽልማቱ አቅም እንደሚፈጥና ህዝባችንን የበለጠ እንድናገለግል የሚያነሳሳና አደራም ጭምር እንጂ ወደኋላ የሚጎትት እንዳይደለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ አስረድተዋል ። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ ለውጤቱ ትልቅ ሚና ለተጫወቱት ለዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት፤ ለማኔጅመንት አካላትና ለዩኒቨርስቲው ልዩ የዕውቅና እና ሽልማት አበርክተዋል፡፡ በፕሮግራሙ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር እንድርያስ ጌታን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግለዎችና የኃይማኖት አባቶች እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰን ጨምሮ ማኔጅመንት አካላት ተገኝተዋል

  August 18, 2021

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • በወላይታ ዲስትሪክት የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ አገልግሎት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ የዲስትርክት ባለሰባት ፎቅ ህንፃ ሊገነባ ነው

  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እና የደቡብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክንፈ ነጋሽ ለደቡብ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለወላይታ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ባለ ሰባት ፎቅ የቢሮ ህንጻ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ።
  ፕሮጀከቱ በአገር ደረጃ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማዘመን የተያዘው ዕቅድ አካል ሲሆን በተግባራትም 80 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ፣ 59 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ፣ 13 ትራንስፎርመር የመልሶ ግንባታና 20 አጋዥ ትራንስፎርመር ዝርጋታም ይደረጋል ።
  በዚህም የአከባቢው ህብረተሰብ በቀጥታ ተጠቃሚ ሲሆን ዘርፋን ለማዘመንም ፉይደዉ የጎላ ነው ብለዋል ።
  የኢትዮጵያ ኤሌ/አገ/ሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ በዎላይታ ሶዶ ከተማ የኢትዮ ኤሌክትሪክ ወላይታ ዲስትሪክት ባለሰባት ወለል የአስተዳደር ህንጻና ስድስት ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይልና ግንባታ መልሶ የማልማት ፕሮጀከት መሠረተ ድንጋይ መቀመጡ ታውቀዋል።

  August 18, 2021

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳና ሌሎች የክልሉና የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በወላይታ ዞን በሆብቻ ወረዳ አባያ ቢሳሬ የሚገኝ የግለሰብ ማሳን ጎብኝተዋል።

  ግለሰቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማርተው ውጤታማ መሆን ችሏል።
  በአንድ ወር ውስጥ 450 ሄ/ር በላይ ማሳ በሰብል እንዲሸፈን መደረጉን ኢንቨስተር አቶ ዳኜ ዳባ ገልጸዋል።
  አቶ ዳኜ አያይዘውም በሁለት መቶ ሄ/ር ማሳ ሎሚ፤ ብርቱካን እና ሙዝ ችግኞችን ለመትከል መዘጋጀቱንም ተናግረዋል።
  በመኸር ወቅት አድንጎሬ/ቦሎቄ እና ማሾ ዘር በማሳው ተሸፍኗል ያሉት አቶ ዳኜ ማሾ ምርት ለውጪ ሀገር Export ለማደረግ ተጠናክሮ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
  ኢንቨስተሩ በስሩ ከ250 በላይ ጊዜያዊና ቋሚ ሰራተኞች የሥራ ዕድል መፈጠር መቻሉን ጠቅሰው በዚህም ከአከባቢውና ከሌሎች አጎራባች ዞኖች የተወጣጡ ሰራተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።
  አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ 450 ሄ/ር በላይ ማሳ በዘር እንዲሸፈን የተደረገው ጥረት እጅግ የሚደነቅና ለሌሎች አርዓያ የሚሆን ተግባር መሆኑን የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ተናግረዋል።
  ይህ ተግባሩ ለሀገር እድገት በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠቅም በመሆኑ ሌሎች ኢንቨስተሮች የእሱን እንደምርጥ ተሞክሮ በመወሰድ ተጠናክሮ መሰራት እንደሚገባ አቶ እርስቱ አሳስበዋል።
  መሬትን ኢንቨስት ለማደረግ ብለው ተረክበው መሬትን በጾም እያሳደሩ ያሉ ግለሰቦች የማይሰሩ ከሆነ ለቀው ለሚሰሩ ኢንቨስተሮች ማስረከብ እንደሚገባና በዚህም ጉዳይ መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥጥሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ እርስቱ አሳስበዋል።
  ይህ ትልቅ ጅማሪ ስለሆነ ሊበረታታ የሚገባ እንደሆነ እና ችግሮች የሚያጋጥሙ ቢሆን እንኳ ለውጤት እስኪበቃ ድረስ የምችለውን ሁሉ እንደግፈዋለን ሲል ተናግረዋል።
  አቶ ደመቀ ኩኬ የወላይታ ዞን ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ በበጀት ዓመቱ የተጣለውን ግብ ለማሳካት ውስን የህዝብና የመንግስት መሬት ተረክበው ለውጤታማነት ለሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የባለሀብቶች ጥሩ ጅምር ወደ ሌሎቹም በማስፋት ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ዓላማውም በአጭር ጊዜ ዉስጥ መሬት ተረክበው ሙሉ በሙሉ ማልማት የጀመሩ ኢንቨስተሮችን ለማበረታታት እና ተሞክሮአቸውን ወደ ሌሎች ለማስፋት ያለመ ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል ።
  በጉብኝቱ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ፤ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች የክልሉና የወላይታ ዞን ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

  August 18, 2021

  | የወላይታ ዞን ዜና

 • ጊፋታ በዓል በወላይታ ብሔር ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ሲሆን አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበት የዘመን መለወጫ በዓል ነው፡፡
  በቀደመዉ ጊዜ በወላይታ አሮጌው ዓመት እየተገባደደ ሲሄድ የጨረቃንም ሆነ የከዋክብቶችን እንቅስቃሴ በጥልቀት በመመራመር የአዲሱን ዓመት መምጫ ቀን የሚለዩ ባህላዊ የዘመን አቆጣጠር ጠቢባን እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ጠቢባን በዓሉ እየተቃረበ ሲመጣ በንግሱ አማካሪዎች ወደ ቤተመንግስት ተጋብዘዉ ይመጣሉ፡፡
  ከዚያም ሌሊት ሌሊት እየወጡ የጨረቃን ኡደት መነሻ ለማወቅ የጨረቃን አራት ክፍሎች ማለትም (ፖኡዋ፣ጡማ፣ጤሯ እና ጎባና) በየትኛው ክፍል እንደሚውል የዓመቱን የቆጠራ ምልክቶች ይዘው መጥተው የሙሉ ጨረቃዋን ኡደት ተመልክተው ለንጉሱና ለአማካሪዎቹ ያበስራሉ፡፡ ከዚያም ኮከብ ቆጣሪዎቹ በዓሉ የሚከበርበትን ቀን በትክክል ለንጉሱ ከነገሩ በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፡፡ ቀጥሎም ንጉሱ የበዓሉን መቃረብ ለህዝቡ “በጫላ ኦዱዋ” (አዋጇ) በየገበያውና በየህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች እንዲነገር ሲያደርግ ህዝቡ ይህንን በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቀን ለሚከበረዉ ታላቅ በዓል በየፈርጁ ዝግጅቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
  ይህ በዓል በተለያዩ ዘመናት በደረሰበት ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ምክንያት ከፍተኛ ፈተና ውስጥ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ የወላይታ ህዝብና የዞኑ አስተዳደር ባደረጉት ብርቱ ጥረት ጊፋታ ወደ ቀድሞ ልዕልናሙ እየተመለሰ ይገኛል፡፡ ባለፉት 10 ዓመታት በዞኑ አስተዳደርና የቅርሱ ባለቤት በሆነዉ የወላይታ ህዝዝ ጥረት ለበዓሉ ዘላቂ ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ ይህን የማይዳሰስ ቅርስ ትዉልድ ተሸጋሪ ለማድረግ በርካታ ጥረቶች ተደርጓል፡፡ ከእነዚህም መካከል ቅርሱን የሰዉ ልጆች ወካይ ቅርስ አድርጎ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት እንዲ መዘገብ የሚሠራዉ ሥራ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
  ዋናዉ ዓላማ ቅርሱን በዓለም ቅርስነት ማስመዝገብ ብቻዉን ግብ እንዳል ሆነ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ተግባር ለቅርሱ ዘላቂ ጥበቃና እንክብካቤ ለማድረግ አቅደን ለምንሠራው ሥራችን የማይናወጥ መሠረት መጣል እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በመሆኑም ዘንድሮ ከሌላው ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን፣ከደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ፣ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከመምሪያችን ጋር ባደረግነዉ እንቅስቃሴ ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ አካላት በተሰጠን አቅጣጫ መሠረት የጊፋታን “Nomination File” በማዘጋጀት ከ March-21/2022 በፊት ለ”UNESCO” ለማቅረብ ግብ ጥለን እየሠራን እንገኛል፡፡
  ይህ ተግባር ሊሳካ የሚችለው እነዚህ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዉ የሥርዉን ሙሉ ኃላፊነት ተቀብለዉ እየሰሩ ባሉ ተቋማት ጥረት ብቻ ሳይሆን የሁሉንም የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የቅርሱ ባለቤት የሆነውን የወላይታን ህዝብ እንዲሁም የመላዉን ኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ ድጋፍ የሚጠይቅ ስለሆነ የእነዚህና የሚዲያ ተቋማት ድጋፍ እንዳይለየን እንጠይቃለን፡፡
  በመጨረሻም የ2014ዓ.ም የጊፋታ በዓል በከፍተኛ የሕዝብ ንቅናቄ በዞን፣በወረዳዎች እና በቀበሌያት ደረጃ በድምቀት እንደሚከበር ለማረጋገጥ እንፈልጋለን፡፡ ዮ ዮ ጊፋታ

  August 18, 2021

  | የወላይታ ዞን ዜና