| የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰንጠረዥ




| የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰንጠረዥ


| ስፖርት ዜና






  • የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ዳራሮ 'ዳራሮ' 5 ኪሜ ሩጫ በዲላ ከተማ ተካሂዷል። በሩጫው የከተማው ነዋሪዎች፣ የጤና ስፖርት ቡድን አባላትና በአካባቢው የሚሰለጥኑ ታዳጊ አትሌቶች ተሳትፈዋል። በወድድሩ ከወንዶች ሳሙኤል ገናሌ፣ አለማየሁ አለሙ እና ዘላለም አማዶ ከአንደኛ እስከ ሦሥተኛ ድረስ ያለውን ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ ሲሆን ከሴቶች አዛለች አለማየሁ፣ ለምለም ደሳለኝ እና መድኃኒት ዘሩ ከአንደኛ እስከ ሦሥተኛ ድረስ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቅቀዋል። ለአሸናፊዎቹ የሜዳሊያና ገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

    January 28, 2023

    | ስፖርት





  • በቻን ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዘጋጇ አገር አልጄሪያ 1 ለ 0 ተሸነፈ በሰባተኛው የአፍሪካ አገራት እግር ኳስ ሻምፒዮና(ቻን) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአልጄሪያ አቻው 1 ለ 0 ተሸንፏል። በኔልሰን ማንዴላ ስታዲየም በተደረገው የምድብ አንድ ጨዋታ አይሜን ማሂኡስ በ52ኛው ደቂቃ ለበረሃዎቹ ቀበሮዎች የማሸነፊያ ግቧን አስቆጥሯል። የ25 ዓመቱ አጥቂ በውድድሩ ላይ ሁለተኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል። ውጤቱንም ተከትሎ የቻን አዘጋጅ አልጄሪያ በስድስት ነጥብ ጥሎ ማለፏን የተቀላቀለች የመጀመሪያ አገር ሆናለች። በአንጻሩ በሁለት ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ ያገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ የቤት ስራው ከባድ ሆኖበታል። ዋልያዎቹ ወደ ጥሎ ማለፉ ለመግባት በመጨረሻ የምድብ ጨዋታቸው ሊቢያን ሁለት እና ከዛ በላይ የግብ ልዩነት አሸንፋ ሞዛምቢክን በአልጄሪያ መሸነፍ አለባት። በምድብ አንድ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ሞዛምቢክ ሊቢያን 3 ለ 2 አሸንፋለች። ውጤቱንም ተከትሎ ሞዛምቢክ ነጥቧን ወደ አራት ከፍ አድርጋለች። በአንጻሩ ሊቢያ ሁለተኛ ሽንፈቷን ማስተናገዷን ተከትሎ በቻን ውድድር ከምድቧ የወደቀች የመጀመሪያ አገር ሆናለች። በምድብ አንድ የመጨረሻ ጨዋታዎች የፊታችን ቅዳሜ ጥር 13 2015 ዓ.ም የሚካሄዱ ሲሆን ኢትዮጵያ ከሊቢያ፤ አልጄሪያ ከሞዛምቢክ በተመሳሳይ ከምሽቱ 4 ሰአት ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ኢዜአ በዘገባው አትቷል።

    January 18, 2023

    | ስፖርት





  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት በካሳብላንካ የሚገኘውና በክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሥም የተሰየመውን ስታዲየም በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

    በጉብኝቱ ወቅት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ባደረጉት ንግግር ይህ በይድነቃቸው ተሰማ የተሰየመው ስታዲየም ትልቅ ትርጉም ያለው እና ለቡድናቸው አባላት የሚያስተላልፈው ቁም ነገር ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል። የቡድኑ አባላትም የ30 ሰከንድ ጭብጨባ በማድረግ ለአቶ ይድነቃቸው ተሰማ ያላቸውን ክብር ገልፀዋል።

    በስታዲየሙ መግቢያ ላይ ስለ ስታዲየሙ በፍሬንች እና አረብኛ ቋንቋዎች አጭር መግለጫ የተቀመጠ ሲሆን '' እ.ኤ.አ በ1988 በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው 16ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወቅት በሞሮኮ ንጉሥ ሐሰን ዳግማዊ በተሰጠ መመርያ ይህ ስታዲየም ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ይድነቃቸው ተሰማ ሥም እንዲሰየም ማርች 1988 ላይ ተወስኗል። '' የሚል መግለጫን ይዟል።

    ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ እግር ኳስ እድገት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆኑት ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አመዛኙ የህይወት ዘመናቸውን ባሳለፉበት እግር ኳስ በተጫዋችነት ፣ አሰልጣኝነት እና አመራርነት እ.ኤ.አ በ1987 ህልፈተ ሕይወታቸው እስከተሰማበት ጊዜ ድረስ ከፍተኛ አበርክቶ የነበራቸው ታላቅ የእግር ኳስ ሰው ነበሩ።

    January 10, 2023

    | ስፖርት





  • አርባምንጭ ከተማ በአሰልጣኝ ቡድን አባላቱ ላይ ለውጦች አድርጓል

    የአርባምንጭ ከተማ ቦርድ ባደረገው ስብሰባ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት የስንብት እና የሹመት ውሳኔዎችን አሳልፏል።

    በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ በድጋሚ አድገው እየተሳተፉ ካሉ ክለቦች መካከል አንዱ አርባምንጭ ከተማ ነው።

    2011 ክረምት ወር ላይ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን በመቅጠር የከፍተኛ ሊግ ተሳትፎውን ከሊጉ ከወረደ በኋላ የቀጠለው ክለቡ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ድጋሚ ወደ ሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን አድጎ እየተሳተፈ ተከታታይ ሁለተኛ ዓመቱን ይዟል።

    በሊጉ ካደረጋቸው አስራ ሦስት ጨዋታዎች አራቱን ተሸንፎ ሰባት አቻ ወጥቶ በሁለቱ ድል ቀንቶት በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ ላይ የተቀመጠው አርባምንጭ ከተማ ውጤቱን አስመልክቶ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።

    የክለቡ ቦርድ አባላት ባደረጉት በዚህ ሰሞነኛ ስብሰባ ክለቡ እያስመዘገበ ካለው ደካማ ውጤት መነሻነት ለዋና አሰልጣኙ መሳይ ተፈሪ የሁለት ጨዋታ ዕድል እንዲሰጥ ሲወሰን ቡድን መሪውን ጨምሮ ሦስት ረዳት አሰልጣኞች ከኃላፊነት መነሳታቸውን እና በቦታውም አዳዲሶች ስለመተካታቸው ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ በላከው መረጃ አመላክቷል።

    በዚህም መሰረት ቡድን መሪው መንግሥቱ ደምሴ ፣ ሁለቱ ረዳት አሰልጣኞች ማቲዮስ ለማ እና አበው ታምሩ እንዲሁም የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ስለሺ ሽፈራው እንዲሰናበቱ ተወስኗል።

    በምትካቸው ደግሞ የቀድሞው የክለቡ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች እና የቡድኑ ከ20 ዓመት በታች አሰልጣኝ የነበረውን በረከት ደሙን እና የቀድሞው የአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ ተጫዋች እና ከ15 ዓመት በታች አሰልጣኝ ሆኖ ሲሰራ የቆየውን ገረመው ተበጀን በረዳት አሰልጣኝነት ሾመዋል።

    የቀድሞው የክለቡ ግብ ጠባቂ እና የሴት ቡድኑ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሆኖ ሲያገለግል ለቆየው አንተነህ መሳ ደግሞ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ኃላፊነትን መስጠቱን ክለቡ አሳውቋል ሲል ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

    January 10, 2023

    | ስፖርት





  • ወላይታ ድቻ ለጋጣፎ ለገዳዲን 4ለ3 አሸነፈ።

    7 ጎሎች በተስተናገዱበት በዛሬው ጨዋታ ወላይታ ድቻ ለጋጣፎ ለጋዳድን 4 ለ 3 አሸንፎ 3 ነጥብ በመያዝ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

    ለጦና ንቦች ጎሎቹን በ34ኛው ደቂቃ ስንታየሁ መንግሥቱ፣ በ70ኛው ደቂቃ ዘላለም አባቴ፣ በ75ኛው ደቂቃ ቃልኪዳን ዘላለም እና በ82ኛው ደቂቃ ላይ በረከት ወልደዮሐንስ ያስቆጠሩ ሲሆን የለጋዳዲ ለጋጣፎ ጎሎችን አማኑኤል አረቦ በ39ኛና በ77ኛው ደቂቃ እና ካርሎስ ዳምጠው በ61ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል።

    December 26, 2022

    | ስፖርት





  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሚጠብቀው የቻን ውድድር የተጫዋቾች የመጨረሻ ስብስብ ተለይቷል።

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣዩ ወር በአልጃሪያ አስተናጋጅነት ለሚደረገው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮን ሺፕ ማለፉ ይታወሳል።

    ከቀናት በኋላ ዝግጅቱን ለሚጀምረው ቡድን ከዚህ ቀደም የ42 ዕጩ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ተደርጎ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የተጨዋቾች ዝርዝሩ ወደ 28 ዝቅ ብሏል።

    የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከደቂቃዎች በፊት ካጋራው ዝርዝር ላይ በተመለከትነው መሰረት ወንድምአገኝ ኃይሉ ፣ አለልኝ አዘነ እና ሚሊዮን ሰለሞን ከዚህ ቀደም ከነበረው የ42 ተጫዋቾች ዝርዝር በአዲስ መልክ የተጠሩ ተጫዋቾች ሆነዋል።

    ግብ ጠባቂዎች፦ ፋሲል ገ/ሚካኤል – ባህር ዳር ከተማ በረከት አማረ – ኢትዮጵያ ቡና ባህሩ ነጋሽ – ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካዮች፦ አስቻለው ታመነ – ፋሲል ከነማ ምኞት ደበበ – ቅዱስ ጊዮርጊስ ሚሊዮን ሰለሞን – አዳማ ከተማ ጊት ጋትኩት – ሲዳማ ቡና ፈቱዲን ጀማል – ባህር ዳር ከተማ ገዛኸኝ ደሳለኝ – ኢትዮጵያ ቡና ሱለይማን ሀሚድ – ቅዱስ ጊዮርጊስ ረመዳን የሱፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓለምብርሃን ይግዛው – ፋሲል ከነማ ብርሃኑ በቀለ – ሀዲያ ሆሳዕና አማካዮች፦ ጋቶች ፓኖም – ቅዱስ ጊዮርጊስ ይሁን እንዳሻው – ፋሲል ከነማ አለልኝ አዘነ – ባህር ዳር ከተማ መስዑድ መሐመድ – አዳማ ከተማ ከነዓን ማርክነህ – መቻል ወንድማገኝ ኃይሉ – ሀዋሳ ከተማ ታፈሰ ሰለሞን – ፋሲል ከነማ ፉዓድ ፈረጃ – ባህር ዳር ከተማ ቢኒያም በላይ – ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂዎች፦ ጌታነህ ከበደ – ወልቂጤ ከተማ አማኑኤል ገ/ሚካኤል – ቅዱስ ጊዮርጊስ ይገዙ ቦጋለ – ሲዳማ ቡና ቸርነት ጉግሳ – ቅዱስ ጊዮርጊስ ኪቲካ ጀማ – ኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዱሬሳ ሹቢሳ – ባህር ዳር ከተማ

    December 24, 2022

    | ስፖርት





  • ወላይታ ድቻ በሀዋሳ ከተማ 1 ለ 0 ሲመራ ቆይቶ መደበኛው የጨዋታ ጊዜ ከጠናቀቀ በኋላ ከተጨመሩ ደቂቃዎች በ93ኛው ደቂቃ ዮናታን ኤልያስ ባስቆጠረው ግብ 1 ነጥብ ይዞ ወጥቷል።

    December 22, 2022

    | ስፖርት





  • በዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ አርጀንቲና ፈረንሳይን በፍጹም ቅጣት ምት 4 ለ 2 በማሸነፍ የዓለም ሻምፒዮን ሆነች። በዚህም ፈረንሳይ እና አርጀንቲና መደበኛ ጨዋታውን 2 ለ 2 በሆነ አቻ ሁጤት ያጠናቀቁ ሲሆን÷ ተጨማሪ 30 ደቂቃውንም 3 ለ 3 አቻ ተለያይተዋል፡፡ የፍጻሜ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምትም አርጀንቲና ፈረንሳይን በማሸነፍ ከ36 ዓመታት በኋላ የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማንሳት ችላለች፡፡

    December 19, 2022

    | ስፖርት





  • የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) በአልጄርያ አስተናጋጅነት ከጥር 5/2015 – ጥር 27/2015 ድረስ እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ በድረ ገጹ ላይ ባስነበበው መረጃ ገልጸዋል። በዚህ ውድድር ላይ ከሚሳተፉት 18 ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ እንደሆነችም መረጃው ያትታል። በምድብ ሀ ከአስተናጋጇ አልጄርያ ፣ ሞዛምቢክ እና ሊቢያ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ ለውድድሩ የምታደርገው ዝግጅት ከሊጉ መቋረጥ በኋላ እንደሚጀመር ተገልጿል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለብሔራዊ ቡድኑ እያደረገ ከሚገኘው አስተዳደራዊ ድጋፍ ጎን ለጎን ለቅድመ ዝግጅት እና ከውድድሩ ጋር ተያያዥ ለሆኑ ወጪዎች ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም የሚያስፈልግ በመሆኑ የኢፌዲሪ መንግሥት የ50 ሚልዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ በፌዴሬሽኑ በኩል ተጠይቆ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል ላይ እንደሚገኝና በቅርቡ በጎ ምላሽ ይገኛል ብሎ እንደምጠብቅ ተገልጿል። ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት ድጋፍ በተጨማሪ የተለያዩ የገቢ አማራጮችን እየተመለከተ እና አጋር ተቋማትን በማፈላለግ የሚጠበቀው የፋይናንስ አቅም ላይ ለመድረስ እየሰራ እንደሚገኝ ተብራርቷል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ታህሳስ 17 ላይ እንደሚቋረጥ የወጣው መርሐ ግብር ሲያሳይ ከተቋረጠበት ቀን በኋላ ያለውን ጊዜ በመጠቀም ተጫዋቾች ተሰባስበው ለቻን ውድድር ዝግጅት የሚደረግ ይሆናል። ምንጭ፦ የፌዴሬሽኑ ድረ-ገጽ

    December 17, 2022

    | ስፖርት





  • ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ወላይታ ድቻ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በ10:00 ሰዓት እና ሲዳማ ቡና ከባህርዳር ከተማ ጋር ማታ 1:00 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

    December 13, 2022

    | ስፖርት





  • የአሜሪካ ቡድን በኳስ ቁጥጥር ብልጫ የነበረው ቢሆንም ከሽንፈት አልዳነም።

    ለኒዘርላንድ ጎሎቹን መምፔስ ዴፓይ፣ ዳኒ ብላይንድ እና ዳምፍራይስ በ10ኛ፣ በ46ኛው እና በ81ኛው ደቂቃዎች ሲያስቆጥሩ አሜሪካን ከመሰናበት ያላዳነችውን ጎል ደግሞ ዊራይት በ76ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

    December 3, 2022

    | ስፖርት





  • በኳታር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ አገር ጋና ኮሪያ ሪፐብሊክን 3ለ 2 አሸነፈች።

    November 28, 2022

    | ስፖርት





  • በ22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የዘጠነኛ ቀን ውሎ በምድብ ሰባት በተደረገ ጨዋታ አፍሪካዊቷ አገር ካሜሮን ከሰርቢያ ጋር ያደረገችው ጨዋታ 3 ለ 3 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

    November 28, 2022

    | ስፖርት





  • ሩዝቡህ ቼሲሚና ራሚን ሬዛያን በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በጭማሪ ሰአት ባስቆጠሯቸው ግቦች ኢራንንን አሸናፊ አድርጋለች።

    የኢራን ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ጨዋታ በእንግሊዝ ከደረሰበት የ6 ለ 2 ሽንፈት የተሻለ ብቃት ማሳየት ችሏል። ኢራን ከዌልስ የተሻለ የግብ እድሎችን የፈጠረች ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ የግብ አግዳሚና ቋሚ የመለሰባቸው አጋጣሚ አስቆጪ የሚባል ነበር።

    በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ኢራን የተሻል ብልጫ መውሰድ ችላለች። በአንጻሩ ዌልስ በመልሶ ማጥቃትና ከክንፍ መስመር በሚጣሉ ኳሶች ይግብ እድሎችን ለመፍጠር ጥረት ሲያደርጉ ታይቷል። የዌልሱ ግብ ጠባቂ ዌይን ሄንሲይ ከፍጹም ቅጣት ክልል ውጪ በኢራኑ ሜህዲ ታሬሚ ላይ በሰራው ጥፋት በ87ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

    ግብ ጠባቂው በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ የቀይ ካርድ የተመለከተ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።

    በምድብ ሁለት ከምሽቱ 4 ሰአት እንግሊዝና ከአሜሪካ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

    November 25, 2022

    | ስፖርት





  • በ22ኛው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ስፔን ኮስታሪካን ከግማሽ ደርዘን በላይ ጎል በማስቆጠር አሸነፈች። በኳታር አየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ጨዋታ ስፔን ኮስታሪካን 7ለ0 አሸነፈች።

    November 23, 2022

    | ስፖርት





  • በኳታር እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ዋንጫ 2022 ጃፓን ጀርመንን 2ለ1 አሸነፈች።

    November 23, 2022

    | ስፖርት





  • የአርጀንቲናው አጥቂ ሊዮኔን ሜሲ በ9ኛ ደቂቃ ከሽንፈት ያልታደገውን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረ ሲሆን ለሳውድ አረቢያ አሊ ሼሪ በ47ኛ ደቂቃ አቻ ያደረገ ጎል ሲያስቆጥር አልዳዋሳሪ ቡድኑን አሸናፊ ያደረገው ጎል በ52ኛ ደቂቃ በማስቆጠረ ሀገሩን ያልገመተ ድል ባለቤት አድርጓል።

    November 22, 2022

    | ስፖርት





  • 2015 በኳታር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 22ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

    ፈረንሳይ የዓለም ዋንጫ ክብሯን የማስጠበቅ ጉዞ ከአውስትራሊያ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ትጀምራለች።

    በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከዚህ ቀደም ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ በኳታር በአንድ ቀን አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

    ይሄም ዛሬ በምድብ ሶስት እና በምድብ አራት በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል። በምድብ ሶስት 80 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ሉሳይል ስታዲየም አርጀንቲና ከሳዑዲ አረቢያ ከቀኑ 7 ሰአት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

    አምስተኛ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎውን የሚያደርገው አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ የዘንድሮው ውድድር የመጨረሻው እንደሚሆን እየተነገረ ነው።

    አገሩ የዓለም ዋንጫውን ለማንሳት ቅድሚያ ከተሰጣቸው አገራት መካከል ትገኝበታለች።

    በምድብ አራት ከቀኑ 10 ሰአት አፍሪካዊቷ አገር ቱኒዚያ ከዴንማርክ በ‘ኢጁኬሽን ሲቲ’ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

    ከምሽቱ 1 ሰአት በምድብ አራት ሜክሲኮ ከፖላንድ በ ‘ስታዲየም 974’ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

    በምድብ ሶስት የወቅቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ፈረንሳይ የዋንጫ ክብሯን የማስጠበቅ ጉዞ ዛሬ ከምሽቱ 4 ሰአት በአል ጃኑብ ስታዲየም ከአውስትራሊያ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ትጀምራለች።

    ሰማያዊዎቹ (ለስ ብሉስ) በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የዘንድሮው የባለንዶር አሸናፊ ካሪም ቤንዚማ፣ንጎሎ ካንቴና ፖል ፖግባ በጉዳት አጥቷል።

    ትናንት በዓለም ዋንጫው በተደረጉ ጨዋታዎች በምድብ አንድ ኔዘርላንድስ አፍሪካዊቷን አገር ሴኔጋልን 2 ለ 0 አሸንፋለች።

    በምድብ ሁለት እንግሊዝ ኢራንን 6 ለ 2 በሆነ ሰፊ ውጤት ስትረታ ከ64 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ ዓለም ዋንጫ የተመለሰችው ዌልስ ከአሜሪካ ያደረገችው ጨዋታ 1 ለ 1 ተጠናቋል።

    በዓለም ዋንጫው ዛሬን ጨምሮ ለ 10 ተከታታይ ቀናት በቀን አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

    November 22, 2022

    | ስፖርት





  • ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 22ኛ ዓመቱን አስመልክቶ ባዘጋጀው የእውቅና መርሐግብር ለአትሌቶችና ሌሎች ባለድርሻዎች እውቅና ሰጠ።

    መርሐግብሩ ትናንት ማምሻውን "ኢትዮጵያዊነቴ ያኮራኛል" በሚል መሪ ሀሳብ ተከናውኗል። በዚሁ መሰረት በወንዶች አትሌት ፀጋዬ ከበደ፣ ኮማንደር አትሌት ሞስነት ገረመው እና አትሌት ታምራት ቶላ ፤በሴቶች ውዴ አያሌው፣ አሰለፈች መርጊያ እና ያለምዘርፍ የኋላው የእውቅና ሽልማት የተሰጣቸው አትሌቶች ናቸው።

    አትሌቶቹ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ለስኬታቸው መነሻ እንደሆናቸውና ከአትሌቲክሱ ማህበረሰብ ጋር እንዲተዋወቁ እድል ፈጥሮልናል ብለዋል።

    ከአትሌቶቹ በተጨማሪ የቱሪዝም ሚኒስትር፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ በታላቁ ሩጫ ኢትዮጵያ የእውቅና ሽልማት ያገኙ ተቋማት ናቸው። በእውቅና መርሐግብሩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ታዋቂ አትሌቶች፣የመገናኛ ብዙሃን አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

    የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የተጀመረው በ1994 ዓ.ም በአትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ አማካኝነት ነው። የዘገበው ኢዜአ ነው።

    November 18, 2022

    | ስፖርት





  • ለአዳማ ከተማ ቦና ዓሊ የመጀመሪያ 45 ደቂቃ ከተጠናቀቀ በኋላ ከተሰጡ ተጨማሪ ደቂቃዎች በአንደኛው ደቂቃ ቡድኑን ከሽንፈት ያልታደገውን ጎል አስቆጥሯል።

    ከእረፍት መልስ ተጠናክረው ለገቡት ለጦና ንቦች ዮናታን ኤልያስ በ61ኛው ደቂቃ የመጀመሪያውን ጎል ያስቆጠረ ሲሆን፣ ቃልክዳን ዘላለም በ65ኛው ደቂቃ ላይ ቡድኑን አሸናፊ ያደረገችውን ኳስ ከመረብ ጋር አገናኝቷል። ምንጭ:_ ሶከር ኢትዮጵያ

    November 17, 2022

    | ስፖርት





  • የከተማው ወጣቶች እና ስፖርት ፅህፈት ቤት ባዘጋጀው መርሀ ግብር Mass Sport/ በርካታ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

    የወላይታ ሶዶ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንተርፕራይዞች እና ኢንዱስትሪ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ ሞገስ ደማቅ እና ስኬታማ የስፖርት ጊዜ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

    የበርካታ ወጣት የስፓርተኞች ምንጭ ከተማ በሆነችው ወላይታ ሶዶ በየቀኑ ጠዋት በመነሳት በየጎዳናው እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ነዋሪዎችን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሰራ አቶ ሲሳይ ገልፀዋል።

    ስፖርት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ስለሚያስችል ሁሉም እንዲሳተፍ አቶ ሲሳይ በከተማ አስተዳደር ስም ጥሪያቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በህብረተሰብ አቀፉ የስፓርት እንቅስቃሴ የተሳተፉትን ደግሞ አመስግነዋል።

    የከተማው ወጣቶች እና ስፖርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ህይወት ዮሀንስ በበኩላቸው በየሳምንቱ ቅዳሜ ቀጣይነት ያለው የስፖርት እንቅስቃሴ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

    ስፖርቱን በማሰራት የተሳተፉ እና በስፍራው የተገኙ ሁሉም በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ እንዲገኙ ሀላፊዋ መክረዋል።

    በማህብረተሰብ አቀፉ የስፖርት እንቅስቃሴ /Mass Sport /የተሳተፉ ነዋሪዎች ደግሞ ደስተኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን የዘገበው የወ/ሶዶ ከተማ መ/ኮ/ጽ/ቤት ነው።

    November 5, 2022

    | ስፖርት





  • በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት አቀባበል ተደርጎለታል::

    ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው አቀባበል የተደረገለት ።

    August 16, 2021

    | ስፖርት





  • ብራዚል በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች እግር ኳስ አሸናፊ ሆነች።

    በፍጻሜው ከስፔን ጋር የተገናኘችው ብራዚል ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
    መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ብራዚል ተጨማሪ ጎል አስቆጥራ የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች።
    ለብራዚል የድል ጎሎቹን ሳንቶስ እና ማልኮም እንዲሁም ኦያርዛባል ደግሞ የስፔንን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል።

    August 16, 2021

    | ስፖርት





  • የአትሌት ለተሰንበት ግደይ የ10ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ፀደቀ፡፡

    ከአንድ ወር በፊት በሁለት ቀናት ልዩነት ውስጥ ከ15 ሰከንዶች በላይ በሄንግሎ ማጣሪያ ተሻሽሎ በኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ እጅ የገባው የ10 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ጸደቀ።
    የዓለም አትሌቲክስ የበላይ አካል ታላቁ የኦሊምፒክ ውድድር በቶኪዮ ከተጀመረ ከቀናት በኋላ እንዳሳወቀው÷ ከ4 ዓመት በፊት በሪዮ ኦሊምፒክ ላይ በኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና ተይዞ የነበረው የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በ2 አትሌቶች በተከታታይ መሰበሩን ማጽደቁን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

    August 16, 2021

    | ስፖርት





  • በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

    በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝቷል፡፡ ዑጋንዳውያኑ ጆሹዋ ቺፕቴጌና ጃኮፕ ኪፕሊሞ አትሌት ሰለሞን ባረጋን ተከትለው በመግባት የብር እና ነሃስ ሜዳልያ አግኝተዋል፡፡
    አትሌት ሰለሞን ባረጋ ርቀቱን በ27 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ ከ22 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ነው ያሸነፈው፡፡ በውድድሩ የተሳተፉት አትሌት በሪሁ አረጋዊ 27 ደቂቃ ከ46 ሰከንድ ከ16 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 4ኛ ደረጃ ሲያገኝ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ደግሞ በ27 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ ከ3 ማይክሮ ሰከንድ 8ኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

    August 16, 2021

    | ስፖርት