| ሳይንስና ቴክኖሎጂ






  • አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ልክ እንድታድግ የአፍሪካውያን የእርስ በእርስ ግንኙነት የበለጠ ማደግ እንዳለበት ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

    በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 6ኛው የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እንዳሉት የመሰረተ ልማት ፍላጎትና አቅርቦት በፍጥነት እያደገ ነው።

    አፍሪካ መልማትና መበልጸግ የሚያስችላት የተፈጥሮ ሀብት ቢኖራትም ተባብሮ መስራት አለመቻል ትልቅ ፈተና ሆኖ ቆይቷል ብለዋል።

    አህጉሪቱ ያላትን እምቅ አቅም መጠቀም ትችል ዘንድ በአፍሪካውያን መካከል የእርስ በእርስ ግንኙነቱ ከዚህ በላይ ማደግ እንዳለበት ገልጸዋል። የአፍሪካ ኢንጂነሮች ጉባኤ አፍሪካን በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር ጉልህ ድርሻ እንዳለው የገለጹት ፕሬዝዳንቷ፤ይህ አይነቱ ምክክር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

    ኢትዮጵያ የሸገርና አንድነት ፓርክ ፕሮጀክቶችን በመገንባት አፍሪካውያን ኢንጂነሮች አፍሪካን መቀየር እንደሚችሉ አሳይታለች ብለዋል።

    ጉባኤው በኢንጂነሮች መካከል ጤናማ የውድድር መንፈስ በመፍጠር የአፍሪካን የመሰረተ ልማት ግንባታ ፈጣንና ጥራት ያለው እንዲሆን ያግዛል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ናቸው።

    November 8, 2022

    | ሳይንስና ቴክኖሎጂ





  • ናሳ የስነ ምድርና የከባቢ አየር ምርምር ለማድረግ ሁለት ልዑኮችን ወደ ቬኑስ እንደሚልክ አስታወቀ፡፡

    እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር በ2028 እና 2030 ወደ ቬኑስ ለሚደረጉት ተልዕኮዎች እያንዳንዳቸው 500 ሚሊየን ዶላር እንደሚወጣባቸውም ተገልጿል።
    የናሳ አስተዳዳሪ ቢል ኔልሰን ተልዕኮዎቹ “ከ30 ዓመታት በላይ ያልደረስንበትን ፕላኔት ለመመርመር እድል ይሰጡናል” ብለዋል፡፡
    በፕላኔቷ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ምርምር የተደረገው እንደ አውሮፓውያኑ 1990 ነበር።
    ናሳ ተልዕኮዎቹን ለመፈጸም ከውሳኔ ላይ የደረሰው የተለያዩ ግምገማዎችን ካከናወነ፣ ያላቸውን ሳይንሳዊ አስፈላጊነትና አዋጭነት ካረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል፡፡
    ሁለት ጥምር ተልእኮዎች ቬኑስ እንዴት እርሳስ [lead] ማቅለጥ የሚችል የእሳትን ገጽታ የተላበሰ ዓለም ሊሆን እንደቻለ ለመረዳት ዓላማ ያደረጉ መሆናቸውን አስተዳዳሪው ኔልሰን አስረድተዋል፡፡
    ቬኑስ ከጸሀይ በመቀጠል ሁለተኛዋ ሞቃታማ ፕላኔት ስትሆን፣ እስከ 500 ሴልሺየስ የምትሞቅና እራሳስን ማቅለጥ የሚችል የአየር ሁኔታ ላይ የምትገኝ መሆኗን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

    August 16, 2021

    | ሳይንስና ቴክኖሎጂ





  • ፌስቡክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ፖለቲካዊ ማስታወቂያዎች ላይ ተጠያቂነት የሚያሰፍን አሰረራር ዘረጋ።

    ፌስቡክ ኢትዮጵያና ኬንያን ጨምሮ የማህበራዊ ጉዳይ፣ ምርጫ እና ፖለቲካዊ ማስታወቂያዎች ላይ ተጠያቂነት እና ቁጥጥርን የሚያሳድግ አሰራር እንደሚዘረጋ ነው ያስታወቀው።
    በዚህም በኢትዮጵያ በፌስቡክ ማህበራዊ ጉዳይ፣ ምርጫ እና ፖለቲካን በተመለከተ የሚያስተዋውቁ አካላት ፈቃድ መውሰድ እና በፌስቡክ ለሚተላለፉ ይዘቶች ሃላፊነት እንደሚወስዱ ኩባንያው አስታውቋል።
    ይህም የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በገፆቻቸው የሚተላለፉ ማስታወቂያዎችን የበለጠ ቁጥጥር እንዲኖራቸው የሚያስችላቸው መሆኑ ተነግሯል።
    በዚህም ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ፣ ምርጫ እና ፖለቲካዊ ጉዳይ የተወሰነ ማስታወቂያ ብቻ እንዲመለከቱ ያስችላል።
    እንዲሁም ተጠቃሚዎቹ የእራሳቸው ፍላጎት እና ሀሳብ በመለየት የማህበራዊ ፣ ምርጫ እና ፖለቲካዊ ማስታወቂያዎችን መቆጣጠር ያስችላቸዋል ነው የተባለው።
    ይህም ከመጭው ሀሙስ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ እና በሀገራቱ ከሚካሄዱ ምርጫዎች ጋር እንደሚያያዝም ተጠቁሟል።

    August 16, 2021

    | ሳይንስና ቴክኖሎጂ





  • ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስ የኢንተርኔት አገልግሎት በማእከላዊ ምስራቅ ሪጅን በሀረር፣ አወዳይ እና ሀረማያ ከተሞች በይፋ አስጀምሯል።

    በመርኃግብሩ የደምበኞች ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ የቴክኖሎጂ ተደራሽነትና ትውውቅ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

    ተቋሙ በዲጅታል ኢኮኖሚ ተቋማትን ለመቃኘት ብሎም የግብይት ስርዓቱን ለማዘመን መሰረተ ልማት በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል።

    በተያዘው በጀት አመት በ103 ከተሞች የ4ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስ ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱንም ጠቁሟል።

    በማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን በ33 ከተሞች 67 ሺህ ተገልጋዮች ማግኘት እንደሚችሉ የኢትዮ የቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።

    የ4ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስ አገልግሎት ምስሎችን በፍጥነት ለማውረድ እና መለዋወጥ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

    አዲሱ ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ገንዘብን በእጅ ስልኮች ማንቀሳቀስ የሚያስችል የቴሌ ብርን ማስተዋወቁ የሚታወቅ ሲሆን፣ በአምስት አመት ውስጥ 3.5 ትሪሊዮን ብሮችን በቴሌ ብር ለማንቀሳቀስ መታቀዱንና በሁለት ሳምንት ውስጥ 2.4 ሚሊየን ተገልጋዮች የቴሌ ብር ቤተሰብ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

    August 16, 2021

    | ሳይንስና ቴክኖሎጂ





  • የዓለማችን ቱጃር የሆነው የግዙፉ የበይነ መረብ የግብይት ተቋም “አማዞን” መስራች እና ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ወደ ጠፈር የተሳካ ጉዞ አድርጓል።

    ጄፍ ቤዞስ ለዚህ ጉዞው በጥንቃቄ የተሰራች 6 መቀመጫዎች ያሏት እና “ኒው ሼፐርድ” የተሰኘች መንኮራኩርን በመጠቀም የተደረገ ጉዞ ነው።
    ጄፍ ቤዞስ “ብሉ ኦርጂን” የተሰኘ የኤሮስፔስ አምራች እና ንዑስ ምህዋር የጠፈር በረራ አገልግቶችን የሚሰጥ ኩባንያ ባለቤት ሲሆን፣ በረራውን ያደረገው ከሌሎች ሦስት ሰዎች ጋር በመሆን በ“ኒው ሼፐርድ” በተሰኘችው መንኮራኩር ነው።
    ወደ ጠፈር ጉዞ ያደረጉት የ82 ዓመቷ ዊሊ ፋንክ፣ የ18 ዓመቱ ወጣት ኦሊቨር ዳኤሜን እና የጄፍ ቤዞስ ወንድም ማርክ ቤዞስ መሆናቸው ተጠቅሷል።
    ከዌስት ቴክሳስ ወደ ጠፈር የተደረገው ጉዞ ለ11 ደቂቃ የቆየ ሲሆን፣ በህዋ ላይ ከምድር በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት በመድረስ ስበት አልባነትን መሞከር እና የምድር ቅርጽ ለመመልከት ችለዋል፡፡
    ይህ ጉዞ ጄፍ ቤዞስን ወደ ህዋ ለሽርሽር የተጓዘ ሁለተኛው የዓለማችን ባለሃብት እንዲሆን አስችሎታል፡፡
    ለድርጅቱ ብሉ ኦሪጅን ደግሞ የመጀመሪያው ሰው ይዞ ወደ ህዋ የተደረገ ጉዞ ሲሆን፣ እስከአሁን ወደ ህዋ ያደረጋቸውን ጉዞዎች 16 አድርሶታል፡፡

    “ኒው ሼፐርድ” ከ60 ዓመታት በፊት ወደ ጠፈር የተጓዘውን የመጀመሪያውን አሜሪካዊ ጠፈርተኛ አለን ሼፐርድ ለማስታወስ ለመንኮራኩሯ የተሰጠ የመታሰቢያ ስም ነው።
    ባለፈው ሳምንት እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ሪቻርድ ባርንሰን ለ17 አመታት በጥናት እና በግንባታ ላይ በቆየችው በ“ቨርጂን ጋላክቲክ ሮኬት” የተሳካ የጠፈር ሽርሽርን ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
    ባለሀብቱ ምድርን ለቆ በጠፈር ላይ ለአንድ ሰአት ያክል ከቆየ በኋላ በሰላም ወደ ምድር መመለሱ ይታወሳል።

    August 16, 2021

    | ሳይንስና ቴክኖሎጂ





  • የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ከየአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ጋር በዲጂታል የክትትልና ሪፖርት አቀራርብ ሥርዓት (D~MRS) ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

    ይህ የልምድ ልውውጥ ጠቃሚ አሰራር ዘዴዎችን ከአንዱ ወደሌላው ለማስተላፍ እንዲሁም የሚኖሩ ጉድለቶችን እና ክፍተቶችን ለመሙላት የታሰበ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
    በዌብናር በመታገዝ በተካሄደው የልምድ ልውውጥ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የተዘጋጀው IPRT የተሰኘው ሥርዓት በዶ/ር ታደለ ፈረደ የቀረበ ሲሆን፣ በፕላንና ልማት ኮሚሽን የተዘጋጀው የዲጂታል ክትትልና ሪፖርት አቀራረብ ሥርዓት(D~MRS) በበፕላንና ልማት ኮሚሽን አማካሪ በሆኑት አቶ ሰለሞን ተስፋሥላሴ በኩል ቀርቧል።
    በማስከተልም በሁለቱ የዲጂታል ክትትልና ሪፖርት አቀራርብ ሥርዓቶች ዙሪያ ውይይቶች ተደርጎ ከሁለቱም በኩል ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል፡፡
    የልምድ ልውውጡ ከአንደኛው ወገን ያለውን ክፍተት ከሌላው በመማር ክፍተቱን የማሟላት ዕድል እንዲፈጠር ከማድረጉም በላይ በክትትልና ግምገማ ሥርዓት ዙሪያ በተለይም የተቀናጀ ዲጂታል የዕቅድ ክትትልና ግምገማ አሰራሮችን ለማጎልበት ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
    በመጨረሻም ሁለቱ ተቋማት ከዚሁ ጋር በተገናኘ በቀጣይ ትኩረት አድርገው በጋራ መስራት ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

    August 16, 2021

    | ሳይንስና ቴክኖሎጂ